2 days ago
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ወደ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ተሸጋገረ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) በይፋ"ፋይዳቨርስ" በመባል ወደ የመንግሥት የልማት ድርጅት ማዕቀፍ ማደጉ ተገለጸ።
ይህ አዲስ ድርጅት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) ሥር የተጠቃለለ ሲሆን፤ ፕሮጀክቱ ከነበረበት ማዕቀፍ ወጥቶ በንግድ አሠራር የሚመራ እና ዘላቂ ዲጂታል መሠረተ ልማት አቅራቢ ሆኖ እንዲቀጥል ታስቦ የተቋቋመ መሆኑ ተጠቁሟል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ እንደገለጹት፤ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለፋይናንስ አካታችነት እና ለቀልጣፋ አገልግሎት አሰጣጥ ወሳኝ ድርሻ አለው።
ፕሮግራሙ አሁን ላይ ከ50 ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎችን መመዝገብ የቻለ ሲሆን፣ 150 የሚደርሱ የንግድ ተቋማት የደንበኛ ማረጋገጫ (eKYC) ውህዶችን አከናውኗል። በተጨማሪም ከ190 ሚሊዮን በላይ ደህንነታቸው የተጠበቁ የማረጋገጫ ሂደቶችን በማከናወን ከ15 ሚሊዮን በላይ ዲጂታል መታወቂያ ምስክር ወረቀቶችን መስጠቱ ተገልጿል።
ተቋሙ አሁን የያዘውን አዲስ መዋቅር በመጠቀም የዲጂታል መታወቂያ መፍትሔዎችን ከአህጉራዊ አጀንዳዎች ማለትም ከአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጠና እና ከስማርት አፍሪካ ጋር ለማስተሳሰር እና አገልግሎቱን በክልሉ ለማስፋፋት ተነግሯል።
Seledadotio

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትራምፕ አስተዳደር ባለፈው ዓመት በውጭ ሀገር የዩኒቨርሲቲ እና የኮሌጅ ተማሪዎች ላይ የጀመረውን ጥብቅ ቁጥጥር ተከትሎ፣ ለቻይና እና ህንድ አመልካቾች የሚሰጠው የተማሪነት ቪዛ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱን አዲስ ጥናት አመላከተ። መቀመጫውን ዋሽንግተን ያደረገው ሴንተር ፎር ኢሚግሬሽን ስተዲስ የተሰኘው ተቋም እንዳወጣው መረጃ፣ ከግንቦት እስከ ነሐሴ ሁለት ሺህ ሃያ አምስት ባለው ጊዜ ውስጥ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተሰጠው ቪዛ በሁለት ሺህ አስራ ሰባት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በአርባ ስድስት በመቶ ቀንሷል። በህንድ ተማሪዎች ላይ ደግሞ የስልሳ በመቶ ቅናሽ ታይቷል።
ቻይናውያን እና ህንዳውያን ተማሪዎች በአሜሪካ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከሚማሩት አጠቃላይ የውጭ ሀገር ተማሪዎች ሃምሳ ሶስት በመቶውን ይሸፍናሉ። የተቋሙ ከፍተኛ የህግ ተመራማሪ ጆርጅ ፊሽማን ባወጡት ትንታኔ፣ ይህ የቪዛ ቅናሽ ለትምህርት ወደ አሜሪካ የሚገቡትን የውጭ ዜጎች አጠቃላይ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዳ መሆኑን አስገንዝበዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው የከፍተኛ ትምህርት ማሻሻያን ኢላማ በማድረግ የጀመሩት ጫና፣ ጉዳዩን ወደ ግላዊ ፍልሚያነት የቀየረው ይመስላል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የትምህርት ዘርፉ ከስደተኞች ጉዳይ እስከ የፆታ አመለካከት፣ እንዲሁም ከተማሪዎች የብድር ስረዛ እስከ ካምፓስ ውስጥ የመናገር ነፃነት ድረስ የባህል እና የፖለቲካ ሽኩቻዎች ማዕከል ሆኗል። የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የቆየ ጥርጣሬ ያላቸው ሲሆን፣ ምሁራን ወጣቶችን አክራሪ በሆኑ የፖለቲካ አመለካከቶች እየመረዙ ነው ብለው ይከሳሉ። ትራምፕም የኮሌጅ ካምፓሶች ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአክራሪነት ተወርረዋል በማለት ወቀሳ አቅርበዋል። የፕሬዝዳንቱ ዋነኛ ትኩረት የብዝሃነት፣ የእኩልነት እና የአካታችነት ፖሊሲዎችን በመቀልበስ፣ የተወሰኑ ተማሪዎች ያላግባብ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው ያሉትን አሰራር ማስቆም ላይ ያነጣጠረ ነው።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የፌደራል መንግስቱን ስልጣን በመጠቀም የዩኒቨርሲቲዎችን የገንዘብ ድጋፍ ለማቋረጥ በማስፈራራት እና የውጭ ሀገር ተማሪዎችን መብት በመገደብ ላይ ይገኛሉ። ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን በሚቀበሉበት መንገድ፣ በትምህርት ስርዓታቸው እና በአጠቃላይ አሰራራቸው ላይ ታይቶ የማያውቅ ጣልቃ ገብነት እያደረጉ ነው። በአብዛኛው የፀረ ሴማዊነት ክሶችን ወይም የህግ እና ስርአት መርሆችን በመጠቀም የከፍተኛ ትምህርት አስተዳዳሪዎች ላይ ጥብቅ ምርመራ እንዲካሄድ እያስገደዱ ይገኛሉ። አሜሪካ ውስጥ የፍትሃዊነት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የወጡ የሲቪል መብቶች ህጎችን በመጠቀም፣ በታሪክ ተጨቁነው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚጠብቁ አሰራሮችን ወደ ኋላ ለመመለስ እየሰሩ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህ የትራምፕ አስተዳደር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የገጠመው ፍልሚያ ወደ አጠቃላይ ጦርነት ያደገ ሲሆን፣ በተለይም የእሳቸውን ፍላጎት ለማስተናገድ ፈቃደኛ ባልሆኑ እንደ ታዋቂው ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጠንካራ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ በዘገባው ተብራርቷል።

ወደ ዘላቂ ልማት የሚደረግ ሽግግር
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለመዋቅራዊ ሽግግር፣ ለኢኮኖሚ ጥንካሬ እና ለአካታች ሀገራዊ እድገት ቁርጠኝነት ባለው ሥርዓት እየተመራች በዘመናዊ ታሪክ ግንባታዋ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።
በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ኢትዮጵያ በዋና ዋና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ላይ አበይት ስኬቶችን እያስመዘገበች ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መሰረት የሆነው ግብርና ወደ ቴክኖሎጂ መር ያደረገው ሽግግር ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል፡፡
በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እና በክላስተር እርሻ እቅዶች አማካኝነት ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ምርትን በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጋለች፡፡ይህም ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ጥገኝነትን ቀንሷል፡፡
በሀገሪቱ በአረንጓዴ ዐሻራ ፕሮግራሞች በአትክልትና ፍራፍሬ ላይ የተደረጉ ኢንቨስትመንቶች የአየር ንብረት ተፅዕኖን ለመቋቋም ሥነ ምህዳርን ለማከም እና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የሚደረገውን ጉዞ እየደገፈ ነው፡፡
የኃይል ማመንጨት አቅምን በማሳደግ የመንገድ መረቦችን በማዘመን እና በማስተሳሰር የኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት ገጽታ አስደናቂ ለውጥ በማድረግ፤ የሀገር ውስጥ ትስስርን እያጠናከረ ኢትዮጵያን በአህጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና ስር የንግድ ማዕከል እያደረጋት ይገኛል።
በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የተካሄደው የኮሪደር ልማት የሕዝብ ቦታዎችን በመሠረታዊነት በማደስ፤ መንገዶችን በማዘመን፣ አረንጓዴ የሕዝብ ቦታዎችን በመገንባት፣ የመገልገያ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት እና የንፅህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን በማሻሻል ተስማሚ የከተማ አካባቢን እየፈጠረ ነው፡፡
ዘላቂ ኢኮኖሚ ለመገንባት ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ አማካኝነት የዲጂታል ሽግግርን በከፍተኛ ሁኔታ እያፋጠነች ትገኛለች።
በቴሌኮሙኒኬሽን እና በፋይናንስ ዘርፍ ላይ የተደረጉ ኢንቨስትመንቶች የፋይናንስ አካታችነትን እያሳደገ ነው፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማስፋፋት የሀገር ውስጥ ማኑፋክቸሪንግን ለማነቃቃት እና ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የውጭ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ የሚደረጉ ጥረቶች የኤክስፖርት ገቢን በማሳደግ የሰለጠነ የሰው ሀይል መፍጠራቸውን ቀጥለዋል።
የኢኮኖሚ እድገት ያለ ማህበራዊ ልማት ትርጉም የለውምና የኢትዮጵያ መንግሥት በትምህርት፣ ጤና እና ሌሎች ዘርፎች መሠረተ ልማቶችን በማሻሻል የሰራተኛውን ክህሎት ከዘመናዊ የገበያ ፍላጎት ጋር በማጣጣም የዜጎችን ሁለንተናዊ ለውጥ ማጠናከር ተችሏል።
ኢትዮጵያ እስካሁን ላስመዘገበቻቸው ስኬቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሰጧት እውቅናዎች የበለጸገች ሉዓላዊት ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ፈተናዎች ቢኖሩም ህዝብ ከውጤት ተኮር አመራር ጋር ተቀናጅቶ ወደ ዘላቂ ልማት የሚያደርገው ጉዞ በተገቢ መስመር ላይ ስለመሆኑ ማሳያ ናቸው።
በምሕረት ደምሴ

3 days ago
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) የ'ሪያል ማድሪድ ፋውንዴሽን' በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በመላው አፍሪካ ካከናወናቸው ስኬታማ ተግባራት መካከል በኢትዮጵያ አዲስ የማህበራዊ ስፖርት አካዳሚ መክፈቱ በዋና ማሳያነት ተጠቅሷል። ፋውንዴሽኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ23 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ 52 የማህበራዊ ስፖርት ፕሮጀክቶችን ያካሄደ ሲሆን፣ በዚህም 10,628 የሚሆኑ ህጻናትን፣ ታዳጊዎችን እና ወጣቶችን የዕድሉ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።
በዘመኑ ከተመዘገቡት ትልልቅ ስኬቶች አንዱ በሀገራችን ኢትዮጵያ አዲስ የማህበራዊ ስፖርት አካዳሚ መከፈቱ ነው። ከኢትዮጵያ በተጨማሪም አንጎላ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሴኔጋል እና ግብጽን ጨምሮ በ23 የአፍሪካ ሀገራት ፕሮጀክቱ ተደራሽ ሆኗል።
በአካታችነት በኩል ፋውንዴሽኑ ሴት ታዳጊዎች በስፖርቱ ያላቸውን ተሳትፎ በማሳደግ እና ሴት አሰልጣኞችን በማበረታታት ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቷል። ከዚህም በተጨማሪ አካል ጉዳተኛ ህጻናት፣ ወጣት ስደተኞች እንዲሁም በከባድ ድህነት እና በግጭት የተጎዱ ማህበረሰቦችን የዕድሉ ተጠቃሚ አድርጓል። ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ባሻገር ትምህርታዊ ድጋፍን፣ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን፣ የህጻናት ጥበቃን፣ የጾታ እኩልነትን እና ማህበረሰባዊ ትስስርን ማጠናከር የትምህርት ቤቶቹ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው።
የአካባቢውን አሰልጣኞች አቅም በስልጠና፣ በክትትል እና በተሞክሮ ልውውጥ ማሳደግ የፕሮጀክቱ ሌላኛው ስኬት ነው። ይህ አካሄድ ከዚህ ቀደም የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የነበሩ ወጣቶች አሁን ላይ ለተተኪው ትውልድ አሰልጣኝ እና አርአያ የሚሆኑበትን ቀጣይነት ያለው ሞዴል ለመፍጠር አስችሏል።
ፋውንዴሽኑ ይህንን ዘላቂ እና አዎንታዊ ተጽዕኖ ለማምጣት ከተለያዩ ማህበራዊ ተቋማት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ ሌሎች ፋውንዴሽኖች፣ ኩባንያዎች እና የአካባቢው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውቋል።

