1 month ago
የአዲስ አበባ ሯጮች በአፍሪካ እምብርት ላይ በሚካሄድ ማራቶን ላይ እንዲሳተፉ ግብዣ ቀረበ
#ethiopia | በኢትዮዽያ ሩጫ ከስፖርት በላይ ነው ፤ ሩጫ የሀገር ኩራት፣ የጋራ በዓል፣ የጤና ፣ የህብረተሰብ ትስስር እና የነፍስ ደስታ ነው።
በአፍሪካ ዕምብርቷ ኡጋንዳም ተመሳሳይነት ያለውን ስሜት ለመጋራት፣ ታላቁ ሩጫ በኢትዮዽያ ከተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን ጋር በመተባበር ለሩጫ ወዳጆች ጥሪን አቅርቧል።
ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የምስራቅ አፍሪካን ተራራማ መልክዓ ምድር ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን የሩጫ ውድድር ወደ ታላቅ በዓል የመቀየር ተመሳሳይ ባህል አላቸው። ከአዲስ አበባ ለሚሄዱ ሯጮች በካሴሴ የሚስተዋለው የባህል ድባብ፣ ሙዚቃ እና የህዝብ አቀባበል እንደ ቤት እንዲሰማ የሚያደርግ የቅርብነት ስሜት አለው።
በሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ፣ በእንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ እና ሌሎችም የሩጫ አፍቃሪያን፣ ያንኑ የሩጫ መንፈስ በመያዝ ከሀገር ውጪ በመጓዝ ውድድሩን እንዲቀላቀሉ እንጋብዛለን።
ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በኡጋንዳ፣ ካሴሴ ከተማ የሚካሄደው ተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን፣ ከአዲስ አበባ የባህር ዛፍ ጠረን ካለው ቀዝቃዛ አየር ወደ ሳቫናው ግርማ ሞገስ እና ወደ ሩዌንዞሪ ተራሮች ግርጌ የሚያደርጉት ልዩ የሩጫ ጉዞ ነው። በኢትዮጵያ የክረምቱ ዝናብና ቅዝቃዜ ሲጠነከር፣ በዩጋንዳ ካሴሴ ደግሞ ሞቅ ያለ ፀሐይና የኢኩዌተር መስመር ላይ የሚደረግ ውድድር ይጠብቅዎታል።
የተስከር ላይት ሩዌንዞሪ ማራቶን የዓለም አትሌቲክስ ሌብል (World Athletics Label Road Race) ደረጃ ያለዉ ዉድድር ነዉ። ይህም በአትሌቶች ጥራት እና በአደረጃጀት በዓለም ላይ ካሉ ምርጥ 200 ውድድሮች አንዱ ያደርገዋል። በውድድሩ ከማራቶን በተጨማሪ በ5 ኪ.ሜ.፣ 10 ኪ.ሜ.፣ እና 21 ኪ.ሜ . (ግማሽ ማራቶን) መሳተፍ ይችላሉ።
የሩጫው መስመር በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ በሆነው የንግስት ኤልሳቤጥ ብሔራዊ ፓርክ ይጀምራል። በከበሮና በሙዚቃ በምትደምቀው የካሴሴ ከተማ መንገዶች አድርጎ፣ በበረዶ በተሸፈኑት የሩዌንዞሪ ተራሮች ግርጌ በሚገኘው አስደናቂው የኪሌምቤ ሸለቆ ይዘልቃል። ማጠናቀቂያው ላይ ሲደርሱ፣ ከኋላዎ የተዘረጋው ግዙፍ የተራራ ሰንሰለት ለእርስዎ የሚሰጠው ስሜት ምን ያህል ድንቅ እንደሆነ በራስዎ ይመሰክራሉ።
እንዴት መመዝገብ ይቻላል?
ይህንን ታላቅ የሩጫ በዓል ለመቀላቀል እና በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ፣ አሁኑኑ ከዚህ በታች በተቀመጠው ድረ-ገጽ አማካኝነት በመግባት መመዝገብ ይችላሉ።
www.rwenzorimarathon.com/r...

