ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
ዓለማችን የተከበበች እና 71 በመቶዋም የውኃ አካል ሆኖ እያለ ኢትዮጵያችን ለምን የባህር በር ተነፈገች? ውኃ እንዲህ በበዛበት ዓለም ላይ እያለን፣ ለምን ከባህር በር ተገለልን?
ከቀይ ባህሩ የአሰብ ወደብ በቅርብ ርቀት ላይ እያለን ለምን ውኃውን እንዳናይ ተከልክለን የጂኦግራፊ እስረኛ ሆንን?
ኢትዮጵያ ከ30 ዓመታት በላይ ሲነወር የቆየ የባህር በር ጥያቄ አላት፡፡ ጥያቄው የብሔራዊ ጥቅም፣ የደህንነትና ህልውና ጉዳይ ነው፡፡
የባህር በር ከባህር ላይ የሚነሱ የደህንነት ስጋቶችንና ተጋላጭነትን ለመከላከል ያግዛል፡፡
አሁን አሁን በቀይ ባህር ቀጣና በርካታ ኃያላን የኃይል ፉክክርና ጂኦ ፖለቲካዊ ጥቅማቸውን የማስጠበቅ ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል፡፡
አይበለውና ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር አጥፊ የህልውና ሥጋት የሆነ የጦር መሣሪያ ቢጠመድባት፣ የባህር በር ስለሌላት እንዴት አድርጋ ነው ራሷን መከላከል የምትችለው?
ዓለም የባህር በር ተጠቃሚነት ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ ጥረት አድርጋለች፡፡
ለዚህ መፍትሄ ይሆናል የተባለው የዓለምን የባህር በር አጠቃቀም የሚወስነው የተባበሩት መንግሥታት የባህር አጠቃቀም ስምምነት በፈረንጆቹ 1982 ነበር ለሀገራት ፊርማ ይፋ ሆኖ በ1994 ወደ ሥራ የገባው፡፡ ኢትዮጵያም ሕጉን በፈረንጆቹ 1984 ፈርማለች፡፡
ነገር ግን ኢትዮጵያ ለሕጉ ተገዢ ብትሆንም እንደ ኤርትራ፣ አሜሪካ፣ እስራኤል፣ ቱርክ፣ ሶሪያን ጨምሮ 15 የዓለም ሀገራት ስምምነቱን አልፈረሙም፤ በነጻነት ግን ይጠቀማሉ፡፡
በዓለም አቀፉ ሕግ ሀገራት የባህር በር የመጠቀም መብት ቢኖራቸውም፣ በነጻነት ወደብ የመጠቀምም ሆነ በባህር የመንቀሳቀስ መብታቸው ግን በጂኦግራፊ የተገደበ ሆኖ ዘልቋል፡፡
በዚህም ምክንያት የጎረቤት ሀገራትን ወደብ ለመጠቀም ይገደዳሉ፡፡ ይህ ደግሞ ሀገራት በሌሎች ፍላጎቶችና ስሜት ጫና ስር እንዲወድቁ አድርጓቸዋል፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የብሔራዊ ደህንነት ስጋትም ይደቅናል፡፡
ኢትዮጵያም ይህ ኢ-ፍትሀዊነት ነው በሚል በጠቅላይ ሚኒስትሯ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አማካኝነት ጥያቄ በማንሳት ጉዳዩን የዓለም አጀንዳ አድርጋለች፡፡
ጉዳዩም የዓለም አቀፍ የፍትሓዊ ተጠቃሚነትና የባለቤትነት እንዲሁም የሕግ እና የዲፕሎማሲ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በዓለም አቀፉ ሕግ እና ዲፕሎማሲ ፊትም የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
ሀገራችን የባህር በር ስለሌላት፣ የጎረቤት ሀገራት የባህር በሮችን እና ወደቦችን ትጠቀማለች፡፡ ይህ ደግሞ የወጪ እና ገቢ ምርት እንቅስቃሴዋ እና የምርቶች ዋጋ ላይ ከፍተኛ የወጪ ጫና እያስከተለባት ነው፡፡
