20 days ago
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ትንሣኤ
***************
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለዘመናት ከባሕር ጋር የነበራት ቁርኝት ከጂኦግራፊያዊ መሳ ለመሳነት በዘለለ የሀገራችን የሉዓላዊነት፣ የኢኮኖሚ ጥንካሬ እና የቀጣናዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት መሠረት ሆኖ ኖሯል።
በጥንታዊው የአክሱም ሥልጣኔ ወቅት የአዱሊስ ወደብ የዓለም የንግድ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል፣ ኢትዮጵያውያን እ.ኤ.አ በ518 ወደ የመን ባሕር ተሻግረው ወታደራዊ ዘመቻዎችን ለማካሄድ የሚያስችሉ ከ70 በላይ የጦር መርከቦችን በአገር ውስጥ የመገንባት ጥበብ ነበራቸው።
ይህ ጥንታዊ የባሕር ግርማ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኦቶማን ቱርኮች ምጽዋን እስከተቆጣጠሩበት ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያን የባሕር ሉዓላዊነት ሲያስከብር ቆይቷል።
የባሕር ኃይሉ መሥራችና ታሪካዊው ምዕራፍ ...
የዚህን መረጃ ሙሉ ሐሳብ አስተያየት መስጫው ውስጥ ካለው ሊንክ ያገኛሉ፦
#ebc #ethiopia #seaaccess #redsea

22 days ago
u12a2u1275u12eeu1335u12eb u1320u120bu1276u127fu1295 u12a8u1263u1215u1229 u12a5u1295u12f4u1275 u1273u1295u133b? | u12a2u1275u12ee u1218u120du1215u1245 | ETHIO MELHIK | #ethiopia #redsea #seaaccess #asseb #egypt #eritrea #nomorelandlocked #accesstothesea #ebc #etv #ebcdotstream ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ኢትዮጵያ ጠላቶቿን ከባሕሩ እንዴት ታንጻ? | ኢትዮ መልሕቅ | ETHIO MELHIK | #ethiopia #redsea #seaaccess #asseb #egypt #eritrea #nomorelandlocked #accesstothesea #ebc #etv #ebcdotstream
23 days ago

25 days ago
ቀይ ባሕር - ኢትዮጵያ ወደ ተፈጥሯዊ ቤቷ ትመለሳለች!
*****************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ በታሪክ ማኅደር ውስጥ ስሟ በገዘፈው ልክ፣ በመልክዓ-ምድራዊ እስር ውስጥ እንድትማቅቅ የተፈረደባት ሀገር ሆና እንድትቆይ የተደረገው በድንገቴ የታሪክ አጋጣሚ ሳይሆን በረቀቀ የባዕዳን ሴራ እና በውስጥ ባንዳዎች የታሪክ ክህደት ጭምር መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።
“ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” እንደሚባለው ሀገራችን የባሕር በሯን ስታጣ እና የየብስ እስረኛ ስትሆን ጉዳቱ የገባቸው ጥቂቶች ነበሩ። ዛሬ ግን ያ የታፈነ ታሪክ ትንፋሽ አግኝቶ ወደ ዓለም አቀፍ አጀንዳነት ተሸጋግሯል።
የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የቅንጦት ወይም የፍላጎት ጥያቄ ሳይሆን፣ ከሕልውና ጋር የተቆራኘ የሞት እና የሽረት ጉዳይ መሆኑን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት በአንድ ድምፅ እያስተጋቡት ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቁርጠኝነት እንደገለጹት ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት ካልሆነች ልማቷ ብቻ ሳይሆን ሰላሟም አደጋ ላይ ይወድቃል።