2 months ago
19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት መሰለች ዓለማየሁ በበላይነት አጠናቀቀች
#ethiopia | በ19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር የሴቶች ምድብ የአዲስ አበባ ፖሊስ ክለብ ተወካይ የሆነችው አትሌት መሰለች ዓለማየሁ ቀዳሚ በመሆን አሸንፋለች።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የወከለችው አትሌት ዝማም ባራኪ ደግሞ ውድድሩን በሁለተኛነት በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ባለቤት መሆን ችላለች።
#ethiopia #athletics #marathon #halfmarathon #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

በ19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት መሰለች ዓለማየሁ አሽነፈች
******************
በ19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት መሰለች ዓለማየሁ ከአዲስ አበባ ፖሊስ አሽንፋለች።
አትሌት ዝማም ባራኪ ደግሞ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛ ሆና አጠናቅቃለች።
#ethiopia #ebc #athletics #marathon #halfmarathon

በ19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ጌታቸው ማስረሻ አሽነፈ
******************
በአዲስ አበባ በተካሄደው 19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ጌታቸው ማስረሻ ከሸገር ሲቲ አሸንፏል።
በውድድሩ አትሌት ባለይልኝ ተሻገር ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሁለተኛ፣ እንዲሁም አትሌት በላይ ጥላሁን ከአዲስ አበባ ፖሊስ 3ኛ በመውጣት አጠናቅቀዋል።
#ethiopia #ebc #athletics #marathon #halfmarathon
******************
በአዲስ አበባ በተካሄደው 19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ጌታቸው ማስረሻ ከሸገር ሲቲ አሸንፏል።
በውድድሩ አትሌት ባለይልኝ ተሻገር ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሁለተኛ፣ እንዲሁም አትሌት በላይ ጥላሁን ከአዲስ አበባ ፖሊስ 3ኛ በመውጣት አጠናቅቀዋል።
#ethiopia #ebc #athletics #marathon #halfmarathon
Sponsored by
Surafel
2 months ago
19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው
*************
638 አትሌቶች የተሳተፉበት 19ኛው የኢትዮጵያ ግማሽ ማራቶን ውድድር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
መነሻ እና መድረውሻን መስቀል አደባባይ ባደረገው ውድድሩ 455 ወንዶች እና 183 ሴቶች በድምሩ 638 ተሳትፈዋል።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድር ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ብስራት ለጥይበሉ የውድድሩ ዓላማ በዴንማርክ ኮፐንሀገን ለሚካሄደው የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ለመምረጥ እና ተተኪዎች ለማፍራት ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የፌዴሬሽኑ ውድድር እና ተሳትፎ ተወካይ ዳይሬክተር አቶ ጊዜ አድነው በበኩላቸው የውድድር ኮርስ ካርታ ላይ ያበራሩ ሲሆን ከ1-6 ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች የገንዘብ፣ ሜዳልያ እና የዋንጫ ሽልማት እንደሚበረከተላቸው በማንሣት ውድድሩ ከአምናው 434 አትሌቶች ቁጥር ጭማሬ ማሳየቱን መናገራቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ታዋቂዋ ማራቶን አትሌት ፋጡማ ሮባ እና ጋዜጠኛ ካሳሁን ፈይሳ ከዓመታት በኋላ በደስታ ተገናኙ
#ethiopia | የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ካስጠሩ ስመ ጥር የስፖርት ባልባለቶች መካከል አንዷ የሆነችው አትሌት ፋጡማ ሮባ እና ጋዜጠኛ ካሳሁን ፈይሳ ከረጅም ዓመታት በኋላ በድጋሚ ተገናኝተዋል።
አትሌት ፋጡማ ሮባ በታሪካዊው የአትላንታ ኦሎምፒክ በሴቶች ማራቶን ውድድር ለኢትዮጵያ ከአርባ ዓመታት በኋላ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘች ታላቅ ባለውለታ ናት።
በወቅቱ ይህንን ታላቅ ድል ተቀዳጅታ ወደ ሀገሯ ስትመለስ በነበረው ከፍተኛ የደስታ ድባብ ውስጥ ጋዜጠኛ ካሳሁን ፈይሳ ለኢትዮጵያ ሬድዮ ፕሮግራም የሚሆን አጭር ቃለ መጠይቅ አድርጎላት እንደነበር ይታወሳል።
ያኔ በወጣትነት ዘመናቸው በስራ አጋጣሚ ተገናኝተው የተነሱትን የማይረሳ ትዝታ የያዘ ፎቶግራፍ በማስታወስ፣ ከአያሌ ዓመታት በኋላ አሁን ላይ በድጋሚ በመገናኘታቸው ለተባረከው ዕድሜና ለአምላክ ምስጋና በማቅረብ ለታዋቂዋ አትሌት መልካም ጤንነትና ረጅም ዕድሜ ተመኝቷል።
ጋዜጠኛ ካሳሁን ፈይሳ በኦንታሪዮ፣ ቶሮንቶ ካናዳ 🇨🇦 ነዋሪ ነው።
#sport #marathon #atlanta1996 #olympics #athletics #history #legend #ethiopianathletes #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