6 days ago
"ዘመናዊቷን ኢትዮጵያ ከአማራና ኦሮሞ ውህደት ውጭ ማየት አይቻልም"
#ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሀገሪቱን ለመቀየር ፖለቲካውንም ሆነ ኢኮኖሚውን ጎን ለጎን ክፍት ማድረግ አስፈላጊ እንደነበር ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲያብራሩም የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ከአማራና ከኦሮሞ ሕዝቦች ጥብቅ ውህደትና ትስስር ውጭ ሊታይ አይችልም። የዓድዋ ድልም የዚሁ ታሪካዊ አንድነት ትልቁ ማሳያ ነው፤ አብሮ የመኖር ባህልም የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ እሴት እንደሆነ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል፣ በሀገራችን ስልጣንን በኃይልና በሰው ግድያ ለመያዝ የመሞከር አጥፊ ባህል እንደነበር አውስተዋል። በዚህም የሰኔ 15ቱ ክስተት በለውጡ ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራቸውን ሰዎች ያጣንበት የሕመም ጠባሳችን ነው ብለዋል።
ሆኖም ሕዝቡ ለውጡን በሙሉ ልብ የተቀበለ ሲሆን፣ በአንድነትና በትብብር አንዲት ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደምንችል በምርጫው ወቅት በተግባር ማረጋገጡን ገልጸዋል።
***
“የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎች ለአጭር ጊዜ እፎይታ ተብሎ በአንድ ወገን ፍላጎት መመለስ አይቻልም”
በአማራ ክልልም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚነሡ የወሰን እና የማንነት ጥያቄዎችን ለአጭር ጊዜ እፎይታ ብሎ በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ መመለስ እንደማይቻል እና ጉዳዩ በሕግ አግባብ እና በሀገራዊ ምክክር ዘላቂ መፍትሔ እንደሚያገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የወልቃይትን ጉዳይ እንደ አብነት በማንሣት በትግራይም ሆነ በአማራ ክልል በኩል የሚነሡ ጥያቄዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ዘላቂ መፍትሔው የሁለቱንም ሕዝቦች ጥቅም በማይጎዳ፣ በውይይት እና ሁለቱም አሸናፊ በሚሆኑበት ሕገ-መንግሥታዊ መንገድ ካልሆነ መልሶ ለግጭት የሚዳርግ ቆይቶ የሚፈነዳ ቦምብ ይሆናል ብለዋል።
በሌላ በኩል ከውጡ ማግስት ጀምሮ በርካታ ዋና ዋና ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹ ሲሆን በዚህም በፓርቲ ውስጥ የነበረውን ኢ-ዴሞክራሲያዊ አሠራር ማስተካከል እና የክልሎችን ራስን የማስተዳደር መብት ማክበር ተችሏል ብለዋል ።
በተጨማሪም በመንግሥት ተቋማት አካታችነትን ማረጋገጥ እና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በካቢኔ እና በፖለቲካ ምኅዳር ማሳተፍ እንዲሁም አግላይ የነበሩ ትርክቶችን ማረቅም ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል እንደሆነ አስረድተዋል።
***
በአማራ ክልል የሰኔ 15ቱ ክስተት በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል-
በአማራ ክልል የሰኔ 15ቱ ክስተት በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የሰኔ 15ቱን መጥፎ ክስተት በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ታሪክን ማዛባት ለነገው ትውልድ የሚተርፍ እዳ ነው ብለዋል።
ለውጥን ለማምጣት በጽናት ሲሰሩ የነበሩ የለውጥ አበጋዞችን ያጣንበት፣ በፖለቲካው መካከል የመተማመን መንፈስ እንዲሸረሸር ያደረገ እና የስልጣን ሽሚያ በሃይል የማስከበር መጥፎ ባህልን ያስቀጠለ አጋጣሚ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ስለ እለቱና ስለተፈጠረው ክስተት ሲያብራሩ፤ እለቱ ቅዳሜ ነበረ፤ መረጃውን እንደሰማሁ ለህዝብ መግለጫ እንዲሰጥ ሚዲያዎች እንዲጠሩ አደረግኩ፤ ፋና እና ኢቢሲ በምሽቱ ፈጥነው አልደረሱም ነበር፤ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ግን እዚሁ 4 ኪሎ አቅራቢያ ስለነበር በፍጥነት ደረሰ ብለዋል።
መግለጫውን እኔ ቤት ሆኜ ለአሚኮ ሰጠሁ፤ በኋላ ግን 'ባህር ዳር ሆኖ መግለጫ ሰጠ' ተብሎ የሴራ ትንተና ተፈበረከበት በማለት አስታውሰዋል።
ይህ ክስተት ያስተማረን ትልቅ ሀቅም ታሪክን በትክክል አለማስቀመጥና ማዛባት ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገውም ትውልድ እዳ ያተርፋል ሲሉ ተናግረዋል።
ገዳይም ሟችም በአንድ ላይ 'ጀግና' የሚደረግበት የታሪክ ስብራት ሊቆም እንደሚገባም በአፅንኦት አስገንዝበዋል።
***
"በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሕዝቦች በዘመናት መካከል አብረው ሲኖሩ በብዙ መልኩ የተጋመዱ፣ የተሳሰሩ፣ የተጋቡ፣ የተዋለዱ በጋራ የኖሩ ናቸው''
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
#ethiopia #pmabiyahmed #currentaffairs #pmabiyahmed #amico #ethiopia #medemer #amharaandoromo #ethiopianunity

8 days ago
የመከረ ቤቱን አጠናከረ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራችን በአንድ ግዙፍ የታሪክ ምዕራፍ እጥፋት ላይ ትገኛለች፡፡ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የውስጥ ጉዳዮቿን የሀገር ልጆች ቁጭ ብለው ተመካክረው ሀገር ሊያጸኑ ተሰባስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምክክሩን አስፈላጊነት በተመለከተ ሲናገሩ፣ "ለልጆቿ ኩራት የሆነች፣ ተስፋ ያላት ምድር ለማድረግ አንድንችል ምክክሩ በእጅጉ ያስፈልጋል" ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች የሚኖሩባት ባለ ብዝሃ ባህል፣ ብዝሃ ታሪክ፣ ብዝሃ ማህበረ ኢኮኖሚ ሀገር እንደመሆኗ በዘመናት ጉዞዋ የልማት፣ የአስተዳደራዊ እና ሌሎች አለመግባባቶች እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡
የእነዚህን በህዝቦች መካል የሚስተዋሉ ልዩነቶች አለመግባባቶችና ጥያቄዎች በዘላቂነት በመፍታት ህብረ ብሔራዊ አንድነቷ የተጠበቀ፣ የበለጸገችና የታፈረች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ ምክክሩ እጅግ ያስፈልጋል።
ብሔራዊ ምክክሩ የታለመለትን ግብ እንዲመታ እና ሀገር እንድትጸና ለማድረግ የሁሉምን ህብረተሰብ ክፍሎች ያካተተ እና ያሳተፈ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የምክክር ሂደቱ፣ "በፖለቲካ ልሂቃን መካከል የሚደረግ ብቻ ሳይሆን የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ያገናዘበ፣ በኢትዮጵያውያን የተመራ ሀገር በቀል መፍትሄዎችን ለማፍለቅ ታልሞ የሚከናወን ይሆናል" ባሉት መሰረት የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ሠራተኞች፣ አካል ጉዳተኞች፣ እንዲሁም ተፈናቃዮች እንዲሳተፉ ተደርጓል።
የተለያዩ የዘርፉ ምሁራን በምክክርና ውይይት ሂደት የአካታችነት እና አሳታፊነትን ፋይዳ ያሰምሩበታል፡፡ በስዊዝፒስ የድርድር ፕሮግራም ኃላፊ የሆኑት ዴቪድ ላንዝ የአንድን ሀገር መሰረታዊ ማንነትና የአስተዳደር ስርዓት ለመወያየት የሚያስችል ሁሉን አቀፍ አሰራር ከሌለ፣ ከዚያ በኋላ የሚደረጉ ማናቸውም ውሳኔዎች ወይም ተቋማዊ ማሻሻያዎች በአሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት ይሆናሉ ይላሉ፡፡
ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የሆኑ በዘመናት ተሞክረው እና ተፈትነው በውጤታማነት የዘለቁ የልዩነትና የግጭት መፍቻ ስርዓቶች ባለቤት እንደመሆኗ አሁን እየተካሄደ ያለው የምክክር ጉባኤ የእነዚህ እሴቶች አዲስ ምዕራፍ መገለጫ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ምክክሩ ሁሉም ሃሳቡን የሚገልፅበት፣ የሌሎች ጥያቄዎችና ቅሬታዎች የሚደምጥበት፣ በጋራ መፍትሄ የሚፈለግበትና የጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት በመሆኑ ውጤቱም ዘላቂና ሀገርን የሚያጸና ነው፡፡
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር መላው ኢትዮጵያውያን በአንድ ዜማ ተግባብተው ታሪክ እንደሰሩ ሁሉ በሀገራዊ መግባባትና ሀገር መፅናት ጉዳይም ተመሳሳይ ድል የመቀዳጀት ጉዞ ላይ ናቸው።
ይህ ለአፍሪካውያን ብሎም ለዓለም ተምሳሌት ሊሆን የሚችል የኢትጵያውያን፣ በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተዘጋጀ ታሪካዊ መድረክ የበለጸገች ህብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ ፅኑ መሰረት ይጥላል።
የምክክር ሂደቱ በስኬት እስኪጠናቀቅ፣ ኢትዮጵያውያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ

Sponsored by
Surafel
8 days ago
የሀገርን ዕጣ ፈንታ ከፖለቲካ ልሂቃን እጅ ፈልቅቆ ለዜጎች ያስረከበው ሀገራዊ ምክክክር
*********************
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አንዱ የኅብረተሰብ ክፍል እንደ ወርቃማ የታሪክ ዘመን የሚያየውን፣ ሌላው እንደ ጭቆና እና መገለል ዘመን ሲመለከተው መኖሩ የተለመደ ክስተት ሆኖ ቆይቷል።
ይህ የተራራቀ የታሪክ ግንዛቤ እና ያልተፈቱ መዋቅራዊ ቅራኔዎች ሀገራችንን ከትውልድ ወደ ትውልድ ለሚሸጋገር የትርክት ግጭት ዳርገዋታል።
ዘውዳዊውን ሥርዓት ተክቶ የመጣው ወታደራዊ አገዛዝም ሆነ፣ እርሱን ተከትሎ የመጣው የኢሕአዴግ ሥርዓት የዜጎችን የዴሞክራሲ፣ የፍትህ እና የእኩልነት ጥያቄዎች በዘላቂነት መፍታት አልቻሉም።
በተለይም ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት የተዘረጋው የልዩነት ፖለቲካ፣ በዜጎች መካከል መጠራጠርን በማንገሥ የጋራ ሀገራዊ ማንነታችንን በጽኑ ፈትኖታል።
የ2010 ዓ.ም ሀገራዊ ለውጥ የፈጠረው የፖለቲካ መነቃቃት ትልቅ ተስፋን ያሰነቀ ቢሆንም፣ ከዴሞክራሲያዊ ባህል ማነስ እና ከጽንፈኛ ብሔርተኝነት ጋር ተዳምሮ አዳዲስ ሀገራዊ ስጋቶችን መፍጠሩ አልቀረም።
ይሁንና ከእነዚህ ሁሉ ውጣ ውረዶች ኢትዮጵያውያን አንድ ትልቅ ትምህርት ቀስመዋል። ይኸውም ታሪካዊ እና መዋቅራዊ ቀውሶችን በጦርነት፣ በኃይል እና በአሸናፊነት ሥነ-ልቦና ለመፍታት የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ ጊዜያዊ ማስታገሻ እንጂ ዘላቂ መፍትሔ እንደማያመጣ ነው።
እውነተኛው መፍትሔ ያለው ጠብመንጃን አስቀምጦ በጠረጴዛ ዙሪያ በመቀመጥ፣ በመደማመጥ እና በሀሳብ ልዕልና በማመን ላይ ብቻ መሆኑ ታምኖበታል።
ይህን ታሪካዊ የዕይታ ሽግግር እውን ለማድረግ ነው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 1265/2014 ተቋቁሞ ወደ ሥራ የገባው። ከተቋሙ አወቃቀር ጀምሮ ሂደቱ ፍፁም የተለየ ነበር።
ከመነሻው፣ ከ632 እጩዎች ውስጥ በሕዝብ ተሳትፎ የተመረጡ 11 ኮሚሽነሮች ገለልተኛ ሆነው ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ተደርጓል።
ይህ እርምጃ የፖለቲካ ልሂቃን ብቻ የሀገርን ዕጣ ፈንታ ሲዘውሩበት የነበረውን ባህል በመስበር፣ መሠረታዊው ዜጋ የሀገሩን ዕጣ ፈንታ በራሱ እንዲወስን ዕድል የፈጠረ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ነው።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ1 ሺህ 200 በላይ ወረዳዎችን በማዳረስ ያከናወነው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የዜጎች ተሳትፎ የተረጋገጠበት ነው።
ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አርሶ አደሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ተፈናቃዮች እንዲሁም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላት እና የዳያስፖራው ማኅበረሰብ ሳይቀሩ በምክክሩ እንዲሳተፉ መደረጉ የሂደቱን አካታችነት እና ህዝባዊ መሠረት ያጎላዋል።
በአሁኑ ወቅት በመዲናችን አዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው።
ከ4 ሺህ በላይ በሕዝብ የተመረጡ ተወካዮች በራሳቸው ባህልና ቋንቋ፣ በነፃነት ስጋታቸውን እና ምኞታቸውን እያንፀባረቁበት ይገኛሉ።
ይህ ጉባኤ ስብሰባ ብቻ ሳይሆን፣ የተዛባውን የሀገራችንን ትርክት አርሞ፣ የተበታተነውን ሰፍቶ አንድ ላይ የሚያያይዝ የትውልዶች ድልድይ ነው።
መላ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ችግር በራሳቸው አቅም፣ በሰከነ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ የምክክር ባህል ለመፍታት ያሳዩት ይህ ቁርጠኝነት ጠንካራ መሠረት ያለን ሀገረ-መንግሥት እንድንሆን ያስችለናል።
ጉባኤው የሚያቀርባቸው የፖሊሲ አማራጮች እና የሚያስቀምጣቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች፣ ለቀጣናው ሰላም ብቻ ሳይሆን በውስብስብ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ለሚገኙ የዓለም ሀገራት ጭምር ትልቅ ተምሳሌት እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
በሰለሞን ገዳ
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus #peacebuilding #ebc

