1 day ago
በተቋማዊ ሪፎርሙ ሕዝባዊነቱን ያጠናከረው ሠራዊት
**************
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ሉዓላዊነት፣ የሕዝብ ደኅንነት እና የጽናት ታላቅ ምሰሶ ነው።
ባለፉት ስምንት ዓመታት በሠራዊቱ ውስጥ የተተገበሩት ጥልቀት ያላቸው የሪፎርም እና የተቋማዊ መዋቅር ማሻሻያዎች ሠራዊቱን ወደ አዲስ የልህቀት ደረጃ ያሸጋገሩ ናቸው።
ይህ የሪፎርም ሂደት የሠራዊቱን ሕዝባዊነት የበለጠ ያጠናከረ፣ ሙያዊ ገለልተኝነቱን ያረጋገጠ እና መዋቅራዊ አደረጃጀቱን በዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስ መርሆዎች ላይ ያቆመ ነበር።
ተቋሙን ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት በማፅዳት እና አደረጃጀቱን በማዘመን የአየር ኃይል፣ የባሕር ኃይል እንዲሁም የሳይበር ደኅንነት ክፍሎች ዘመኑ የሚጠይቀውን አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የዝግጁነት ደረጃ እንዲላበሱ አስችሏቸዋል።
በተቋማዊ ሪፎርሙ ከተመዘገቡት ዋና ዋና ውጤቶች መካከል በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሰው ኃይል ግንባታ ላይ የታየው የላቀ ዕድገት ይጠቀሳል።
ሠራዊታችን ዘመናዊ የክትትል ቴክኖሎጂዎችን፣ የሰው አልባ አየር (ድሮን) ሥርዓቶችን እና የተራቀቁ የመረጃ መረቦችን በመታጠቅ ተቋማዊ ቁመናውን አዳብሯል።
በየደረጃው ባሉ ወታደራዊ አካዳሚዎች የተሰጡት የላቁ የስልጠና መርሐ-ግብሮች የሠራዊቱን ሥነ-ልቦናዊና ቴክኒካዊ አቅም በማሳደግ፣ አደጋዎችን በሳይንሳዊ ስልት፣ አነስተኛ የሰው እና የቁሳቁስ ጉዳት በሚያስከትል መልኩ የመከላከልና የማክሸፍ ብቃቱን አጎልብተውለታል።
በሀገራችን ያጋጠሙ ውስብስብ የውስጥ ደኀንነት ፈተናዎችን በማረጋጋት ሂደት ሠራዊቱ ያሳየው አስተዋይነት እና ሕዝባዊ ወገንተኝነት ጎልቶ የወጣበት ነው።
የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የትዕግሥት እና የሰላም መንገዶችን በማስቀደም፣ የሲቪሎችን ሕይወት ከጉዳት በመጠበቅ እና የሀገር ሀብት የሆኑ መሠረተ-ልማቶችን በጥንቃቄ በመጠበቅ ረገድ ውጤታማ ሥራ ሠርቷል።
ይህም ሠራዊቱ የኃይል አጠቃቀምን የመጨረሻ አማራጭ በማድረግ የሰላም እና የሕግ ሥርዓት ዋስትና መሆኑን ያስመሰከረበት ነው።
ከሀገር ውስጥ ተልዕኮ ባሻገር፣ ሠራዊታችን በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ለሚከናወኑ የሰላም ማስከበር ሥራዎች የጸና አለኝታ ሆኖ ዘልቋል።
በአፍሪካ ኅብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተልዕኮዎች የሚያሳየው የላቀ ሙያዊ ሥነ-ምግባር፣ ለሕዝብ ያለው ቅርበት እና የተላበሰው ሕዝባዊነት የሀገራችንን በጎ ገፅታ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ አድርጎታል።
ባለፉት የሪፎርም ዓመታት የተገነቡት ዘመናዊ አቅሞች እና ተቋማዊ ነፃነት፣ ሠራዊታችን ወደፊትም የሀገርን ሉዓላዊነት እና የሕዝብን አደራ በላቀ ብቃት ለመወጣት የሚያስችለውን አስተማማኝ መሠረት ጥለዋል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ
#ethiopiandefenseforce #endf #ethiopianarmy #heroesofethiopia #militarypower #ethiopiandiplomacy

1 month ago
የኢትዮጵያ የባሕር በር ታሪካዊ መብትና የፍትህ ጥያቄ
******************
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ከባህር በሮቿ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው ሲሆን፣ ለቀይ ባህር በቀረበች ቁጥር የከፍታ ዘመኗን ስታረጋግጥ ቆይታለች።