አትሌት አበባ አረጋዊ በኦታዋ ማራቶን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ጻፈች
#ethiopia | በአንድ ወቅት በ1,500 ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ በነበራት ተደጋጋሚ ስኬት የርቀቱ ልዩ ባለሙያ በመባል የምትታወቀው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አበባ አረጋዊ የ2026 የኦታዋ ማራቶንን በሴቶች ዘርፍ በአንደኝነት አጠናቃለች።
በዚሁ ውድድር ላይ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ኩፍቱ ታሂር በ2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ33 ሰከንድ ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ ኬንያዊቷ ቤቲ ቺፕኮሪር ደግሞ በ2 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ከ51 ሰከንድ ሦስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
በውድድሩ ላይ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች መሰረት በለጠ 4ኛ፣ መስከረም አሰፋ 5ኛ፣ መሰረት ደከቦ 7ኛ እንዲሁም ታደለች በቀለ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን ፈጽመዋል።
በ2012 የለንደን ኦሎምፒክ የትውልድ ሀገሯን ኢትዮጵያን ወክላ በ1,500 ሜትር የብር ሜዳሊያ ያገኘችውና በ2013 የሞስኮ አለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ ያሸነፈችው አበባ አረጋዊ በ2014 የቤት ውስጥ አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ደግሞ ስዊድንን ወክላ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቷ ይታወሳል።
የሁለት ጊዜ የዳይመንድ ሊግ አሸናፊዋ አትሌት አበባ አረጋዊ ከዚህ የድል ጉዞዋ በኋላ በሰጠችው አስተያየት ለኦታዋ ማራቶን ከፍተኛ ዝግጅት ማድረጓንና በማሸነፏም ታላቅ ደስታ እንደተሰማት ገልጻለች።
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷና ስዊድናዊቷ አትሌት አበባ አረጋዊ የኦታዋ ማራቶንን ለማሸነፍ የፈጀባት ጊዜ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ባለቤቷ አትሌት የማነ ፀጋይም በ2014 እና በ2018 የካናዳን የቦታው ሪከርድ በመስበር ማሸነፉ ይታወሳል።
ይህ አጋጣሚ ባልና ሚስቱ የኦታዋ ማራቶንን በተለያዩ አመታት በማሸነፍ አዲስ ታሪክ በጋራ እንዲጽፉ አድርጓቸዋል።
✍️ በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል
#marathon #ottawamarathon #athletics #running #sportnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
)

3 months ago
አትሌት የብርጓል መለሰ በድንገተኛ አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
****************
ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድሮች ስታስጠራ የቆየችው አትሌት የብርጓል መለሰ በዛሬው ዕለት በደረሰባት ድንገተኛ አደጋ በ36 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
አትሌቷ ዛሬ ማለዳ በጃን ሜዳ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ልምምድ ላይ ሳለች በድንገት የመውደቅ አደጋ ደርሶባት ወደ ጤና ተቋም ብትወሰድም ሕይወቷን ማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል።
ሚያዝያ 1982 ዓ.ም የተወለደችው አትሌት የብርጓል መለሰ፤ ከ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አንስታ በበርካታ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ስኬታማ ውጤቶችን አስመዝግባለች።
በተለይም በሂዩስተን፣ በፕራግ እና በሻንጋይ ማራቶን በተለያዩ ዓመታት በቀዳሚነት ያጠናቀቀች ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2018 የሻንጋይ ማራቶንን ስታሸንፍም የስፍራውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር ነበር።
በፓሪስ ግማሽ ማራቶን ሁለት ጊዜ፣ በፖርቹጋል ግማሽ ማራቶን ደግሞ አንድ ጊዜ ባለድል ለመሆን የበቃችው የብርጓል፤ በ2015 ኮንጎ ብራዛቪል ላይ በተካሄደው ውድድር ኢትዮጵያን ወክላ የነሐስ ሜዳሊያ አስመዝግባለች።
በዚሁ ዓመት በቺካጎ ማራቶን ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በማግኘት በ"ማራቶን ሜጀርስ" ስሟን አስጠርታለች።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌቷ ሕልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጾ፤ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ፣ ለአድናቂዎቿ እንዲሁም ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መጽናናትን ተመኝቷል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #yebrgualmelese #ethiopianathletics #marathon

