Logo
Zehabesha
"እውነቱን ለመናገር፣ ከሥልጣን በመነሳቴ የተለየ ቅሬታ ወይም ቁጣ የለኝም። በፖለቲካችን ውስጥ የተወሰነ ጤናማ አካሄድ ለማስገባት የምችለውን ያህል ጥሬያለሁ፤ ምናልባትም ሙሉ በሙሉ ባይሆንም በከፊል አልተሳካልኝም (ክሽፏል)። ስለዚህ እኔ እንደማስበው፣ ከሥልጣን የምነሳበት ጊዜው ደርሶ ነበር። ምክንያቱም የሥልጣን ዘመኑ የሁለት ዓመት ሲሆን፣ ያ የሁለት ዓመት ጊዜ ደግሞ አብቅቶ ነበር። ይህንን የምልበት ምክንያት... ከእኔ ሥልጣን የተረከበው ሰው እኔን ለመተካት ያላደረገው ጥረት አልነበረም። ስለዚህ መናደድ ካለብኝ፣ ከማንም በላይ በእሱ ላይ መናደድ ነበረብኝ፤ ነገር ግን ጉዳዩ የኔ መናደድ አይደለም።
"ዋናው ነጥብ ተቋማት እስካሉ ድረስ ነገሮች አስቀድመው የሚታወቁበትና የተረጋጉ የሚሆኑበት ሥርዓት እንዲኖር የተወሰኑ ሕጎችን ማክበር ይጠይቀናል። አሁን ያለው የህወሓት አመራር ያደረገው ነገር ግን መፈንቅለ-ሥልጣን በማካሄድ ራሱን እንደ ሕጋዊ አካል አድርጎ መሾም ነው፤ ነገር ግን ሕጋዊ አይደለም። በመሆኑም ይህ አካል ለነፃ እና ፍትሃዊ ምርጫ የሚያስፈልገውን አስተማማኝ ጸጥታ ማረጋገጥ አይችልም።"

ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለቲአርቲ ከሰጡት ቃለምልልስ

8 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.