የባህር በር የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ እና የውጭ ንግድ የሚወስን ወሳኝ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ነው። በርካታ የወደብ፣ የጉምሩክ እና የሎጂስቲክስ የስራ እድሎችንም ለዜጎች ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ ቀጥታ የባህር በር የሌላት ሀገር በመሆኗ በአሁኑ ወቅት አማራጭ ወደቦችን ትጠቀማለች፡፡ የጅቡቲ ወደብ፣ የኢትዮጵያን የወጪና ገቢ ንግድ ከ90 በመቶ በላይ ያስተናግዳል።
በሶማሊላንድ ያለው የበርበራ ወደብ ሌላኛው የቅርብ አማራጭ ነው። የታጁራ እና የአሰብ ወደቦችም እንደ ተጨማሪ አማራጭ የሚጠቀሱ ናቸው።
በፈረንጆቹ እስከ 1995 ድረስ ከ90 በመቶ በላይ የኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ንግድ በአሰብ በኩል ሲከናወን የነበረ ሲሆን፣ ከ30 እስከ 40 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በምጽዋ ወደብ በኩል ይሳለጥ ነበር።
የባህር በር የሌለው ሀገር ከዓለም የንግድ ሥርዓት እኩልና ፍትሃዊ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ የባህር በር የኢኮኖሚ እድገት እንዲፋጠን ከማድረግ አንጻር ሚናው እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡
ምሁራን የባህር በር ካለህ ዓለምን ታገለግላለህ፣ የባህር በር ከሌለህ ግን የጎረቤት ሀገራት አገልጋይ ትሆናለህ የሚል ብሂል አላቸው፡፡
ይህንን የሚሉት የባህር በር ለአንድ ሀገር እድገትና ብሔራዊ ደህንነት ያለውን ጥቅም በደንብ ስለሚረዱ ነው፡፡
የባህር በር አንድ ሀገር ከዓለም ጋር ያለውን ሁለንተናዊ መስተጋብር ይወስናል፡፡
በዓለማችን ላይ ወደ 45 ሀገራት የባህር በር እንደሌላቸው ይነገራል፡፡ ይህም ከዓለም ሀገራት 20 በመቶ እንደ ማለት ሲሆን፤ አዳጊ የሚባሉ ሀገራትን 40 በመቶ የሚሸፍን ነው፡፡
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ለማደግና ለመበልፀግ የባህር በር ካላቸው እኩል አይደክሙም፡፡ የባህር በር የሌላቸውና አዳጊ የሚባሉ 32 ሀገሮች በአፍሪካ፣ አውሮፓ፣ እሲያ እና ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ ሀገራትም ወደ 500 ሚሊየን ሕዝብ አሏቸው፡፡
ይህም የዓለምን ሰባት በመቶ የህዝብ ብዛት ማለት ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 16ቱ በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከእነሱም ትልቋ ኢትዮጵያ ናት፡፡ እነዚህ ሀገራት የባህር በር ስለሌላቸው በዓለም ንግድ ውስጥ ያላቸው ድርሻ ከአንድ በመቶ ማለፍ አልቻለም፡፡
ይህም የባህር በር ስለሌላቸው ነው፡፡ ይህ ጂኦግራፊ የሀገሮችን እጣ ፈንታ እየበየነ እንዳለ ማሳያ ነው፡፡
የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በውድ የትራንስፖርት ወጪና በሌሎችም የንግድ እንቅፋቶች የተነሳ ከዓለም ገበያ ያላቸው ትስስር የላላ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡
ከዚህ የተነሳም በዓለም የፋይናንስ ስርዓት ችግሮችና በብድር እዳ ጫና ይማቅቃሉ፡፡
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ ቅርጽ ይዞ ትግሉ ቀጥላል፡፡
እናማ የባህር በር ባለቤት ለመሆን ታሪካዊና ሕጋዊ መብት የለንም ትላላችሁ?

13 days ago