10 days ago
አሜሪካ የምትመካበት የጦር ሰፈር ፈጣሪ አዳነላት
#ethiopia | በእንግሊዝ የሚገኝው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ሊፈጸም የነበረው የሽብር ጥቃት መክሸፉ ተገለፀ።
በእንግሊዝ በሚገኘው ታዋቂው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ሊፈጸም የነበረ ታላቅ የሽብር ጥቃት መከሸፉ ተገልጿል።
የአሜሪካ ስትራቴጂካዊ የቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች እና ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የሚገኙበት RAF Fairford በተባለው የጦር ሰፈር አቅራቢያ ጥቃት ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በጦር ሰፈሩ እና በውስጡ ባሉ ወታደራዊ መሠረተ ልማቶች ላይ "ታላቅ ውድመት" ለማድረስ እቅድ አውጥተው እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ነበር ተብሏል።
ይህ የጦር ሰፈር አሜሪካ በዓለም አቀፍ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎቿ ወቅት እንደ ዋና መነሻ የምትጠቀምበትና የምትመካበት የጦር ሰፈሯ ነው።
ጥቃቱ ቢሳካ ኖሮ ትልቅ ዓለም አቀፍ ውጥረት ይፈጥር እንደነበር ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ጥብቅ የሆነ የደህንነት ጥበቃ እየተደረገ እንደሚገኝ ቢቢሲ ፅፏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #raffairford #usairforce #ukpolice #counterterrorism #militarybase #defencenews #nationalsecurity

22 days ago
የጸጥታ ተቋማት ሪፎርም፡ ሉዓላዊነትን ከመጠበቅ እስከ የዜጎችን ደኅንነት ማረጋገጥ
**************
የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት፣ ሰላምና የዜጎች ደኅንነት በጠንካራ የጸጥታ ተቋም ላይ የተመሠረቱ ናቸው። የዘመኑ የጸጥታ ምህዳር ግን ቀድሞ ከነበረው በእጅጉ ተለውጧል። ዛሬ ሀገራት ከባህላዊ የደኅንነት ስጋቶች በተጨማሪ ሳይበር ጥቃት፣ የተደራጀ ወንጀል፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ስጋቶችን መቋቋም ይጠበቅባቸዋል።
ይህ ሁኔታ የጸጥታ ተቋማት የሚሠሩበትን መንገድ እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል። በኢትዮጵያም በቅርብ ዓመታት የተካሄዱ የጸጥታ ዘርፍ ሪፎርሞች ተቋማትን በአደረጃጀት፣ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ፣ በመሠረተ ልማትና በአሠራር ለማዘመን ያተኮሩ ናቸው።
የጸጥታ ተቋማት ተልዕኮ የሀገርን ሉዓላዊነትና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት ከመጠብቅ ባሻገር የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት ማረጋገጥ፣ ወንጀልን መከላከልና ሕግ ማስከበርን ያካትታል።
በዘመናዊ የጸጥታ አሠራር ውስጥ ደግሞ ተቋም አደጋ ከተፈጠረ በኋላ ብቻ ምላሽ የሚሰጥ ሳይሆን ስጋቶችን ቀድሞ መለየት፣ መተንበይና መከላከል የሚችል አቅም መገንባት ይጠበቅበታል። በዚህ ረገድ የመረጃ አቅም፣ የምርመራ ብቃት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና ተቋማዊ ቅንጅት ወሳኝ ናቸው።
በተለይ የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ሳይንስ አቅምን ማሳደጉ የወንጀል ምርመራን ከግምትና ከግል ግንዛቤ ወደ ሳይንሳዊ ማስረጃ ለማሸጋገር የሚያግዝ ለውጥ ነው። የፌዴራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ የምርመራ ቴክኒኮችን ጨምሮ ዘመናዊ አቅምን እንድገነባ ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል።
የጸጥታ ምህዳሩ ወደ ዲጂታል ዓለም በመስፋፋቱ የሳይበር ደኅንነት የብሔራዊ ደኅንነት ዋና አካል ሆኗል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሳይበር ደኅንነት ፖሊሲም ዲጂታል ለውጥ ከሚያመጣቸው ዕድሎች ጎን ለጎን በዜጎች፣ በመረጃዎችና በወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ የሳይበር ስጋቶችን መቋቋም አስፈላጊ መሆኑን ያስቀምጣል።
