24 days ago
ቻይና ታይዋን የምትባል ሀገር ስለማላውቅ በዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ እንዳትሳተፍ አለች
#ethiopia | በመጪው ግንቦት 18 የሚከፈተው 79ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ ላይ ታይዋን እንዳትሳተፍ መወሰኗን ቻይና ይፋ አደረገች። የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሰጡት መግለጫ፣ ታይዋን የቻይና ግዛት የማይነጠል አካል በመሆኗ በጉባኤው ላይ የሚኖረው ተሳትፎ ቻይናን ብቻ የሚመለከት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም፣ የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግስት መላውን ቻይና የሚወክል ብቸኛ ሕጋዊ መንግስት መሆኑንና ይህም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደንብ የተደገፈ መርህ መሆኑን ገልጸዋል።
በታይዋን የሚገኘው "ዴሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ" የነፃነት አቋም በማራመድ የ"አንድ ቻይና" መርህን ጥሷል ሲሉ የወቀሱት ቃል አቀባዩ፣ የታይዋንን ካርድ በመጠቀም የሚደረግ ማንኛውም የፖለቲካ ማጭበርበር ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል።
በዚህም መሰረት የዓለም ጤና ድርጅትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ውሳኔዎች ለማስከበር ታይዋን በዘንድሮው ጉባኤ ላይ እንደማትሳተፍ ግሎባል ታይምስ የቃል አቀባዩን መግለጫ ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#china #taiwan #who #worldhealthassembly #onechinapolicy #geopolitics #globalnews