የኢትዮጵያ የህልውና ጥያቄ የሆነው የባህር በር ጉዳይ የሌላ ሀገር ግዛት የመውሰድ ጉዳይ አይደለም፤ በፍትሀዊነት መብቷን የመጠየቅ እንጂ፡፡ ለዚህ ማሳያ ደግሞ ከዲፕሎማሲ አንፃር አስፈላጊ አለም አቀፍ ድርጅቶች የተለያዩ መርሆችን አስቀምጠዋል።
በ1982 የፀደቀው የተባበሩት መንግስታት የባህር ሕግ ስምምነት (UNCLOS) የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ወደ ባህር የመድረስና የትራንዚት መብት እንዳላቸው ያስቀምጣል። ሆኖም ይህ መብት በጎረቤት ሀገራት ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት በማክበር እንዲፈጸም ይደነግጋል።
የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ የአፍሪካ ሀገራት ሉዓላዊነትና ድንበር መከበርን እያጎላ በተመሳሳይ ጊዜ የክልል ትስስር፣ የንግድ ትብብር እና የጋራ ልማት እንዲጠናከር ያበረታታል።
የመንግስታቱ የልማት ድርጅት (UNCTAD) ደግሞ የባህር በር አልባ ሀገራት ከፍተኛ የመጓጓዣ ወጪ እንደሚሸከሙና ይህም የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነታቸውን እንደሚጎዳ ይገልጻል።
የዓለም ባንክም በምሥራቅ አፍሪካ የወደብ ተደራሽነት፣ የባቡር መስመሮች እና የንግድ ኮሪደሮች መጠናከር የክልሉን ኢኮኖሚ እድገት እንደሚያፋጥን ያሳያል።
ኢትዮጵያ ለወደብ አገልግሎት፣ ለትራንስፖርት እና ለሎጂስቲክስ በየዓመቱ ቢሊዮን ዶላሮችን የምታወጣ ሲሆን፤ የሕዝብ ቁጥሯ እየጨመረ እና ኢኮኖሚዋ እየሰፋ ባለበት ሁኔታ ደግሞ ይህ ወጪ የበለጠ እየጨመረ ይሄዳል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከ95 በመቶ በላይ የውጭ ንግዷን በጅቡቲ ወደብ በኩል ታከናውናለች። ይህም በአንድ መስመር ላይ ያለ ከፍተኛ ጥገኝነት ነው።
ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በሕዝብ ብዛት ትልቋ የባህር በር አልባ ሀገር ናት። የራሷ ወደብ ሳይኖራት ለውጭ ንግድ እና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት በጎረቤት ሀገራት ወደቦች ላይ ተመርኩዛ ቆይታለች።
ይህም በየዓመቱ ቢሊዮን ዶላሮች የሚያስወጣ ከመሆኑም በላይ የንግድ፣ የኢኮኖሚ፣ የብሔራዊ ደህንነት እና የቀጠናዊ መረጋጋት ጉዳይ ሆኖ ቀጥሏል።
የባህር በር ማለት አንድ ሀገር ከዓለም አቀፍ የባህር ንግድ መስመሮች ጋር በቀጥታ የምትገናኝበት መዳረሻ ነው።
ዛሬ ከዓለም አቀፍ ንግድ 80 በመቶ በላይ በባህር መንገድ የሚከናወን በመሆኑ፣ ወደብ ለሀገራት የኢኮኖሚ መተንፈሻ በር ተደርጎ ይታያል።
የባህር ማጓጓዣ የአለም ኢኮኖሚ ፍፁም የጀርባ አጥንት ሲሆን፣ በየአመቱ ከ11 ቢሊዮን ቶን በላይ ጥሬ እቃዎች፣ ሃይል እና የፍጆታ እቃዎች ይንቀሳቀሳል።
ውቅያኖሶች 70% የሚሆነውን የምድርን ገጽ ስለሚሸፍኑ መርከቦች ከባድ እና ግዙፍ ጭነትን ረጅም ርቀት ለማንቀሳቀስ በጣም ወጪ ቆጣቢ እና ቀልጣፋ መንገድ ይሰጣሉ።
ኢትዮጵያ የባህር ባለቤት ስትሆን ተጠቃሚዋ እሷ ብቻ አትሆንም። የጎረቤት ሀገራት ወደቦች ተጨማሪ ገቢ ያገኛሉ፤ ንግድ ይስፋፋል፤ መሠረተ ልማት ይጠናከራል፤ የቀጠናው የኢኮኖሚ ትስስርም ይጨምራል።
ይህም የዜሮ ድምር ጨዋታ ሳይሆን ሁሉም ተጠቃሚ የሚሆኑበት የጋራ ልማት እድል ነው።
የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ፖለቲካ አይደለም፤ የመላው ኢትዮጵያዊ የህልውና ጉዳይ እንጂ። ይህ ጥያቄ በጦርነት ሳይሆን በዲፕሎማሲ፣ በህግ እና በጋራ ጥቅም መርህ ሊመለስ የሚችል ነው።
በልዩ እሸቱ
#ethiopia #seaoutlet #redsea #ethiopiandiplomacy #geopolitics

Sponsored by
Surafel
Comments