10 days ago
በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው እየተሳተፉ ያሉ ተመካካሪዎች ምን አሉ?
******************
✅ሰፊ እና ያልተገደበ አካታችነት፦ ውይይቱ የታጠቁ የፖለቲካ ኃይሎችን፣ ባለሥልጣናትን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የሃይማኖት አባቶችን እና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሳተፈ ከመሆኑም በላይ ሁሉም በእኩል ደረጃ የሚወያዩበት መድረክ ነው።
✅ከታች ወደ ላይ (Bottom-Up) የመጣ የአጀንዳ ቀረጻ፦ ውይይት እየተደረገባቸው ያሉት ስምንት አጀንዳዎች የግለሰቦች ሳይሆኑ ከመሰረታዊው ኅብረተሰብ የተሰበሰቡ እና ተጨምቀው የቀረቡ ናቸው፤ እንዲሁም ውይይቱ ፍሬያማ እንዲሆን እስከ አስር አባላት ባሏቸው ትንንሽ ቡድኖች ተከፋፍሎ እየተካሄደ ነው።
✅ የስሜት ተጋሪነት (በሌላው ጫማ ውስጥ ሆኖ ማሰብ)፦ ተሳታፊዎች ከራሳቸው ሰፈር እና አካባቢ ወጥተው የሰሜኑን በደቡብ፣ የደቡቡን በምሥራቅ ችግር ለመረዳት እና የሌላውን ስጋት፣ ፍላጎት እና ባህል በራሳቸው ጫማ ውስጥ ሆነው ለመመልከት ዝንባሌ እያሳዩ ነው።
✅ሀገር በቀል ዕውቀትን እና ውይይትን እንደ ሥልጣኔ መጠቀም፦ እንደ ከዚህ ቀደም ከሩቅ ሆኖ ከመወጋገዝ ይልቅ በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብሎ የሌላውን ስጋት መረዳት ያስፈልጋል፤ ለዘመናት ለነበሩ ቁርሾዎች ነባር ሀገር በቀል ዕውቀቶችን መፍትሔ አድርጎ መጠቀም ለችግሮቻችን ፍቱን መድኃኒት ነው።
✅ከግል እና ከቡድን ፍላጎት ይልቅ ሀገርን ማስቀደም፦ ተሳታፊዎች የነበሯቸውን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት እና የግል ጥቅሞች ወደ ጎን በመተው ለቀጣዩ ትውልድ የሚጠቅም መልካም ታሪክ ለማስቀመጥ እና ሀገርን ለማስቀደም እየተወያዩ ነው።
✅ሙሉ የሃሳብ ነፃነት እና የውጫዊ ተጽዕኖ አለመኖር፦ ውይይቱ ያለ ምንም ስጋት፣ ፍርሃት እና ውጫዊ ግፊት የሚካሄድ ነው፤ ተመካካሪዎች የወከሏቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች ድምጽ በነፃነት የሚያሰሙበት መድረክም ነው።
✅ከተቀመጡ አጀንዳዎች በላይ የሆኑ መፍትሔዎችን ማመንጨት፦ ከተሰጡት ስምንት አጀንዳዎች ውጭ ተሳታፊዎች ትልልቅ ሀገራዊ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማመንጨት በመቻላቸው፣ ሂደቱ ለአፍሪካ እና ለቀሪው ዓለም ተምሳሌት የሚሆን ልምድ እየፈጠረ ነው።
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus #ebc

15 days ago
ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት አመቱ 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
#ethiopia | ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት የ“ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂውን በመተግበር በሁሉም የሥራ ክንውንና የፋይናንስ መለኪያዎች የላቀ ስኬት ማስመዝገቡን የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገለጹ።
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ በማመንጨት የዕቅዱን 99.7 በመቶ ማሳካቱንና ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ33.2 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አስታውቀዋል።
በዚህም የታሪካዊ ስኬት ምዕራፍ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዳታና ኢንተርኔት አገልግሎት የተገኘው ገቢ 31.1 በመቶ ከሞባይል ድምፅ ገቢ 23.5 በመቶ ብልጫ በመውሰድ ኩባንያው ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያደረገውን ስኬታማ ሽግግር በግልጽ አሳይቷል።
በተጨማሪም የኩባንያው ደንበኞች ቁጥር 90.12 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የፋይናንስ አካታችነትን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ድርሻ ያለው የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚዎች 60.6 ሚሊዮን ደርሰዋል።
ቴሌብር በበጀት ዓመቱ ብቻ 4.19 ትሪሊዮን ብር የሚያንቀሳቅስ 2.61 ቢሊዮን ግብይቶችን ማስተናገዱን የጠቀሱት አበይት ማብራሪያዎች፣ ተቋሙ ከወትሮው የቴሌኮም ኦፕሬተርነት ወደ ሁለንተናዊ የቴክኖሎጂ ተቋም የመሸጋገር ጉዞውን በተሳካ ሁኔታ እያከናወነ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው።
የኔትወርክ ጥራትንና ተደራሽነትን ለማስፋፋት በተደረገው ጥረት 603 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች ተገንብተው የ4ጂ የሕዝብ ቁጥር ሽፋን 82.23 በመቶ ደርሷል።
ከዚህ ጎን ለጎን ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ሕዝባዊ አክሲዮን ማኅበርነት በመሸጋገር በኢትዮጵያ ሴኪውሪቲስ ኤክስቼንጅ የመጀመሪያውን ይፋዊ የአክሲዮን ምዝገባ ማካሄዱን፣ እንዲሁም በበጀት ዓመቱ 73.5 ቢሊዮን ብር ታክስ በመክፈል ለአገራዊ ኢኮኖሚ ግንባታ ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ መቀጠሉን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ አብራርተዋል።
#ethiotelecom #ethiotelecomreport #digitalethiopia #telebirr #techco
#telecomnews #ethiopiatech
#digitaltransformation

17 days ago
በመደመር መንግሥት ራዕይ የኢትዮጵያ ከተሞች እመርታ
የሀገራት ኢኮኖሚ፣ የሥልጣኔ ደረጃ እና የወደፊት ተስፋ የሚገለጥባቸው ዋና ማዕከላት የሆኑት ከተሞች በዘመናችን የሚታየው ፈጣን የከተሜነት እድገት ከተሞችን ከመኖሪያ ስፍራነት በላይ የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንት፣ የፈጠራ እና የማኅበራዊ ለውጥ ሞተር አድርጓቸዋል።
ኢትዮጵያም በዚህ ዓለም አቀፍ እድገት ውስጥ የራሷን ድርሻ ለማረጋገጥ በመደመር ፍልስፍና የተመራ የከተማ ልማት አቅጣጫን በመከተል የተለያዩ ዘርፎችን ያካተተ ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች።
በዚህም ባለፉት ስምንት ዓመታት የከተሞች ልማት የሕንፃ ግንባታና የመንገድ ዝርጋታ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ እድገት፣ የመዋቅራዊ ሽግግር፣ የማኅበራዊ አካታችነት እና የዜጎች የኑሮ ጥራት ማሻሻያ የተዋሃደበት አቅጣጫ ሆኗል።
በዚህ መነሻም ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለቱሪዝም ሳቢ፣ ለኢንቨስትመንት አስተማማኝ እና ተወዳዳሪ የንግድ ማዕከላት እንዲሆኑ የሚያግዙ ፖሊሲዎችና ሪፎርሞች ተተግብረዋል።
የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች የከተሞችን ገጽታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከለወጡ ታላላቅ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ሲሆን በአዲስ አበባ የተጀመረው ፕሮጀክት ከ50 በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ ከተሞች መስፋፋት ችሏል።
የተሻለ የትራንስፖርት አውታረ መረብ፣ የእግረኛ መንገዶች፣ አረንጓዴ ስፍራዎች እና ለባህልና ለመዝናኛ የተመቹ የሕዝብ አደባባዮችን የፈጠረው ይህ ለውጥ የከተሞችን ውበት ብቻ ሳይሆን የነዋሪዎችን ጤና እና የሕይወት ጥራትን ለማሻሻልም አስተዋጽኦ አበርክቷል።
የከተማ ልማቱ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ዕድሎችንም በማስፋት ረገድ ጉልህ ሚና የተጫወተ ሲሆን፤ የተሻሻሉ መሠረተ ልማቶች አዲስ አበባን የኮንፈረንስና የቱሪዝም መዳረሻ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ከማሳደግ ባሻገር ለወጣቶችና ለሴቶች አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ፈጥረዋል።
የከተማ ልማትን በሰው ተኮር እይታ የሚመለከተው የመደመር ፍልስፍና በዚህ መሠረት የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔትና ሥራ ፕሮግራም ከ11 ከተሞች ተነስቶ ወደ 88 ከተሞች በመስፋፋት ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ አድርጓል።
ፕሮግራሙ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ በከተሞች የሚከናወኑ የጽዳት፣ የአረንጓዴ ልማትና የተፋሰስ ሥራዎችን በመደገፍ ማኅበራዊ ተጠቃሚነቱን አሳይቷል።
የመደመር እሳቤ በኢትዮጵያ ከተሞች የታየው ለውጥ የግንባታ ሥራዎች ውጤት ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚያዊ ብልጽግናን፣ ማኅበራዊ አካታችነትን፣ አካባቢያዊ ዘላቂነትን እና የዜጎችን ኑሮ ጥራት በአንድነት የሚያሳድግ መዋቅራዊ ሽግግር ነው።
ይህ ጉዞ በሁሉም የሀገሪቱ ከተሞች በስፋት ተጠናክሮ ሲቀጥል፣ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪ፣ ለዜጎቿ ምቹ እና ለቀጣይ ትውልድ ጠንካራ መሠረት የጣለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ወሳኝ ዓምድ ሆኖ ይቀጥላል።
በዮናስ ጌትነት

27 days ago
ኢትዮጵያውያን ለመነጋገርና ለመደማመጥ በአንድነት መሰባሰባቸው ትልቅ ምዕራፍ ነው!
- ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለሚያካሂደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በመዘጋጀት፣ ለተሳታፊ ተመካካሪዎች የቅድመ ምክክር ገለጻ በአድዋ ድል መታሰቢያ እየሰጠ ነው።
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ኢትዮጵያውያን ስለ ሀገራቸው ሰላም፣ ሀገር ግንባታ፣ ሰብዓዊ መብት፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችና ሌሎች ወሳኝ ጉዳዮች ለመነጋገርና ለመደማመጥ በአንድነት መሰባሰባቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር መስፍን አክለውም፣ ሀገሪቱ በአንድነትና በመተባበር ነፃነቷን እንዳስጠበቀች ሁሉ፣ ዛሬም በረጅም የመንግሥት ግንባታ ሂደት የተፈጠሩ አለመግባባቶችንና ቁርሾዎችን በውይይት ለመፍታት መሰባሰቧ ከችግሮች ለመውጣት ያለውን ፅኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዛሬው መርሃ ግብር ኮሚሽኑ ምክክሩ በሚመራበት ስልት፣ ተሳታፊዎች በሚኖራቸው ሚና እና በምክክሩ መርሆዎች ዙሪያ ሰፊ ገለጻ ሰጥቷል። በዚህም አካታችነት፣ አሳታፊነት፣ ትብብር፣ እኩልነት፣ መልካም ግንኙነት ግንባታ፣ የጋራ አስተሳሰብን ማጎልበት እና ሰፊ ስምምነትን መፈለግ እንደ መሠረታዊ እሴቶች ቀርበዋል።
በተጨማሪም የምክክር ሂደቶች፣ የቡድን አደረጃጀት፣ የጊዜ ሰሌዳ እና የተሳታፊዎች ኃላፊነት ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፣ ይህ መድረክ ወደ ሀገራዊ መግባባት ለመድረስ የሚደረገውን ሂደት በይፋ ያስጀመረ መሆኑ ተገልጿል።
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus

የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ለሁለንተናዊ ብልጽግና…
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የዲጂታል ገንዘብ ዝውውርን የሁለንተናዊ ብልጽግናዋ ወሳኝ ምሰሶ አድርጋ እየተከተለች ትገኛለች።
አስደናቂ የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምዕራፍ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በጥሬ ገንዘብ ላይ ከተመሰረተ አሰራር ወጥታ በዲጂታል ምህዳር በየዓመቱ በትሪሊየን የሚቆጠር የገንዘብ ዝውውር ወደሚከናወንባት ሀገር ተቀይራለች።
የመሰረተ ልማት መስፋፋትና የቴሌኮም ዘርፉ ማደግ ደግሞ ለተመዘገበው አስደናቂ ለውጥ ግንባር ቀደም ኃይል ነው፡፡
የሀገሪቱ የቴሌኮም ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 87 ነጥብ 9 ሚሊየን በማደጉ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቱ 99 ነጥብ 8 በመቶ የሕዝብ ተደራሽነትን እንዲያገኝ አስችሎታል።
ከዚህም በላይ የ4ጂ እና የ5ጂ መስፋፋት ለዲጂታል ክፍያ ሥርዓቱ መፋጠን አስተማማኝ መሰረት ጥሏል።
በዚህ የዲጂታል ምህዳር ውስጥ የላቀ ስኬት ያስመዘገበው የኢትዮ ቴሌኮም ‘ቴሌብር’ መተግበሪያ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ቁጥር 58 ሚሊየን አድርሷል፡፡
ቴሌብር ብቻውን ከ58 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን በማፍራት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን፤ እስካሁን ድረስ ከ6 ነጥብ 88 ትሪሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር አስተናግዷል፡፡
ይህ መተግበሪያ ከገንዘብ ማስተላለፍ ባለፈ ለዜጎች የብድር አገልግሎት በመስጠት ለፋይናንስ አካታችነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡
በሞባይል የሚደረገው የገንዘብ ዝውውር በጥሬ ገንዘብ ከሚደረገው መብለጡ የሽግግሩን ጥልቀት ያሳያል።
ይህ የፋይናንስ ዘርፍ ዘመናዊነት የግብይት ወጪን በመቀነስና ለዜጎች ምቾትን በመፍጠር ብቻ የሚገደብ ሳይሆን የፋይናንስ ደህንነትንና ግልጽነትን በማረጋገጥ ረገድ የጎላ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
የፋይናንስ ተቋማትን አሰራር በማዘመንና ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓቶችን በመዘርጋት፤ በሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና በማጭበርበር ወንጀል ሊመዘበር የነበረ በቢሊየን የሚቆጠር ሃብት ማዳን ተችሏል።
እንዲሁም የወንጀል ተጠርጣሪዎች የሚንቀሳቀሱባቸው የባንክ ሂሳቦች እንዲታገዱ በማድረግ ደኅንነቱ የተጠበቀ የኢኮኖሚ ሥርዓት ለመገንባት ትልቅ አቅም ሆኗል።
አጠቃላይ የዲጂታል ሽግግሩ አሁን ላይ ከመሰረተ ልማት ዝርጋታ ባለፈ ወደ ተጨባጭ ድርጊትና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወደሚመራ አስተዳደር እየተሸጋገረ ነው፡፡
የፋይዳ መታወቂያ ደግሞ ለዜጎች ቀልጣፋ አሰራርን በማበርከት ረገድ ትልቅ አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል።
መንግሥት እየተገበረ የሚገኘው የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የተጀመረውን ስኬት ይበልጥ ዘላቂና ሁሉን አቀፍ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።
ይህ የዲጂታል ክፍያና የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ዘመናዊነት ሀገሪቱ በግብርና፣ በኮንስትራክሽን፣ በቱሪዝም እና በሌሎችም ቁልፍ የልማት መስኮች ለጀመረችው የብልጽግና ጉዞ የማይናወጥና አስተማማኝ የፋይናንስ የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል።

29 days ago
የዘመናት የፖለቲካ ስብራቶችን የመጠገን ሀገራዊ ተስፋ
**********************
ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ ታሪካዊ ፈተናዎችን፣ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን በጋራ የመመካከር ባህልና "ከዛፍ ሥር" በመቀመጥ የመፍታት የዳበረ የዘመን አይሽሬ እሴት አላቸው። አሁን የተጀመረው አገራዊ ምክክርም ይህንን የትናንት እርሾ መሠረት ያደረገ ትልቅ ሀገራዊ ተስፋ ነው።
ባለፉት ዓመታት የተፈጠሩ የፖለቲካ ስብራቶችን፣ የትርክት መዛነፎችንና የሰላም እጦቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ የታጠቁ ቡድኖችንና ተደማጭነት ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ሙሉ በሙሉ በማሳተፍ ረገድ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች በነበሩ ግጭቶች ሳቢያ የመረጃ አሰባሰብ ፈተናዎች ቢያጋጥሙትም፣ ሂደቱን በቁርጠኝነትና በትዕግሥት በማለፍ አሁን ላይ ለታላቁ ሀገራዊ ጉባኤ የመጨረሻ ምዕራፍ ዝግጅቱን አጠናቋል።
ይህ ታሪካዊ ሁነት የሃሳብና የውክልና አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ ዜጎች አጀንዳዎቻቸውን በነፃነት እንዲያቀርቡና እንዲደማመጡ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፤ ሂደቱ ፍጹም ግልጽ፣ ገለልተኛና አሳታፊ በሆነ መንገድ መመራቱ ለዘመናት የተንከባለሉ ውስጣዊ ችግሮችን በመፍታት ረገድ የሕዝቡን ከፍተኛ ተሳትፎና ትኩረት ሊስብ ችሏል።
ኮሚሽኑ ታሪካዊውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለመጀመር የሚያስችሉትን ዘርፈ-ብዙ የዝግጅት ሥራዎች በስኬት ማጠናቀቁን ተከትሎ፣ ከሀገሪቱ አራቱም አቅጣጫዎች የተወከሉ የጉባኤው ተሳታፊዎች ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።
ኮሚሽኑ ወደ መፍትሔ የሚወስድ ድልድይ በመሆን በርካታ ፈተናዎችንና ውጣ ውረዶችን ተቋቁሞ፣ አብረውት ለዘለቁት ኢትዮጵያውያን የልፋቱን ፍሬ ለማስረከብ አሁን በዋዜማ ላይ ይገኛል። መላው የሀገሪቱ ሕዝቦች በከፍተኛ ተስፋ የሚጠባበቁት ይህ ታላቅ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በመጪው ሐምሌ 8 ይጀመራል፡፡
ይህ ታሪካዊ የምክክር ሂደት በዜጎች መካከል መተማመንን ለመፍጠር፣ የፖለቲካ ሥርዓቱን ለማሻሻል፣ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ-መንግሥት ለመገንባት እንዲሁም የግጭትና የጦርነት እሳቤዎችን በዘላቂነት ለመፍታት ከፍተኛ ፋይዳ አለው። ይሁን እንጂ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው ሕዝቡ ራሱ የሂደቱ ባለቤትና ጠባቂ ሲሆን፣ ከመንግሥት ወገን የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች የበሰለ ተሳትፎ እንዲሁም ከሌሎች የፖለቲካ ተሳታፊ አካላት የሰላም አማራጭን የመምረጥ ቁርጠኝነት ሲታከልበት ነው።
በብሌን ደምበሎ

1 month ago
የ“እኔ እበልጥ” ትርክት ስብራትን በተጨባጭ እየጠገነ ያለው የ“መደመር” አካታች እሳቤ
*****************************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ “እኔ እበልጣለሁ የሚል አግላይ አስተሳሰብ የዘመናት ድህነታችን ምንጭ ነው፤ ከዚህ ወጥተን እንደ አንድ ዜጋ ልንተባበር ይገባል” በማለት የችግራችንን መሠረት አስቀምጠዋል።
ይህ የበላይነት ስሜት እና አግላይ አስተሳሰብ የዜጎችን ማኅበራዊ እና ጂኦግራፊያዊ እንቅስቃሴ በመገደብ ሀገራዊ የገበያ ትስስርን የሚያደናቅፍ መዋቅራዊ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል።
የፖለቲካ ሥልጣንን እንደ ዜሮ-ድምር ፍልሚያ በሚቆጥር እሳቤ ውስጥ መኖር፣ ሀገራዊ ትብብርን እና የሰው ሀብት ልማትን በእጅጉ ይጎዳል።
ይህን ሥር የሰደደ አግላይ ትርክት ለመቀልበስ የለውጡ መንግሥት የ“መደመር” እሳቤን በማራመድ ዜሮ-ድምር የሆነውን የፖለቲካ ፉክክር በአካታች ሀገራዊ አንድነት ለመተካት እየሠራ ይገኛል።
ይህም ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርባምንጭ ከተማ ባደረጉት ንግግር በግልጽ ተንጸባርቋል።
በወቅቱም፣ እውነተኛ የብልጫ መለኪያ ተጨባጭ ወቅታዊ ሥራ እና ምርታማነት እንጂ ስም ወይም ታሪክ እንዳልሆነ አበክረው ገልጸዋል።
ሰላምን እንደ ኢኮኖሚያዊ እሴት በመቁጠር ቱሪስቶችን መንከባከብ፣ ሌብነትን መጸየፍ እና አካባቢን ማጽዳት ለጋራ ብልጽግና ወሳኝ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
ሀገራዊ አንድነትን እና አካታችነትን ወደ ተጨባጭ ሀብት ለመቀየርም መንግሥት በ“ገበታ” ፕሮጀክቶች እና በብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ ሪፎርም በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ከእነዚህም መካከል ከ1 ሺህ 300 በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችለው እና በአርባ ምንጭ ሐይቅ ላይ 360 ዲግሪ የሚሽከረከር ሬስቶራንትን ያካተተው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት አንዱ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደጠቀሱት፣ ከዚህ ቀደም አንድ የውጭ ባለሀብት አካባቢው ለቅንጦት ልማት ዝግጁ አይደለም ብሏቸው የነበረ ቢሆንም፤ መንግሥት የሀገር ውስጥ አቅምን በማስተባበር ይህን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሪዞርት እውን ማድረግ ችሏል።
ይህ ደግሞ ከመገፋፋት እና "እኔ እበልጥ" ከመባባል ይልቅ፣ ሀገራዊ አቅምን በማስተባበር ተዓምር መፍጠር እንደሚቻል ማሳያ ነው።
ከአርባምንጭ በተጨማሪ በሐዋሳ፣ በቢሾፍቱ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳር፣ በአፋር እና በደንዲ የተሠሩት ግዙፍ የመሠረተ ልማት እና የቱሪዝም ፕሮጀክቶች በሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገትን እኩል ለማዳረስ ያለሙ ናቸው።
እነዚህ ሥራዎች የሚያሳዩት “እኔ እበልጥ” ከሚል አግላይ ፖለቲካ ወጥተን በጋራ ስንቆም የውጭ ማረጋገጫ ሳያስፈልገን የሀገራችንን እምቅ ሀብት ወደ ተግባር መቀየር እንደምንችል ነው።
እውነተኛው የሀገር ግንባታ የሚጀምረው ከእያንዳንዳችን የዕለት ተለት ተግባር ነው። አዎ፣ ሁላችንም በሕይወታችን፣ በሥራ ገበታችን እና በማኅበራዊ መስተጋብራችን "እኔ እበልጥ" ከሚል አግላይ አስተሳሰብ ወጥተን ሀገራችንን ለመገንባት መነሳት አለብን።
ትልቅ አቅም ያለን ሕዝቦች ነን፤ ከተባበርን እና አቅማችንን ካስተባበርን ልንደርስበት የማንችለው ከፍታ የለም።
የምታኮራ እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ዛሬውኑ በመደመር መንፈስ መነሳት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆን አለበት፡፡
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #medemer #dineforgeneration #tourism #development #ebc

በውይይት የምትጸና ሀገር፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለቀጣዩ ትውልድ የተሰናዳ የሰላም ቅርስ
**************
የኢትዮጵያን የቆዩ ታሪካዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት ከጠመንጃ ድምፅ ይልቅ የሰለጠነ ውይይትና ምክክር ብቸኛውና ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ አማራጭ መሆኑ አጠያያቂ አይደለም።
"በውይይት ብቻ የምትጸና ሀገር" የሚለውን እሳቤ እንደ መርህ በማንገብ ወደ ሥራ የገባውና በየደረጃው የሕዝብ አስተያየትና አጀንዳ በማሰባሰብ ከመጨረሻው ምዕራፍ የደረሰው ሀገራዊ ምክክር ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለሰለጠነ ፖለቲካዊ ባህል ግንባታ እና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ምስረታ ዋስትና የሚሆን ታሪካዊ ሁነት መሆኑ ተመላክቷል።
ይህንን ሀገራዊ ምክክር ከሌሎች የቀደሙ ውይይቶችና ንግግሮች ልዩ የሚያደርገው አንዱና ዋናው ነገር ከዚህ ቀደም በፖለቲካ ተዋናዮች ብቻ ይታጠር የነበረውን አሠራር በማስፋት በየደረጃው የሚገኘውን ሕዝብ ከሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ያሳተፈ መሆኑ ነው።
ሂደቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከታዋቂ ግለሰቦች አልፎ አርሶ አደሩን፣ ወጣቱን፣ ሴቶችን፣ የሃይማኖትና የሀገር ሽማግሌዎችን እንዲሁም ልዩ ትኩረት የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ሁሉ ያካተተ ሲሆን፤ እያንዳንዱ የማኅበረሰብ ውይይትና የአጀንዳ ቀረጻ ሂደት በየጊዜው ለሕዝብ ይፋ መደረጉ የሂደቱን ግልጸኝነትና የጋራ አመኔታ ያረጋግጣል።
ኮሚሽኑ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ አሳታፊነትንና አካታችነትን ግንባር ቀደም መርሆቹ በማድረግ ከቀዳሚ የሕብረተሰብ ክፍል ጀምሮ በክልል ደረጃ የተዋቀሩ ማኅበራትን፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እና የሲቪክ ማኅበራትን በማሳተፍ የምክክሩ ባለቤት ሕዝብና ተቋማት እንዲሆኑ ጠንካራ መሠረት ጥሏል።
ታሪክ እንደሚያስተምረው በውስጣዊ ግጭትና በፖለቲካ ልዩነት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለፉ እንደ ቱኒዚያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኮሎምቢያ ያሉ ሀገራት ከመፈራረስ አደጋ ለመዳን የተጠቀሙበት ዋናው መሣሪያ "ሀገራዊ ምክክር" መሆኑ ይታወቃል።
የቱኒዚያው "ሀገራዊ የውይይት ስብስብ" ሀገሪቱን ከእርስ በርስ ጦርነት ታድጎ ለኖቤል ሰላም ሽልማት ያበቃ ሲሆን፣ የደቡብ አፍሪካው የ"እውነትና እርቅ ኮሚሽን" ያለፈውን በደል በይቅርታ በመሻገር ለአዲሲቷ ዲሞክራሲያዊት ደቡብ አፍሪካ መሠረት ጥሏል።
እንዲሁም ለአምስት አስርት ዓመታት የዘለቀውን የኮሎምቢያ ግጭት በድርድር መፍታት መቻሉ ምክክር የረጅም ጊዜ ትዕግስትና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ የጥንካሬ መገለጫ መሆኑንና ሰላም የውይይት እንጂ የግዳጅ ውጤት አለመሆኑን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተሞክሮነት አሳይቷል።
በአንጻሩ ምክክርን ችላ ያሉና የልዩነት ድምፆችን ያፈኑ ሀገራት በቀላሉ ወደ ደካማ መንግሥትነትና መፈራረስ እንደሚያመሩ የታየ በመሆኑ፣ ሀገራዊ ምክክር የሰላም አማራጭ ብቻ ሳይሆን የህልውና ዋስትና መሆኑ ይነገራል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የፖለቲካ ውይይት ብቻ ሳይሆን ሀገራችን በታሪኳ ያሳለፈቻቸውን የተዛቡ ትርክቶች እና የፖለቲካ ቁርሾዎች በውይይት በመፍታት ለቀጣዩ ትውልድ ሰላማዊና የተረጋጋች ሀገርን ለማስረከብ የሚደረግ ታሪካዊ የይቅርታና የመግባባት ጉዞ ነው።
ይህ ሂደት ትውልዱ ከጥላቻ ፖለቲካ ወጥቶ በጋራ እሴቶች ላይ እንዲታነጽና የውይይት ባህልን እንዲያዳብር የሚያስችለው ሲሆን፣ በተለይም ወጣቱ ትውልድ ጉልበቱን ለግጭት ሳይሆን ለፈጠራ፣ ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታና ለሳይንሳዊ ዕድገት እንዲያውል ዕድል የሚፈጥር ነው።
በጥቅሉ በሕዝቦች መካከል የጋራ መግባባትን በመፍጠር የዜግነት ክብርን የሚያሳድገውና በጋራ ሕልም ዙሪያ የሚተጋ ትውልድ የሚቀርጸው ይህ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፣ መላውን ሕዝብ ከክክፍል ወደ አንድነት፣ ከጥርጣሬ ወደ መተማመን እና ተስፋ የሚያሸጋግር ታላቅ ብሔራዊ ሁነት መሆኑ ተመላክቷል።
በብሌን ደምበሎ
#ethiopianbroadcastingcorporation #nationaldialogueethiopia #nationalconsultation #peaceandunity #inclusivedialogue

