2 months ago
የኢትዮጵያና የማላዊ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታቸውን በአንድ አቻ ውጤት አጠናቀቁ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ዛሬ ከማላዊ አቻው ጋር ባደረገው የወዳጅነት ግጥሚያ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በድሬዳዋ ስታዲየም ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ በተጀመረው በዚህ ጨዋታ ለዋልያዎቹ ብቸኛዋን ግብ ቢኒያም በላይ ከመረብ ማገናኘት የቻለ ሲሆን የማላዊን የአቻነት ግብ ደግሞ አዴፖጁ ባባቱንዴ አስቆጥሯል።
በዋና አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባሳለፍነው ቅዳሜ በተመሳሳይ በድሬዳዋ ስታዲየም ከማላዊ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።
#walyas #football #diredawa #ethiopianfootball #malawi #friendlymatch #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 months ago
🇪🇹 ኢትዮጵያ አልተቻለችም
📌ዋልያዎቹ ወደ ምድብ ድልድሉ በክብር ተሻግረዋል!
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ከአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ተግዳሮት በድል ወጥተዋል። ከሳኦ ቶሜ ጋር በተደረገው የመልስ ጨዋታ ዋልያዎቹ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋንና ወሳኝዋን የማሸነፊያ ግብ ከመረብ ያሳረፈው ቸርነት ጉግሣ ነው። በዚህም ውጤት መሰረት ኢትዮጵያ የደርሶ መልስ ጨዋታውን በድምር 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማጠናቀቅ በቀጥታ ወደ ምድብ ድልድሉ ተቀላቅላለች።
አሁን ላይ ሙሉ ትኩረት የሚሆነው በ2027 ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ ሲሆን፣ የቡድኖቹ የዕጣ ድልድልም በቅርብ ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
እንኳን ደስ አላችሁ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #walyas #afcon2027 #ethiopianfootball #chernetgugsa #sportnews #ዋልያዎቹ #ኢትዮጵያ

7 months ago
🇪🇹 ዋልያዎቹ አሰልጣኝ 513 ሺ ብር ደሞዝ ይከፈላቸዋል
#ethiopia | ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ፣ ሹመታቸውን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን የተመራው ይኸው መግለጫ፣ አሰልጣኙ የተመረጡበትን መመዘኛ እና የውል ዝርዝራቸውን ይፋ አድርጓል።
🔍 ምርጫው እንዴት ተካሄደ?
ከአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ስንብት በኋላ፣ ፌዴሬሽኑ ለቦታው ብቁ የሆኑ ሦስት እጩዎችን ይዞ እንደነበር ተገልጿል። እነሱም፦
* አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
* አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
* አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ ነበሩ።
✅ ዮሐንስ ሳህሌ ለምን ተመረጡ?
የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አሰልጣኝ ዮሐንስን ለመምረጥ የተጠቀመባቸው ቁልፍ መመዘኛዎች፦
* ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ቡድን የነበራቸው ልምድ እና ያስመዘገቡት ውጤት።
* ቡድኑን ለቻን (CHAN) እና ለአፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ብቃታቸው።
* በታዳጊዎች ልማት ላይ ያላቸው ስራ እና ከፌዴሬሽኑ ራዕይ ጋር አብሮ የመጓዝ ፍላጎታቸው።
* ያላቸው የታክቲክ ጥልቀት እና ወቅታዊ የስልጠና ብቃት በሰፊው ተገምግሟል።
💰 የውል ዝርዝር እና ደሞዝ
አሰልጣኙ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ብሔራዊ ቡድኑን የሚመሩ ሲሆን፦
* የውል ዘመን፦ ከታህሳስ 27 ቀን 2018 እስከ ታህሳስ 26 ቀን 2020 ዓ.ም.
* የወር ደሞዝ፦ 513,000 (አምስት መቶ አስራ ሶስት ሺህ) ያልተጣራ ብር ከተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞች ጋር።
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ዋልያዎቹን ወደ ቀደመ ዝናቸው ለመመለስ እና በታዳጊዎች ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ቡድን ለመገንባት ትልቅ ኃላፊነት ይጠብቃቸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ኢትዮጵያ #እግርኳስ #ዋልያዎቹ #ዮሐንስሳህሌ #ብሔራዊቡድን #ስፖርት #ethiopianfootball #walyas #eff

Comments