2 months ago
"ኔታንያሁ እስራኤልን እየበተኗት ነው" — ያኢር ላፒድ
#ethiopia | የእስራኤል ተቃዋሚ መሪ ያኢር ላፒድ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ላይ ጠንከር ያለ ትችት ሰነዘሩ።
ኔታንያሁ "መካከለኛውን ምስራቅ ለወጥኩ" ቢሉም፣ በተግባር ግን ምንም የመጣ ለውጥ የለም ሲሉ አጣጥለዋል።
ስትራቴጂካዊ ውድቀት፦ ኔታንያሁ በኢራንና በክልሉ ባሉ ተላላኪዎቿ ላይ ተጨባጭ ድል ማስመዝገብ ተስኖቸዋል።
የስጋት መቀጠል፦ ሄዝቦላህ ሮኬት መተኮሱን አላቆመም፤ ሀማስ አሁንም በጋዛ አለ፤ ኢራንም የባሊስቲክ ሚሳኤል ጥቃቷን ቀጥላለች።
ኔታንያሁ ድልን ከማምጣት ይልቅ እስራኤልን ከውስጥ እየበተኗት ነው ተብሏል።
አራት ወታደሮች በሊባኖስ በተገደሉበት ምሽት፣ ሚኒስትሩ ቤን ግቪር በፓርላማ ሻምፓኝ ሲከፍቱ ነበር ሲሉ ላፒድ ወቅሰዋል።
"ይህ አስከፊ መንግስት በአስቸኳይ መቀየር አለበት!" — ያኢር ላፒድ
#israel #netanyahu #yairlapid #middleeast #breakingnews #ethiopia #የዓለምዜና

3 months ago
ኔታንያሁ የኢራን ሕዝብ በመሪዎቹ ላይ እንዲያምፅ ጥሪ ማቅረባየው ተነጠረ
#ethiopia | የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለኢራን ሕዝብ ባስተላለፉት ያልተለመደ የቪዲዮ መልዕክት፣ የሀገሪቱ ዜጎች የአያቶላህን አገዛዝ እንዲያስወግዱና ለለውጥ እንዲነሱ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገዛዙን መገርሰስ "በሕይወት ዘመን አንድ ጊዜ የሚገኝ ዕድል" መሆኑን በመጥቀስ፣ እስራኤል ከኢራን ሕዝብ ጎን መቆሟን ገልጸዋል።
ኔታንያሁ አክለውም የአያቶላህ አሊ ኻሚኒ አስተዳደር ለጦርነት የሚያወጣውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለሕዝብ አገልግሎትና ለልማት ሊውል እንደሚገባ በመጠቆም፣ "ጦርነቱን እንቋጨዋለን" ሲሉ ተደምጠዋል።
ይህ የኔታንያሁ ንግግር እስራኤል በኢራን ላይ የጀመረችውን ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ጫና አጠናክራ እንደምትቀጥል አመላካች ተደርጎ ተወስዷል።
በተቃራኒው የቴህራን ባለስልጣናት ለጥሪው ፈጣን ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ የኢራን የፖሊስ አዛዥ ዜጎች በማንኛውም ፀረ-መንግስት ተቃውሞ ላይ እንዳይሳተፉ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ አስተላልፈዋል። የኢራን መንግስት ሕዝቡ በአንድነት ቆሞ የ"አሜሪካና እስራኤልን" ጥቃት እንዲመክት ጥሪ በማቅረብ ላይ ይገኛል።
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ፣ የኔታንያሁ ቀጥተኛ የቪዲዮ መልዕክት በኢራን ውስጥ የውስጥ አለመረጋጋት ለመፍጠር የታለመ ቢሆንም፣ በቴህራን በኩል ያለው ምላሽ ግን የከረረና የጦርነቱን አዝማሚያ ይበልጥ የሚያፋፍም ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #middleeastconflict #netanyahu #iran #israel #worldnews #geopolitics #breakingnews