የኢትዮጵያ አዲሱ የዲጂታል ዘመን ስኬቶች
*************
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በቴሌኮሙኒኬሽን ዘርፍ እያስመዘገበች ያለችው ፈጣን ዕድገት ከተበታተኑ አሠራሮች ወጥታ የተቀናጀ የኢኮኖሚ መሠረት እንድትጥል እያስቻላት ይገኛል።
የቴሌኮም ዘርፉን በማዘመን እና ለገበያ ክፍት በማድረግ የተጀመረው ይህ ጉዞ ሀገራችንን ወደ ላቀ የዲጂታል ዘመን እያሸጋገራት ነው።
የመሠረተ ልማት እና የክፍያ ሥርዓት አብዮት
በቅርብ ዓመታት የቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር ከ37.9 ሚሊዮን ወደ 85 ሚሊዮን በላይ መድረሱ ለሀገራዊው የዲጂታል ትሥሥር እና ለገበያ ተሳትፎ የማይናወጥ መሠረት ጥሏል።
የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት መስፋፋት ደግሞ ሌላው ታሪካዊ ስኬት ነው። ከዚህ ቀደም በውል የማይታወቀው ዓመታዊ የዲጂታል ግብይት መጠን አሁን ላይ ወደ 24.2 ትሪሊዮን የኢትዮጵያ ብር ከፍ ብሏል።
ይህ ግዙፍ አሃዝ በጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሠረተውን ግብይት በመቀነስ ግልጽነትን የፈጠረ ሲሆን፣ ለፖሊሲ አውጪዎች ግልጽ የሆነ እና የታለመ የፋይናንስ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ምቹ ሥርዓት ፈጥሯል።
አካታችነትን ያረጋገጠው ዲጂታል መታወቂያ
የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት የዜጎችን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ በማሳደግ በኩል ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ነው።
ይህ ፕሮጀክት ከባዶ ተነሥቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ46.4 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን መመዝገብ ቸሏል።
ፋይዳ በገበያ የሚጠየቀውን የምዝገባ እና የማረጋገጫ ወጪዎችን በእጅጉ በመቀነስ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።
አስተማማኝ የማንነት ማረጋገጫ በመስጠትም የፋይናንስ አካታችነትን ይበልጥ እውን እያደረገ ነው።
ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ አቅም እና የወደፊቱ ራዕይ
በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት ታቅዶ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተሳካው የ"5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች" ኢኒሼቲቭ የዲጂታል ኢትዮጵያን መጻኢ ተስፋ ያረጋገጠ ነው።
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከተጀመረበት ጊዜ አንሥቶ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ 5 ሚሊዮን 5 ሺህ 146 ሰልጣኞች ተመዝግበዋል።
ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለውን የምስክር ወረቀት አግኝተዋል።
ይህ በዲጂታሉ ዓለም የተጀመረው ታሪካዊ ምዕራፍ የጉዞው ማብቂያ ሳይሆን ብሔራዊ ራዕይን ይበልጥ ማፋጠኛ መነሻ ነው።
በመሆኑም እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም ድረስ የሠልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ አዲስ ግብ ተሰንቋል።
በተለይም ወጣት ተማሪዎች የክረምቱን ወቅት በዋዛ ከማሳለፍ ይልቅ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጠውን ይህንን ሥልጠና በመውሰድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያላቸው የዲጂታል መሪዎች እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
እነዚህ ሁሉ እመርታዎች ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ የዲጂታል ኢኮኖሚ ፉክክር ውስጥ ተወዳዳሪ ብቻ ሳትሆን መሪም እንድትሆን የሚያደርጓት ጽኑ መሠረቶች ናቸው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #digitalethiopia #digitaltransformation #techinnovation

የዲጂታል ኢኮኖሚው አብዮት፤ ቴሌብር 5ኛ ዓመት
#fastmereja | የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥርዓት በቴክኖሎጂ ያዘመነው እና በዲጂታል ክፍያ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የከፈተው "ቴሌብር" አገልግሎት መስጠት ከጀመረ 5 ዓመታት ተቆጠሩ። ኩባንያው በተለይም የገንዘብ ዝውውርን ፈጣንና ተደራሽ በማድረግ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ከዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ጋር አስተሳስሯል።
ላለፉት አምስት ዓመታት ቴሌብር በኢትዮጵያ የገበያ ሁኔታ ውስጥ ትልቅ የለውጥ ኃይል ሆኖ ቆይቷል። በተለይም በባንክ አገልግሎት ያልተደራሱ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በዲጂታል መረብ ውስጥ በማካተት የፋይናንስ አካታችነትን (Financial Inclusion) በከፍተኛ ደረጃ አሳድጓል። በጥሬ ገንዘብ ይፈጸሙ የነበሩ የዕለት ተዕለት ግብይቶች፣ የፍጆታ ክፍያዎች እና የገንዘብ ልውውጦች ዛሬ በቴሌብር አማካኝነት በሰከንዶች ውስጥ የሚከናወኑበት ዕድል ተፈጥሯል።
ቴሌብር በዘርፉ ባስመዘገበው ፈጣን እድገት፣ ከአገልግሎት ክፍያ ባሻገር ብድርን እና ቁጠባን የሚያካትቱ ውስብስብ የፋይናንስ መፍትሔዎችን በማቅረብ የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ዋና አከርካሪ ሆኗል። በተለይ በገጠር እና በከተማ መካከል ያለውን የገንዘብ ፍሰት በማቀላጠፍ፣ ለአነስተኛ ነጋዴዎች እና ለግለሰቦች አስተማማኝ የግብይት አማራጭ ሆኖ ተገኝቷል።
በአምስት ዓመታት የሥራ ጉዞው ቴሌብር በርካታ ፈተናዎችን በመሻገር፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አቅሞችን በመዘርጋት እና ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመዋሃድ የተጠቃሚዎቹን ቁጥር ወደ አስደናቂ ደረጃ ከፍ አድርጓል።
ወደፊት በሚኖረው ጉዞ፣ ቴሌብር ከዲጂታል ክፍያ ባለፈ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ሥርዓት ወደ ላቀ የቴክኖሎጂ ደረጃ ለማሸጋገር እና አለም አቀፍ የክፍያ ሥርዓቶችን ለመቀላቀል ትኩረት እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ይህ የ5 ዓመት ጉዞ ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ያላትን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ እንደሆነ ታዛቢዎች ይገልጻሉ።

የጠረጴዛ ዙሪያ ብስለት፦ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም መሠረት
**************************
(የዕለቱ መልዕክት)
የአንድ አገር ታላቅነትና የሕዝቦቿ ስልጣኔ የሚለካው በትጥቅ ኃይል የበላይነት ወይም በጦር ሜዳ ጊዜያዊ ድል ሳይሆን ውስብስብና ስር የሰደዱ የታሪክ መዋቅራዊ ቀውሶችን በሰለጠነ መንገድ፣ በጠረጴዛ ዙሪያ የመፍታት ብስለት ሲታይ ብቻ ነው።
ዛሬ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የፖለቲካ አዙሪቶችን፣ የታሪክና የትርክት ጽንፎችን እንዲሁም የማንነትና የፍትህ ጥያቄዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የምታደርገው አገራዊ ምክክር፣ አዲስና ሁሉን አቀፍ "ማህበራዊ ውል" ለመፈረም የተዘረጋ ታሪካዊ መድረክ ነው።
ይህ ታላቅ ሂደት አሁን ላይ የደረሰበት የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍና ለሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የተደረገው መጠነ ሰፊ ዝግጅት፣ አገራችንን ለዘመናት ከተጋረጠባት የጥርጣሬ፣ የርስ በርስ መናቆርና የፖለቲካ ክስረት አዙሪት አውጥቶ ወደ አዲስ ብሔራዊ መግባባት የሚያሸጋግር ብርቅዬ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።
የዚህ ምክክር ዋነኛ ስኬት የሚለካው፣ አንዱ አሸንፎ ሌላው የሚጠፋበትንና "አሸናፊው ሁሉንም ይወስዳል" የሚለውን አሮጌና አውዳሚ የፖለቲካ ባህል በጋራ አገራዊ መግባባት መተካት ሲቻል ነው።
ይህም ማለት የጋራ ታሪክንና ስብጥር የብሔር ማንነቶችን በትውውቅና በመከባበር አጣጥሞ፣ የትኛውንም ማህበረሰብና የፖለቲካ ኃይል የማያገል፣ ሁሉንም ዜጋ እኩል ተጠቃሚና ባለቤት የሚያደርግ ጠንካራ የሀገረ-መንግስት ግንባታ መርሆዎችን በጽኑ መሠረት ላይ መቅረጽ ማለት ነው።
የሰላም እውነተኛው ኃይል የሚገኘው በጠመንጃ አፈሙዝ ሳይሆን የልዩነት ድምፆችን አዳምጦ አብሮ የመኖርን ጥበብ በሚኖረዉ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ውስጥ ነው።
በመሆኑም በትጥቅ ትግልና በአመጽ ስልጣን ለመያዝ የሚደረገው አውዳሚ አካሄድ አክትሞለት፣ የታጠቁ ኃይሎች ጭምር ልዩነቶቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታትና በሂደቱ ላይ እምነት እንዲጥሉ ማድረግ የምክክሩ ህያውና ተንቀሳቃሽ መንፈስ ሊሆን ይገባል።
ይህ ታሪካዊ ሂደት የዘላቂ ሰላምና የመረጋጋት መሠረት ከመጣል ባለፈ የሕግ የበላይነት የነገሰባት፣ የሰብዓዊ መብቶች የተከበሩባትና የፍትህ ስርዓት ማሻሻያዎችን የምትወልድ አዲስ አገር ለመገንባት ወሳኝ ግብዓት ነው።
የምክክሩ የመጨረሻ ውጤታማነትና ፍሬያማነት የሚለካው በሦስት ዋና ዋና ማዕዘናት ላይ ነው፤ እነሱም በመጀመሪያ ሂደቱ በዜጎችና በሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ዘንድ ሙሉ እምነትና ተአማኒነት እንዲኖረዉ መደረጉ ነዉ፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ከዳር እስከ ዳር የትኛውንም የህብረተሰብ ክፍል ሳያገልሉ የሁሉም ድምፅ የሚሰማበት አካታችነት መረጋገጡ ነዉ።
በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ከፖለቲካ ቃል ኪዳን ባለፈ በቀጠይ ስምምነት በሚደረስባቸዉ ነጥቦች ላይ የሚታይና መሬት የሚረግጥ እውነተኛ ተግባራዊ አፈጻጸምም ያስፈልጋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የዚህ ታላቅ ውሳኔና የታሪክ ባለቤት እንዲሆን አሁን ላይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ የፖለቲካ ኃይሎች ቅንነት፣ ሆደ-ሰፊነትና እውነተኛ የፖለቲካ ቁርጠኝነት የታሪክ ግዴታ ሆኖ ቀርቧል።
ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ በአግባቡ መጠቀም ካልቻልን ለትውልድ የሚተርፍ የታሪክ ተጠያቂነትና የህሊና ጠባሳ እንደሚያጋጥመን ተገንዝበን ለዘላቂ ሰላምና ለዲሞክራሲያዊ ሽግግር ሁላችንም የድርሻችንን በሃላፊነት ልንወጣ ይገባል።
አገራዊ ምክክሩ የነገዋን የበለጸገችና የተረጋጋች ኢትዮጵያን የሚንገነባበት መሰረት የሚጥል ይሆናል፡፡
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
Ethiopian Broadcasting Corporation