5 months ago
የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊዋ ናንሲ ጄላጋት ሜቶ በዶፒንግ ታገደች
#ethiopia | የቀድሞዋ የቫሌንሲያ ማራቶን አሸናፊ ኬንያዊቷ ናንሲ ጄላጋት ሜቶ፣ የተከለከለ አበረታች ንጥረ ነገር (Doping) ተጠቅማ በመገኘቷ የሁለት ዓመት የእገዳ ቅጣት ተጣለባት።
የቅጣቱ ዝርዝር ሁኔታ፦
* የተገኘው ንጥረ ነገር፦ ‘ፉሮሴማይድ’ (Furosemide) የተባለ የአቅም ማጎልበቻ።
* ምርመራው የተደረገበት ወቅት፦ ሰኔ 2016 ዓ.ም. በኬንያ በነበረ የልምምድ ወቅት።
* የእገዳው ጊዜ፦ ከጁላይ 11 ቀን 2024 ጀምሮ ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።
ከውጤቱ በስተጀርባ፦
አትሌቷ መጀመሪያ ላይ ጥፋተኛ አይደለሁም ብላ ብትከራከርም፣ የአትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (AIU) ባቀረበው ዝርዝር ማስረጃና የላቦራቶሪ ውጤት መሠረት፣ በመጨረሻም ማርች 13 ቀን 2026 ጥፋቷን አምና የቅጣት ቅጹን ፈርማለች።
የ40 ዓመቷ አትሌት ናንሲ ጄላጋት፣ በ2021 የቫሌንሲያ ማራቶንን በ2:19.31 በሆነ የግል ምርጥ ሰዓቷ አሸንፋ እንደነበር ይታወሳል። አትሌቷ ቅጣቷን ጨርሳ በመጪው ክረምት ወደ ውድድር እንደምትመለስ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #nancyjelagat #athleticsnews #dopingban #kenyaathletics #aiu #breakingnews #sportsupdate #marathon #valenciamarathon

6 months ago
🏃♂️ እንግሊዛውያን አንጋፋ አትሌቶች አዲስ አበባ ገቡ
#ethiopia | በ14ኛው የኢትዮ ቴሌኮም ሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን ላይ ለመሳተፍ የመጡት የእንግሊዝ አንጋፋ አትሌቶች (ከ55 ዓመት በላይ) ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የቡድኑ ኮከቦች:
ቤን ሬይኖልድስ: በ65 ዓመት እድሜ ክልል የማራቶን ሪከርድ ባለቤት (2:47 ሰዓት)።
ፈጣን የእንግሊዝ የ60 ዓመት በላይ ሯጮች።
ውድድሩ:
ቀን: የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም
ቦታ: ሀዋሳ
ተፎካካሪ:
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ያዘጋጀው የኢትዮጵያውያን አንጋፋ አትሌቶች ቡድን።
ይህ ውድድር በቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በኢትዮ ቴሌኮም እና በአጋሮች ትብብር የተዘጋጀ ነው።
#hawassa #marathon #veterans #greatrun #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago
በሳምንቱ መጨረሻ እንደተለመደው አትሌቶቻችን በተለያዩ ሀገራት በተለያየ ርቀት አሸንፈዋል።
2025 Incheon marathon, South Korea
Men's
1. Gerba Dibaba 2:06:52 🇪🇹
2. Gilbert Kibet 2:06:54 🇰🇪
3. Felix Kibitok 2:06:57 🇰🇪
4. Abdisa Tola 2:08:40 🇪🇹
5. Robert Ngeno 2:09:02 🇰🇪
2025 ETHIOPIAN GREAT RUN 10KM
Men's
1. Yismaw Dillu 28:25 🇪🇹
2. Eyob Simegn 28:28 🇪🇹
3. Dinkalem Ayele 28:29 🇪🇹
4. Beniyam Melak 28:30 🇪🇹
5. Jerata Lensa 28:31 🇪🇹
6. Negesa Dekeba 28:34 🇪🇹
7. Adisu Negash 28:39 🇪🇹
8. Chim'sa Debele 28:40 🇪🇹
9. Zenebe Ayele 28:47 🇪🇹
10. B. Gatahun 28:48 🇪🇹
WOMEN
1. Likina Amebaw 27:25 🇪🇹
2. Sheila Jebet 27:55 🇰🇪
3. V. Gemetto 28:11 🇮🇹
4. Idaira Suarez 28:19 🇪🇸
5. Noshim Kimuge 28:33 🇰🇪
Men
1. Mathew Kipsang 23:10 🇰🇪
2. Rodrigue Kwizera 23:11 🇧🇮
3. Mathew Kipkoech 23:13 🇰🇪
4.T. Ndikumwenayo 23:13 🇪🇸
5. Naibei Kiplimo 23:45 🇰🇪
NBF Fujairah 10km (Émirats arabes unis)
1. Abu Salim Mayanja UGA 28:28, 2. Dagne Demsie ETH 28h30,
3. Feyisa Tadese ETH 28:31,
6.7km Cross Cinque Mulini, Italy
Winner: Yenenesh Shimket 19:11 🇪🇹
Via: Toprun news
#athletics #running #5km #10km #15km #halfmarathon #worldathletics #followers #highlight #ethiorunners #ethiorunnersfan #ethiopianathletics #ethiopianathleticsfederation
✍️
Wondmagegn Getachew Yigezu

9 months ago
🇺🇸 ባንክ ኦፍ አሜሪካ ከታላቁ ሩጫ ጋር ስምምነት ፈፀመ
* የስፖርት ተደራሽነትን ለማስፋት ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት ለመስራት ተስማምተዋል።
* እ.አ.አ. በ2026 የሚጀምረው አጋርነት የስኬታማውን ውድድር ዓለም አቀፋዊ ስም የበለጠ ከፍ ያደርጋል
እንዲሁም ለልጆች የሩጫ እድሎችን በእጅጉ ያሰፋል፡፡
አዲስ አበባ እና ሻርለት - ኖርዝ ካሮላይና - 12 ህዳር 2018 ዓ.ም.
