1 day ago
ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ባለስልጣን የምዝገባ ፈቃድ አገኘ
👉ራሚስ ባንከ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ታሪከ አዲስ ምዕራፍ የከፈተለትን ታላቅ ስኬት በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል
በይፋ አብስሯል፡፡
ባንኩ በነባር ባለአክስዮኖች ተይዘው የሚገኙ 2 ሚልየን 101ሺ 106 አክስዮኖች በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) በይፋ መመዝገባቸውና የምዝገባ መግለጫው በመጽደቁ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) ዋና ገጽ ላይ ለመመዝገብ ያቀረበው ማመልከቻ ፈቃድ ያገኘ መሆኑን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።
ይህ ታሪካዊ ስኬት ራሚስ ባንክ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ታሪክ ውስጥ በ ESX ዋና ገጽ ለመመዝገብ የመርህ ደረጃ ፈቃድ ካገኙት ከመጀመሪያዎቹ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንዱ አድርጎታል።
የራሚስ ባንከ የዳይሬከተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ራቢ ሼክ ሁሴን፥ ባንኩ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በፅኑ የሸሪዓ መርሆች፣ በግልጽነት እና በጠንካራ ተቋማዊ አስተዳደር ላይ በመቆም የህብረተሰቡን እምነት ያተረፈ ሲሆን፣ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሙን በመጠቀም በምስራቅ አፍሪካ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ዋና ማዕከል የመሆን ታላቅ ሀገራዊ ግቡን ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ማለታቸውን ብስራት ሰምቷል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሊ እንደገለጹት ይህ በካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተሰጠው የምዝገባ ፈቃድ የራሚስ ባንክን የፋይናንስ ጥንካሬ፣ የኮርፖሬት አስተዳደር ብቃት እና ተቋማዊ አስተማማኝነት በግልጽ ያረጋገጠ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል።
ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል

14 days ago
#crowdfunding
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ በአገሪቱ ኢንቨስትመንት ክራውድ ፈንዲንግን ለመቆጣጠር የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቶ ለውይይት አቅርቧል።
ባለሥልጣኑ ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት፣ ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው ጽሑፋዊ አስተያየት እስከ ጥቅምት 04፣ 2019 ድረስ ወደ crowdfundingfeedbackecma.gov.et መላክ ይችላል ብሏል።
በተጨማሪም ባለሥልጣኑ የሕዝብ ውይይት መድረክና ማብራሪያ ጥቅምት 05 ቀን 2019 ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በስካይላይት ሆቴል ማዘጋጀቱን የገለጸ ሲሆን ፍላጎት ያለው ማንኛውም ሰው በአካል ተገኝቶ አስተያየት መስጠት እንደሚችል አስታውቋል።
@TikvahethMagazine

3 months ago
ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ የአክሲዮን ምዝገባ ፈቃድ አገኘ!
#fastmereja I ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የፋይናንስ ተቋም በመሆን የሚታወቀው ዘምዘም ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA) ይፋዊ የአክሲዮን ምዝገባ ማፅደቂያ ማግኘቱን አስታወቀ።
ባንኩ ከግብይት አማካሪው ወጋገን ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በመሆን በሰጠው የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በሰነደ ሙዓለ‐ንዋይን ለሕዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያ ቁጥር 1030/2024 መሠረት ምዝገባው በይፋ መጽደቁን ይፋ አድርጓል።