130 ሚሊዮን ሕዝብ ያቀፈች ግዙፍ ሀገር፣ የዓለም የንግድ መስመር በሆነው ቀይ ባሕር ላይ ተሳትፎ እና ባለቤትነት ሳይኖራት መቅረቷ ለቀጣናውም ቢሆን ዘላቂ ሰላምን አያመጣም። ትናንሽ ሀገራት ግዙፉን የንግድ ወሽመጥ የመጠበቅ አቅም ስለሌላቸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራት ከጉዳዩ መራቃቸው ለባሕር ላይ ወንበዴነት እና ለሽብርተኝነት በር የሚከፍት ነው። ስለሆነም የባሕር በር ጥያቄያችን ከስሜታዊነት በራቀ፣ በታሪክ፣ በሕግ እና በፍትሕ ላይ የተመሠረተ መሆኑን አሁን ዓለም ሊገነዘበው ይገባል።
ኢትዮጵያ የሌላውን ሉዓላዊነት የመንካት ፍላጎት ሳይኖራት፣ የራሷን የተፈጥሮ እና የታሪክ መብት ማስከበር ላይ ትኩረት ማድረጓ ፍጹም ምክንያታዊ ነው። የሌለንን ሳይሆን የነበረንን እና የሚገባንን ነው የምንጠይቀው።
ከኢኮኖሚ አኳያ ስንመለከተው፣ የባሕር በር ማጣት ለሀገራችን ትልቅ የደም ሥር መቋረጥ ነው። ዛሬ ላይ በዓመት እስከ 20 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚደርስ የገቢ እና ወጪ ንግድ የምናስተናግድ ሲሆን ይህም በ2030 ወደ 35 ሚሊዮን ከፍ እንደሚል ይገመታል። ለወደብ አገልግሎት በየዓመቱ የምንከፍለው በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮች የሀገራችንን ካዝና ከማድረቅ ባለፈ፣ ለልማት የሚውል ሀብታችንን አሳልፎ እየሰጠ ይገኛል።
የባሕር በር ማጣት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ነው።
“ጀግና ካልወደቀ አይነሣም” እንደሚባለው፣ ኢትዮጵያ ካለፈችባቸው የታሪክ ስብራቶች ታላቅ ትምህርት ቀስማለች። የባሕር በሯን ያጣችበት መንገድ ሕጋዊነት የጎደለው፣ በሕዝብ ውሳኔም ሆነ በተቋማት ዕውቅና ያልተደገፈ መሆኑ ዛሬ ላይ ለጥያቄያችን የሞራል እና የሕግ ልዕልናን ሰጥቶታል።
ጎረቤቶቻችን ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የኢኮኖሚ ትሥሥር ቢያጠናክሩ የሁላችንም ተጠቃሚነት ይረጋገጣል። የኢትዮጵያ በባሕር ላይ መገኘት ለቀጣናው ደኅንነት ዋስትና እንጂ ስጋት አይደለም።
የራሷ የባሕር ኃይል እና የወደብ ይዞታ የነባራት ኢትዮጵያ፣ በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ ያለውን የጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት ለማርገብ እና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮችን ለመጠበቅ የሚኖራት ሚና ከፍተኛ ነው።
ይህ የትውልድ ጥያቄ እና የታሪክ አደራ ነው። ኢትዮጵያ “የመልክዓ-ምድር እስረኛ” ሆና የምትቆይበት ዘመን ማክተም አለበት።
የባሕር በር ጥያቄ ከስሜታዊነት የፀዳ፣ በፍትሕ ላይ የተመሠረተ እና ለዘላቂ ሰላም የሚቆም ነው። ኢትዮጵያ ከጂኦግራፊ እስረኝነት የምትላቀቅበት ቀን ሩቅ አይሆንም።
በደም እና በአጥንት ሀገራቸውን ጠብቀው ያቆዩልን አባቶቻችን የባሕር ላይ ጀግንነት ታሪክ ዛሬም በልባችን ታትሞ ይገኛል።
የሕዳሴው ግድብ የኤሌክትሪክ ብርሃናችንን እንዳረጋገጠልን ሁሉ፣ የወደብ ባለቤትነታችንም የባሕር ላይ ክብራችንን ዳግም የሚያበስር መሆኑ አይቀሬ ነው።
መጪው ትውልድ በየብስ የታጠረች ሳይሆን አድማስ ተሻጋሪ እና የባሕር ላይ ክብር ያላት ሀገር እንደሚረከብ ጽኑ እምነታችን ነው።
ዛሬ የምንዘራው የዲፕሎማሲ ዘር ነገ ለሀገራችን የብልፅግና ፍሬ ሆኖ ይበቅላል። ኢትዮጵያ በክብር ወደ ባሕሯ ትመለሳለች!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ebc #ethiopia #seaaccess #redsea #diplomacy

1 month ago
የባሕር በር ዋና ጉዳይ የሆነበት የፓርቲዎች ክርክር
ዛሬ ምሽት 2:30 ይጠብቁን! #ethiopiabroadcastingcorporation #ethiopia #nationalinterest #redsea #seaaccess
Sponsored by
Surafel
3 months ago
የኢትዮጵያ የባህር በር አልባነት በዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ያሳደረው ጫና
#ethiopia | የኢትዮጵያ የባህር በር አልባ መሆን ከሀገራዊ ኢኮኖሚ ተጽዕኖ ባለፈ፣ በእያንዳንዱ ዜጋ የኑሮ ደረጃ እና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ እንደሚገኝ ተነገረ።
