1 hr. ago
የሜሲ ስንበት ጨዋታ ትኬት ዋጋ ጨመረ !
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ዛሬ ሌሊት የብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻ ጨዋታውን ያደርጋል።
አሁን ላይ አርጀንቲና ከቤኒን የሚያደርጉት ጨዋታ የስታዲየም መግቢያ ትኬት ዋጋ መናሩ ተገልጿል።
የጨዋታው ትኬት በአሁኑ ሰዓት ይፋዊ ዋጋው ላይ 567% ጭማሪ ተደርጎበት መልሶ እየተሸጠ መሆኑ ተነግሯል።
ትኬቶች በ 905 ዩሮ እየተሸጡ የሚገኙ ሲሆን የአርጀንቲና እግር ኳስ ፌዴሬሽን ህገወጥ ሽያጮችን አስጠንቅቋል።
@tikvahethsport kidusyoftahe

#odabultumuniversity
በ2019 ዓ.ም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ትምህርት ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● ስምንት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
የምዝገባ ቦታ፡-
● በዩኒቨርሲቲው አዲሱ ካምፓስ
@tikvahuniversity

2 hours ago
“ እንደ ሲቲ መሆን አንፈልግም “ የኮሞ ፕሬዝዳንት
የኮሞ ፕሬዝዳንት ሚርዋን ሱዋርሶ ክለባቸው እንደ ማንችስተር ሲቲ መሆን አይፈልግም በማለት ተናግረዋል።
ስለ ማንችስተር ሲቲ ክስ የተጠየቁት ፕሬዝዳንቱ “ እውነት ሆኖ ከተረጋገጠ በጣም አስከፊ ነገር ነው ” ብለዋል።
“ ፍትሀዊ በሆነ ስፖርት ስኬታማ ለመሆን ማጭበርበር ለምን እንዳሰቡ አልገባኝም “ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
አክለውም “ ስኬታቸውን ተጠቅመው የሰሩትን ስህተት ማስተካከል አለባቸው ፤ እኛ በጭራሽ እንደነሱ መሆን አንፈልግም "ሲሉ ገልጸዋል።

5 hours ago
ዳኒ ካርቫል ወደ ሄታፌ ?
ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ዳኒ ካርቫል ሄታፌን ለመቀላቀል በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።
የላሊጋው ክለብ ሄታፌ ዳኒ ካርቫልን በነፃ ዝውውር ለማስፈረም እየሰራ መሆኑን አረጋግጧል።
በሁለቱ ወገኖች መካከል ከስምምነት ባይደረስም ንግግሮች የተሻለ ደረጃ ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።
ዳኒ ካርቫል በዚህ ክረምት ሪያል ማድሪድን ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ መልቀቁ አይዘነጋም።

Sponsored by
Surafel
5 hours ago
#uog
በ2019 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
በተመሳሳይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
የምዝገባ ቦታ፡-
● ለማኅበራዊ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በማራኪ ግቢ
● ለተፈጥሮ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ
● ለድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በግቢው ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሰቲው ከመሔዳችሁ በፊት በኦንላይን (Registration.uog.edu.et) ምዝገባችሁን እንድትፈጸሙ ተብሏል። (የምዝገባ ሒደቱ ቅደም ተከተልን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)

#dillauniversity
በ2019 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ (Freshman) ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
በተመሳሳይ በ2ኛ ዲግሪ (Masters) እና በ3ኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራሞች ለመማር አመልክታችሁ ተቀባይነት ያገኛችሁ አዲስ ገቢ የድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
በ2019 ዓ.ም ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 19 እና 20/2019 ዓ.ም መሆኑ ተመላክቷል።
አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ፈተና ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፣
● አንድ የሰነድ መያዣ ክላሰር።
የምዝገባ ቦታ፦
ኦዳያኣ ግቢ የሬጅስትራር ህንፃ ቁጥር 609 በአካል

6 hours ago
#debarkuniversity
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜን አራዝሟል።
የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 28-29/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ለሪማዲያል ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ ተማሪዎች መረጃ ባለመላኩ የምዝገባው ወቅት ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
በመሆኑም አዲስ ለተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

7 hours ago
“ ራሴን ለማንም ማረጋገጥ አያስፈልገኝም ” አራውሆ
የሊቨርፑሉ ዩራጓዊ ተከላካይ ሮናልድ አራውሆ ለሰዎች ራሱን ለማሳየት እንደማይጫወት ገልጿል።
“ ለሰዎች ምላሽ ለመስጠት ወይም ለማንም ራሴን ለማሳየት አልጫወትም ” ሲል አራውሆ ተናግሯል።
አክሎም “ ያለኝን አቅም እና ምን ማድረግ እንደምችል አውቃለሁ በዚህ እርግጠኛ ነኝ "ሲል ገልጿል።
“ አሁን የምፈልገውን ወጥ የሆነ አቋም እያሳየሁ ነው በራስ መተማመን እና ወጥ አቋም ሲኖረኝ ያለኝ ዋጋ ይታያል "አራውሆ