ይህ ዕውቅና ተቋሙ በኢትዮጵያ አዲስ ለተጀመረው የካፒታል ገበያ ታሪክ የመጀመሪያውን የአክሲዮን ምዝገባ ፈቃድ የወሰደ ቀዳሚ ባንክ የሚያደርገዉ ሲሆን ይህ ፈቃድ ተቋሙ ነባር አክሲዮኖቹን በሕጋዊ መንገድ እንዲመዘግብና አዳዲስ አክሲዮኖችን ለሕዝብ በማቅረብ ካፒታሉን በቀልጣፋ መንገድ እንዲያሳድግ ዕድል እንደሚፈጥርለት ተገልጿል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ መሊካ በድሪ እንደገለፁት፤ በጸደቀው የምዝገባ መግለጫ መሠረት ተቋሙ ያሉትን ነባር 5 ሚሊዮን አክሲዮኖች ያስመዘገበ ሲሆን፣ በተጨማሪም በትርፍ ድርሻ ወደ ካፒታል የሚቀየር 1 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው 1 ሚሊዮን አዳዲስ አክሲዮኖችን ይፋ ማድረጉን ገልፀዉ በጥቅሉ አጠቃላይ ካፒታሉን ወደ 15 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ማቀዱንም ጨምረው ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ጄነራል ወይዘሮ ራሄል ካሳ በበኩላቸዉ፤ ይህ ስኬት በሀገሪቱ አዲስ ለተጀመረው የካፒታል ገበያ መዳበር እና ከወለድ ነፃ ለሆነው የባንክ ኢንዱስትሪ መስፋፋት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ሲሉ ገልፀዋል።
ባንኩ ካፒታሉን ከማሳደጉ ባሻገር፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም የፋይናንስ መለኪያዎች ላይ ከፍተኛ ዕድገት ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በዚህም መሠረት አጠቃላይ ገቢው የ36% ዕድገት በማሳየት 3 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የተጣራ ትርፉ ደግሞ የ35% ጭማሪ በማሳየት 1.8 ቢሊዮን ብር ሆኗል። እንዲሁም የፋይናንስ ጥንካሬውን በሚያሳይ መልኩ የተከፈለ ካፒታሉ (Paid-up Capital) ከፍተኛ እምርታ በማሳየት ከ2.65 ቢሊዮን ብር ወደ 5.64 ቢሊዮን ብር ማደጉ ነዉ የተገለፀዉ።
በሌላ በኩል፣ በሕብረተሰቡ ዘንድ ያለውን እምነት በሚያሳይ መልኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ በ81% በማደግ 21 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ ደግሞ 29.1 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል።
ባንኩ ለቴክኖሎጂ በሰጠው ልዩ ትኩረት ባስተዋወቀው "አንሳር ዲጂታል" የተሰኘ የፋይናንስ አገልግሎት፣ በአጭርጊዜ ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የፋይናንስ አቅርቦትን ለ9,800 በላይ ደንበኞች ማድረስ ችሏል።
#ቢዝነስ ዘገባ

4 months ago
#የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ማግኘት፤ የሀገር በቀል ባንኮች ዕድልና ስጋት ምን ሊሆን ይችላል?
አዲስ ወደ ተመሠረተው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ለመቀላቀል የመጀመርያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል (United Capital) ማግኘቱ ታውቋል።
ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ማግኘት፤ የሀገር በቀል ባንኮች ዕድልና ስጋት ምን ሊሆን ይችላል?
ይህ ታሪካዊ እርምጃ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግርና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ በር የሚከፍት ቢሆንም፣ ገና በማቆጥቆጥ ላይ ላሉት የሀገር ውስጥ ባንኮች የራሱ የሆነ ስጋት ይዞ ይመጣል።
ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ስድስት (6) ሀገር በቀል የኢንቨስትመንት ባንኮች ማለትም CBE Capital, Wegagen Capital, First Addis Investment Bank, Awash Capital, Siinqee Investment Bank እና Prime Capital ፈቃድ ወስደው ወደ ገበያው ለመግባት በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ላይ የዩናይትድ ካፒታልን መግባት ተከትሎ የባንኮቹ ቁጥር ወደ ሰባት ከፍ ብሏል።
