9 days ago
የ"ራሴን በጉያዬ፣ የሌላውን በጋራ" የግብጽ የሞኝ ብልጠት አካሄድ ዳግም ሲጋለጥ
********************
ኢትዮጵያ የዓባይን ውኃ 85 በመቶ የምታመነጭ እና ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት የሕይወት እስትንፋስ የሆነች ሀገር ነች።
ይሁን እንጂ ግብጽ ይህንን የማይካድ የተፈጥሮ እውነት ወደ ጎን በመተው ለረጅም ዘመናት "የዓባይ ውኃ ብቸኛ ባለቤት እኔ ነኝ" የሚል የሞኝ ብልጠት ፖለቲካ ስታራምድ ኖራለች።
ካይሮ ይህንን የውኃ ሞኖፖል ለማስቀጠል መሠረት የምታደርገው ኢትዮጵያን ያገለሉትን እና ጊዜ ያለፈባቸውን የ1929 እና የ1959 የቅኝ ግዛት ዘመን 'ስምምነቶች'ን ነው።
ከዚህም አልፋ የውኃ ድርሻዬ የምትለውን ለማረጋገጥ በቀጣናው የውክልና ፖለቲካን በመጠቀም ሀገራት እርስ በርስ እንዲጋጩ፣ ትርምስ እንዲፈጠር እና ኢትዮጵያ በውስጥ ችግር ተተብትባ የራሷን ጸጋ እንዳትጠቀም የተለያዩ የሴራ ድሮችን ስታደራ መኖሯ የአደባባይ ምሥጢር ነው።
ለዘመናት የዓባይ ወንዝን በብቸኝነት ለመጠቀም ስትከተለው የቆየው ይህ አካሄድ ሀገሪቱ በዜሮ ድምር ስሌት የምትመራ እና ከመጠን ያለፈ ራስ ወዳድ መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ ነው።
ኢትዮጵያ ከደጇ የሚመነጨውን ተፈጥሯዊ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን ስታነሣ አምርራ የምትቃወመው ግብጽ፣ በቀይ ባሕር የባሕር ላይ ደኅንነት ዙሪያ ፍጹም ተቃራኒ የሆነ እና "ዐይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ" የሚል ሌላ የሴራ አካሄድ ይዛ ብቅ ማለቷ ነው።
የታችኛው ተፋሰስ ሀገር የሆነችው ግብጽ በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ "የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ድምፅ እና ይሁንታ ሊኖራቸው ይገባል" በማለት የኢትዮጵያን ሉዓላዊ መብት ስትገዳደር ኖራለች።
በተቃራኒው ግን በቀይ ባሕር ጉዳይ ላይ ስትጠየቅ "ውይይት እና ውሳኔው የሚመለከተው የባሕሩ ተዋሳኝ ሀገራትን ብቻ ነው" የሚል የሞኝ ዜማ ማቀንቀን ከጀመረች ውላ አድራለች። ይህ ተቃራኒ እና ሚዛን የሳተ አካሄድ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ለማወናበድ እና የማይመስሉ ጥያቄዎችን በማንሣት ኢትዮጵያን ከጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነቷ ለማግለል ያሰላችው ያረጀ ስትራቴጂዋ ነው።
ይህንን የካይሮን የሚጣረስ እና የተፈጥሮ ሕግን የሚቃረን አካሄድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሁለት ዓመታት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ባደረጉት ታሪካዊ ማብራሪያ በግልጽ አስቀምጠውታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀይ ባሕር እና ዓባይ ከኢትዮጵያ ዕድገት እና ሕልውና ጋር በቀጥታ የተሣሠሩ መሠረታዊ ጉዳዮች መሆናቸውን በመጠቆም፣ ተፈጥሯዊ ትሥሥራቸውን አብራርተዋል።
ዓባይ ከኢትዮጵያ እየፈለቀ ለግብጽ የሕልውና ጉዳይ ከሆነ እና ስለ እርሱ በግልጽ መነጋገር ከቻለች ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ኢትዮጵያ በጂኦግራፊያዊ እስር ቤት ታሥራ መኖር ስለማትችል ስለ ቀይ ባሕር መነጋገርም ሆነ መደራደር ነውር ሊሆንባት አይገባም ነው ያሉት።
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አባባል፣ ተፈጥሮ በውኃ አዙሪት ያስተሣሠረቻቸውን እነዚህን ሁለት የውኃ አካላት እና ጂኦ-ፖለቲካዊ እውነታዎች አንዱን የብቸኝነት ንብረት አድርጎ ሌላውን መከልከል ከፍትሕ እና ከተፈጥሮ ሕግ ጋር ፈጽሞ የሚጣረስ ነው።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ይህንኑ ጽኑ አቋም እና የግብጽን ግብዝነት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በሚገባ መረዳት ጀምሯል።