#ethiopia | ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እ.አ.አ. ከ2026 ጀምሮ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር አብረው ለመስራት የበርካታ ዓመታት የአጋርነት ስምምነት ማድጋቸውን ዛሬ አሳውቋል፡፡ አጋርነቱ ባንኩ በረዥም ርቀት ሩጫ ላይ የነበረውን ግዙፍ እንቅስቃሴ ከአፍሪካ እጅግ ተለዋዋጭ እና በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ የሩጫ ማህበረሰቦች ወደ አንዱ እንዲያሰፋ ያግዘዋል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሶስት ትልልቅ የሩጫ ሁነቶች (events) ላይ በጋራ ይሰራሉ - የ2019 ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ፣ የልጆች ሩጫዎች እና ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.። ባንክ ኦፍ አሜሪካ እነዚህን ውድድሮች ተጠቅሞ የኢትዮጵያን ደማቅ የሩጫ ባህል እይታ ለማሳደግ እና በስፖርት፣ ቱሪዝም እና ንግድ አማካይነት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ ለማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አጋር የመሆኑ ምክንያት ተቋሙ ቀጣዩን ትውልድ ለማነሳሳት እና በኢትዮጵያ እና በመላው ዓለም የፅናት ስፖርቶችን ለማስፋፋት ካለው ማህበረሰብ-ተኮር መርሆ የተነሳ ነው፡፡ ይህ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በስፖርት አማካይነት እድገትን የማነሳሳት እና ማህበረሰቦችን የማገዝ የረዥም ጊዜ ቁርጠኝነቱን ሲያጠናክር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫን የሁሉም የህይወት ዘይቤ የማድረግ ዋነኛ ራዕይ ጋርም የተስማማ ሆኗል።
‹‹ባንክ ኦፍ አሜሪካ በስራዎቻችን ሁሉ አጋር ሆኖን ወደምንንቀሳቀስበት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጉዞ ቀጣዩ ደረጃ ልንገባ በመሆናችን እጅግ ደስተኞች ነኝ›› የሚሉት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ ‹‹ለማህበረሰባችን እና ለልጆቻችን ባለን ጠንካራ መሰጠት፣ ትልቁ ውድድራችንን ተጠቅመን መዳረሻችንን ለማስፋት እና ለልጆች እና ወጣቶች የሩጫ እድሎችን ለመጨመር በጋራ እንሰራለን›› ሲሉ ያክላሉ፡፡
በጋራ የመስራቱ ዋነኛ ዓላማ በየዓመቱ 50.000 ገደማ ተሳታፊዎችን የሚቀበለውን የዝነኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ 10ኪ.ሜ ተሳትፎ ይበልጥ ማሳደግ እንዲሁም በታዳጊዎች እና ሴቶች ሁነቶች ላይ ተሳትፎን ማስፋት ነው፡፡ እነዚህ እንቅስቃሴዎች በየአካባቢው ያለ ተሰጥኦን የማሳደግ፣ ጤነኛ የህይወት ዘይቤን የማስተዋወቅ እና የኢትዮጵያን የተለየ የሩጫ ባህል እና የመሰባሰብ መንፈስ የሚያከብሩ መድረኮችን የመፍጠር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን የሚያጎሉ ናቸው፡፡
‹‹ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የስፖርቶችን አዎንታዊ ተፅዕኖ በኢትዮጵያ፣ አፍሪካ እና በዓለም ዙሪያ እያሳደገ የሚገኝ እጅግ የላቀ ድርጅት ነው፡፡ እኛም በዓለም ዙሪያ ማህበረሰቦች እንዲያድጉ ለመርዳት፣ ተፅዕኗቸው የገዘፈ እድሎችን ለመፍጠር እና አትሌቶችን ለማገዝ ካለን ህልም መነሻ፣ የልጆች እና ሴቶች ውድድሮች ተሳትፎ እንዲያድግ ብሎም በስፖርት አማካይነት ቀጣዩን ትውልድ ለማብቃት ከታላቁ ሩጫ ጋር በመተባበሩ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ኩራት ይሰማዋል›› የሚሉት የባንክ ኦፍ አሜሪካ የዓለም አቀፍ ማርኬቲንግ ትብብሮች ኃላፊው ብራድ ሮስ ናቸው፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሺዎች የሚቆጠሩ የዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን በመሳብ ለአዲስ አበባ ቱሪዝም እና መሰረተ ልማት ግዙፍ አስተዋፅኦ ያበረክታል፤ በከተማዋ ያሉ የንግድ እንቅስቃሴዎችንም ያነቃቃል። ይህ አጋርነትም እነዚህን ጥቅሞች - ስራዎችን መፍጠር፣ የከተማዋ ንግዶችን ማነቃቃት እና በአዲስ አበባ ውስጥ እና ዙሪያ ለሚኖሩ ማህበረሰቦች የተለዩ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ማቅረብ - የበለጠ ያጎላሉ።