የዚህ ልምድ ያለው የውጭ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መቀላቀል በሀገሪቱ የኢኮኖሚ መነቃቃት ላይ የራሱ የሆነ ሰፊ ጥቅምና ስጋት ይዞ እንደሚመጣ የዘርፉ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።
የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ መግባት ከሚሰጣቸው ቀዳሚ ጥቅሞች መካከል የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር (Knowledge Transfer) ዋናው ነው።
የኢንቨስትመንት ባንክ ሥራ የረጅም ጊዜ ልምድና የዳበረ ቴክኖሎጂን የሚጠይቅ ሲሆን፣ ዩናይትድ ካፒታል በአፍሪካ የቦንድ እትም እና በሕዝብ አክሲዮን ሽያጭ (IPO) ላይ የቆየ ልምድ ያለው በመሆኑ ገበያው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል።
ለምሳሌ ያህል፣ እንደ የኢትዮጵያ ቴሌኮም ያሉ ግዙፍ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አክሲዮኖቻቸውን ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ ለመሸጥ (IPO) በሚዘጋጁበት ጊዜ፣ ባንኩ ያለውን ዘመናዊ የዋጋ ትመና እና የቴክኖሎጂ አደረጃጀት በመጠቀም ሂደቱ ስኬታማ እንዲሆን ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
በተጨማሪም የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትና የውጭ ምንዛሬን በመሳብ ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል።
የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች ከዓለም አቀፍ ባለሀብቶችና የፈንድ አደራጆች ጋር ሰፊ ትስስር አላቸው።
በሌላ በኩል፣ ይህ ሂደት ሊከተሉ የሚችሉ ዋና ዋና ስጋቶችንም የደቀነ ነው። የመጀመሪያው የሀገር በቀል ባንኮች በገበያው የመዋጥ ስጋት (Infant Industry Threat) ነው።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ገና በጅምር ላይ ያለና ፈቃድ የወሰዱት ስድስቱ የሀገር ውስጥ ባንኮች ገና በተግባር ያልተፈተኑ ድርጅቶች በመሆናቸው፣ ትልቅ ካፒታልና ሰፊ የሰው ኃይል ያለው የውጭ ባንክ ሲገባ ገበያውን የመጠቅለል ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
ባጠቃላይ የዩናይትድ ካፒታል መግባት የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ በአቋራጭ መንገድ በፍጥነት እንዲያድግና ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ የሚያደርግ ቢሆንም፣ የሀገር ውስጥ ባንኮችን ህልውና አደጋ ላይ እንዳይጥል ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) የሀገር ውስጥ ባንኮች ተወዳዳሪ ሆነው እስኪያድጉ ድረስ የተወሰኑ ትልልቅ የሀገር ውስጥ ሥራዎች በጋራ (Joint Venture) እንዲሠሩ ሕግ ማውጣትን ጨምሮ፣ ተገቢውን የቁጥጥርና የጥበቃ ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት የዘርፉ ተንታኞች በማሳሰብ ላይ ናቸው።
ይህንን ዘገባ ስናዘጋጅ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ያወጣቸውን የሕግ ማዕቀፎች እና መመሪያዎች ተጠቅመናል። በተጨማሪም መሰል የውጭ ኢንቨስትመንት ባንኮች ወደ ታዳጊ ሀገራት ገበያ ሲገቡ የሚኖራቸውን ጥቅምና ስጋት፣ በተለይም በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የታዩትን ተጨባጭ ተሞክሮዎችና የፋይናንስ ዘርፍ መርሆዎች መሠረት በማድረግ ዘገባው ተዘጋጅቷል፡፡
Seledadotio

5 months ago
እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮ ቴሌኮም ባለአክሲዮኖቹ አክሲዮናቸውን በሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ መሸጥ፣ መግዛት እና ማስተላለፍ እንደሚችሉ በታላቅ ደስታ ያበስራል!