18 hours ago
ፈረንሳይ እና ጣልያን አሸንፈዋል !
በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ መርሐግብር ፈረንሳይ ቤልጂየምን 4ለ1 ፤ ጣልያን ቱርክን 3ለ1 ማሸነፍ ችለዋል።
የፈረንሳይን የድል ግቦች ኦሊሴ 2x ፣ ሼርኪ እና ዱዌ ከመረብ ሲያሳርፉ ለቤልጅየም ሉኬባክዮ አስቆጥሯል።
ካላፊዮሪ ፣ ሳካማካ እና እስፖሲቶ የጣልያንን ግቦች ሲያስቆጥሩ ስምሲር የቱርክን ግብ ከመረብ አሳርፏል።
ስዊድን በበኩሏ ሮማንያን በቪክቶር ዮኬሬሽ ግብ 1ለ0 አሸንፋለች።
ቪክቶር ዮኬሬሽ በሰባት ተከታታይ የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎች ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው ተጨዋች ሆኗል።
ዮኬሬሽ ለብሔራዊ ቡድኑ ባደረጋቸው ያለፉት አራት ጨዋታዎች አራት ግቦችን አስቆጥሯል።
በሌሎች ጨዋታዎች :-
- ሀንጋሪ ዩክሬይንን 2ለ1
- ቦስኒያ ፖላንድን 1ለ0 ማሸነፍ ችለዋል።

እናት ባንክ የመጀመሪያውን የሥርዓተ ፆታ ቦንድ ለገበያ ለማቅረብ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መሆኑን ገለጸ
እናት ባንክ በሴቶች ለተያዙና ለሚመሩ ኢንተርፕራይዞች የረጅም ጊዜ ፋይናንስ ለማቅረብ ያዘጋጀውን የሥርዓተ ፆታ ቦንድ/ Gender Bond ሽያጭ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰሎሞን ገለጹ።
ሰብሳቢዋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ እንደተናገሩት፣ የቦንድ ሽያጩን ለመጀመር የሚያስፈልጉ ጥናቶች ተጠናቀው የመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
የቦንዱ የመግዣ ዋጋ እና ወደ ሽያጭ የሚገባበት ትክክለኛ ቀን ቦንዱን ከሚያስተዳድረውና ከሚቆጣጠረው አካል ፈቃድ ሲገኝ የሚወሰን እንደሆነም ነው የጠቆሙት።
ከዚህ የቦንድ ሽያጭ የሚሰበሰበው የፋይናንስ ምንጭ መደበኛ የብድር ዋስትና ማስያዣ ማቅረብ ለማይችሉ ሴቶች ብድር ለማቅረብ ከመዋሉም ባሻገር፣ ለፋይናንሺያል ስልጠናዎችና የሴቶችን የሥራ ፈጠራ አቅም ለማጎልበት በሚደረጉ ድጋፎች ላይ ውላል።
"እስካሁን ሴቶችን ለማገዝ በሰራናቸው ስራዎች በሴቶች ላይ ለውጦችን አይተናል። በዚህ የቦንድ ሽያጭ ላይ ይሳተፋሉ ብለን ያሰብናቸው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር አለም አቀፍ ተቋማቶች አሉ። ተቋማቶች የቦንድ ሽያጩ እስኪጀመር እየጠበቁ ነው፣ ከዛም በኃላ ለየትኛውም ህዝብ ክፍት ይሆናል" ነው ያሉት።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በሱብ-ሳሃራ አፍሪካ የሚገኙ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የ42 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት ቢኖርባቸውም፣ ሴት ተበዳሪዎች ብድር የመመለስ ታማኝነታቸው ከፍተኛ መሆኑና የማይመለስ ብድር (NPL) መጠናቸው ከወንዶች በ53 በመቶ ዝቅተኛ እንደሆነ ያሳያል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@TikvahethMagazine