ዘመናዊ መሣሪያ መግዛት ብቻ የጸጥታ ተቋምን ዘመናዊ አያደርገውም። ቴክኖሎጂውን በብቃት የሚጠቀም፣ መረጃን የሚተነትን፣ ሕግንና የሰብዓዊ መብት መርሆዎችን የሚያከብር የሰው ኃይል ከመሣሪያው እኩል ወሳኝ ነው።
በዚህም የፖሊስ ምርምርና ስልጠና ተቋማት የግጭት አመራር፣ የሰላም ግንባታ፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ያሉ ዘርፎችን በምርምር መዳሰሳቸው የሙያዊ አቅም ግንባታው አካል ነው።
የጸጥታ ተቋማት ሪፎርም በአንድ ጊዜ ተከናውኖ የሚያበቃ ሂደት አይደለም። የስጋቶች ባህሪ በየጊዜው ስለሚለዋወጥ ተቋማትም በተመሳሳይ ፍጥነት መማር፣ መላመድና መታደስ ይኖርባቸዋል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ የጸጥታ ተቋማት ሽግግር ከባህላዊ የጸጥታ አሠራር ወደ ተቋማዊ አደረጃጀት፣ ሳይንሳዊ ምርመራ፣ ዲጂታል አቅም፣ የሰው ኃይል ግንባታና የተቀናጀ የጸጥታ አሠራር የሚያመራ ሂደት ነው። የዚህ ሽግግር ዋና ግብም ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ብቻ ሳይሆን የሀገርን ሉዓላዊነት በማስጠበቅ፣ ሕግን በማስከበር እና የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት በዘላቂነት ማረጋገጥ ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopia #ebc #securityreform #regionalstability #endf #nationalsecurity #institutionbuilding

1 month ago
የፀጥታ ተቋማት ዘመናዊ ቁመና እና ፅናት ለሀገር አለኝታነትና ሉዓላዊነት
*********************
በሀገረ-መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሉዓላዊነት መከበር፣ የዜጎች ደኅንነት እና የሀገር ዘላቂ መረጋጋት ዋነኛ መሠረቱ ጠንካራ፣ ጽኑ እና ዘመናዊ የፀጥታ ተቋማት ናቸው።
የፀጥታ ተቋሞቻችን ዘመናዊነት በታጠቁት መሳሪያ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ዲስፕሊን፣ በሙያዊ ብቃት እና ማንኛውንም ስጋት በላቀ ስትራቴጂካዊ ዝግጁነት የመመከት አቅም ባለው ሠራዊት የሚገለጽ ነው።
ተቋማቱ ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነፃ በመሆን ለሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እና ለሕዝብ ደኅንነት ብቻ ታማኝ በመሆን እውነተኛ የሕዝብ አገልጋይነታቸውን አስመስክረዋል።
ዓለም በፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሳይበር እና በውስብስብ ጂኦ-ፖለቲካዊ ለውጦች ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ ተቋሞቻችን በሳይበር ደኅንነት፣ በዘመናዊ የመረጃ ፍሰት እና በላቁ የመከላከያ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ የማክሸፍና የመከላከል አቅማቸውን በከፍተኛ ደረጃ አሳድገዋል።
የሀገራችንን ዳር ድንበር አስከብሮ የሀገርን ክብር እና ነፃነት ለማስጠበቅ በሚደረግ እያንዳንዱ እርምጃ ውስጥ የጀግኖቻችን ውድ ህይወት ተከፍሎበታል።
ይህ የተከፈለው መስዋዕትነት ለነገው ትውልድ የምትሻገር የተረጋጋች፣ የጸናች እና የተከበረች ኢትዮጵያን የማስረከብ ታላቅ ታሪካዊ አደራ ነው።
ጳጉሜን 3 የምናከብረው የጽናት ቀን ሀገርን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም ያለመታከት የሚተጉ፣ ለሀገር ፍቅር እና ለሕዝብ ሰላም ሲሉ የእናት ሀገር ጥሪን አክብረው በየግንባሩ የቆሙ የፀጥታ አካላትን ውሎ፣ ጽናት እና ከፍተኛ የሀገር ፍቅር የምናስብበት ታላቅ ዕለት ነው።
በዚሁ የጽናት ቀን ለሀገር ፍቅር፣ ለሉዓላዊነት እና ለሕዝብ ሰላም ሲሉ ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ የጀግኖቻችንን መስዋዕትነት ማሰብ፣ ማክበር እና በሥራ ላይ ያሉ የፀጥታ አካላትን ሞራል መገንባት የሁላችንም የዜግነት ግዴታ ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ebc #dayofresilience #nationalsecurity #ethiopiandefense #sovereigntyandpeace #ethiopiarising

የባህር በር፤ የአሁን ፍላጎት ወይስ የትውልድ ዘመን ጥያቄ?