ባንክ ኦፍ አሜሪካ ሁነቶቹ በጋራ የ1.1 ቢሊየን ዶላር የኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ እና ለበጎ አድራጎት ስራዎች ከ90ሚሊየን ዶላር የበለጠ የሚያሰባስቡ ሁለት የአቦት ወርልድ ማራቶን ሜጀሮች (Abbott World Marathon Majors) - ቦስተን እና ሺካጎ ማራቶኖች - ስፖንሰር መሆኑ ሲታወስ፣ ይህ አጋርነት ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ ሀብቶችን እና አሰራሮችን ወደ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እና ወደሚያዘጋጃቸው ሁነቶች እንደሚያመጣ መጠበቅ ይቻላል።
ባንክ ኦፍ አሜሪካ ዓለም አቀፋዊውን የሩጫ መድረኩን ከአፍሪካ ቀጣይ የሯጮች ትውልድ ጋር በማስተሳሰር ስፖርት እንዴት እድሎችን ሊፈጥር እንደሚችል ማሳየቱን ቀጥሎበታል፡፡ ይህም ሰዎችን፣ ገበያዎችን እና ማህበረሰቦችን በማሰባሰብ እና በአውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍሪካ ዙሪያ ካለው ሰፊ የንግድ ስትራቴጂ ጋር በሚስማማ መልኩ በቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ እድገት ላይ እንደአጋር የራሱን ሚና በማጠናከር ነው፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋነኛ ራዕዩ የሆነው ‹‹ሩጫን የሁሉም የህይወት ዘይቤ ማድረግ››ን ይዞ ሲጓዝ፣ በላቀ ቴክኖሎጂ የውድድር ዝግጅቱን ይበልጥ የዘ'መነ እንዲያደርግ ለማገዝ፣ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ሀብቶችን እና የሩጫ እውቀትን ያቀርባል፡፡
ይህ ስትራቴጂያዊ ትኩረት የሯጮችን ተሞክሮ ማሻሻልን፣ የሁነት ዝግጅትን ይበልጥ ማዘ'መንን እና የሁነቱን እየሰፋ የሚገኝ ዱካ በብቃት ማስተዳደርን ያለመ ነው፡፡ ይህ አጋርነት የበለጡ ተሳታፊዎችን ይስባል፤ የመሪ ዓለም አቀፍ የሩጫ ሁነት ደረጃውን ያጠናክራል፤ የሁነቱን የረዥም-ጊዜ ዘላቂነት ያረጋግጣል፤ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ደማቅ የባህል ክብረ-በዓል ሆኖ እንዲቀጥል ያደርጋል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ አዲስ እና ጠለቅ ያለ የደንበኛ ግንኙነትን የመፍጠር፣ የቡድን አጋሮችን የማሳተፍ እና በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ የኢኮኖሚ ተፅዕኖን የማገዝ እንቅስቃሴው አካል አድርጎ በስፖርት ውስጥ ካሉ እጅግ ታዋቂ ብራንዶች ጋር በአጋርነት ይሰራል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ካለው አጋርነት ባሻገር በሩጫ፣ እግር ኳስ እና ጎልፍ ከዓለም አቀፍ ብራንዶች እና ሁነቶች ጋር በአጋርነት ይሰራል፡፡ እነዚህም Boston Marathon presented by Bank of America፣ Bank of America Chicago Marathon እና Chicago Distance Series፣ የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ፣ የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ሁሉም 27 የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድኖች እንዲሁም በጎልፍ የማስተርስ ውድድር እና Augusta National Women’s Amateur ናቸው፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ የስራ እንቅስቃሴውን ለማሳደግ፣ ብራንዱን ለማጎልበት እና በሚንቀሳቀስባቸው 35 ሀገራት እና 100 የሚጠጉ የአሜሪካ ገበያዎች በጎ ተፅዕኖ ለማሳደር በእነዚህ አጋርነቶች ዙሪያ በትኩረት ይሰራል፡፡

ኢሊዩድ ኪፕቾጌ፦
"አንታርቲካ ላይ መሮጥ እፈልጋለሁ"
(ምስጋናው ታደሰ)