" የኦቶና ሆስፒታል በተገቢው ሁኔታ መልሶ አለመገንባቱና አለመጠገኑ ታካሚዎችን ለአላስፈላጊ እንግልት እየዳረጋቸው ነው " - ነዋሪዎች እና የጤና ባለሙያዎች
ከአንድ ዓመት በፊት በድንገተኛ የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የኦቶና ሆስፒታል አሁንም ድረስ ተገቢው ጥገናና መልሶ መገንባት ስላልተደረገለት ታካሚዎች ለዘርፈ ብዙ ችግሮች እና እንግልት እየተዳረጉ ስለመሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ተናግረዋል።
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ስማቸው እንዲገጸል ያልፈለጉ የሆስፒታሉ ታካሚዎች እና የጤና ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ፣ የተቋሙ መልሶ አለመገንባት አጠቃላይ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከፍተኛ እክል ስለመፍጠሩ ያስረዳሉ።
ታካሚዎች ምን አሉ ?
ለረጅም ዓመታት በሕክምና ተቋሙ ይመላለሱ እንደነበር የገለጹት የመጀመሪያው ታካሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል " በቃጠሎው ምክንያት በርካታ የአገልግሎት ክፍሎች ተዘግተው በመቆየታቸው በሆስፒታሉ ውስጥ ከፍተኛ መጨናነቅ ፈጥሮ ቆይቷል " ብለዋል።
በእንዲህ ያለው ሁኔታ በርካታ ሰዎች ለሕክምና መጥተው ሳይታከሙ ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ መመልከታቸውን ገልጸው " እኔም ብሆን የኢኮኖሚ አቅም ውሱንነት ስላለብኝ ባለሙያዎችን እየለመንኩ ለመታከም ተገደጃለሁ " ብለዋል።
አክለውም " ሆስፒታሉ ' ፈጥኖ ይታደሳል፣ ይጠገናል ' በሚል በተስፋ ስንጠባበቅ ብንቆይም፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምንም ዓይነት የተሻለ የጥገና እርምጃ አለመወሰዱ እጅግ አሳዝኖናል፤ ታካሚዎችንም ለከፍተኛ እንግልት ዳርጓል " ሲሉ ገልጸዋል።
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡት ሁለተኛው የመረጃ ምንጭ በበኩላቸው፤ " ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ይሰጣቸው የነበሩና በቃጠሎው ምክንያት ሙሉ በሙሉ የቆሙ በርካታ የምርመራ ዓይነቶች አሉ " ብለዋል።
ቀጥለውም " በቅርቡም አንድ የቤተሰብ አባሌን ለማሳከም ወደ ሆስፒታሉ በሄድኩበት ወቅት፣ ከቃጠሎው በፊት እዚያው ይሰጡ የነበሩ ነገር ግን አሁን ላይ የቆሙ ምርመራዎችን ለማድረግ ሁለት ጊዜ ወደ ሌላ የግል ተቋም እንዲሁም ወደ አርባምንጭ ከተማ ጭምር ለመሄድ ተገደድናል " ሲሉ አስረድተዋል።
የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች ምን አሉ ?
ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ሁለት የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፤ " ተቋሙ በድንገተኛ ቃጠሎ ጉዳት ከደረሰበት በኋላ በሕክምና አገልግሎቱ ላይ ሰፊ ክፍተት ተፈጥሯል። የታካሚዎች እንግልትና ቅሬታ ሙሉ በሙሉ ተገቢና እኛም የምንጋራው እውነታ ነው " ብለዋል።
አክለውም " ለሆስፒታሉ መልሶ መገንባት ከፌዴራል ተጠሪ መስሪያ ቤት (ከጤና ሚኒስቴር) ጀምሮ እስከ ክልል አካላት፣ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ድረስ ከፍተኛ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ቢደረግም፣ ብዙም ግልጽ ባልሆኑ ምክንያቶች እስካሁን ጥገናውና ግንባታው ሳይከናወን መቅረቱ አሳዛኝ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
" ከሰሞኑ የተቃጠለውን ሕንፃ የማፀዳዳት ስራዎች እየተከናወኑ ነው " ያሉት ሁለቱ የጤና ባለሙያዎች " ሆስፒታሉ በአስቸኳይ ተጠግኖ የሕብረተሰቡን እንግልት ቢያስቀር ጥሩ ነው " ሲሉ አሳስበዋል።
ባለድርሻ አካላት ምን አሉ ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ፦
- ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ፣
- ከወላይታ ሶዶ ጤና መምሪያ
- ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ሙከራ ስልክ ባለማንሳት እንዲሁም በሰሞኑ በተደረገው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአመራር ለውጥና ሽግሽግ ምክንያት የስራ ኃላፊዎች በመቀያየራቸው መረጃ ማግኘት አልተቻለም።
ተጨማሪ ሙከራዎችን አድርገን ምላሻቸውን ለማቅረብ እንሞክራለን።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
ፎቶ ፦ ፋይል
@tikvahethiopia ፎቶ ፦ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የተከሰተው የእሳት አደጋ በህዝቡ ብርቱ ጥረት በቁጥጥር ሥር ማዋል እንደተቻለ ተገልጿል። በአደጋው የሆስፒታሉ ቀዶ ሕክምና ፣ የውስጥ ደዌ ሕክምና እና ተመላላሽ ሕክምና ክፍሎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተጠቁሟል። መንስኤው እየተጣራ ነው ተብሏል። #wolaitazoneadministration #tikvahethiopiafamilywolaitasodo…