***************
ኢትዮጵያ በብዙ ሺህ ዓመታት ታሪኳ ከቀይ ባህርና ከዓለም የባህር ንግድ መስመሮች ጋር በታሪካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በስትራቴጂያዊ ትስስር የኖረች ሀገር ናት። ዛሬ ግን ከባህር በር የራቀች የብዙ ሚሊዮኖች ሕዝብ ሀገር መሆኗ፣ ጉዳዩን ከቀጥታ የንግድ ልውውጥ ባሻገር ሰፊ ሀገራዊና ቀጣናዊ የመዋቅር ልማት ጥያቄ ያደርገዋል።
የባህር በር ጉዳይ ሲነሳ ጥያቄው “ኢትዮጵያ ዛሬ ወደብ ትፈልጋለች?” በሚለው ብቻ የሚወሰን አይደለም። ይልቁንም እየጨመረ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር፣ እያደገ ያለውን ኢኮኖሚና የመጪውን ትውልድ ፍላጎት በዘላቂነት እንዴት ማስተናገድ ይቻላል? የሚለው ዋናው መነሻ ነው።
በቀይ ባህርና በአፍሪካ ቀንድ ያለው ስትራቴጂያዊ አቀማመጥ የኢትዮጵያን ደህንነት ከአካባቢው የጂኦፖለቲካ ሁኔታ ጋር በቀጥታ ያገናኛል። ሀገሪቱ ከውጭ ወረራ ጋር በተያያዘ ባሳለፈቻቸው ታሪካዊ ክስተቶች የቀጣናው የባህርና የየብስ መስመሮች ያላቸው ከፍተኛ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ተረጋግጧል።
የቀይ ባህር አካባቢ የንግድ መስመር ብቻ ሳይሆን የሀገራት የደህንነትና የስትራቴጂ ፍላጎቶች የሚገናኙበት ቀጣና በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ አካባቢውን በራሷ የብሔራዊ ደህንነት እይታ እንድትመለከተው ያስገድዳታል። ዛሬ የሚነሳው የባህር በር ጥያቄም የትናንት ታሪክን ለመመለስ ሳይሆን፣ ከታሪካዊ ተሞክሮዎች በመማር ነገ እንዳይደገም የሚያስችል የተሻለ የብሔራዊ ደህንነት አስተሳሰብ የመገንባት ጉዳይ ነው።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ አገልግሎትና የንግድ ዘርፎች የሚያመነጩት ምርት ወደ ዓለም ገበያ በተሻለ ሁኔታ እንዲደርስ የባህር በር ተደራሽነት ዋናው የሎጂስቲክስ መሠረት ነው። በተመሳሳይ መልኩ ማሽነሪዎች፣ ጥሬ ዕቃዎችና ሌሎች የልማት ግብዓቶች ወደ ሀገር ለማስገባት አስተማማኝ የባህር ንግድ መስመር ወሳኝ ነው። ስለሆነም የባህር በር ጥያቄ በራሱ የመጨረሻ ግብ ሳይሆን ምርትን፣ ንግድንና ኢኮኖሚያዊ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የሚያገለግል ቁልፍ መሣሪያ ነው።
የባህር በር ጉዳይ ከዛሬው ትውልድ በላይ የነገውን ትውልድ ያማከለ ነው። የሚመጣው ትውልድ በቁጥር ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ፍላጎት፣ በንግድ፣ በሥራ ዕድልና በዓለም አቀፍ ተሳትፎ የተሻለ አቅም ይፈልጋል። ዛሬ የሚገነቡ የመንገድ፣ የባቡር፣ የሎጂስቲክስና የወደብ አማራጮች የነገው ትውልድ ዋና የንግድ አውታር ይሆናሉ።
በአጠቃላይ “የባህር በር የአሁን ፍላጎት ነው ወይስ የትውልድ ዘመን ጥያቄ?” የሚለው ጉዳይ ሁለቱንም የሚያጠቃልል ነው። አሁን የሚያስፈልገው የንግድና የኢኮኖሚ አማራጭ ሲሆን፣ ለነገው ትውልድ ደግሞ በዓለም ንግድ የበለጠ ተወዳዳሪ የሆነች፣ የራሷን ሀብት ወደ ምርት የምትቀይርና ለዜጎቿ ሰፊ ዕድል የምትፈጥር ኢትዮጵያን የማስረከብ ራዕይ ነው።
በኢንቲሃድ አብራር
#ethiopia #seaoutlet #redsea #nationalsecurity #ethiopianeconomy #diplomacy

Sponsored by
Surafel
2 months ago
u12a8u12a0u1263u1275 u12c8u12f0 u120du1305 u12e8u1200u1308u122d u134du1245u122d
https://youtu.be/ePwPHuvoQ... #ethiopiandefenseforces #airborneandcommando #ethiopianarmy #nationalsecurity ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"ExternalUrl","__isEntity":"ExternalUrl","url":"https://l.facebook.com/l.p...