2 months ago
ኮሚሽኑ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የመገናኛ ብዙኃን የንቅናቄ ዘመቻ አስጀመረ
*************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን ለማሳካት የሚያስችል የንቅናቄ ዘመቻ ለመጀመር በኢትዮጵያ ከሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሞያዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር፣ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም እና ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር) መገናኛ ብዙሀን ከኮሚሽኑ ጋር በመስራት እስካሁን ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።
ቀጣዩ ሀገራዊ ጉባኤ ከቅድመ ጉባኤ ጀምሮ ጥንቃቄ የተሞላበት የአዘጋገብ ስልት ስለሚጠይቅ ይህንን ለማስገንዘብ እና ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ለመጀመር መድረኩ መዘጋጀቱን አክለዋል።
መገናኛ ብዙሀን የሀገራዊ ምክክሩን ሂደት ሲዘግቡ በአካታችነት መርሁ መሰረት የሁሉንም ዜጎች ድምፅ በማካተትት፣ የኮሚሽኑን ነፃና ገለልተኛ አሰራር በመጠበቅ እንዲሁም ዘላቂ ሰላምና መግባባት ለመፍጠር በሚያግዝ መልኩ መሆኑን እንዳለበት ነው አፅንኦት ሰጥተው ያስገነዘቡት።
ከቅድመ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ እስከ ድህረ ጉባኤ መገናኛ ብዙኃን ትክክለኛ፣ ሚዛናዊ እና ተደራሽ መረጃ በማቅረብ ሚናቸውን እንዲወጡም አክለዋል።
በመድረኩ የመወያያ ፅሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ሀላፊ ዮሀንስ ሽፈራው (ዶ/ር) ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመጥቀስ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን መገናኛ ብዙሀን ሊከተሏቸው የሚገቡ የአዘጋገብ ስልቶችና ሙያዊ ስነምግባሮችን አመላክተዋል።
የመገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች በበኩላቸው የሀገራዊ ምክክር ሂደቱን ለሕዝብ በስፋት ለማስተዋወቅና በሂደቱ ዙሪያ የሚቀርቡ መረጃዎች ተዓማኒነት እንዲኖራቸው በትኩረት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።
በዕለቱ ኮሚሽኑ በራሱ የውስጥ አቅም ያዘጋጃቸውን 15 የክልል የምክክር መድረክ ዘጋቢ ፊልሞች፣ 19 የቴሌቪዥንና የማህበራዊ ሚዲያ የቅስቀሳ መልዕክቶችን፣ 6 የሬዲዮ መልዕክቶችን እንዲሁም በልዩ ልዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ አጫጫር መልዕክቶችን ለሚዲያ አመራሮቹ አስረክቧል።
ኮሚሽኑ ያስረከባቸው መልዕክቶች መገናኛ ብዙኃኑ በራሳቸው አቅም ከሚያዘጋጇቸው ተጨማሪ ሆነው እንደ ግብዓት እንደሚያገለግሉ ተነግሯል።
መልዕክቶቹን ከመጪው ሰኞ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ በስፋት ወደ ሕዝብ ለማድረስ በኮሚሽኑና በመገናኛ ብዙሀኑ መካከል መግባባት ላይ ተደርሷል።
በዚህ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ ከ80 በላይ የቴሌቪዥን፣ የሬዲዮና የሕትመት ሚዲያ አመራሮችና ከፍተኛ ባለሞያዎች እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮሚ፣ የትምህርት፣ የጤና እና የትራንስፓርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የኮሙኒኬሽን ሀላፊዎች እና የተለያዩ የክብር እንግዶች ተሳትፈዋል።
ኮሚሽኑ ባለፈው ሳምንት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 50 የማህበረሰብ መገናኛ ብዙሀን ሀላፊዎችንና ባለሙያዎችን ያገኘበት መድረክ አከናውኖ ተመሳሳይ የሚዲያ ንቅናቄ ዘመቻ ማስጀመሩ ይታወሳል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopiannationaldialoguecommission #nationaldialogue #mediacampaign #peaceandunity

የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር እመርታ
*********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ዓለማችን በቴክኖሎጂ እና በኢኖቬሽን ፈጣን ግስጋሴ ውስጥ ትገኛለች። ኢትዮጵያም ይህንን ዓለም አቀፋዊ እውነት በውል በመገንዘብ፣ ሁለንተናዊ ኢኮኖሚዋን ከመሠረቱ የሚቀይር ታሪካዊ የዲጂታል ሽግግር እያከናወነች ትገኛለች።
በተለይም ባለፉት ዓመታት ሀገራችን ያለባትን ዘላቂ የቢሮክራሲ እና የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመቅረፍ ዲጂታላይዜሽንን እንደ ዋነኛ ስትራቴጂያዊ መሣሪያ በመውሰድ በቁርጠኝነት እየሠራችበት ነው።
ይህ ጉዞ የሀገርን የልማት ምሰሶ በጠንካራ መሠረት ላይ የሚያጸና የመንግሥት የረጅም ጊዜ ራዕይ ማሳያ ነው።
በአንድ ወቅት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ሩቅ ሕልም ይታይ የነበረ ቢሆንም በ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂ በተከናወኑት መሠረታዊ ሥራዎች ዛሬ ውጤት መገኘት ችሏል።
አሁን ደግሞ የሀገራችንን የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥን እና ይበልጥ ስኬታማ የሚያደርገው “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” የተሰኘው ብሔራዊ ስትራቴጂ በትግበራ ላይ መዋሉ የሂደቱን ቀጣይነት ያረጋግጣል።
ከዚህ ጎን ለጎን የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በየተቋመት ጥቅም ላይ መዋል ለሚሰጠው አገልግሎት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል።
የ“ፋይዳ” ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምም ለጠቅላላው የዲጂታል ሥነ ምኅዳር ግንባታው መሠረት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
እስከ 90 ሚሊዮን ዜጎችን በሥርዓቱ ውስጥ ለማቀፍ የታቀደው ይህ ግዙፍ መርሐ ግብር ለባንክ፣ ለፋይናንስ፣ ለንግድ እንቅስቃሴ እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ ምሰሶ ነው።
የሀገርን የሰው ኃይል በዕውቀት ሳያደራጁ ዘላቂ ስኬትን ማሰብ ስለማይቻል፣ ከዚህ መሠረት ጋር ተያይዞ በ“ኢትዮ ኮደርስ” ኢኒሼቲቭ 5 ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና መጀመሩ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ የሚረከቡ ባለሙያዎችን ለማፍራት የተጣለ ታላቅ መሠረት ነው።
ይህ የዲጂታል መሠረት የዜጎችን እንግልት ወደሚቀንስ የሲቪል ሰርቪስ ዝማኔ በተግባር ተሻግሯል።
የአገልግሎት አሰጣጥን በዘመናዊ መልክ ለመቅረጽ በሁሉም አካባቢዎች እየተገነባ የሚገኘው “የመሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት የተንዛዛ ቢሮክራሲን በማስቀረት የመንግሥትን ግልጽነት እና ተጠያቂነት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል።
ይህ ዓይነቱ የተቀናጀ አሠራር ሙስና እና ብክነትን በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል አስተማማኝ ተቋማዊ አቅም እየፈጠረ ይገኛል።
በፋይናንስ ዘርፍም ቢሆን በዲጂታል የተከናወነው የግብይት ዋጋ 16 ትሪሊዮን ብር መድረሱ የዲጂታል ኢኮኖሚው ምን ያህል ውጤታማ እና ተደራሽ እየሆነ ለመምጣቱ ማሳያ ነው።
ይህ ስኬት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ አካታችነትን በተግባር አረጋግጧል።
ለወደፊቱም መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ፕላትፎርሞች ተደራሽ ለማድረግ የታቀደው ዕቅድ የሀገራችንን የነገ ገጽታ በእጅጉ የሚቀይር ነው።
መንግሥት የሳይበር ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ እና የስታርትአፕ ሥነ ምኅዳርን በማጠናከር፣ የዲጂታል ሽግግር ሂደቱን አስተማማኝ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ እያደረገው ይገኛል።
ይህ ታሪካዊ ጉዞ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚያቀልል፣ ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግ እና የኢኮኖሚ ልማታችንን ከሕልም ወደ እውነት የለወጠ የጋራ ብሔራዊ ስኬታችን በመሆኑ ሁሉም አካላት ለስኬቱ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ethiopia #ebc #digitalethiopia #ai #technology

የ5ቱ ዓመታት ገፆች፦ የኢትዮጵያ ዲጂታል ክፍያ ሥርዓት እመርታ እና የኢኮኖሚው አዲስ ምዕራፍ
*********************
ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገራችን የተከናወኑ መጠነ ሰፊ የዲጂታል መሠረተ ልማት ግንባታዎችና የፖሊሲ ማሻሻያዎች በኢትዮጵያ የክፍያ ሥርዓት ላይ ታላቅ አብዮት ፈጥረዋል።
"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" እና "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂዎች ይፋ ከሆኑ ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ከባህላዊው የጥሬ ገንዘብ ዝውውር ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ያደረገችው ሽግግር አስገራሚ ዕድገት አስመዝግቧል።
ቀደም ሲል በኦፕሬተር የሚመራ የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት ባለመኖሩ የጥሬ ገንዘብ ጥገኝነት መላቀቅ ተስኖ የነበረ ቢሆንም፣ የፖሊሲ ማሻሻያ ተደርጎ የኢትዮ ቴሌኮም "ቴሌብር" ወደ ሥራ መግባቱ ሁኔታዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀይሮታል።
ቴሌብር በሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ45 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራቱ የሀገራችንን የዲጂታል አቅም ለዓለም ያሳየ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሞባይል ዋሌት አካውንቶች ቁጥር 161 ሚሊዮን በላይ ደርሷል።
ይህም ከአጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር በላይ መሆኑ የአገልግሎቱን ተደራሽነት የሚያሳይ ሲሆን፣ በፕላትፎርሙ የሚከናወነው የገንዘብ ዝውውርም ከኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 82 በመቶ ደርሷል።
ይህ የዲጂታል ክፍያ አብዮት ለሀገራዊ ኢኮኖሚው በርካታ ጥቅሞችን እያስገኘ ይገኛል።
የመጀመሪያው የፋይናንስ አካታችነት ሲሆን፣ የባንክ አገልግሎት ባልደረሰባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ዜጎች በስልካቸው ብቻ ገንዘብ መቆጠብ፣ መላክ እና መቀበል በመቻላቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች ወደ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው እንዲገቡ አድርጓል።
በሌላ በኩል፣ መንግሥት እንደ ነዳጅ ግብይት፣ የትራፊክ ቅጣት፣ የግብር ክፍያ እና የውኃና መብራት አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ በማድረጉ ብክነትን በመቀነስ ገቢው በቀጥታ ወደ ካዝናው እንዲገባ አስችሏል፤ ለምሳሌ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል ብቻ መሆኑ ሕገ-ወጥ ዝውውርን በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል።
በተጨማሪም ብሔራዊ ባንክ ለገንዘብ ሕትመትና ጥገና የሚያወጣውን በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬ ለማዳን የተቻለ ሲሆን፣ የገንዘብ ምንጭና መድረሻው ስለሚታወቅ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመከላከልና የጥቁር ገበያን ለመቆጣጠር የተሻለ አቅም ተፈጥሯል።
ባጠቃላይ ይህ ዕድገት ወደ ዘመናዊ ኢኮኖሚ ለምናደርገው ጉዞ ትልቅ ሞተር እየሆነ ሲሆን፣ ዘርፉ በፖሊሲ መደገፉን መቀጠሉ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት የዲጂታል ምጣኔ ሀብት ተጠቃሚ ሀገራት ተርታ እንደሚያሰልፋት ይጠበቃል።
በላሉ ኢታላ
#digitalethiopia #telebirr #cashlesssociety #digitaleconomy #ethiopianbroadcastingcorporation Ethiopian Broadcasting Corporation