#tigray
#mekelle
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይል መቐለን ከተቆጣጠሩ በኋላ ስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መጀመሩ የሚታወቅ ሲሆን ቤተሰቦችም እየተገናኙ ነው።
የባንክ አገልግሎትም ተጀምሯል።
በመቐለ ከተማ የፀጥታ ሁኔታው እና የሚፈጸመው ዝርፊያ ካለፉት ቀናት መሻሻል ቢያሳይም ሙሉ በሙሉ ሊቆም እንዳልቻለ ሁለት ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
" ትላንት ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ከታክሲ እያወረዱ ሞባይልና ገንዘብ ሲዘርፉ ተመልክተናል " ሲሉ አንድ እማኝ ተናግረዋል።
" በቢላዋ እና ትጥቅ በማስፈራራት የግለሰቦች ቤት በመስበር የመሰሉ ዘረፋዎችም በስፋት አሉ " ሲል ሌላኛው ነዋሪ ገልጿል።
በሌላ በኩል፥ የከተማዋ እንቅስቃሴ ወደ መደበኛነት እየመጣ መሆኑን አመልክተዋል። በርካታ ወጣቶች ፣ መኪኖች እና ባጃጆች በከተማዋ በብዛት ወጥተው መንቀሳቀስ ጀምረዋል።
ይህ በእንዳህ እያለ ከሳምንት በላይ የተቋረጡት በክልሉ የሚገኙ የመንግስትና የግል ሚድያዎች መልሶ ለማስጀመር የሚያስችሉ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ የውስጥ ምንጮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥቆማ ሰጥተዋል።
ለ104.4 መቐለ FM አዲስ አስተባባሪ እንደተመደበ ለማውቅ ችለናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
ፎቶ፦ ማኅበራዊ ሚዲያ
@tikvahethiopia በትግራይ መቐለ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መመለስን ተከትሎ ነዋሪዎችን አነጋግረናል። ነዋሪዎቹ " ጭልምልም ብሎብን ነበር። አሁን ከወዳጅ ዘመዶቻችን ጋር ስለተገናኘን ደስ ብሎናል " ብለዋል። " አሁን በከተማዋ የተሻለ መረጋጋት አለ ፤ አልፎ አልፎ ከሩቅ የተኩስ ድምጽ ይሰማል ተኩሱ የትግራይ ሰላም ኃይሎች ከበረሃ ወደ ከተማ ሲገቡ ስለሚተኩሱ ነው " ሲሉ ገልጸዋል። ትናንት…

19 hours ago
#astu
በትግራይ ክልል ከሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ወደ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተመደባቸሁ ተማሪዎች፣ ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ጥሪ እስኪደረግላችሁ ባላችሁበት በትዕግስት እንድትጠብቁ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አሳስቧል።

20 hours ago
“ በእንግሊዝ የገጠመንን ሽንፈት መርሳት አንችልም ” ስላቨን ቢሊች
“ ነገ ምላሽ እጠብቃለሁ "
የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ስላቨን ቢሊች በእንግሊዝ የደረሰባቸውን ሽንፈት " ሊረሳ የማይችል " ሲሉ ገልፀውታል።
ሽንፈቱ “ ሊጠፋ አይችልም በታሪክ የገጠመን አስከፊው ሽንፈት ነው ” ያሉት አሰልጣኙ “ ለዘለዓለም አብሮን ይኖራል " ብለዋል።
" ተጨዋቾቹ ማስታወስ እንዳለባቸው ነግሬያቸዋለሁ ነገሮች ቀላል እንደሆነ ሲያስቡ ትዝ ይላቸዋል "ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።
አክለውም “ ነገ በስፔን ጨዋታ ከተጫዋቾቹ ምላሽ እጠብቃለሁ " ሲሉ ተደምጠዋል።

21 hours ago
የቀድሞው " የማቲዎስ ወንዱ ካንሰር ሶሳይቲ " የአሁኑ " የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን " መስራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንዱ በቀለ ስርዓተ ቀብር ዛሬ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም በቦሌ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ተፈጽሟል።
በ1996 ዓ/ም ህፃን ልጃቸውን በደም ካንሰር የተነጠቁት አቶ ወንዱ "ብዙ ማቲዎሶችን ማዳን እንችላለን" በሚል ለ22 ዓመት አገልግሎት የሰጠውን የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዳሽንን መስርተው ለበርካቶች ወገኖቻቸው ደርሰዋል።
አቶ ወንዱ፣ ለአንድ አመት ከ10 ወር ከካንሰር ህመም ጋር ታግለው ህክምና ሲከታተሉ ቢቆዩም፣ መስከረም 24 ቀን 2019 ዓ/ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ኢትዮጵያን አልፎ ለአፍሪካ እና ዓለም ሀገራት መድረስ የሚችል ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ችግር ለመፍታት ያለመ "ጤናማ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል" የተሰኘ ፕሮጀክት ቀርጸው በመስራት ላይ ነበሩ። ይህንኑ ፕሮጀክት ከግብ ለማድረስ ፋውንዴሽኑ ጥሪ አቅርቧል።
አቶ ወንዱ በቀለ የ3 ልጆች አባት ነበሩ።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia "ታሞ ሕክምና ሲከታተል ነበር። ባልጠበቅነው ሁኔታ በድንገት ነው ያረፈው" - የሟች ቤተሰብ ልጃቸው ህፃን ማቲዎስን የካንሰር በሽታ ሲነጥቃቸው በልጃቸው ስም የህክምና ተቋም ያቋቋሙት "የማቲዎስ ወንዱ ፋውንዴሽን" መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ወንዱ በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ፋውንዴሽኑና ቤተሰባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። አንድ ቤተሰባቸው በሰጡን ገለጻ፣ አቶ ወንዱ በቀለ ሕይወታቸው…