በዛሬው ዕለት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ ኩባንያው አስፈላጊ ሕጋዊ አሠራሮችን በማሟላት ባለአክሲዮኖች በሁለተኛ ገበያ (ESX) አክሲዮኖችን መግዛት፣ መሸጥና ማስተላለፍ እንዲጀምሩ ዝግጁ ማድረጉን በይፋ አብስረዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን፤ አንጋፋውን የሀገራችንን ተቋም ወደ አክሲዮን ማኅበር በማዛወር ዜጎችን የጋራ ሀብት ባለቤት ለማድረግ፣ የሀገሪቱን የካፒታል ገበያ ለማጠናከርና የጋራ ዕድገትን ለማፋጠን የተወሰደው እርምጃ ታሪካዊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተለይም ባለፉት ወራት በተከናወነ መጠነ-ሰፊ የማጣራት ሥራ ከ47,377 ባለአክሲዮኖች ውስጥ 45,366ቱ (95.8 በመቶ) ምዝገባቸውን በስኬት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። ይህም በገንዘብ ሲሰላ 3.04 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው 10.1 ሚሊዮን አክሲዮኖች ለግብይት ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል ብለዋል።
በሌላ በኩል መረጃ ያልተሟላላቸው 1,646 ባለአክሲዮኖች መረጃቸውን በአፋጣኝ እንዲያሟሉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ በአክሲዮን ሽያጩ ለመሳተፍ ብቁ ያልሆኑ 248 የውጭ ዜጎች ክፍያም በአሠራሩ መሠረት ተመላሽ ይደረጋል።
በዕለቱ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ተዋናዮች በተገኙበት የአክሲዮን ግብይት ማስጀመሪያ የደወል ሥነ ሥርዓት የተከናወነ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ግብይትም በሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያው በይፋ ተከናውኗል። በተጨማሪም ኩባንያችን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ በይፋ መመዝገቡን በማስመልከት የምስክር ወረቀቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ከኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር ዶክተር ጥላሁን እስማኤል ተረክበዋል።
ባለአክሲዮኖች አክሲዮናቸውን ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት በመጀመሪያ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ፈቃድ ከተሰጣቸው አገበያዮች ወይም የኢንቨስትመንት ባንኮች ዘንድ በመቅረብ የንግድ አካውንት መክፈት ይኖርባቸዋል።
በመጪው በጀት ዓመት የፋይናንስ ኦዲቱ እንደተጠናቀቀ በሚጠራው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ (AGM) ላይ የትርፍ ክፍፍል መጠን ተወስኖ ይፋ ይደረጋል። የባለቤትነት ድርሻቸውን ሂደት ያጠናቀቁ ባለአክሲዮኖች፤ የባለቤትነት መብታቸው ከያዝነው በጀት ዓመት መጀመሪያ ጀምሮ የሚጠበቅላቸው ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ፦ https://bit.ly/4nROnuL
#ethiotelecom #ecma #capitalmarket #esx #csd

Sponsored by
Surafel
6 months ago
🚨 ከባይራ አክሲዮን ማኅበር የአክሲዮን ግዢ ይቆጠቡ!
#ethiopia | የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን "ባይራ አክሲዮን ማኅበር" በተባለውና "የውሃ ፋብሪካ አቋቁማለሁ" በሚል ስም በሚንቀሳቀሰው ድርጅት ላይ ጥብቅ የጥንቃቄ ማሳሰቢያ አውጥቷል።
ድርጅቱ "አርባ ምንጭ ውሃ" በሚል ስያሜ በባለሥልጣኑ ያልተመዘገቡ አክሲዮኖችን ለሕዝብ ለሽያጭ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝ በክትትል ተደርሶበታል።
ባለሥልጣኑ ባደረገው ምርመራ ድርጅቱ በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 እና በሰነደ መዋለ ንዋዮች መመሪያ ላይ የተቀመጡ ድንጋጌዎችን በግልጽ ጥሷል። ማንኛውም ድርጅት አክሲዮን ለሕዝብ ከመሸጡ በፊት በባለሥልጣኑ መመዝገብ እና የቅድመ-ማስታወቂያ ፈቃድ ማግኘት ቢገባውም ባይራ አክሲዮን ማኅበር ግን ይህንን ሕጋዊ ሂደት ሳይከተል በማኅበራዊ ሚዲያ እና በተለያዩ አውታሮች ሽያጭ እያከናወነ ይገኛል።
ይህ ድርጊት በሕግ ፊት በወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር መሆኑን ባለሥልጣኑ በጽኑ አሳስቧል።