የዲጂታል ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ - ከስትራቴጂ ወደ ስኬት
***********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ዛሬ ዓለማችን በቴክኖሎጂ እና በኢኖቬሽን ፈጣን ግስጋሴ ውስጥ ትገኛለች። ኢትዮጵያም ይህንን ዓለም አቀፋዊ እውነት በውል በመገንዘብ፣ ሁለንተናዊ ኢኮኖሚዋን ከመሠረቱ የሚቀይር ታሪካዊ የዲጂታል ሽግግር እያከናወነች ትገኛለች።
በተለይም ባለፉት አምስት ዓመታት ሀገራችን ያለባትን ዘላቂ የቢሮክራሲ እና የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመቅረፍ ዲጂታላይዜሽንን እንደ ዋነኛ ስትራቴጂያዊ መሣሪያ በመውሰድ እየሠራችበት ትገኛለች።
ይህ ጉዞ የሀገርን የልማት ምሰሶ በጽኑ መሠረት ላይ የሚያጸና የመንግሥት የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለን እናምናለን።
በአንድ ወቅት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ሩቅ ሕልም ይታይ እንደነበር አይዘነጋም፤ ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑት መሠረታዊ ሥራዎች ግን ዛሬ ላይ ሊሻር በማይችል እውነታ ላይ የቆመ መሠረት ተጥሏል።
መንግሥት ያደረጋቸው ሰፊ የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያዎች “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂን በስኬት ለማጠናቀቅ አስችለዋል።
አሁን ደግሞ የሀገራችንን የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥን እና ይበልጥ ስኬታማ የሚያደርገው “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” የተሰኘው ብሔራዊ ስትራቴጂ ፀድቆ ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉ የሂደቱን ቀጣይነት ያረጋግጣል።
ከዚህ ጎን ለጎን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ለችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች መበልጸግ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩ የሚበረታታ እርምጃ ነው።
በዚህ ዘመናዊ የታሪክ እጥፋት ውስጥ የ“ፋይዳ” ብሔራዊ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም እና የ“ኢትዮኮደርስ” ኢኒሼቲቭ ሚና እጅግ የላቀ ነው።
የዲጂታል መታወቂያ ለኢኮኖሚው ግንባታ ልክ እንደ ቤት መሠረት ነው። እስከ 90 ሚሊዮን ዜጎችን በሥርዓቱ ውስጥ ለማቀፍ የታቀደው ይህ ግዙፍ መርሐ ግብር ለባንክ፣ ለፋይናንስ፣ ለንግድ እንቅስቃሴ እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ ምሰሶ ነው።
“የቆጠሩት እህል አያልቅም” እንደሚባለው የሀገርን የሰው ኃይል በዕውቀት ሳያደራጁ ዘላቂ ስኬትን ማሰብ አይቻልም። በመሆኑም በ“ኢትዮኮደርስ” ኢኒሼቲቭ 5 ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ክህሎት ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ የሚረከቡ ባለሙያዎችን ለማፍራት የተጣለ ታላቅ መሠረት ነው።
የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን በሁሉም አካባቢዎች እየተገነባ ያለው “የመሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎትም የተንዛዛ ቢሮክራሲን እና የዜጎችን እንግልት በማስቀረት የመንግሥትን ግልጽነት እና ተጠያቂነት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ሙስና እና ብክነትን በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል አስተማማኝ ተቋማዊ አቅም ይፈጥራል።
በፋይናንስ ዘርፍም ቢሆን በ2017 በጀት ዓመት ብቻ በዲጂታል የተከናወነው የግብይት ዋጋ 16 ትሪሊዮን ብር መድረሱ የዲጂታል ኢኮኖሚው ምን ያህል ውጤታማ እና ተደራሽ እየሆነ ለመምጣቱ ሕያው ማሳያ ነው።
ይህ ስኬት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች በቀላሉ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ አካታችነትን በተግባር አረጋግጧል።
ለወደፊቱም መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ፕላትፎርሞች ተደራሽ ለማድረግ የታቀደው ዕቅድ የሀገራችንን የነገ ገጽታ በእጅጉ የሚቀይር ነው።
መንግሥት የሳይበር ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ እና የስታርትአፕ ሥነ ምኅዳርን በማጠናከር፣ የዲጂታል ሽግግር ሂደቱን አስተማማኝ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ እያደረገው ይገኛል።
በአጠቃላይ ይህ ታሪካዊ ጉዞ የዜጎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚያቀልል፣ ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግ እና የኢኮኖሚ ልማታችንን ከሕልም ወደ እውነት የለወጠ የጋራ ብሔራዊ ስኬታችን በመሆኑ ሁሉም አካላት ለስኬቱ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ethiopia #ebc #digitalethiopia #5millioncoders #success #𝐃𝐢𝐠𝐢𝐭𝐚𝐥𝐄𝐜𝐨𝐧𝐨𝐦𝐲

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በሥርዓት እየተካሄደ ነው - የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ
#ethiopia | የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክን የሚመሩት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ መጀመሩን ገልጸዋ።
አሁሩ ኬንያታ በመራጮች ማዕከላት የተመለከቱትን ሁኔታ ሲገልጹ፣ የድምፅ አሰጣጡ ሂደቱ በሥርዓት እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ ቀኑን ሙሉ በተመሳሳይ መንፈስ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
"ድምፅ መስጠት ዜጎች የሚወክሏቸውን መሪዎች እና ተወካዮች በነፃነት የሚመርጡበት መሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብት ነው" ያሉት ኬንያታ፣ የአፍሪካ ኅብረት በአህጉሪቱ እውነተኛ ውክልና፣ አካታችነት እና ሕዝቦች የራሳቸውን መሪዎች የመምረጥ አቅም እንዲጠናከር እንደሚሠራ አስታውቀዋል።
በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የምርጫ ሂደቶች ፈተናዎች እንዳሉ ቢገልጹም፣ ከእያንዳንዱ ምርጫ በኋላ የተሻለ ዲሞክራሲያዊ ባህል ለመገንባት ዕድል እንዳለ ጠቅሰዋል።
"ኢትዮጵያ የዚህች ታላቅ አህጉር ዋና ከተማ ናት፤ በዚህች ሀገር የሚገኝ ስኬት በመላው አፍሪካ ውስጥ ይንጸባረቃል" ሲሉ የተናገሩት ኬንያታ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም ምኞታቸውን ገልጸው የምርጫው ሂደት በሥርዓት እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ያላቸውን እምነት አረጋግጠዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ebc #ethiopia #ebcdotstream #democracy #africanunion

የ54 ሚሊዮን ዜጎች ድምጽ፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲሱ አቅጣጫ
*******************
(የዕለቱ መልዕክት)
ለዘመናት የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጥርጣሬ ዉስጥ መኖሩ የአደባባይ ምስጢር ነው። ዛሬ ግን ያ የድሮው መንገድ አክትሞለታል። የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዋዜማ አዲስ ተስፋ ይዞልን መጥቷል፤ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተመዘገቡበት፣ በተለይ ደግሞ ከእነዚህም ዉስጥ ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ደግሞ በ“ምርጫዬ” ዲጂታል መድረክ ስማቸውን ያሰፈሩበት ይህ ሂደት፣ ሀገራችን ከጎዳና ጫጫታ ወደ ውይይት መድረክ፣ ከስሜት ወደ ዴሞክራሲያዊ ፉክክር መሸጋገሯን በግልጽ ያሳያል።
በዚህ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከ10 ሺህ በላይ እጩዎችና 80 የግል ተወዳዳሪዎች በአንድ የህግ ጥላ ስር ቆመው፣ በምርጫ ስነ-ምግባር ሕግ ተሳስረው ለመወዳደር መዘጋጀታቸው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መለያ ነው።
ይህ ምርጫ የአንድ ቀን የድምፅ መስጠት ተግባር ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የዴሞክራሲ ትርጉም ከፖለቲካ ልሂቃን ጠባብ አዳራሾች ወጥቶ ወደ ህዝብ ልብና ህሊና እየገባ መሆኑን የሚያበስር ብሔራዊ ንቅናቄ ነው።
ውድድሩ ከብሽሽቅ ወደ ፖሊሲ ክርክር አድጓል። በርካታ የሕዝብ ውይይት መድረኮች በአምስት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች ተዘጋጅተው መቅረባቸው አካታችነትን በተግባር ያሳየ፣ የተፎካካሪና የገዢ ፓርቲዎችን እኩልነት በገሃድ ያረጋገጠ፤ የተቋማዊ ብስለት የታየበት እርምጃ ነው።
ዓለም አቀፍ እና የሀገር ውስጥ ታዛቢዎችን በኩራት ጋብዞ፣ የአፍሪካ ህብረትንና የኢጋድን ታዛቢዎችን በማሳተፍ አፍሪካ የራሷን ጉዳዮች በራስ አቅም የመመልከት አቅሟን ያሳየችበት እንዲሁም በሰላማዊ መንገድ ምርጫን ለማካሄድ መነሳት ራሱ ትልቅ ታሪካዊ ድል ነው። እንደ ኡሁሩ ኬንያታ ያሉ የአህጉሪቱ አንጋፋ መሪዎች የታዛቢ ቡድኖችን ይዘው መግባታቸው የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ጥረት በአፍሪካ መድረክ ከፍ አድርጎታል።
መልዕክቱ ግልጽ ነው፤ ፖለቲካ በሀይል ሳይሆን በህዝብ ድምፅ፣ በስሜት ሳይሆን በውይይት፣ በመገለል ሳይሆን በብሔራዊ ተሳትፎ ሊመራ እንደሚችል በተግባር እያሳየን ነው።
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ትልቁ ድል የትኛው ፓርቲ አሸነፈ የሚለው ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዝብና ተቋማት በዴሞክራሲያዊ ብስለት ማሸነፋቸው ነው።
ይህ የዲጂታል ዘመን ትውልድ የሀገሩን እጣ ፈንታ በራሱ እጅ እየጻፈ ነው። የነገዋን የበለፀገችና የተረጋጋች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሁላችንም በሰላም፣ በህግና በውይይት መስመር ላይ እናጽና፤ ምክንያቱም የነጻነትና የፍትህ መሠረቱ የህዝብ ድምፅ ብቻ ነውና።
ኢትዮጵያ ትመርጣለች!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopiavotes #democracy #ethiopia

3 months ago
በምርጫው የወጣቶችና ሴቶችን ውክልና ለማረጋገጥ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የወጣቶችና ሴቶችን ውክልና ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው አሉ ምሁራን።
ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራን እንደገለጹት÷ በምርጫው ሂደት የወጣቶችንና ሴቶችን ውክልና ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አመራርና አስተዳዳር መምህር በዳሳ ፍራጃ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ጉዞ በተግዳሮቶች የታጠረ ቢሆንም መጪው ምርጫ ፍትሐዊ አስተዳደርን ለማስፈን ትልቅ ዕድል ይዞ የሚመጣ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።
የቦረና ዩኒቨርሲቲ መምህር በፍቃዱ ጨመረ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት ያሳለፈቻቸው የፖለቲካ ውጥረቶች ምንጫቸው የአካታችነት መጓደል መሆኑን አመላክተዋል።
በዘንድሮ ምርጫ ቀደም ሲል በታሪክ አጋጣሚ የተገፉ ድምፃቸው ያልተሰማ የማሕበረሰብ ክፍሎችንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወደ መድረኩ ያመጣ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ወጣቱ ትውልድ የሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን ባለቤት መሆኑን በተግባር ለማሳየት በዕጩነትና መራጭነት መሳተፋቸው ወሳኝ መሆኑን ምሁራን ገልጸዋል።
ምርጫው ከቴክኒካዊ ሂደት ባለፈ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ፣ ዴሞክራሲንና ፍትሐዊ አስተዳደር ማስፈኛ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በተስፋሁን ከበደ

በኢትዮጵያ የሚዲያ ዘርፍ የተከናወኑ ጥልቅ ሪፎርሞች ውጤት እያመጡ ነው:- የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን
****************
የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ከለውጡ በፊት የነበሩባቸውን የፖሊሲ፣ የመዋቅር እና የሙያ ሥነ-ምግባር ስብራቶች ለመጠገን የተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች ስኬታማ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ ገለጹ።
ዋና ዳይሬክተሯ እንዳመለከቱት፣ መንግሥት የሚዲያ ምህዳሩን ለማከም በወሰዳቸው እርምጃዎች ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነ ባለስልጣን መቋቋሙ፣ የሚዲያ የእርስ በእርስ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋቱ እና ዘርፉ ራሱን በራሱ እንዲቆጣጠር የሚያስችሉ የሙያ ማህበራት መበራከታቸው በዘርፉ የታዩ ትልልቅ ለውጦች ናቸው።
እነዚህ ሪፎርሞች ትክክለኛ ውሳኔዎች ስለመሆናቸውም አሃዛዊ ስኬቶች ማሳያ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
✅ከለውጡ በፊት 122 የነበረው አጠቃላይ የመገናኛ ብዙሃን ቁጥር በአሁኑ ወቅት ወደ 310 ከፍ ብሏል።
✅የሬድዮ ጣቢያዎች ከ52 ወደ 126 አድገዋል።
✅የቴለቪዥን ጣቢያዎች ከነበሩበት 25 ወደ 128 ከፍ ብለዋል።
✅የመገናኛ ብዙሃን የቋንቋ ተደራሽነት ከ39 ወደ 60 አድጓል።
✅በተጨማሪም 35 የውጭ ሚዲያዎች እና 50 የማህበረሰብ ሚዲያዎች በሀገራችን የሚዲያ ምህዳር ውስጥ በንቃት መሳተፋቸው የዘርፉን አካታችነት ይበልጥ አረጋግጧል።
ጥልቅ የሆነው የሚዲያ ሪፎርም የኢትዮጵያን የሚዲያ ምህዳር በሙያዊ ሥነ-ምግባር እና በዲሞክራሲያዊ አደረጃጀት ለመቅረጽ ትልቅ መሰረት መጣሉ ተመላክቷል።
#ebc #ethiopia #mediareform #ethiopianmediaauthority