22 hours ago
ሊዮኔል ሜሲ ምን ተደረገለት ?
አርጀንቲናውያን የብሔራዊ ቡድኑን ታሪካዊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በነገው ዕለት በይፋ ይሰናበታሉ።
አሁን ላይ ደጋፊዎች በአርጀንቲና ለሊዮኔል ሜሲ ምስጋና የሚያቀርብ መልዕክት አስቀምጠዋል።
ደጋፊዎቹ በሊዮኔል ሜሲ ትውልድ መንደር ሮዛሪዮ ጎዳና ላይ ሰላሳ ሜትር የሚለካ ማልያ አስቀምጠው ታይቷል።
በማልያው ላይ " GRACIAS 10 " ( እናመሰግናለን ) የሚል ፅሁፍ አስፍረዋል።

23 hours ago
የሊቨርፑል እና ሲቲን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?
የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ከሊቨርፑል ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።
አንፊልድ ስታዲየም ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ የማንችስተር ከተማ ተወላጁ ክሪስ ካቫናህ በመሐል ዳኝነት እንዲመሩ ተመርጠዋል።
ጨዋታውን በቫር ዳኝነት ፖል ሆዋርድ እንደሚመሩት ተገልጿል።
ጨዋታው እሁድ ምሽት 12:30 ሲል የሚጀምር ይሆናል።
ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?

#constitution
" በቀጣይ ጊዜያት በሀገራዊ ምክክር ምክረ ሃሳቦች መሰረት የህገመንግስት ማሻሻያ ይደረጋል " ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia " መረር ያለ እርምጃ እንወስዳለን " ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሙስናን ፣ ሌብነትን ፣ የዘመድ አሰራርን እንዲሁም ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግስታቸው መረር ያለ እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቀዋል። በሌላ በኩል ከበጀት ጋር በተያያዘ " ጠንካራ ቁጥጥር እና ክትትል የሚደረግበት የበጀት አካሄድን እንከተላለን " ሲሉም አሳውቀዋል። https://www.youtube.com/li...

" መረር ያለ እርምጃ እንወስዳለን "
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሙስናን ፣ ሌብነትን ፣ የዘመድ አሰራርን እንዲሁም ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግስታቸው መረር ያለ እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቀዋል።
በሌላ በኩል ከበጀት ጋር በተያያዘ " ጠንካራ ቁጥጥር እና ክትትል የሚደረግበት የበጀት አካሄድን እንከተላለን " ሲሉም አሳውቀዋል።
https://www.youtube.com/li...
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia 🕊 በኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታን የበለጠ ለማጽናት መንግስታቸው " የውይይት እና የይቅርታ መንገድ " እንደሚከተል ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሰሙት ንግግር " በጫካ ያላችሁ ወገኖች ወደ ሰላማዊ መንገድ ኑ ፤ ያኮረፋችሁ ወገኖችም የይቅርታ መንፈስን ተላብሳችሁ በሀገር ግንባታ ተሳተፉ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በሌላ በኩል፤ በሀገሪቱ የተጠናከረ የጸጥታ እና የደህንነት ዝግጅትና…

🕊
በኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታን የበለጠ ለማጽናት መንግስታቸው " የውይይት እና የይቅርታ መንገድ " እንደሚከተል ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሰሙት ንግግር " በጫካ ያላችሁ ወገኖች ወደ ሰላማዊ መንገድ ኑ ፤ ያኮረፋችሁ ወገኖችም የይቅርታ መንፈስን ተላብሳችሁ በሀገር ግንባታ ተሳተፉ " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በሌላ በኩል፤ በሀገሪቱ የተጠናከረ የጸጥታ እና የደህንነት ዝግጅትና ክትትል እንዲሁም ስምሪት እንደሚኖር አሳውቀዋል።
https://www.youtube.com/li...
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia " ... በቀጠናው ጉዳይ ላይ የምትወስን መሆኗን በሰዎች ችሮታ ሳይሆን በጉልበቷ ታረጋግጣለች ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ያላትን ሚና ማንም በሚሰጣት ችሮታ ሳይሆን በገዛ አቅሟና ጉልበቷ እንደምታረጋግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " ኢትዮጵያ በቀጠናው አንከር (መሰረት) ሀገር ብቻ ሳትሆን፣ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ…