#ethiopia | አንጋፋው አትሌት ኢሊዩድ ኪፕቾጌ ከታላላቅ የማራቶን ውድድሮች ራሱን ማግለሉን አስታወቀ። በ40 ዓመቱ ትናንት በተካሄደው የኒውዮርክ ማራቶን ተሳትፎ 17ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኬንያዊው ፊቱን ከትራክ ወደ ማራቶን ካዞረ በኋላ የቀረው ብቸኛ ውድድር የኒውዮርክ ማራቶን እንደነበርና እሱን በማሳካቱም ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።
"ማራቶንን የማቆመው አርጅቼ አይደለም" ያለው አንጋፋው አትሌት "ሁልጊዜም ወደ ውድድር የምገባው ለመሳተፍ ሳይሆን ለማሸነፍ ነው። የሽልማት መድረኩ ላይ መቆም እፈልጋለሁ። አሁን ባለው ተጨባጭ ዕውነታ ደግሞ ውድድሮችን ጀምሮ ለመጨረስ የሚያስችል እንጂ የሽልማት መድረኩ ላይ ለመቆም የሚያስችል ጉልበት አለኝ ወይ? አይመስለኝም። ስለዚህ በክብር ማቆሙ ይሻላል። ጥንካሬዬ ግን አሁንም አብሮኝ እንዳለ ነው። ሌላው ቀርቶ በሳውዲ አረቢያ ሙቀት ውስጥ እንኳን 50 ኪሎሜትር ሮጦ ለመጨረስ የሚያስችል አቅም አለኝ" ብሏል።
ኪፕቾጌ "World Marathon Majors" ተብለው ከሚጠሩት መድረኮች ራሱን ቢያገልም በተለያዩ ቀለል ያሉ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ በወጣቶች ዘንድ መነቃቃትን እንደሚፈጥርም ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ቀጣይ ህልሙን አስመልክቶ ሲጠየቅም "ያልተሞከሩ ነገሮችን በመሞከር ለአዲሱ ትውልድ ጥሩ ምሳሌ ለመሆን እፈልጋለሁ። ስለዚህ ከተሳካልኝ አንታርቲካ ላይ መሮጥ እፈልጋለሁ" ሲል በሳቅ ታጅቦ መልሷል።
ኢሊዩድ ኪፕቾጌ በዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ ደረጃ በተሰጣቸው ሰባቱ ዋና ዋና ታላላቅ የማራቶን ውድድሮች (በርሊን፣ ለንደን፣ ቦስተን፣ ቶኪዮ፣ ሲድኒ፣ ቺካጎ እና ኒውዮርክ) ላይ በሙሉ በመሳተፍና በማሸነፍ ብቸኛው አትሌት ሆኗል። ለዚህ ክብሩም ከትናንቱ የኒውዮርክ ማራቶን በኋላ ባለ ሰባት ኮከብ አትሌትነቱን የሚያረጋግጥ የክብር ሜዳልያ ተሸልሟል። እሱም በእንባ ታጅቦ ስንብቱን ይፋ አድርጓል።

♦️ኬንያዊያን በኒውዮርክ ማራቶን ነግሠው ዋሉ
♦️በወንዶች ማራቶን ከ1-3 በመግባት ታሪክ ሠሩ
♦️ሶስቱ ኬንያዊያን ከ29.6 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ካዝናቸው ከተዋል
♦️የማራቶን ንጉሱ ኬንያዊው ኤልዩድ ኪፕቾጌ አዲስ ታሪክ በማፃፍ ከውድድር ተሠናብቷል
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)
#ethiopia | ኬንያዊው ኤልዩድ ኪፕቾጌ?ወይስ ኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለ ማን ያሸንፍ ይሆን?በሚል በአትሌቲክስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኒውዮርክ ማራቶን በኤሊት ወንዶች ሶስቱም ኬንያዊያን ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል
የNew York City Marathon በወንዶች አሸናፊዎች
1. 🇰🇪 ቤንሰን ኪፕሩቶ 2:08:09
2. 🇰🇪 አሌግዛንደር ሙቲሶ 2:08:09
3. 🇰🇪 አልበርት ኮሪር 2:08:57 በመግባት የኒውዮርክ ማራቶንን ሲፈሱበት የዋሉ ሲሆን ሶስቱም በጋራ የ200ሺ ዶላር ወይም ከ29.6 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ካዝናቸው ከተዋል።
ከዚሁ ከኒውዮርክ ማራቶን ሳንወጣ ለአሸናፊነት ከፍተኛ ግምት የተሠጠው ኬንያዊው ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ውድድሩን በ17ኛነት ያጠናቀቀ ሲሆን በሜጀር ማራቶን ባለ ስድስት ኮከብ ሜዳልያ ተሸላሚ በመሆን ሌላ አዲስ ታሪክ አፅፏል።
የ40 ዓመቱ የማራቶን ንጉስ በሰባት ሜጀር ማራቶን በመሮጥ ታሪክ የሠራ የመጀመሪያው አትሌት ሆኗል፤ኪፕቾጌ:-
✅ የሎንደን ማራቶን
✅ የበርሊን ማራቶን
✅ የቺካጎ ማራቶን
✅ የቦስተን ማራቶን
✅የቶኪዮ ማራቶን
✅ዛሬ የኒውዮርክ ማራቶንና
✅ የሲድኒ ማራቶን በመሮጥና በማሸነፍ ባለታሪክ ሆኗል።

ወደ እንግሊዝ ሳይጓዙ እዚሁ አዲስ አበባ ላይ በአንድ መድረክ የሁለት ሀገራት የሙዚቃ ባህል ተደግሷል!