ሀገሪቱ ለጎረቤት ሀገራት በየዓመቱ የምትከፍለው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የወደብ ኪራይ፣ በቀጥታ የዜጎችን የመግዛት አቅም እየተፈታተነ ይገኛል።
የሸቀጦች ዋጋ መናር እና የኪስ ባዶነት
ኢትዮጵያውያን ለምግብ፣ ለጤና እና ለትምህርት የሚጠቀሙባቸው መሠረታዊ ቁሳቁሶች የባህር በር ካላቸው ሀገራት ዜጎች በበለጠ ውድ ዋጋ እንዲገዙ ተገደዋል። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ምርቶቹ ወደ ሀገር ውስጥ እስኪገቡ ድረስ የሚጠየቀው ከፍተኛ የወደብ ኪራይ እና ተያያዥ ወጪዎች በምርቶቹ መሸጫ ዋጋ ላይ ተጨምረው ለሸማቹ ስለሚቀርቡ ነው። ይህ ሁኔታ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያለውን ማህበረሰብ ለከፋ የኑሮ ውድነት አጋልጦታል።
የነዳጅ እና የትራንስፖርት ፈተና
እንደ ነዳጅ ያሉ ስትራቴጂካዊ ምርቶች በሌሎች ሀገራት ወደቦች በኩል መግባታቸው፣ የትራንስፖርት ታሪፍ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲናር ምክንያት ሆኗል። የነዳጅ ዋጋ መጨመር ደግሞ እንደ ሰንሰለት የሁሉንም ሸቀጦች ዋጋ በማናር የእያንዳንዱን ዜጋ የኢኮኖሚ አቅም እያዳከመው ይገኛል።
ከእርሻ እስከ ማዕድ
የወደብ እጥረት በሀገሪቱ የጀርባ አጥንት በሆነው ግብርና ላይም ጥላውን አጥልቷል።
* የግብዓት መዘግየት፦ ማዳበሪያና የግብርና ግብዓቶች በወደብ መጨናነቅ ምክንያት በወቅቱ ለገበሬው አለመድረሳቸው።
* የምርት መቀነስ፦ በግብዓት እጥረት ምክንያት የሚፈጠር የምርት መቀነስ በከተማው ነዋሪ ማዕድ ላይ የዋጋ ግሽበትን አስከትሏል።
የሥራ ዕድል እና የኢንዱስትሪ መቀዝቀዝ
በኢንዱስትሪው ዘርፍ የጥሬ ዕቃ ማስገቢያ ዋጋ መናር አምራች ድርጅቶች በሙሉ አቅማቸው እንዳይሠሩ እንቅፋት ሆኗል። ይህ ደግሞ አዳዲስ የሥራ ዕድሎች እንዳይፈጠሩ በማድረጉ፣ በወጣቶች የገቢ ምንጭና የሥራ ዋስትና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል።
ባጠቃላይ የባህር በር አለመኖር ለአንድ ኢትዮጵያዊ የኪስ ባዶነት፣ የሸቀጦች እጥረት እና ለተጨማሪ ወጪዎች ምክንያት በመሆን የኑሮ ጥራቱን ዝቅ እንዲል እያደረገው ይገኛል። በመሆኑም ኢትዮጵያ ዘላቂና አስተማማኝ የባህር በር እንዲኖራት የሚቀርቡ ድምጾች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረቱ መጥተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #መናኸሪያFm #ኢትዮጵያ #የባህርበር #የኑሮውድነት #ኢኮኖሚ #የወደብኪራይ #ethiopia #seaaccess #logistics #economicimpact

5 months ago
🌊 "ከኢኮኖሚ ጥያቄ ባለፈ የህልውና ጉዳይ ነው" — የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች
#ethiopia | የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የትውልዱ የማይታጠፍ አጀንዳ እና የሀገር ህልውና ጉዳይ መሆኑን የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በጽኑ አቋም ገለጹ።
🇪🇹 የታሪክ ቁጭት እና የትውልድ ጥያቄ
ለዘመናት የባህር በር ባለቤት የነበረችው ኢትዮጵያ፣ በአሁኑ ወቅት ከ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይዛ የወደብ አልባ ሀገር መሆኗ አግባብ እንዳልሆነ አመራሮቹ አንስተዋል። የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) አመራር አቶ ደምሴ ሱካሬ፣ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት ሁኔታ ግልጽነት የጎደለውና ቁጭት የፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጥያቄው አሁን ላይ የብሔራዊ ደህንነት እና የቀጣናዊ ትስስር ዋነኛ ጉዳይ ሆኖ መውጣቱን ገልጸዋል።
🌍 የዲፕሎማሲ ስኬት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ግንዛቤ
የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ተወካይ አቶ በለጠ ሲጌቦ በበኩላቸው፣ የባህር በር ጉዳይ በአደባባይ መነሳቱ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን እንዲገነዘበው መደረጉ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑን አብራርተዋል። ይህም ለፍትሃዊ የባህር በር አጠቃቀም የሚደረገውን ትግል እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።
🏗️ "የቅንጦት ሳይሆን የመሰረታዊ ፍላጎት ጥያቄ"
የብልጽግና ፓርቲ አመራር አቶ ተስፋዬ ኤርሚያስ እንዳሉት፣ የባህር በር ጥያቄ እያደገ የመጣውን የሀገሪቱን ህዝብ ለመመገብና በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ተወዳዳሪ ለመሆን ወሳኝ ነው። "ኢትዮጵያ የባህር በር ተቆልፎባት መኖር የማትችል መሆኑን ዓለም ሊገነዘበው ይገባል" ሲሉም አክለዋል።
ቁልፍ ነጥቦች፦
* የባህር በር ጥያቄ ከፖለቲካ ልዩነት በላይ የሆነ የሀገር የህልውና ጉዳይ ነው።
* ለወደፊት ትውልድ የሚተላለፍ ብሔራዊ አጀንዳ ነው።
* ጉዳዩ ከኢኮኖሚ ባለፈ ከብሔራዊ ደህንነት ጋር ቀጥተኛ ትስስር አለው።
* ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት እያገኘ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ኢትዮጵያ #የባህርበር #ብሔራዊጥቅም #የባህርበርባለቤትነት #ዲፕሎማሲ #ምስራቅአፍሪካ #የህልውናጉዳይ #ethiopia #seaaccess #redsea #portaccess

8 months ago
ህዳሴን ለፍጻሜ ያበቃ ትውልድ የመልማት ቁጭቱን በባህር በር ሊደግም ይገባል - የቀድሞ የባህር ኃይል አባላት
#ethiopia | የህዳሴ ግድብን ለፍጻሜ ያበቃው ትውልድ የመልማት ቁጭቱን በባህር በር ሊደግመው ይገባል ሲሉ ከኢቲቪ ጋር ቆይታ ያደረጉ የቀድሞ የባህር ኃይል አባላት ገለፁ፡፡
የቀድሞ የባህር ሀይል አባል ማስተር ቺፍ ዘሩሁን ወዬሳ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር በነበራት ወቅት የንግድ እንቅስቃሴው በጥሩ ደረጃ ላይ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በጊዜው የአሰብ ወደብ ሁል ጊዜ ስራ ይበዛበት ነበር የሚሉት ማስተር ቺፍ ዘሩሁን፤ በዛን ወቅት በነበረው እንቅስቃሴ ላይ አሁን ያለው የተሳለጠ የንግድ እንቅስቃሴ ቢታከልበት ኖሮ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚ የምትገነባ ሀገር እንደምትሆን ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ ጠቅሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ አሁን እያነሳች ያለችው የባህር በር ይገባኛል ጥያቄ ወደብን ከማግኘት የዘለለ እና ሁለንተናዊ የመልማት ፍላጎትን የያዘ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለሀገሪቱ ደህንነትና ህልውና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑንም ተናግረዋል፡
ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በራሷ አቅም ሰርታ መጨረስ እንደምትችል ለዓለም አሳይታለች ያሉት ማስተር ቺፍ ዘሩሁን፤ አሁን ደግሞ የምታነሳውን ግልፅ የባህር በር ጥያቄ ከግብ ለማድረስ ትውልዱ በጋራ ሊቆም እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የቀድሞ የባህር ኃይል አባል ሊዲንግሲማን ጥበቡ ተፈራ በበኩላቸው፤ የባህር በር ጥያቄ የንግድ መስመር ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሉዓላዊነትም ጥያቄ ነው ይላሉ፡፡
የህዳሴ ግድብ ለፍፃሜ መብቃት የዘመናት ቁጭትን የመለሰ እንደመሆኑ አሁንም ትውልዱ በኢኮኖሚ የማደግ ፍላጎቱን በባህር በር ሊደግመው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በሐይማኖት ከበደ
#ebc #ebcdotstream #ethiopia #seaaccess