24 hours ago
" ... በቀጠናው ጉዳይ ላይ የምትወስን መሆኗን በሰዎች ችሮታ ሳይሆን በጉልበቷ ታረጋግጣለች ! " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ያላትን ሚና ማንም በሚሰጣት ችሮታ ሳይሆን በገዛ አቅሟና ጉልበቷ እንደምታረጋግጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ " ኢትዮጵያ በቀጠናው አንከር (መሰረት) ሀገር ብቻ ሳትሆን፣ በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ሁነኛና ወሳኝ ተዋናይ መሆኗን በተግባር የምታሳይበት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች " ብለዋል።
" ኢትዮጵያ በቀጠናችን አንከር ሀገር መሆኗ ብቻ ሳይሆን በቀጠናው ጉዳይ ላይ የምትወስን መሆኗን በሰዎች ችሮታ ሳይሆን በጉልበቷ ታረጋግጣለች ኢትዮጵያ ፎክረው እንደሚገዙ ሳይሆን ተጋድለው ነፃነታቸውን እንደሚያስከብሩ ድንቅዬ ጀግኖች ሀገር ዳግም ፍላጎቶቿን በራሷ መንገድ ታረጋግጣለች " ሲሉ አስገንዝበዋል።
ሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎች፣ ዘመቻዎችና ጫናዎች ቢደቀኑባትም ሉዓላዊነቷንና ክብሯን አስጠብቃ መቀጠሏን ጠቁመዋል።
" በግንባርም ፣ በሚዲያም ፣ በሰይፍም ፣ በሰልፍም ፣ በውሸትም ፣ በሐሜትም ፣ በተንኮልም፣ በሸረባም ባገኙት የትግል ሜዳ ሁሉ ከጉዟችን ሊያደናቅፉን መከራቸውን አዩ፤ ኢትዮጵያን ግን አልቻሏትም፤ አይችሏትም " ሲሉም ተደምጠዋል።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ውድቀቷ ሲናፈቅ ጠንክራ የመውጣት፣ መበተኗ ሲጠበቅ ተሰብስባ የመቆም ትንግርታዊ ማንነት እንዳላት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሉዓላዊ ፍላጎቶቿን፣ የቀጠናዊ ትስስርና የልማት ውጥኖቿን በራሷ መንገድና ብርታት ማሳካት እንደምትችል አረጋግጠዋል።
በተጨማሪ የኢትዮጵያ ዘላቂ ህልውናና ጥንካሬ የሚረጋገጠው በየዘመኑ የሚገጥማትን " የማስቀጠል ፈተና " በማሸነፍ፣ የውስጥ አንድነትን በማጠናከር እና ዘላቂ አዲስ ሥልጣኔን በጋራ ጥረት በመገንባት ብቻ መሆኑን ለምክር ቤቱ አባላትና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
ሙሉ ንግግር ፦ https://www.youtube.com/li...
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia " ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር (የባህር በር) እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሾሙት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል። በዚህም ንግግራቸው በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የባህር በር ጉዳይ ነው። " ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው…

“ አላማችን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ነው ” አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር
የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ቡድን በቀጣይ የ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድሩን ያደርጋል።
በሩዋንዳ የሚካሄደውን ውድድር በተመለከተ የቡድኑ አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ቃላቸውን ሰጥተዋል።
“ አላማችን ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ እና ለዋናው ብሔራዊ ቡድን ግብአት የሚሆኑ ልጆችን ማብቃት ነው። ” ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል።
አክለውም “ ያላቸውን አቅም አውጥተው የሚጫወቱ ልጆችን ትመለከታላችሁ “ ሲሉ ገልጸዋል።
“ ይህ ቡድን በተገቢው እድሜ ላይ የሚገኝ ነው ” ያሉት አሰልጣኙ “ አቅም እና ልዩ ብቃት ያላቸውን ልጆች በቡድኔ ውስጥ ተመልክቻለሁ ” ብለዋል።
“ ከጨዋታ አስቀድሞ በሩዋንዳ በሚኖረን የአምስት የልምምድ ቀናት ጠንካራ ዝግጅታችንን እንቀጥላለን ” ቤንጃሚን ዚመር
ኢትዮጵያ በውድድሩ ከዩጋንዳ እና ቡሩንዲ ጋር ተደልድላለች።
ውድድሩ ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም በሩዋንዳ ኪጋሊ ይካሄዳል።
በውድድሩ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ለ 2027 አፍሪካ ዋንጫ ያልፋሉ።