ከአባት ወደ ልጅ የሀገር ፍቅር
https://youtu.be/ePwPHuvoQ... #ethiopiandefenseforces #airborneandcommando #ethiopianarmy #nationalsecurity
2 months ago
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አቅም አዲስ ምዕራፍ፤ በራስ አቅም የመታጠቅና የቴክኖሎጂ ልህቀት
******************
በዘመናችን የአንድ ሀገር ወታደራዊ አቅም የሚለካው በወታደሮቿ ቁጥር ብዛት ወይም በውጭ ሀገራት የጦር መሳሪያዎች ጥገኝነት ሳይሆን፣ በራስ አቅም በሚከናወን የማምረት ብቃት እና በቴክኖሎጂ ልህቀት መሆኑ አከራካሪ አይደለም።
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የመከላከያ ዘርፏን በቴክኖሎጂና በሀገር ውስጥ ምርት ለማጠናከር የያዘችውን ራዕይ በስኬት እየተገበረች ትገኛለች።
ሀገራችን በጦር መሳሪያዎች ጥገና፣ በታንኮችና ተሽከርካሪዎች እድሳት፣ በአቪዬሽን ጥገና እንዲሁም በጥይት ማምረት ዘርፍ የቆየ ልምድ ያላት ቢሆንም፤ ከለውጡ በኋላ በመደመር መንግሥት መሪነት በራስ አቅም የመታጠቅና የቴክኖሎጂ ባለቤት የመሆን ስራዎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።
በዚህም መሠረት የጥይት ምርት መጠንን ማሳደግ፣ የወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን አቅም ማሻሻል፣ የድሮን ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ማልማትና የመከላከያ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ማስፋፋት ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ሆነዋል።
ይኸው የኢንዱስትሪው እድገት ዘመናዊ ጦርነቶች የሚጠይቋቸውን የመረጃ ቴክኖሎጂ፣ የሳተላይትና የኤሌክትሮኒክስ ስርአቶች በጥረት ለማሟላት ያስችላል።
የኢትዮጵያ የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች የጦር መሳሪያዎችን እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ የማምረትና የመጠገን አቅማቸውን በከፍተኛ ደረጃ አሳድገዋል።
ለአብነት በመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ጋፋት አርማመንት ዘመናዊ ቀላልና ከባድ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያዎችን በማምረት ላይ ሲሆን፣ ሆሚቾ አሙኒሽን ደግሞ ጥይቶችንና ከባድ መድፎችን በስፋት በማምረት ላይ ይገኛል።
በተጨማሪም የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ ጥንካሬ ያላቸውን የውጊያና የሰው ማጓጓዣ የታጠቁ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን (APCs) እና ታንኮችን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ በማምረትና በማደስ ላይ ያተኮረ ስራ እያከናወነ ይገኛል።
በሌላ በኩል ደጀን አቪዬሽን ኢንጂነሪንግ የጦር ጄቶችንና ሄሊኮፕተሮችን ሙሉ ጥገናና ማሻሻያ ከማድረግ ባለፈ፣ ዘመናዊ የድሮን ቴክኖሎጂዎችንና የራዳር ሥርዓቶችን የመገንባት ከፍተኛ አቅም ላይ ደርሷል።
ይህ ስትራቴጂካዊ ስኬት የመከላከያ ሠራዊቱን በቀጣናው ግዙፍና በቴክኖሎጂ የበለፀገ የማይበገር ሃይል ያደረገው ሲሆን፣ ቀደም ሲል ለጦር መሣሪያ ግዢ ይወጣ የነበረውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በማዳን ሀብቱ ለሌሎች የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ፕሮጀክቶች እንዲውል አስችሏል።
ይህ የመከላከያ ዘርፍ ማሻሻያ ለሀገራዊ ደህንነት ከሚሰጠው ዋስትና ባሻገር፤ የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቀነስ፣ ሰፊ የሰራ እድል በመፍጠር፣ የብረት፣ ኬሚካልና ሶፍትዌር ኢንዱስትሪዎችን በማነቃቃት እንዲሁም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርምር ጋር በማስተሰረፍ ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ውህደት ፈጥሯል።
የመከላከያ ኢንዱስትሪው በራስ አቅም የመቆም ጉዞን ማፋጠኑ፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ወታደራዊና ጂኦፖለቲካዊ ሚዛን ውስጥ ያላትን ጉልህ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ይበልጥ የሚያጠናክርም ነው።
#ethiopia #defenseindustry #selfreliance #nationalsecurity #dronetechnology

የታፈነውን የሀገር እስትንፋስ ማስለቀቅና የተገፈፈውን ሀገራዊ ገመና የመሸፈን የትውልድ አደራ
*****************
የባህር በር ማጣት የሀገርን የደህንነት ምስጢር፣ የህዝብን ኪስ እና የሀገራችን ኢኮኖሚ እስትንፋስ በሌሎች እጅ አሳልፎ የሚሰጥ እጅግ አንገብጋቢ የህልውና ጉዳይ ነው።
