2 months ago
በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ በሕገወጥ የገንዘብና የሰዎች ዝውውር ላይ በተወሰዱ የሕግ ማስከበር እርምጃዎች ዙሪያ መግለጫ አወጣ
#ethiopia | በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ በሕገወጥ የሐዋላ አገልግሎትና በሰዎች ዝውውር ወንጀል የተሰማሩ አካላትን ለሕግ ለማቅረብ እየተወሰዱ ያሉ አገራዊ እርምጃዎችን ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፍ አስታወቀ።
ኤምባሲው ይፋ ባደረገው መግለጫ፣ የኢፌዲሪ መንግሥት አገራዊ የኢኮኖሚ ደህንነትን ለማስጠበቅና ሙስናን ለመግታት እያደረገ ባለው ጥረት በርካታ ወንጀለኞች ተለይተው ለሕግ መቅረባቸውን ገልጿል።
በቅርቡ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና በዱባይ ፖሊስ መካከል በተደረገ የተቀናጀ ክትትል በከባድ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ዋነኛ ግለሰቦች በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች ተይዘው ለሕግ እንዲቀርቡ ተደርጓል።
ሁለቱ አገራት ወንጀለኞችን አሳልፎ የመስጠትና የሕግ ትብብር ስምምነት ያላቸው በመሆኑ፣ በየትኛውም ወገን ወንጀል ፈጽሞ ድንበር ተሻግሮ ማምለጥ እንደማይቻል ኤምባሲው አረጋግጧል።
በሁለቱ አገራት መካከል ባለው የሁለትዮሽ የሠራተኛ ስምምነት መሠረት የኤምሬቶች የሥራ ገበያ በሕጋዊ መንገድ ለሚመጡ ዜጎች ክፍት ቢሆንም፣ ሕገወጥ ደላሎችና ሽፋን ያላቸው ኤጀንቶች የሐሰት የተስፋ ቃል በመስጠት ዜጎችን ለአደጋ ዳርገዋል።
በመሆኑም አገር ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦችም ሆኑ በውጭ አገር የሚኖሩ ዜጎች ማንኛውንም የጉዞና የሥራ ቅጥር ከማድረጋቸው በፊት ሕጋዊነቱን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ታስቧል።
ኤምባሲው ያስተላለፋቸው ዋና ዋና ጥሪዎች፡
በሕገወጥ የሐዋላና የሰዎች ዝውውር ላይ የተሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው በአስቸኳይ እንዲቆጠቡና ካልሆነ ግን የተቀናጀው የሕግ ማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጥብቅ ማጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ዜጎች ወደ አገር ቤት ገንዘብ ሲልኩ ሕጋዊ የባንክና ፈቃድ ያላቸው የሐዋላ ተቋማትን ብቻ እንዲጠቀሙ፣ እንዲሁም የሥራ ስምሪትን በሕጋዊ መስመር ብቻ እንዲፈጽሙ ጥሪ ቀርቧል።
ኅብረተሰቡ ስለ ሕገወጥ ደላሎችና ወንጀለኞች መረጃ ሲኖረው በስልክ ቁጥር +971500001522 ወይም በዋትስአፕ መልዕክት ለኤምባሲው በምስጢር ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠይቋል።
በመጨረሻም በኤምሬቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሁለቱን አገራት ሕግ አክብረው በመንቀሳቀስ ራሳቸውንና ወገኖቻቸውን ከጉዳት እንዲጠብቁ ኤምባሲው ጥሪውን አቅርቧል።
#uae #dubai #abudhabi #ethiopianembassy #lawenforcement #extradition #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በሚኒሶታ በጠሩት ስብሰባ የአማራ እና የትግራይ ኮምዩኒቲዎች መገለላቸው ጥያቄ አስነሳ #ethiopia #ethiopianembassy #minnesota #geopolitics
Comments