በምርጫው የወጣቶችና ሴቶችን ውክልና ለማረጋገጥ…
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የወጣቶችና ሴቶችን ውክልና ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው አሉ ምሁራን።
ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራን እንደገለጹት÷ በምርጫው ሂደት የወጣቶችንና ሴቶችን ውክልና ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሥነ አመራርና አስተዳዳር መምህር በዳሳ ፍራጃ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ጉዞ በተግዳሮቶች የታጠረ ቢሆንም መጪው ምርጫ ፍትሐዊ አስተዳደርን ለማስፈን ትልቅ ዕድል ይዞ የሚመጣ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።
የቦረና ዩኒቨርሲቲ መምህር በፍቃዱ ጨመረ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ባለፉት ዘመናት ያሳለፈቻቸው የፖለቲካ ውጥረቶች ምንጫቸው የአካታችነት መጓደል መሆኑን አመላክተዋል።
በዘንድሮ ምርጫ ቀደም ሲል በታሪክ አጋጣሚ የተገፉ ድምፃቸው ያልተሰማ የማሕበረሰብ ክፍሎችንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ወደ መድረኩ ያመጣ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ወጣቱ ትውልድ የሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን ባለቤት መሆኑን በተግባር ለማሳየት በዕጩነትና መራጭነት መሳተፋቸው ወሳኝ መሆኑን ምሁራን ገልጸዋል።
ምርጫው ከቴክኒካዊ ሂደት ባለፈ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ፣ ዴሞክራሲንና ፍትሐዊ አስተዳደር ማስፈኛ ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በተስፋሁን ከበደ

3 months ago