እኛ ኢትዮጵያውያን በችግርም ሆነ በደስታ ጊዜ ገመናችንን ሸፍነን በክብር መኖር ከፍተኛ ማህበራዊ እሴታችን ያደረግን ህዝቦች ብንሆንም፣ የባህር በር አልባነታችን ግን ይህንን ክብራችንን ገፎ ገመና አልባ አድርጎናል።
ዛሬ ሀገር የምታስገባው እያንዳንዱ ስትራቴጂካዊ የደህንነት ቁሳቁስም ሆነ ወደ ውጭ የምትልከው አንጡራ ሀብት በሌሎች ሀገራት እጅና እይታ ስር ማለፉ፣ ሀገራዊ ምስጢራችንን ለአደባባይ ያጋለጠው ሲሆን፤ አንድ ግለሰብ በቤቱ ውስጥ የሚበላውን፣ የሚጠጣውን፣ የሚገዛውንና የሚሸጠውን ጎረቤቱ እንዲያውቅበት እንደማይፈልገው ሁሉ፣ የኢትዮጵያም የዲጂታል እና የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ በሌሎች መዳፍ ላይ መውደቁ ሀገራችን በቀላሉ ሊጠለፍ ለሚችል የጂኦ-ፖለቲካ ሴራ አጋልጧታል።
ታሪካዊ ጠላቶቻችን ማናቸውንም ሀገራዊ እንቅስቃሴዎቻችንን ለማጨናገፍ እድል የሚያገኙትም ይኸው ሉዓላዊ ገመናችን በወደብ አልባነታችን ሳቢያ በመገፈፉ ነው።
በሌላ በኩል፣ ዛሬ በገበያዎቻችን ላይ የምናየው የዋጋ ንረት ዋነኛ ምንጭ የወደብ አልባነታችን የፈጠረው የሎጂስቲክስ ስብራት ጠባሳ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉዳዩን ሲገልጹት አንድ ምርት ከቻይና ተነስቶ ጎረቤት ሀገር ናይሮቢ ከሚሸጥበት ዋጋ ይልቅ፣ ወደ እኛ ሀገር ሲገባ የባህር በር ባለመኖሩ ምክንያት ብቻ ቢያንስ የ30 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዲኖረው ያስገድዳል።
ከባህር በር ባለቤት ሀገራት አንጻር ሲታይ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ ተጨማሪ የሎጂስቲክስ ወጪ በቀጥታ የሚጫነው በሸማች ትከሻ ላይ ሲሆን፣ ምርቶች በረዥም የየብስ ጉዞ ሲጓተቱ ጥራታቸው ይበላሻል፣ ወሳኝ የንግድ ኮንትራቶች ይሰረዛሉ፤ በዚህም የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ እግሩ ተጠፍንጎ ይያዛል።
ከፖለቲካዊ ተጋላጭነትና ከኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ባሻገር የባህር በር ጥያቄን እጅግ ስሜት ሰጪ እና ቀጥተኛ የሞትና የሽረት ጉዳይ የሚያደርገው በጤናው ዘርፍ ላይ የሚያደርሰዉ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ነው።
ኢትዮጵያ የህይወት አድን መድሃኒትና የህክምና መሳሪያ ፍላጎቷን የምታሟላው ከውጭ በማስገባት ሲሆን፣ እጅግ ጥብቅ የሆነ የሙቀት ቁጥጥር የሚፈልጉ ክትባቶችና መድሃኒቶች፣ በሌሎች ሀገራት ወደብ ላይ በሚፈጠር ቢሮክራሲያዊ መጓተትና በረዥም ጉዞ ለከፍተኛ ፀሐይ ሲጋለጡ ፈዋሽነታቸው ይቀንሳል።
የራሳችን ወደብ ቢኖረን ኖሮ፣ የመድሃኒት የሎጂስቲክስ ጊዜን በግማሽ እንዲሁም የትራንስፖርትና የችርቻሮ ዋጋን እስከ 25 በመቶ በመቀነስ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ እናቶችና ህጻናትን ህይወት መታደግ ይቻላል።
በዓለም አስረኛ የሆነውን ግዙፍ የህዝብ ቁጥር የያዘችና ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የምታስተዳድር ሀገር ከምጽዋ ጫፍ እስከ ሞቃዲሾ ጥግ በተዘረጋው አምስት ሺህ ኪሎሜትር ርዝመት ባለው ሀብት በሞላው የውሀ ዳርቻ ላይ ተከባና ታፍና እስከ ወዲያኛው ትኖራለች ብሎ ማሰብ የዋህነት ብቻ ሳይሆን ትልቅ የጂኦ-ፖለቲካ ሴራ ነው።
ይህ አንገብጋቢ የህልውና ጥያቄ በክፋት በሮችን ዘግቶ ኢትዮጵያን ማፈን ለማንም ሀገር ዘላቂ አዋጭነት የለውም። ስለዚህ የባህር በር ባለቤትነት የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የተገፈፈውን ሀገራዊ ገመና የመሸፈን፣ የዜጎችን ኪስ የማዳን እና የሀገርን ደህንነትና ኢኮኖሚ የመታደግ ሀገራዊ አጀንዳችን በመሆኑ፣ ይህን አደራ በአሸናፊነትና በዲፕሎማሲያዊ ጥበብ መወጣት የዚህ ትውልድ የማይታለፍ የታሪክ ግዴታ ነው።
በረከት ሽመልስ
#redseaaccess #ethiopia #nationalsecurity #economicgrowth #logistics

የኅብረ ብሔራዊ አንድነት አርማ በፈተናዎች መካከል ዐለት ሆኖ የፀናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት
**********************
በአንድ ሀገር የኅልውና ታሪክ ውስጥ የሀገርን ሉዓላዊነት፣ የሕዝብን ሰላምና የድንበር ደኅንነትን ለማስከበር ከፊት ተሰልፎ መስዋዕትነት የሚከፍል ጠንካራ መከላከያ ሠራዊት መገንባት እጅግ ወሳኝ መሆኑ ይታመናል።
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በረዥም ታሪኩ በርካታ ውስብስብ እና ፈታኝ ሁኔታዎችን ቢያልፍም፣ በሚያሳየው ወደር አልባ ፅናት እና በፅኑ የሀገር ፍቅር መንፈስ የሀገርን ሰላምና አንድነት በማስጠበቅ ረገድ የማይናወጥ የወቅቱ የፅናት ምልክት ሆኖ ቀጥሏል።
ሠራዊቱ የሀገርን ደኅንነት ከውስጥም ሆነ ከውጭ ከሚቃጡ አደጋዎች የመጠበቅ ዋነኛ ግዴታውን በብቃት እየተወጣ ይገኛል።
በተለያዩ ጊዜያት የሀገርን ሰላም ለማናጋት፣ የሕዝቦችን አብሮ መኖር ለማደፍረስ እና ሀገርን ለማፍረስ የሚሸረቡ የባንዳዎችና የጠላቶች ሴራዎችን በከፍተኛ ወታደራዊ ዲስፕሊን፣ በስልታዊ አመራር እና በጀግንነት እያከሸፈ ነው።
ንጹሃን ዜጎች ከጥቃት እንዲጠበቁ እና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ውድ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠት የሕዝብን ደኅንነት በተጨባጭ እያረጋገጠ ይገኛል።
ከዚህም ባሻገር የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የብሔር፣ የሃይማኖት እና የቋንቋ ልዩነቶች ሳይበግሩት ሁሉንም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአንድ ዓላማ ስር ያሰባሰበ እውነተኛ የኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማሳያ ሆኗል።
ይህ የሠራዊቱ ጥንካሬ የሚመነጨው ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ከተጣመሩ አባላቱ የጋራ ፍቅር እና ለአንዲት ሀገር ከቆመ ፅኑ መርህ መሆኑ ሲገለጽ፣ እያንዳንዱ አባል የግል ማንነቱን ለሀገር ሉዓላዊነት አሳልፎ በመስጠት ሕዝቦች የአብሮነት አርዓያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
ሀገራችን በታሪኳ ከተጋፈጠቻቸው ዘመናዊ ፈተናዎች፣ የጂኦፖለቲካ ጫናዎች እና የውስጥ አለመረጋጋቶች አንጻር የመከላከያ ሠራዊቱ የተጫወተው ሀገራዊ ሚና እጅግ የጎላ ነው።
ሠራዊታችን ከቀላል ወታደራዊ ግዴታ ባለፈ የሀገር የጀርባ አጥንት፣ የሰላም ዘበኛ እና የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን ማህተም በመሆን የሚያስመዘግበው አንፀባራቂ ገድል፣ በታሪክ ማህደር ውስጥ ሁልጊዜ በክብር ሲወደስ የሚኖር መሆኑ ተብራርቷል።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopianarmy #endf #nationalsecurity #ethiopia #unityindiversity

የኢትዮጵያ የፀጥታና ደህንነት ኃይል ግንባታ | ከ2014ቱ የመንግሥት ቃል እስከ ዛሬው ስኬት
#ebcdotstream #ethiopiansecurity #nationalsecurity #pmabiyahmed #ethiopiandefense #securityreform
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
#ebcdotstream #ethiopiansecurity #nationalsecurity #pmabiyahmed #ethiopiandefense #securityreform
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
Sponsored by
Surafel
3 months ago
የኢትዮጵያ የደኅንነት እና የፀጥታ ተቋማት ሁለንተናዊ አቅም
**************************
ኢትዮጵያ ታሪካዊ ክብሯን እና የሕዝቦቿን ሰላም ለማስጠበቅ የገነባቻቸው የደኅንነት እና የፀጥታ ተቋማት በማንኛውም ዓይነት የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላት ሤራ የማትበገር እና የማትሸበር ጽኑ ሀገር መሆኗን በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ።
ይህ አስተማማኝ አቅም የተገነባው ከሀገር መከላከያ ባሻገር ዘመኑ በደረሰበት ከፍተኛ የቴክኖሎጂ እና የሥልጠና ልክ ራሳቸውን ባደራጁ ልዩ ልዩ የደኅንነት፣ የቴክኖሎጂ እና የስትራቴጂክ ተቋማት ጥምረት ነው።
በዚህ ዘመናዊ የደኅንነት መዋቅር ውስጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው የኢፌዴሪ አየር ኃይል የላቁ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎችን እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስልታዊ ድሮኖችን በመታጠቅ የአየር ክልሉ ፍፁም የማይደፈር አድርጎታል።
ከዚህ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የኢትዮጵያን የወደፊት ላይ ጥቅም እና ቀጣናዊ ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ሌት ተቀን እየተጋ የሚገኝ ስልታዊ ተቋም ነው።
የዘመኑ ጦርነት ከሜዳ ባለፈ በቴክኖሎጂ የሚመራ በመሆኑ በሳይበር ምህዳር ኢትዮጵያን ለመጠበቅ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (INSA) እና የስትራቴጂክ መረጃዎችን አስቀድሞ በመተንተን ሴራዎችን የሚያከሽፈው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት (NISS) ሌሎቹ የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንቶች ናቸው።