ዩኬ ኢትዮ ሚዮዚክ ኮንሰርት
ለማይረሳው ውብ ምሽት ይዘጋጁ!
ከእንግሊዝ የተውጣጡ The sassenachs Ceilidh Band
ከኢትዮጵያ ድምፃዊት ጠረፍ ካሳሁን ከኪዩ ጃምስ ባንድ ጋር በተወዳጅ ዲጄዎች ዘና እያሉ ውብ ቅዳሜ አመሻሽን ከኛ ጋር ያሳልፉ
ይህ ውብ የሙዚቃ ባህል እና የሁለቱን ሀገራት የሙዚቃ ምሽት ባለን ጥቂት ቦታ በነፃ ተመዝግበው ብቻ ይሳተፋ!
👉https://nz-events.vercel.a...
ቅዳሜ ጥቅምት 29 ጃክሮስ በሚገኘው በቬኑ ዌር ሀውስ በሮች ከ9:00 ጀምሮ ይከፈታሉ።
ብሪቲሽ ካውንስል ከብሪቲሽ ኢንባሲ እና ከ ኤን ዜድ ኮሚዮኒኬሽን ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል
አሁን ከታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም ይመዝገቡ!
👉https://nz-events.vercel.a...
nzcommunications britishcouncilet ukandethiopia abbay.tv marathon_spirits thesassenachs kiya.kassahun milupresents youbel.music blackstarboy01 venuewh natnaelzer

10 months ago
የልጅ እናት
የግማሽ ማራቶን አሸነፈች
#ethiopia | በአስደናቂ ሁኔታ የተመለሰችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሀብታምነሽ ተስፋይ በ2025 የትሬንቶ ግማሽ ማራቶን The TRENTO HALF MARATHON በማሸነፍ አስደናቂ ብቃት አሳይታለች።
ድሏን የበለጠ የሚያስገርመው ደግሞ በቅርቡ እናት መሆኗ ነው።
የ31 አመቷ አትሌት ውድድሯን በ1 ሰአት ከ11 ደቂቃ እና 53 ሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቃለች ።
ሀብታምነሽ እኤአ በ2012 የአለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ ተወዳድራ ያከናወነች ሲሆን በሴቶች 3000 ሜትር ሩጫ አራተኛ ወጥታ ነበር።
አትሌቷ በ2013 የአፍሪካ ወጣቶች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በ9፡32.3 የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ነበረች።
በ2018 የአፍሪካ ጨዋታዎች በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር 6ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች ።
2018 በአፍሪካ ሻምፒዮናዎች በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ሰባተኛ ደረጃን ይዛ ፈፅማለች ።
አትሌት ሀብታምነሽ በ2018 የዱባይ ማራቶን የገባችበት 2:20:13 የግል ምርጥ ሰዓቷ ሲሆን የውድድሩ አራተኛው ፈጣን ሰዓት ነበር ።
የ31 አመቷ አትሌት በወሊድ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ከውድድር እርቃ መቆየቷ ይታወሳል።
ከወሊድ በኋላ በስፖርቱ መቆየት እንደሚቻል የሀብታምነሽ የዳግም ምልሰት ለሁሉም እህቶቻችን ጥሩ ምሳሌ ነው።#ወርቅነህ ጋሻሁን

አትሌት ሸዋረግ አለን አማረ አረፈች
#ethiopia | አትሌቷ ትላት በአዲስ አበባ ዙሪያ በልምምድ እያለች ነው የድካም ስሜት ተሰምቷት ወደ ሆክፒታል ተወሰዳ እንዳረፈች ነው የደረሰኝ መረጃ የሚጠቁመው ።
ኑሮዋን በላቲን አሜሪካ ሜክስኮ ያደረገችው ፤ አለሽኝ የ2025 የሲውድን ስቶኮልም ማራቶን አሸናፊ ስትሆን ለልምምድ አዲስ አበባ መጥታ ነው ህይወቷ ያለፈው።
አትሌቷ የቀድሞ አትሌት አለነ አማረ ልጅ ስትሆን የቀድሞ አትሌት አለነ አማረ ደግሞ ኑሮውን በአሜሪካ ኒዮርክ ካደረገ ከ25 አመት በላይ ሆኖቷል።
Shewarge Alene, our 2025 Stockholm Marathon champion.
Mexico City Marathon - 2012 & 2014
Santiago de Chile Marathon - 2013 & 2014
Maratón Internacional Lala - 2014
Via #ethiorunners
#restinpeace #foreverourchampion #gonebutneverforgotten

Comments