4 months ago
የኢትዮጵያ ድምፅ በኦክስፎርድ
አቶ ገድለሚካኤል አበበ ለዓለም አቀፍ እውቅና ተመረጡ
#ethiopia | በየዓመቱ የዓለም የላቁ የማህበረሰብ ስራ ፈጣሪዎችን (Social Entrepreneurs) የሚያከብረው የስኮል ወርልድ ፎረም (Skoll World Forum)፣ ዘንድሮ በኦክስፎርድ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያዊውን አቶ ገድለሚካኤል አበበን ሊያከብር ነው።
ስለ ስኬቱ ዋና ዋና ነጥቦች
ሚሲንግ ቢሊየን ኢኒሼቲቭ
በአካል ጉዳተኝነት አካታችነት ላይ በሰሩት የላቀ ስራ ለዘንድሮው የ2026 እውቅና ከተመረጡ ጥቂት የዓለም ሰዎች መሀከል አንዱ ሆነዋል።
የሚዲያ ተፅዕኖ
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝዳንትና የብስራት ፕሮሞሽን መስራች የሆኑት አቶ ገድለሚካኤል፣ በሬዲዮና ቴሌቪዥን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ግንዛቤ በማስጨበጥ ይታወቃሉ።
የኦክስፎርድ ጉዞ
ከሚያዝያ 13 እስከ 16 ቀን 2018 ዓ.ም (2026) በሚቆየው ጉባኤ ላይ፣ የኢትዮጵያን ተሞክሮ በተመለከተ ንግግር ያደርጋሉ፤ ልምዳቸውንም ያጋራሉ።
ታሪካዊ መድረክ
ቀደም ሲል እንደ ኮፊ አናን፣ ዴዝሞንድ ቱቱ እና ጂሚ ካርተር ያሉ ታላላቅ ሰዎች ንግግር ባደረጉበት በዚህ መድረክ ላይ መገኘት ለኢትዮጵያ ትልቅ ስኬት ነው።
አቶ ገድለሚካኤል በአካል ጉዳተኞች ተደራሽነትና በአጋዥ ቴክኖሎጂዎች ላይ የሰሩት ስራ ሀገራችንን በዓለም መድረክ ከፍ አድርጓታል።
እናንት ያገሬ ልጆች
ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
መሥራት ጀግንነት ነው፤ ማድነቅ ደግሞ መሰልጠን ነው!
ጋዜጠኛ ገድለሚካኤል አበበ ለአገር እና ለሕዝብ እየሠራ፤ እየታተረ ይገኛል - ሽልማቱ ይገባሃል።
እንኳን ደስ ያለህ!
#getu #skollworld Forum #socialentrepreneurship #inclusionmatters #ethiopianexcellence #disabilityrights #oxford2026 #missingbillion #gedlemichaelabebe #አቶገድለሚካኤል #ኢትዮጵያ #ስኮልፎረም #አካታችነት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ዲሞክራሲና የሕዝብ ውክልና
በኢትዮጵያና ዓለም አቀፍ የሕግ ማእቀፍ
ፋንታሁን ደለለው ጠበቃና የህግ አማካሪ
መግቢያ #ethiopia | ዲሞክራሲ የሚለው ቃል አመጣጡ ከግሪክ ሲሆን ዲሞ ማለት ህዝብ ሲሆን ግራፊክ ማለት ስልጣን እንደሆነ በታሪክ ያወቅነው ነው። በግሪክ የህዝብ ውክልና የተጀመረበት ዜጎች መብታቸውን የሚያስከብሩበት መንገድ ጭላንጭል በር የታየበት ሲሆን ቀስ በቀስ እያደገ እና የተስፋፋበት የመጣ በታሪክ እድገት እንቅሰቃሴ ቀስ በቀስ በአውሮፓ በአሜሪካ በሌሎችም ሀገራት እየተስፋፋ የዲሞክራሲ ስረአተ መንግስት እያደጉ መጥተው ዛሬ በሀገራችን የ1987 ዓ.ም መንግስት በዲሞክራሲያዊ ህገመንግስት ህዝብን ማስተዳደር መጀመሩ ስለ ዲሞክሪያሲ እንድናወራ መሠረታዊ እድል የሚፈጥርልን ነው።
1. የዲሞክራሲ መርሆችና እሴቶች
1.1 የዲሞክራሲ መርሆች ማለት በመርህ ደረጃ በተለይም በሀገሪቱ ህገመንግስት መሠረታዊ እውቅና ያላቸው/Pillars of Democracy/ ተብለው እውቅና የተሰጣቸው ናቸው። ከዚሄ በታች የተዘረዘሩት የዲሞክራሲ መርህ ሲሆኑ እሴቶችም አንድ ላይ ተዘርዝረው የተቀመጡበት ነው።
1.2 እሴቶች
በማህበረሰቡ ውስጥ ሊጎለብቱ ሊጠቅሙ የሚችሉ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው በዚህ ጹሁፍ ይዘት የዲሞክራሲ መርሆች መከበር ውጤት የሆኑ ማ ህዘብ የሚረካባቸው የህገመንግስቱ ግኝቶች ናቸው።
1.3 ዴሞክራሲ መርሆዎችና እሴቶች እነማን ናቸው?
ምንድን ናቸው የሚለውን ከላይ ባለው የገለጽን ሲሆን እነ ማን ናቸው የሚለውን ከታች ባለው ዘርዝረን አስቀምጠናል። በኢፊድሪ ህገመንግስት ምእራፍ ሁለት ላይ የህገመንግስት መርሆች የተቀመጡ ሲሆን በሶስትና በአራት ላይም እሴቶች ጭምር ተደንግገው የተቀመጡ ናቸው።
መርሆችና እሴቶች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል።
✅ የሕዝብ ሉዓላዊነት
✅ የሕግ የበላይነት
✅ ነፃ እና ፍትሐዊ ምርጫ
✅ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ
✅ አሳታፊነት
✅ የሕዝብ ውክልና
✅ ነፃነት፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት
✅ እኩልነት እና ፍትሐዊነት
✅ የመናገር ነፃነት
✅ የማንነት እና የፖለቲካ ብዙኃነትን ማክበር፣ መቻቻል፣ አካታችነት ወዘተ... ናቸው።
2. የህዝብ ውክልና
የህዝብ ውክልና በኢፊድሪ ህገመንግስት አንቀጽ 8 ላይ በግልጽ ተደንግጎ የተቀመጠ ሲሆን ይህም የህዝቦች ሉአላዊነት በመረጡአቸው ተወካዮች አማካኝነት እንደሚገለጽ የተቀመጠ ሲሆን ይህ ህገመንግስትም የሉአላዊነታቸው መገለጫ እንደሆነ እንዲሁም ሉአላዊነታቸው ማለትም የሀገር ባለቤተንታቸው የሚገለጸው በቀጥታም ሆነ በምክር ቤት በሚወክሏቸው ተወካዮች አማካኝነት በሚያደርጓቸው ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ እንደሆነ በዚህ ህገሠንግስት አንቀጽ 8 ላይ ተደንግጓል። ይህ ማለት የህዝብ ውክልና ቀጥተኛ ያልሆነ በተወካዮቻቸው አማካኝነት የሚደረግ የህዝብ ተሳትፎ ሲሆን ቀጥተኛ የሆነ የህዝብ ተሳትፎ ደግሞ ቀጥታ የሚያደርጉት ሀገር አቀፍ ምርጫ ቀጥተኛ ተሳትፍ ይባላል። ዲሞክራሲ ማለት እንግዲህ ህዝብ የፈለገውን መንግስት የሚመርጥበት ተሳትፎ ነው።
3. ዲሞክራሲና ውክልና
ህዝብ የፈለገውን መንግስት የሚመርጥበት ስረአት ቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ማለትም በቀጥታ ተወካዩን የሚመርጥበት በተወካዩም ህዝብ ፍላጎቱን በህዝብ ውክልና የሚያስከብርበት ህገመንግስታዊ መገለጫ ዲሞክራሲ ይባላል።
4. ሲጠቃለል
ዲሞክራሲ ማለት ህዝቦች ወይም ዜጎች በቀጥታም ሆነ ቀጥታ ባልሆነ መንገድ በህዝብ ውክልና በህግ በዲሞክራሲያዊ ህገመንግስት መርህ መሠረት መብቶቻቸውን የሚያስከብሩበት አለምአቀፍ መርህ ነው።
https://www.facebook.com/s...
https://t.me/Fantahunlawye...
ማጣቀሻዎች
1. የኢፊድሪ ህገመንግስት አዋጅ ቁጥር 1/1987
2.Georg Sorensen,Democracy And Democratization: Processes And Prospects In A Changing World (Dilemmas in World Politics)

5 months ago
እናት ባንክ የሴቶች የፋይናንስ ተጠቃሚነት ለማሳደግ 'የሥርዓተ ፆታ ቦንድ' ሊጀመር ነው!
#fastmereja :እናት ባንክ የሴት አመራሮችን ክህሎትና ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ "High Level Women Leadership" የተሰኘ የፓናል ውይይት በዲሊዮፖል ሆቴል አካሄደ።
የባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት፤ ባንኩ ባለፉት 13 ዓመታት የሴት ሰራተኞችን አቅም በማሳደግና ወደ አመራር በማምጣት የደንበኞችን አገልግሎት ማሻሻል መቻሉን ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅትም የባንኩን እድገት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሴት ሰራተኞች ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት እናት ባንክ ካሉት ከ2,000 በላይ ሰራተኞች መካከል 952ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ ከ11 የቦርድ አባላት መካከል 7ቱ ሴቶች መሆናቸዉ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም በከፍተኛ የሥራ ካውንስል ውስጥ የሴቶች ድርሻ 44 በመቶ መድረሱ የባንኩን አካታችነት እንደሚያሳይ ተገልጿል።
ባንኩ ላሳየው ተከታታይነት ያለው የሴቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና በዓለም ባንክ የጋራ ምዘና (Gender Scorecard) "ፈር ቀዳጅ ባንክ"(The First and Only Transformational Bank) የሚል እውቅና ማግኘቱም በዝግጅቱ ላይ ይፋ ሆኗል።
ይህ እውቅና የተሰጠው ባንኩ በፋይናንስ አካታችነት፣ በሴቶች የሥራ ዕድገትና ለሴቶች ተብለው በተቀረጹ የብድርና ቁጠባ አገልግሎቶች ባከናወነው ውጤታማ ተግባር መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በቀጣይነትም በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚተገበረውንና የሴቶችን የፋይናንስ ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል የተባለለትን የሥርዓተ ፆታ ቦንድ (Gender Bond) ወደ አገልግሎት ለማስገባት ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ ዶ/ር ተዋበች ቢሻው፣ ወ/ሮ ናስሪን መሐመድ እና ዶ/ር ገመቹ ዋቅቶላ የካበተ የሥራና የሕይወት ተሞክሮአቸውን ለታዳሚዎች አጋርተዋል።
እናት ባንክ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገሪቱ 222 ቅርንጫፎችን በመክፈትና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቱን በማስፋፋት ተደራሽነቱን እያሳደገ ይገኛል።

ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ማህበረሰቦች እና ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው ታላቁ የማይክሮ ፋይናንስ ኮንፈረንስ ተጀመረ!
#fastmereja :የኢትዮጵያ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ማህበር (AEMFI) ከአውሮፓ ህብረት (Eሀ) እና ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ የነገው ትውልድ ማይክሮ ፋይናንስ ኮንፈረንስ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ከመጋቢት 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የስብሰባ ማዕከል በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ላይ፤ የፖሊሲ አውጪዎች፣ የፋይናንስ ዘርፍ መሪዎች፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።
“ዕድሎችን በፈጠራ፣ በአካታችነት እና በማገገም አቅም ባላቸው የፋይናንስ አገልግሎቶች መክፈት'' በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ይህ ኮንፈረንስ፣ በዋናነት ዲጂታል ፈጠራዎች እና የፖሊሲ ማሻሻያዎች የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት ያላቸውን ሚና ይፈትሻል።
በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ማህበረሰቦች እና ሴት ስራ ፈጣሪዎች የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑና የኢኮኖሚ ጥንካሬ እንዲገነቡ በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሰፊ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
ለሶስት ቀናት በሚቆየዉ ጉባኤ ውስጥም የከፍተኛ የፋይናንስ ባለሙያዎች የፓናል ውይይቶች፣በፈጠራ የታጀቡ የፋይናንስ መፍትሄዎች ገለጻዎች፣እንዲሁም የፊንቴክ (Fintech) እና የማይክሮ ፋይናንስ ውጤቶች የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽን እንደሚካሄድም ነዉ የተገለፀዉ።
ይህ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመንና አካታች ለማድረግ በምታደርገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው የተገለጸ ሲሆን፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ያላቸውን ሚና ለማጎልበት ያለመ ነው፡፡
ይህ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉን ለማዘመንና አካታች ለማድረግ በምታደርገው ጥረት ውስጥ እንደ ትልቅ ምዕራፍ የሚቆጠር መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተለይም ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ዘመናዊ አሰራሮችን በመከተል የገጠሩን ማህበረሰብ እና አነስተኛ የንግድ ዘርፎችን ወደ ፋይናንስ ስርዓቱ በማስገባት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ያላቸውን ድርሻ እንዲያሳድጉ ትልቅ መድረክ ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል።
ኮንፈረንሱ እስከ መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቀጥል ሲሆን፣ በስተመጨረሻም በዘርፉ ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት ይጠናቀቃል ተብሎ ይገመታል።

Comments