4 hours ago
የኢትዮጵያ አትሌቶች በሞስኮ የደመቀ ድል አስመዘገቡ
#ethiopia | በሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ በተካሄደው የ2026 የዝናሜንስኪ ሜሞሪያል የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ከፍተኛ የበላይነት በመቀዳጀት አራት የወርቅ፣ ሁለት የብር እና ሁለት የነሐስ በድምሩ ስምንት ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አበርክተዋል።
በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ፉክክር አትሌት ብርቄ ኃይሎም አንደኛ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ስታሸንፍ ሳሮን በርሔ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በተመሳሳይ በሴቶች የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ፈንታዬ ጫኔ፣ ቤተልሄም ኦላና እና ሰላማዊት ሻምበል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የሀገራቸውን የበላይነት አስመስክረዋል።
በወንዶች የ10 ሺህ ሜትር የመስመር ውድድር አትሌት እዮብ ስመኝ የሩሲያ አትሌቶችን አስከራሪ ፉክክር በመስበር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት መሆን የቻለ ሲሆን ሽመልስ ንጉሴ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ የወጣበት ነበር።
በወንዶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር ዲንቃ ፍቃዱ ቀዳሚ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ሲያጠልቅ ሂርኮ ኃይሉ ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል።
በተጨማሪም በሴቶች የ3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ብርቱካን ገዳሙ የብር ሜዳሊያ ያስገኘች ሲሆን በ800 ሜትር የሴቶች ማጣሪያ ሀብታም ገበየሁ ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን ፈጽማለች።
#ethiopianathletics #znamenskymemorial2026 #ethiopianpride #runningchampions #greenflood #moscow2026 #athletics #running #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments