10 hours ago
🚨 በህወሓት አመራሮች ላይ የተጣለው የአሜሪካ ቪዛ እገዳ ማብራሪያ! በጠበቃ ሙሉዓለም ጌታቸው ማብራሪያ ተሰጥቶበታል። #usvisa #tplf #ethiopiannews #ussanctions #asylum

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት ቪዛ ሰጪ (ኮንሱላር) ኦፊሰሮች ወደ አሜሪካ የሚገቡ ጊዜያዊ መንገደኞች ጥገኝነት (አሳይለም) እንዳይጠይቁ ለማገድ የሚያስችል አዲስ የውስጥ መመሪያ ማስተላለፉን የኢሚግሬሽን ጠበቃ ሙሉአለም ጌታቸው ገለጹ። ጠበቃው ለዘ-ሐበሻ እንዳብራሩት፣ መመሪያው በዋናነት ጊዜያዊ የቱሪስት፣ የህክምና እና የተማሪ ቪዛዎችን (እንደ B1, B2, F1 እና J1 ያሉትን) በመጠቀም አሜሪካ ገብተው ጥገኝነት ለመጠየቅ የሚያስቡ ሰዎችን ኢላማ ያደረገ ነው። የስቴት ዲፓርትመንት ኦፊሰሮች ቪዛ ከመስጠታቸው በፊት፣ አመልካቾች አሜሪካ ውስጥ እንደማይቀሩና ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ማረጋገጥ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
በአዲሱ መመሪያ መሰረት የቪዛ ኦፊሰሮች ማንኛውንም አመልካች ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ ታዘዋል። አንደኛው ጥያቄ፣ አመልካቹ በሀገሩ ወይም አሁን በሚኖርበት ቦታ ከዚህ በፊት በማንነቱ፣ በዘሩ፣ በሀይማኖቱ ወይም በፖለቲካ አመለካከቱ የደረሰበት ጥቃት መኖር አለመኖሩን የሚያጣራ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፣ ወደ ሀገሩ ቢመለስ ጥቃት ይደርስብኛል ብሎ የሚፈራ መሆን አለመሆኑን የሚጠይቅ ነው። አንድ አመልካች ለእነዚህ ጥያቄዎች "አዎ" የሚል ምላሽ ከሰጠ፣ በአዲሱ መመሪያ መሰረት የአሜሪካ ቪዛ ወዲያውኑ ይከለከላል።
በአንጻሩ ደግሞ አንድ ሰው ቪዛውን ለማግኘት ሲል ምንም ጥቃት እንዳልደረሰበት በመግለጽ ቪዛ አግኝቶ አሜሪካ ከገባ በኋላ ጥገኝነት (Asylum) ቢጠይቅ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይወድቃል። ምክንያቱም አሜሪካ ገብቶ "ጥቃት ደርሶብኛል" ብሎ የሚያቀርበው ማመልከቻ፣ ቀደም ሲል ለኢምባሲ ኦፊሰሩ ከተናገረው ጋር በቀጥታ ይጋጫል። በዚህም የተነሳ የአሜሪካን መንግስት ዋሽተሃል ወይም አጭበርብረሃል ተብሎ አመኔታ (ክሬዴብሊቲ) ስለሚያጣ፣ የጥገኝነት ጥያቄው ሙሉ በሙሉ ውድቅ ሊደረግበት እንደሚችል ጠበቃ ሙሉአለም አስጠንቅቀዋል። አመልካቹ ይህንን ለማስተካከል ልዩ የይቅርታ መጠየቂያ (ዌቨር) እስከማቅረብ ሊገደድ ይችላል።
ይህ አሰራር በተለይም በሰብዓዊ መብት ስራዎች ላይ የተሰማሩ ጋዜጠኞችን፣ የፖለቲካ አክቲቪስቶችን እና በመንግስት ጥቃት የደረሰባቸውን ሰዎች በእጅጉ የሚጎዳ እና ቪዛ እንዳያገኙ የሚያግድ ነው። መመሪያው በኮንግረስ የህግ ሂደት ሳያልፍ በውስጠ-መስሪያ ቤት ትዕዛዝ ብቻ የተላለፈ መሆኑም ውሳኔውን አሳዛኝ ያደርገዋል ተብሏል። አዲሱ መመሪያ ተግባራዊ መሆን የጀመረው ከዚሁ ሳምንት አንስቶ በመሆኑ፣ ከዚህ በፊት ቪዛ ያገኙትን እና አሜሪካ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን አይመለከትም። ሆኖም ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ቪዛ ለሚጠይቁ እና የኢምባሲ ቃለ-መጠይቅ ለሚያደርጉ በሙሉ ተግባራዊ ይሆናል።
ጠበቃ ሙሉአለም እንዳሉት የትራምፕ አስተዳደር በስልጣን ከቀጠለ ይህ ህግ የመቀጠል እድሉ ሰፊ ነው። ነገር ግን ቀጣዩን ምርጫ አሸንፎ የዲሞክራት አስተዳደር ስልጣን ከያዘ፣ ከዲሞክራሲ መርሆች ጋር የሚጋጨውን ይህንን አሰራር ሊያነሳው እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ቪዲዮውን VOEA Television የዩቱብ ቻናል ላይ ይመልከቱ።