1 day ago
" ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር (የባህር በር) እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን " - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሾሙት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል።
በዚህም ንግግራቸው በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የባህር በር ጉዳይ ነው።
" ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው ወዳጆቻችን ናቸው " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) " ከሁሉም ጎረቤቶች ጋር በሰላም ፣ በጋራ ጥቅምና በትብብር የመስራት መርሃችንን እንገፋበታለን " ብለዋል።
" ነገር ግን የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልምና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላው ያነሱት የመከላከያን ጉዳይ ነው።
" የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ የዓለምና የአካባቢያችን ወቅታዊ ሁኔታ ብሎም የወደፊቱን የዓለም አካሄድ ያገናዘበ የመከላከያ ኃይል እንዲኖረን እንሰራለን " ብለዋል።
" በቀጣናችን የአየር የበላይነት ለመፍጠር የሚያስችል አቅም ኢትዮጵያ ትገነባለች። የሚኖረን መከላከያ ዘመናዊ ፣ ፈጣሪ፣ ሁሌም ዝግጁ ብቁና ንቁ በየአውዶቹ የመሰማራት አቅምና ቁመና ያለው ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ችግሮች ሳይፈጠሩ በፊት አስቀድሞ ማወቅና መግታት ከመጡም መከላከል ከባሰም እንደ አባቶቹ እንደልማዱ ማሸነፍ የሚችል ኃይል ሆኖ ይገነባል " ሲሉ ተናግረዋል።
ሙሉ ንግግር ፦ https://www.youtube.com/li...
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #pm
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል። ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን ለተጨማሪ 5 ዓመት ለመምራት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል። መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
ኢትዮጵያን ለቀጣይ አምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሾሙት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል።
በዚህም ንግግራቸው በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል። ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ የባህር በር ጉዳይ ነው።
" ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው ወዳጆቻችን ናቸው " ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) " ከሁሉም ጎረቤቶች ጋር በሰላም ፣ በጋራ ጥቅምና በትብብር የመስራት መርሃችንን እንገፋበታለን " ብለዋል።
" ነገር ግን የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን አይችልምና በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ተግተን እንሰራለን " ሲሉ ተናግረዋል።
ሌላው ያነሱት የመከላከያን ጉዳይ ነው።
" የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ የዓለምና የአካባቢያችን ወቅታዊ ሁኔታ ብሎም የወደፊቱን የዓለም አካሄድ ያገናዘበ የመከላከያ ኃይል እንዲኖረን እንሰራለን " ብለዋል።
" በቀጣናችን የአየር የበላይነት ለመፍጠር የሚያስችል አቅም ኢትዮጵያ ትገነባለች። የሚኖረን መከላከያ ዘመናዊ ፣ ፈጣሪ፣ ሁሌም ዝግጁ ብቁና ንቁ በየአውዶቹ የመሰማራት አቅምና ቁመና ያለው ይሆናል " ሲሉ ገልጸዋል።
" ችግሮች ሳይፈጠሩ በፊት አስቀድሞ ማወቅና መግታት ከመጡም መከላከል ከባሰም እንደ አባቶቹ እንደልማዱ ማሸነፍ የሚችል ኃይል ሆኖ ይገነባል " ሲሉ ተናግረዋል።
ሙሉ ንግግር ፦ https://www.youtube.com/li...
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #pm
1 day ago
የቼልሲ እና ቶተንሀም ታሪካዊ ተጨዋቾች ጨዋታ ያደርጋሉ !
የሁለቱ የለንደን ክለቦች ቼልሲ እና ቶተንሀም ታሪካዊ ተጨዋች የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።
የወዳጅነት ጨዋታው የቼልሲ ፋውንዴሽን ለሚያደርገው የበጎ አድራጎት ስራ ገንዘብ ለመሰብሰብ እንደሚረዳ ተዘግቧል።
የቀድሞ ታሪካዊ የቼልሲ ተከላካይ ጆን ቴሪ በጨዋታው እንደሚሳተፍ ያሳወቀ የመጀመሪያ የቀድሞ ተጨዋች ሆኗል።
የወዳጅነት ጨዋታው መጋቢት 18/2019 ዓ.ም ይካሄዳል።
@tikvahethsport kidusyoftahe
የሁለቱ የለንደን ክለቦች ቼልሲ እና ቶተንሀም ታሪካዊ ተጨዋች የወዳጅነት ጨዋታ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።
የወዳጅነት ጨዋታው የቼልሲ ፋውንዴሽን ለሚያደርገው የበጎ አድራጎት ስራ ገንዘብ ለመሰብሰብ እንደሚረዳ ተዘግቧል።
የቀድሞ ታሪካዊ የቼልሲ ተከላካይ ጆን ቴሪ በጨዋታው እንደሚሳተፍ ያሳወቀ የመጀመሪያ የቀድሞ ተጨዋች ሆኗል።
የወዳጅነት ጨዋታው መጋቢት 18/2019 ዓ.ም ይካሄዳል።
@tikvahethsport kidusyoftahe
1 day ago
“ እውነቱን ነው ከትልቋ አክስቴ ጋርም ተጣልቻለሁ “ ምባፔ
ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድ እና አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ባሎን ዶር እንዲያሸንፍ ዘመቻ ባለማድረጋቸው እንደተበሳጨ ሲነገር ነበር።
ምባፔ በበኩሉ መረጃውን ላሰራጨው ጋዜጠኛ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ምላሽ ሰጥቷል።
ምባፔ በምላሹም “ መረጃው ትክክለኛ ነው ከትልቋ አክስቴ ጋርም በዚሁ ጉዳይ ተጣልቻለሁ “ ብሏል።
ጋዜጠኛው ባሰራጨው መረጃ ምባፔ በደርቢው ጨዋታ ያደረገው ነገር በክለቡ ተበሳጭቶ ነው ብሎ ነበር።
@tikvahethsport kidusyoftahe
ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድ እና አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ባሎን ዶር እንዲያሸንፍ ዘመቻ ባለማድረጋቸው እንደተበሳጨ ሲነገር ነበር።
ምባፔ በበኩሉ መረጃውን ላሰራጨው ጋዜጠኛ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ምላሽ ሰጥቷል።
ምባፔ በምላሹም “ መረጃው ትክክለኛ ነው ከትልቋ አክስቴ ጋርም በዚሁ ጉዳይ ተጣልቻለሁ “ ብሏል።
ጋዜጠኛው ባሰራጨው መረጃ ምባፔ በደርቢው ጨዋታ ያደረገው ነገር በክለቡ ተበሳጭቶ ነው ብሎ ነበር።
@tikvahethsport kidusyoftahe
1 day ago
“ ሆን ብዬ ሜሲ እንዲያስቆጥር አልፈቅድም ”
የቤኒን ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ማርሴል ዳንጂኖ ሊዮኔል ሜሲ የመጨረሻ ግቡን እንዲያስቆጥር እንደማይለቅ ገልጿል።
“ እኔ ግብ ጠባቂ ነኝ ሥራዬ ደግሞ ሙከራዎችን ማስቆም ነው “ ሲል ግብ ጠባቂው ተናግሯል።
“ ባለቀ ሰዓት ፍፁም ቅጣት ምት ተሰጥቶ ሜሲ ቢመታ እንኳን ለመመለስ የቻልኩትን አደርጋለሁ “ ሲል ተደምጧል።
አክሎም " ይሄ እግርኳስ ነው የሜሲን ሽኝት ልናከብር ነው የተገኘውን ነገርግን ማንም ለሜሲ የጎል ስጦታ ስጡት አላለንም " ብሏል።
@tikvahethsport YisakAH