እነዚህ ተቋማት የሀገርን የዲጂታል ሉዓላዊነት የባንክ እና የኮሙኒኬሽን መዋቅሮችን ከሳይበር ጥቃት ከመታደግ ባለፈ ጠላቶች የሚነዙትን የሥነልቦና ጦርነት እና ድብቅ ሤራዎች አስቀድመው በማምከን ረገድ ወደር የለሽ አቅም ገንብተዋል።
ይህ የተቀናጀ የተቋማት ግንባታ ኢትዮጵያ በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆን የማትነቃነቅ በልጆቿ ጥበብ እና ፅናት የምትመራ መሆኗን በተግባር ያረጋገጠ እና ለትውልድ የሚተርፍ ታላቅ ሀገራዊ ኩራት ነው።
በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #nationalsecurity #airforce #maritimedefense #insa #cybersecurity #ethiopiadefends

4 months ago
u12e8u1240u12cdu1235 u121bu12d8u12e3 u1323u1262u12ebu12ceu1279 u12a5u1295u12f4u1275 u1270u1218u1271? | u12a2u1275u12ee u1218u120du1215u1245 |
#ethiomelhik #electionresults #nationalsecurity #egypteritreaconspiracy #publicdecision #sovereigntyprevails ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የቀውስ ማዘዣ ጣቢያዎቹ እንዴት ተመቱ? | ኢትዮ መልሕቅ |
#ethiomelhik #electionresults #nationalsecurity #egypteritreaconspiracy #publicdecision #sovereigntyprevails
4 months ago
u12e8u12a8u1230u1228u12cd u1261u12f5u1295 u1328u12abu129d u12e8u1326u122du1290u1275 u12a0u12cbu1305 | Ethio Melhik | TPLF | War Proclamation | #ethiomelhik #nationalsecurity #abiyahmed #berhanujula #tplfcrisis #ethiopianarmy ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የከሰረው ቡድን ጨካኝ የጦርነት አዋጅ | Ethio Melhik | TPLF | War Proclamation | #ethiomelhik #nationalsecurity #abiyahmed #berhanujula #tplfcrisis #ethiopianarmy
4 months ago
Safeguarding the dreams of 130 million people requires a modern, tech-driven defense. Ethiopia has built an unshakeable digital and military shield.
#nationalsecurity #digitalshield #ethiopiarising #hornofafrica
4 months ago
ከኢኮኖሚ ዋስትና እስከ ቀጣናዊ ተሰሚነት፦ የባሕር በር ፍላጎት እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ጥቅሞች
************************
አንድ ሀገር የባሕር በር ማግኘቱ ከቀላል የንግድ ልውውጥ ባለፈ፣ የፖለቲካ ነፃነቱ፣ የኢኮኖሚ ዋስትናው እና የብሔራዊ ደኅንነቱ ማረጋገጫ ነው።
ኢትዮጵያ ካላት ግዙፍ የሕዝብ ቁጥር እና ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ ከሚገኘው ኢኮኖሚዋ አንጻር፣ ቀጥተኛ የባሕር በር ማጣቷ በሉዓላዊነቷ እና በረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ጥቅሟ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አለው።
በመሆኑም የባሕር በር ጥያቄ የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን፣ የሀገራችንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እና ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስጠበቅ ያለመ የሕልውና ጉዳይ ነው።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የወጪ እና ገቢ ንግዷን በአንድ ወደብ ብቻ ማካሄዷ ለከፍተኛ ጂኦፖለቲካዊ ስጋት እና ለሎጂስቲክስ መስተጓጎል ተጋላጭ አድርጓታል።
የጅቡቲ ወደብን ለመጠቀም በየዓመቱ የምታወጣው ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ የውጭ ምንዛሬ በሀገራችን የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት፣ በምርቶች የትርፍ ህዳግ እና በዜጎች የኑሮ ውድነት ላይ ቀጥተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል።
ስለሆነም የራስን የባሕር በር ወይም አስተማማኝ እና ዘላቂ የወደብ አማራጮችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማግኘት የሀገር ውስጥ ገበያን ከማረጋጋቱም በላይ፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚኖረንን የኢኮኖሚ ትስስር እና የኃይል ሚዛን በብልሃት ለመምራት ያስችላል።