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ቲቦር ናዥ ይህንን የግብጽን ጨፍኑ ላሞኛችሁ አካሄድ ሰሞኑን በጥልቅ አመክንዮአዊ መልዕክት አጋልጠውታል።
አምባሳደሩ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ "ግብጽ እና ኤርትራ በቀይ ባሕር ላይ መወሰን ያለባቸው ተዋሳኝ ሀገራት ብቻ ናቸው ካሉ፤ እንግዲያውስ በአመክንዮ ደረጃ በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይም መወሰን ያለባቸው ውኃውን የሚያመነጩት የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ብቻ ናቸው" በማለት የካይሮን ክርክር መሠረተ ቢስነት በአደባባይ አሳይተዋል።
አምባሳደሩ ከዚህ ቀደምም ግብጽ ጊዜ ያለፈበትን አካሄድ ትታ መሬት ላይ ወዳለው እውነታ መምጣት እንዳለባት በተደጋጋሚ አሳስበዋል። ኢትዮጵያን በዛቻ እና በግፊት ማንበርከክ እንደማይቻል የገለጹት አንጋፋው ዲፕሎማት፣ የቀይ ባሕር ደኅንነት ያለ ኢትዮጵያ ንቁ ተሳትፎ ሙሉ ሊሆን እንደማይችል በግልጽ አስምረውበታል።
ግብጽ በአንድ በኩል ኢትዮጵያ የታላቁን ሕዳሴ ግድብ ስትገነባ "የታችኛው ተፋሰስ ፈቃድ ያስፈልጋል" እያለች አቤቱታ ስታሰማ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እ.አ.አ በ2020 በሪያድ የተቋቋመውን "የቀይ ባሕር እና የኤደን ባሕረ ሰላጤ ሀገራት ምክር ቤት" በመጠቀም ኢትዮጵያን ከባሕር ደኅንነት ውይይቶች ለማግለል ስትሠራ ቆይታለች።
ይህ የ"ራሴን በጉያዬ፣ የሌላውን በጋራ" የብልጠት ስትራቴጂ አሁን ላይ ጊዜው አልፎበታል። ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ፍትሐዊ የልማት ጥያቄዋን በአግባቡ መጠየቅ እና በውኃዋም ሆነ በባሕር በር አማራጮቿ ተጠቃሚ ለመሆን መንቀሳቀስ በመጀመሯ፣ የግብጽ ያረጀ የሞኖፖል እና የሴራ አካሄድ ፈጽሞ እንደማያዋጣ በተግባር እየተረጋገጠ መጥቷል።
ለግብጽ የሚበጃት ብቸኛ መንገድ ወደ እውነታው መምጣት እና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ የትብብር ማዕቀፍን መቀበል ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ የ130 ሚሊዮን ሕዝቧን የልማት እና የደኅንነት ዋስትና ለማረጋገጥ የጀመረችውን የሰላም እና የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጉዞ ማንም አያስቆመውም።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #redsea #nilebasin #geopolitics #hornofafrica #diplomacy

14 days ago
ውኃ የሚወቅጠው የግብጽ ዲፕሎማሲ እና የማይቀለበሰው የኢትዮጵያ ልማት
*********************
የግብፅ የውኃ ሀብት እና መስኖ ሚኒስቴር “በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች ላይ የተመሰረተ የውኃ መብቴን ለማስከበር ቁርጠኛ ነኝ” በሚል ያወጣው መግለጫ፣ የካይሮ ፖለቲከኞች ለዘመናት ሲያላምጡት የኖሩትና አሁንም መላቀቅ ያቃታቸው የተለመደ የሚዲያ ፍጆታ ነው።
ይህ መግለጫ መሬት ላይ ካለው ነባራዊ እውነት ጋር የማይገናኝ ነው፡፡ ዋናው ዓላማውም ኢትዮጵያ በውኃ ሀብቷ እያስመዘገበች ያለው የልማት ስኬት እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ሚዛን ለውጥ የፈጠረባቸውን የሥነ-ልቦና መረበሽ ለመሸፈን የሚደረግ መፍጨርጨር ነው።
ካይሮ ዓለም አቀፍ ሕግን እንደ ሽፋን ብትጠቀምም፣ ትክክለኛው የውስጥ ሕመሟ የውኃ እጥረት ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን ማንሰራራት እንደ ስጋት የመመልከትና የተፈጥሮ ሃብቷን ለመጠቀም የምታደርገውን ጥረት ለመግታት ያለመ ነው።