#pm
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል።
ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን ለተጨማሪ 5 ዓመት ለመምራት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልፅግና ፓርቲን በመወከል ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለ5 ዓመት ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ እጩ አድርገው አቅርበዋል። መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia

#kabridaharuniversity
በ2019 ዓ.ም ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የቅድመ-ምረቃ (ፍሬሽማን እና ሪሚዲያል) ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 02 እና 03/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጂስትራር ጽ/ቤት
በተገለጹት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ትምህርት ማስረጃዎችን መያዝ ይኖርባችኋል፡፡

#ethiopianpublicserviceuniversity
በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት እንዲከታተሉ የመንግሥት ሠራተኞች ዕጩ ተማሪዎችን መልምለው እንዲልኩ የመንግሥት ተቋማትን መስከረም 08/2019 ዓ.ም በጠየቀው መሰረት፣ ተቋማቱ አስፈላጊውን መረጃ ሞልተው ለዩኒቨርሲቲው መላካቸው ተገልጿል፡፡
በዚህም ማስረጃዎቹን በትምሀርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት የቅበላ መስፈርት መሰረት በማጣራት ለመግቢያ ፈተና የሚቀርቡ ዕጩዎችን ዩኒቨርሲቲው ለይቷል፡፡
የመግቢያ ፈተናው መስከረም 27/2019 ዓ.ም በጠዋት እና በከሰዓት ፈረቃ፣ አዲስ አበባ ሲኤምሲ መንገድ ጉርድ ሾላ አለፍ ብሎ በሚገኘው በዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ ይሰጣል ተብሏል፡፡
ለሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) የተመዘገቡ ዕጩዎችን በማጣራት በቅርብ ቀናት እንደሚገለፅ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
@tikvahuniversity Photo

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብልፅግና ፓርቲን በመወከል ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን ለ5 ዓመት ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ እጩ አድርገው አቅርበዋል።
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia
Comments