ሀገራችን እየተገበረችው ላለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለጀመረችው ሽግግር ስኬት በተለይም እንደ "ኢትዮጵያ ታምርት" ላሉ ብሔራዊ ንቅናቄዎች ውጤታማነት ቀልጣፋና ተደራሽ የሎጂስቲክስ መስመር መኖሩ ወሳኝ ነው።
የባሕር በር ባለቤትነት የሀገር ውስጥ አምራቾች የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶቻቸውን በፈጣን ሂደት እና በተመጣጣኝ ወጪ በቀጥታ ወደ ዓለም ገበያ እንዲልኩ ሰፊ ዕድል ይፈጥራል።
ይህ ተወዳዳሪነት ደግሞ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በስፋት ለመሳብ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የማምረት አቅም ለማሳደግ እና የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ አስተማማኝ ዋስትና ይሆናል።
የባሕር በር መኖር ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው ባሻገር ብሔራዊ ደኅንነትን ለማስጠበቅ እና በቀጣናው አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት ቁልፍ መሣሪያ ነው።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ አቅራቢያ የሚስተዋሉ የፀጥታ ስጋቶችን፣ የባሕር ላይ ወንበዴነትን እና የዓለም አቀፍ ኃይሎችን የጂኦፖለቲካ ሽኩቻ ለመመከት ዘመናዊ የባሕር ኃይል በከፍተኛ የሰው ኃይል እና ቴክኖሎጂ መልሳ ገንብታለች።
አስተማማኝ የባሕር በር ማግኘት የባሕር ኃይሉን ስምሪት ውጤታማ በማድረግ፣ ሀገራችን በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር የደኅንነት መዋቅር ያላትን ተሰሚነት፣ የድርድር አቅም እና የሰላም አስከባሪነት ሚና በእጅጉ ከፍ ያደርገዋል።
የባሕር በር ጉዳይ የአጭር ጊዜ የፖለቲካ አጀንዳ ሳይሆን፣ ከትውልድ ትውልድ የሚሻገር የኢትዮጵያ የብሔራዊ ጥቅም ማዕቀፍ ነው።
ሀገራችን በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች፣ በጋራ ልማት መርሆዎች፣ በሰላማዊ ድርድር እና በሕጋዊ መንገዶች የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት የኢኮኖሚ ጥገኝነትን ለመቀነስ፣ የንግድ መስመሮችን ለማስፋፋት እና የተሟላ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረግ ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ ሂደት ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #seaaccess #redsea #geopolitics #hornofafrica #nationalsecurity #ebc

8 months ago
አውስትራሊያ ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ዜጎቿን "አልቀበልም" አለች
#ethiopia | የአውስትራሊያ መንግስት በሶሪያ የሚገኙ ዜጎቹን በተመለከተ ያለውን ጠንካራ አቋም ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ እንደተናገሩት፣ ማንኛውም በሶሪያ የሚገኝ አውስትራሊያዊ ከአሸባሪው አይኤስ ጋር ንክኪ ካለው ወደ አውስትራሊያ የመግባት ተስፋው ዝቅተኛ ነው።
የምርመራ ሂደት እና ቅድመ ሁኔታዎች
በቅርቡ ከሶሪያ እስር ቤቶች የተፈቱ 34 አውስትራሊያውያንን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፦
* ጥብቅ ምርመራ፦ ማንኛውም ግለሰብ ከመመለሱ በፊት አስፈላጊው የደህንነት ምርመራ ይደረግበታል።
* ርዕዮተ-ዓለም፦ "የአይኤስን አክራሪ ርዕዮተ-ዓለም የደገፉ ግለሰቦችን በጭራሽ አንቀበልም" ሲሉ አልባኔዝ በግልጽ አስታውቀዋል።
* የሕግ ቅጣት፦ በአውስትራሊያ ሕግ መሠረት የአይኤስ አባል ሆኖ መገኘት እስከ 25 ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ተገልጿል።
ውስጣዊ ተቃውሞ
ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ግን በሀገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ላይ ቅሬታን ፈጥሯል። አንዳንድ የፓርላማ አባላት የዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ መብት እና መንግስት የወሰደውን ጥብቅ አቋም በመቃወም አስተያየታቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።
በአሁኑ ወቅት መንግስት እነዚህን ዜጎች ወደ ሀገር ለመመለስ የሚያደርገው ጥረት ከከፍተኛ ምርመራ እና ከርዕዮተ-ዓለም ነፃ የመሆን ማረጋገጫ ጋር የተያያዘ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #australia #thiqah #anthonyalbanese #syria #isis #nationalsecurity #globalnews #skynews #ashraqalawusat

Comments