4 hours ago
በሶማሊያ የተፈጠረው ምንድን ነው ?
#ethiopia | የሶማሊያ መንግስት ሃይሎች እና ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት ባላቸው ሚሊሻዎች መካከል በዋና ከተማዋ በመቋዲሾ ትላንት ሌሊት እና ዛሬ ጠዋት ግጭት ተቀስቅሷል።
ይህ ግጭት በወቅቱ ፕረዚዳንት ሀሰን ሼኽ ሞሃሙድ የታቀደውን የሥልጣን ጊዜ ማራዘሚያ በመቃወም ሊካሄድ ከታቀደው ሰልፍ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የጀመረ ነው።
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን አሊ ኻይሬ በX ላይ ባወጡት መግለጫ፣ መንግስት ሃይሎች በእሱ እና በሌሎች ተቃዋሚ መሪዎች ላይ “ወታደራዊ ጥቃት” መፈጸማቸውን በመግለፅ መንግስት ላይ ክስ አቅርበዋል።
መንግስት በበኩሉ ተቃዋሚዎች ጋር የተቆራኙ የታጠቁ ቡድኖች በኸውልዋዳግ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን አስታውቆ፣ መንግስት ይህን ክስተት አውግዞ ምርመራ እንደሚያካሂድ ገልጿል።
ነዋሪዎች መንገዶች እንደተዘጉ፣ አየር ማረፊያው መዳረሻ እንደተቋረጠ እና በአንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደተቋረጠ ተናግረዋል።
በግጭቱ የተጎዱ ሰዎች ቁጥር እና የአካባቢው ሁኔታ ማረጋገጥ አስቸጋሪ መሆኑ ተዘግቧል።
አሜሪካ እና እና ሌሎች አለም አቀፍ አጋሮች ሁለቱም ወገኖች እንዲታገሱ እና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #tikvahethmagazine #economicnews #labourexploitation