ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው በጀት አመቱ 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ
#ethiopia | ኢትዮ ቴሌኮም በ2018 በጀት ዓመት የ“ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂውን በመተግበር በሁሉም የሥራ ክንውንና የፋይናንስ መለኪያዎች የላቀ ስኬት ማስመዝገቡን የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ገለጹ።
ተቋሙ በበጀት ዓመቱ 215.82 ቢሊዮን ብር ገቢ በማመንጨት የዕቅዱን 99.7 በመቶ ማሳካቱንና ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ33.2 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አስታውቀዋል።
በዚህም የታሪካዊ ስኬት ምዕራፍ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዳታና ኢንተርኔት አገልግሎት የተገኘው ገቢ 31.1 በመቶ ከሞባይል ድምፅ ገቢ 23.5 በመቶ ብልጫ በመውሰድ ኩባንያው ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ያደረገውን ስኬታማ ሽግግር በግልጽ አሳይቷል።
በተጨማሪም የኩባንያው ደንበኞች ቁጥር 90.12 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የፋይናንስ አካታችነትን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ድርሻ ያለው የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚዎች 60.6 ሚሊዮን ደርሰዋል።
ቴሌብር በበጀት ዓመቱ ብቻ 4.19 ትሪሊዮን ብር የሚያንቀሳቅስ 2.61 ቢሊዮን ግብይቶችን ማስተናገዱን የጠቀሱት አበይት ማብራሪያዎች፣ ተቋሙ ከወትሮው የቴሌኮም ኦፕሬተርነት ወደ ሁለንተናዊ የቴክኖሎጂ ተቋም የመሸጋገር ጉዞውን በተሳካ ሁኔታ እያከናወነ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው።
የኔትወርክ ጥራትንና ተደራሽነትን ለማስፋፋት በተደረገው ጥረት 603 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች ተገንብተው የ4ጂ የሕዝብ ቁጥር ሽፋን 82.23 በመቶ ደርሷል።
ከዚህ ጎን ለጎን ኢትዮ ቴሌኮም ወደ ሕዝባዊ አክሲዮን ማኅበርነት በመሸጋገር በኢትዮጵያ ሴኪውሪቲስ ኤክስቼንጅ የመጀመሪያውን ይፋዊ የአክሲዮን ምዝገባ ማካሄዱን፣ እንዲሁም በበጀት ዓመቱ 73.5 ቢሊዮን ብር ታክስ በመክፈል ለአገራዊ ኢኮኖሚ ግንባታ ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ መቀጠሉን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ፍሬሕይወት ታምሩ አብራርተዋል።
#ethiotelecom #ethiotelecomreport #digitalethiopia #telebirr #techco
#telecomnews #ethiopiatech
#digitaltransformation

3 months ago