3 months ago
እስራኤል 8,000 ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ልታባርር ነው
እንደ Middle East Eye ዘገባ፣ የእስራኤል መንግሥት በመጪው ሚያዝያ ወር በሀገሪቱ የሚገኙ 8,000 ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ አቅዷል።
የሕዝብና ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን ከሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ስደተኞቹን በቁጥጥር ስር ማዋልና ማባረር እንደሚጀምር ታውቋል።
የእርዳታ ድርጅቶች እንደሚገልጹት፣ ሊባረሩ ካሉት መካከል 1,000 ያህሉ ከትግራይ ክልል የመጡ ናቸው።
የእስራኤል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መንግሥት "አይሁዳዊ አይደሉም" ያላቸውን እነዚህን ስደተኞች እንዲያባርር ፈቅዷል።
በአሁኑ ወቅት እስራኤል ውስጥ 72,000 ገደማ ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 57% የሚሆኑት በድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ የ Assaf ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
መንግሥት ስደተኞቹን "ህገ-ወጥ ሰርጎ ገቦች" በሚል መፈረጁም ተገልጿል።
ምንጭ፦ Middle East Eye
https://www.middleeasteye....

ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን ሴት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የጥገኝነት ጥሪ አቀረቡ
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በከፍተኛ የደህንነት ስጋት ላይ ለሚገኙት የኢራን ሴት ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች የፖለቲካ ጥገኝነት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አስታወቁ።
የክስ መነሻው ምንድን ነው?
የኢራን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች በሀገሪቱ ይፋዊ ቴሌቪዥን በ"ሀገር ክህደት" ወንጀል መከሰሳቸው የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ስቧል። ተጫዋቾቹ ወደ ሀገራቸው ቢመለሱ ከፍተኛ ስቃይ አልፎ ተርፎም የሞት ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።
የትራምፕ አቋም
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፦
* ለአውስትራሊያ የቀረበ ጥሪ፦ በአሁኑ ወቅት ተጫዋቾቹን ይዛ የምትገኘው አውስትራሊያ በምንም መልኩ አሳልፋ እንዳትሰጥ እና ጥገኝነት እንድትሰጣቸው ጠይቀዋል።
* የአሜሪካ አማራጭ፦ አውስትራሊያ ይህንን የማታደርግ ከሆነ፣ ተጫዋቾቹ ወደ አሜሪካ እንዲመጡና አስተማማኝ የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጣቸው ሀሳብ አቅርበዋል።
ይህ እርምጃ በኢራን እና በምዕራባውያን መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ሊያከርረው እንደሚችል እየተገመተ ይገኛል። በተለይም በስፖርተኞች ሰብአዊ መብት ዙሪያ ትልቅ ክርክር ቀስቅሷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #trump #iran #womensfootball #asylum #usa #humanrights #politicalnews #ethiopia #sportnews

Comments