የኢንቨስትመንት ደህንነትዎን ለመጠበቅ ሲባል ማኅበረሰቡ አክሲዮኖቹ በባለሥልጣኑ ያልተመዘገቡ መሆናቸውን ተገንዝቦ ከማንኛውም ዓይነት ግዢ እንዲቆጠብ ጥሪ ቀርቧል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ለማንኛውም የሽያጭ ወኪልም ሆነ በቀጥታ ለድርጅቱ ምንም ዓይነት ክፍያ እንዳይፈጸም ባለሥልጣኑ በጥብቅ አዟል። በአሁኑ ወቅት በድርጅቱ ላይ ጥልቅ አስተዳደራዊ ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን የኢንቨስተሮችን መብት ለማስጠበቅ አስፈላጊው እርምጃ ሁሉ እንደሚወሰድ ታውቋል።
መሰል ሕገ-ወጥ የሆኑ የአክሲዮን ሽያጭ ተግባራትን ሲመለከቱ በስልክ ቁጥር +251 115 57 6123 በመደወል ወይም በኢሜይል አድራሻ compliantsecma.gov.et በመጠቀም ጥቆማ በመስጠት ከባለሥልጣኑ ጋር እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።
የኢንቨስትመንት ደህንነትዎ በሕግ የተጠበቀ እንዲሆን ሁልጊዜም በባለሥልጣኑ የተመዘገቡ ተቋማትን ብቻ በመምረጥ እራስዎን ከማጭበርበር እንዲጠብቁ ባለስልጣኑ አሳስቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu #menahriafm #eth #sharecompany

10 months ago
አዋሽ ካፒታል አ.ማ በይፋ ሥራ ጀመረ
#fastmereja I የአዋሽ ባንክ ተቀጥላ ኩባንያ የሆነው አዋሽ ካፒታል አ.ማ. በኢትዮጵያ አዲስ ለተጀመረው የካፒታል ገበያ ማዕቀፍ ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቆ ዛሬ ታኅሣሥ 09 ቀን 2018 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል በይፋ ሥራ መጀመሩን አብስሯል።
ተቋሙ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ሙሉ የኢንቨስትመንት ባንክ አገልግሎት ፈቃዱን ሕዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ተረክቧል።
በ200 ሚሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ሥራውን የጀመረ ሲሆን፣ ወደፊት ካፒታሉን ወደ 400 ሚሊዮን ብር ለማሳደግ ዕቅድ ይዟል። አዋሽ ባንክ የተቋሙ የ95 በመቶ ባለድርሻ ነው።
ዶ/ር አንዱአለም ኃይሉ የአዋሽ ካፒታል አ.ማ. ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰይመዋል።
አዋሽ ካፒታል አ.ማ. የሚሰጣቸው አገልግሎቶች፦
📌 የድርጅት ፋይናንስ እና የማማከር አገልግሎት።
📌 የዋስትና ሰነዶች (Securities) ንግድ እና የማገናኘት ሥራ።
📌 የገበያ ጥናትና ምርምር (Research and Market Intelligence)።
📌 የአረንጓዴ ፋይናንስ እና የESG (ከባባዊ፣ ማኅበራዊና አስተዳደራዊ) የማማከር አገልግሎት።
የአዋሽ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የአዋሽ ካፒታል የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ባደረጉት ንግግር የተቋሙ መቋቋም በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍትና ለቢዝነስ ዘርፉ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር ነው ብለዋል።
#ቢዝነስ መረጃ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) የአመራር ለውጥ አደረገ
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) ከፍተኛ ሹመቶች እና በአመራር ምደባ ዙሪያ የተነሳ አለመግባባትን ተከትሎ፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራር በአዲስ መልክ ተዋቅሯል።
ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ብሩክ ታዬ ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል።
ፎርቹን ባየው መግለጫ እና የውስጥ ደብዳቤ ላይ ዶ/ር ብሩክ የአመራር ለውጡን ያደረጉት “ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማስመለስ እና የልማት ባንኩን ከብሔራዊ ልማት ቅድሚያዎች ጋር ለማጣጣም ያለመ ሰፊ የማሻሻያ አጀንዳ” አካል መሆኑን ገልጸዋል።
