Logo
Getu Temesgen
የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በሥርዓት እየተካሄደ ነው - የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ
#ethiopia | የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክን የሚመሩት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊ ሁኔታ መጀመሩን ገልጸዋ።

አሁሩ ኬንያታ በመራጮች ማዕከላት የተመለከቱትን ሁኔታ ሲገልጹ፣ የድምፅ አሰጣጡ ሂደቱ በሥርዓት እየተካሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ ቀኑን ሙሉ በተመሳሳይ መንፈስ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

"ድምፅ መስጠት ዜጎች የሚወክሏቸውን መሪዎች እና ተወካዮች በነፃነት የሚመርጡበት መሠረታዊ ዴሞክራሲያዊ መብት ነው" ያሉት ኬንያታ፣ የአፍሪካ ኅብረት በአህጉሪቱ እውነተኛ ውክልና፣ አካታችነት እና ሕዝቦች የራሳቸውን መሪዎች የመምረጥ አቅም እንዲጠናከር እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት የምርጫ ሂደቶች ፈተናዎች እንዳሉ ቢገልጹም፣ ከእያንዳንዱ ምርጫ በኋላ የተሻለ ዲሞክራሲያዊ ባህል ለመገንባት ዕድል እንዳለ ጠቅሰዋል።

"ኢትዮጵያ የዚህች ታላቅ አህጉር ዋና ከተማ ናት፤ በዚህች ሀገር የሚገኝ ስኬት በመላው አፍሪካ ውስጥ ይንጸባረቃል" ሲሉ የተናገሩት ኬንያታ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም ምኞታቸውን ገልጸው የምርጫው ሂደት በሥርዓት እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ያላቸውን እምነት አረጋግጠዋል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ebc #ethiopia #ebcdotstream #democracy #africanunion

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.