‹‹ኢራን 50 ሰሜን ኮሪያዎችን ትሆናለች›› የኔታንያሁ
#ethiopia | በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለው ወታደራዊ ፍጥጫ አዲስና አደገኛ ምዕራፍ ላይ መድረሱ ተሰምቷል። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እርስ በእርስ የሚወራወሯቸው ጠንካራ ቃላት፣ ዓለምን ለከፋ ስጋት ዳርገዋል።
ኔታንያሁ ለምን ኢራንን ከሰሜን ኮሪያ ጋር አነጻጸሩ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት፣ ኢራን ለዓለም ሰላም ካላት አደገኝነት አንጻር "50 ሰሜን ኮሪያዎችን ትሆናለች" ሲሉ ገልጸዋል። እንደ ኔታንያሁ ገለጻ፣ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር እና የባለስቲክ ሚሳኤል አቅም ቢኖራትም፣ እንደ ኢራን ግን "ሞት ለአሜሪካ" የሚል ግልጽ የጥፋት ርዕዮተ ዓለም አትከተልም።
"ኢራን የአሜሪካን እና የእስራኤልን መጥፋት እንደ ዋና ግብ ይዛ የተነሳች በመሆኗ፣ አጥፊነቷ ከሰሜን ኮሪያ በብዙ እጥፍ ይበልጣል" — ቤንያሚን ኔታንያሁ
የሰሜን ኮሪያው ምላሽ፦ "እስራኤልን ለማጥፋት አንድ ሚሳኤል ይበቃል"
የኔታንያሁ ንግግር ያልተዋጠላቸው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፣ ለቴህራን ያላቸውን ወታደራዊ ድጋፍ በይፋ አረጋግጠዋል። እስራኤልን ከዓለም ካርታ ላይ ለማጥፋት "አንድ ሚሳኤል ብቻ" በቂ እንደሆነ የገለጹት መሪው፣ አስፈላጊ ከሆነም የላቁ ሚሳኤሎችን ለኢራን ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ይህ የፒዮንግያንግ መግለጫ የወጣው በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች መሆኑ ይነገራል፡-
* አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት "ኦፕሬሽን ኤፒክ ፉሪ" (Operation Epic Fury) መጠናከሩ።
* የኢራኑ የበላይ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኒ መገደላቸው መረጋገጡ።
አዲሱ የኃይል አሰላለፍ እና የዓለም ስጋት
በኢራን፣ ሩሲያ፣ ቻይና እና ሰሜን ኮሪያ መካከል እየተፈጠረ ያለው ወታደራዊ ጥምረት፣ ግጭቱን ከቀጣናዊነት አልፎ ዓለም አቀፍ ጦርነት ሊያደርገው ይችላል የሚል ስጋት አንዣብቧል።
* የቻይና ሚና፦ ቻይና ለኢራን የላቁ ሚሳኤሎችን እያቀረበች ነው የሚሉ ዘገባዎች ቢወጡም፣ ቤጂንግ ግን ውንጀላውን አስተባብላለች።
* የትራምፕ ማስጠንቀቂያ፦ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል "ትልቁ ጦርነት ሊመጣ ይችላል" ሲሉ የሰጡት ማስጠንቀቂያ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር እየተገጣጠመ ይገኛል።
ይህ ወታደራዊ ውጥረት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ ከፍተኛ መናወጥን የፈጠረ ሲሆን፣ የጂኦ-ፖለቲካዊ መረጋጋትንም ጥያቄ ምልክት ውስጥ ከትቶታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiofm #middleeastcrisis #israeliranconflict #netanyahu #kimjongun #globalsecurity #operationepic Fury #breakingnews

5 months ago
የትራምፕ ገሃነም
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሃማስ በአስቸኳይ ትጥቅ ካልፈታ "ገሃነም ይጠብቀዋል" ሲሉ ዝተዋል። ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት ሰኞ ዕለት በፍሎሪዳ ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ወቅት ነው።
ትራምፕ ያቀረቡት ባለ 20 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ሃማስ ትጥቅ እንዲፈታ የሚጠይቅ ሲሆን፣ ዕቅዱን "በጣም በፍጥነት" ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ ለማሸጋገር ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
እስራኤል በጋዛ ወታደራዊ እርምጃዋን ብትቀጥልም፣ የዩናይትድ ስቴትስን ዕቅድ መቶ በመቶ እየተገበረች መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
ኢራን የኒውክሌር ፕሮግራሟን ወይም የባለስቲክ ሚሳኤል ግንባታዋን በድጋሚ ከጀመረች፣ አሜሪካ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥቃት እንደምትሰነዝር አስጠንቅቀዋል።
የኢራን ከፍተኛ የፖለቲካ አማካሪ አሊ ሻምኻኒ በበኩላቸው፣ በማንኛውም የጠብ አጫሪነት ተግባር ላይ ሀገራቸው "ፈጣን እና የከፋ ምላሽ" እንደምትሰጥ በኤክስ (X) ገጻቸው መልሰዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ዓለም_አቀፍ_ፖለቲካ #የመካከለኛው_ምስራቅ_ውጥረት #trump #netanyahu #israel #hamas #iran #gazapeaceplan #usa #middleeast #geopolitics

Sponsored by
Surafel