የቀድሞ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ እና ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር እመቤት መለሰ (ዓርብ፣ ታኅሣሥ 3 ቀን 2018 ዓ.ም.) የተተኩት፣ በምክትል ፕሬዝዳንቶች ሹመት እና ለከፍተኛ ሠራተኞች የብቃት ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ በቦርዱ እና በዋና ሥራ አስፈጻሚው መካከል የነበረው አለመግባባት ከጠነከረ በኋላ ነው። ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ የተካረረ ልዩነት ስትራቴጂያዊ የውሳኔ አሰጣጥን እያደናቀፈ ነበር። ለባንኩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳሉት፣ አለመግባባቱን ለማርገብ የመጨረሻ ጥረት የተደረገው ከአንድ ሳምንት በፊት ሲሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ እና የማዕከላዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በአቶ ተክለወልድ እና በዶ/ር እመቤት መካከል ስብሰባ ጠርተው ነበር። ሆኖም ውይይቱ ልዩነቱን ማጥበብ እንዳልቻለ ምንጮቹ ገልጸዋል። ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ሲመሠረት በዶ/ር ብሩክ ይመራ የነበረው መስራች ሥራ አስፈፃሚ አካል ውስጥ ነበሩ።
seledadotio

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአመራር ለውጥ አደረገ
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) ከፍተኛ ሹመቶች እና በአመራር ምደባ ዙሪያ የተነሳ አለመግባባትን ተከትሎ፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራር በአዲስ መልክ ተዋቅሯል።
ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ብሩክ ታዬ ደግሞ የቦርዱ ሰብሳቢ ሆነው ተሰይመዋል።
ፎርቹን ባየው መግለጫ እና የውስጥ ደብዳቤ ላይ ዶ/ር ብሩክ የአመራር ለውጡን ያደረጉት “ተቋማዊ ውጤታማነትን ለማስመለስ እና የልማት ባንኩን ከብሔራዊ ልማት ቅድሚያዎች ጋር ለማጣጣም ያለመ ሰፊ የማሻሻያ አጀንዳ” አካል መሆኑን ገልጸዋል።
የቀድሞ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ እና ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር እመቤት መለሰ (ዓርብ፣ ታኅሣሥ 3 ቀን 2018 ዓ.ም.) የተተኩት፣ በምክትል ፕሬዝዳንቶች ሹመት እና ለከፍተኛ ሠራተኞች የብቃት ፈተና አሰጣጥ ዙሪያ በቦርዱ እና በዋና ሥራ አስፈጻሚው መካከል የነበረው አለመግባባት ከጠነከረ በኋላ ነው። ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ የተካረረ ልዩነት ስትራቴጂያዊ የውሳኔ አሰጣጥን እያደናቀፈ ነበር። ለባንኩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንዳሉት፣ አለመግባባቱን ለማርገብ የመጨረሻ ጥረት የተደረገው ከአንድ ሳምንት በፊት ሲሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ እና የማዕከላዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ በአቶ ተክለወልድ እና በዶ/ር እመቤት መካከል ስብሰባ ጠርተው ነበር። ሆኖም ውይይቱ ልዩነቱን ማጥበብ እንዳልቻለ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ሲመሠረት በዶ/ር ብሩክ ይመራ የነበረው መስራች ሥራ አስፈፃሚ አካል ውስጥ ነበሩ። የዶክትሬት ዲግሪያቸውን የተከታተሉት ደግሞ በአሜሪካ ዋልደን ዩኒቨርሲቲ ነው። ከ2010 እስከ 2011 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። በተጨማሪም በኢንተለጀንስ እና ደህንነት መረጃ መረብ ኤጀንሲ (INSA) የስትራቴጂ እና የሳይበር ምርምር ዳይሬክተር እንዲሁም የሕግ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል።
አዲስ ፎርቹን

ሰበር ዜና : የኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) የአመራር ለውጥ አደረገ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ልማት ባንክ (DBE) ከፍተኛ ሹመቶች እና በአመራር ምደባ ዙሪያ የተነሳ አለመግባባትን ተከትሎ፣ የባንኩ ከፍተኛ አመራር በአዲስ መልክ ተዋቅሯል።

ዶ/ር ኢሣያስ ካሣ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን (ECMA) ሲመሠረት በዶ/ር ብሩክ ይመራ የነበረው መስራች ሥራ አስፈፃሚ አካል ውስጥ ነበሩ። የዶክትሬት ዲግሪያቸውን የተከታተሉት ደግሞ በአሜሪካ ዋልደን ዩኒቨርሲቲ ነው። ከ2010 እስከ 2011 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል። በተጨማሪም በኢንተለጀንስ እና ደህንነት መረጃ መረብ ኤጀንሲ (INSA) የስትራቴጂ እና የሳይበር ምርምር ዳይሬክተር እንዲሁም የሕግ አማካሪ ሆነው አገልግለዋል ሲል አዲስ ፎርቹን ዘግቧል።

Comments