ግብፅ በረሃን እያለማች፣ ቶሽካን በመሳሰሉ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ውኃ የሚጠይቁ ሰብሎችን በበረሃ እያመረተች፣ በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋዋን ተጠቅማ ዜጎቿን ከድህነት ለማውጣት የምታደርገውን ጥረት እንደ ሥጋት መመልከቷ የፖለቲካ ግብዝነቷ ማሳያ ነው።
ታሪካዊ ዳራዎችን ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንፈትሽ ግብፅ ኢትዮጵያን በውኃ ሀብቷ እንዳትጠቀም ስትጎነጉነው የኖረችው ሤራ ዘርፈ ብዙ ነው። በአንድ በኩል ኢትዮጵያ ፈፅሞ ዕውቅና ያልሰጠቻቸውን የ1929 እና የ1959 (እ.አ.አ) የቅኝ ግዛት ውሎችን እንደ ብቸኛ የሕግ ማዕቀፍ እያነሳች ለማስፈራራት ትሞክራለች።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ ኢትዮጵያ የውኃ ሃብቷን ለማልማት ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ብድር እና እርዳታ እንዳይሰጧት ያልቆፈረችው የዲፕሎማሲ ጉድጓድ አልነበረም።
ከዚህም አልፎ ኢትዮጵያ ዕረፍት አግኝታ ወደ ልማቷ እንዳታተኩር የውስጥ ግጭቶችን በሎጂስቲክስ እና በፋይናንስ በመደገፍ እንዲሁም ፀረ-ሰላም ኃይሎችን በማሰባሰብ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ስታራምድ ኖራለች።
ይሁን እንጂ ይህ የዘመናት ሤራ ከሽፎ፣ ኢትዮጵያ የውጭ የፋይናንስ በሮች መዘጋትን በገዛ ዜጎቿ አቅምና ላብ ተክታ ልማቷን እውን ስታደርግ ማየቷ ካይሮን ወደ ያልተገባ መደናገጥ ከትቷታል። የአሁኑ መሠረተ ቢስ መግለጫም የዚሁ ድንጋጤ ማስተጋቢያ ነው።
የኢትዮጵያ በዓባይ ውኃ ላይ ያላት አቋም ከመቼውም ጊዜ በላይ የጠራ፣ ዓለም አቀፍ የውኃ ሕግጋትን ያከበረ እና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ ነው።
ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ስትገነባም ሌሎች የተፋሰሱን ሀገራት በማግለል ሳይሆን፣ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ተመስርታ ነው። ለዚህም ማሳያው ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር ያደረገችው ተከታታይ ውይይት እና ያሳየችው ግልፅነት ነው።
ከዚህም ባሻገር የናይል ተፋሰስ ሀገራት የትብብር ማዕቀፍ (CFA) በቅርቡ ወደ ትግበራ መግባቱ የጋራ ተጠቃሚነትን በተግባር ያረጋገጠ እና የግብፅን የብቻ የበላይነት ፍላጎት ሕገ-ወጥነት ያጋለጠ ትልቅ ፖለቲካዊ እና ሕጋዊ ድል ነው።
የግብፅ የአሁኑ ጥያቄ እና ጩኸት ጊዜ ያለፈበት እና አዲሱን የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። ካይሮ ጉዳዩ ፈፅሞ የማይመለከታቸውን የሩቅ ኃይሎችና ተቋማት ደቦ በመሰብሰብ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር የምታደርገው ጥረት ዛሬ ላይ ውኃ አያነሳም።
የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ መንግሥት በዲፕሎማሲ ጫና እጁ የማይጠመዘዝ መሆኑን በሕዳሴው ግድብ ስኬት በተግባር አሳይቷል።
በመሆኑም ለግብፅ የሚበጃት ብቸኛው አዋጭ አማራጭ ከንቱ ከሆነው የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ እና የደቦ ዲፕሎማሲ ወጥታ፣ አዲሱን የትብብር ማዕቀፍ (CFA) በመቀበል ከኢትዮጵያ እና ከተቀሩት የተፋሰሱ ሀገራት ጋር በጋራ መሥራት ብቻ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ebc #ethiopia #gerd #nilebasin #africansolutions #abay #diplomacy

Comments