6 months ago
ቅሬታ በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ላይ
"ላባችን ሳይደርቅ ክፍያችን ይፈጸምልን!" 🏃♂️⚖️
#ethiopia | በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደው አገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች አትሌቲክስ ውድድር በድምቀት ቢጠናቀቅም፣ ከጀርባው ግን የባለሙያዎች እሮሮና ምሬት ሰፍኖ ይገኛል። ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ50 በላይ ዳኞችና የፌዴሬሽኑ ባለሙያዎች ላለፉት 10 ቀናት አበላቸው ሳይከፈላቸው ለእንግልት መዳረጋቸውን ገልጸዋል።
📌 ዋና ዋና ቅሬታዎች፦
የክፍያ መዘግየት፦
ውድድሩ ካለቀ 10 ቀናት ቢቆጠሩም፣ በህጉ መሠረት መከፈል የነበረበት አበል እስካሁን አልተከፈለንም ብለዋል።
ማህበራዊ ቀውስ፦
"በቀን 900 ብር አበል እየተሰጠን፣ በዚህ የኑሮ ውድነት መኝታና ምግብ ችለን፣ አንድ መኝታ ላይ ሁለት እየተኛን ስራችንን ብንሰራም አበላችንን በመከልከላችን ለከፍተኛ ችግርና ለብድር ተጋልጠናል" ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል።
የሚኒስቴሩ ድጋፍና የፌዴሬሽኑ ዝምታ፦ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለውድድሩ አስፈላጊውን ፈሰስ ቀደም ብሎ ቢያደርግም፣ ፌዴሬሽኑ ለምን ክፍያውን እንዳዘገየው ግልጽ እንዳልሆነ ተገልጿል።
🚨 የመረጃ መውጣትና የፌዴሬሽኑ ድንገተኛ ሩጫ፦
ይህ መረጃ ለሚዲያ መድረሱ ከተሰማ በኋላ፣ ፌዴሬሽኑ "መረጃው ቀድሞን እንዳይወጣ" በሚል ስጋት ለዳኞቹ በአካውንታቸው ክፍያውን ለመፈጸም ሩጫ መጀመሩን የሀትሪክ ስፖርት ዘገባ አመልክቷል።
🔇 የተቋሙ ምላሽ፦
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ጥረት፣ "ከሚዲያ የሚደወል ስልክ አታንሱ" በሚል መመሪያ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል። ይህ የህዝብን የመረጃ ባለቤትነት የሚክድ አሰራር በስፖርቱ አመራር ላይ ያለውን የአመለካከት ክፍተት ያሳያል።
#ethiopianathletics #athleticsfederation #adama #fairpay #sportnews #hattricksport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments