1 month ago
የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ጠንቅ ነው - የኤርትራ ባሕረኞች ማህበር ፕሬዝደንት
*************
በአፍሪካ ቀንድና በቀይ ባሕር አካባቢ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ፥ የቀጣናው ሀገራት በተለይም ኢትዮጵያና ኤርትራ በመተማመንና በጋራ ጥቅሞች ላይ የተመሠረተ ጠንካራ ግንኙነት መመሥረት እንዳለባቸው የኤርትራ ባሕረኞች ማህበር ፕሬዝደንት ፓውሎ አንቶኒዮ ገለጹ።
የኤርትራ ባሕረኞች ማህበር ፕሬዝደንት ፓውሎ አንቶኒዮ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ከአካባቢው አገራት ይልቅ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሚኖረው ሰላማዊ ጉርብትና እና በ«ሰጥቶ መቀበል» መርህ ላይ አብሮ የመበልጸግ ፍላጎት በቀጣናው ላይ አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን ቁልፍ ሚና አለው።
የውስጥ ደኅንነት ሥጋት ያለባቸው ሥርዓቶች የውጭ ኃይሎችን በመጋበዝ ሥልጣናቸውን ለማራዘም የሚያደርጉት ጥረት ለቀጣናው ሰላም ጠንቅ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝደንቱ፤ በተለይም የግብፅ ኃይሎች በኤርትራ መገኘት ለኢትዮጵያም ሆነ ለአካባቢው ሰላም እንደማይበጅ አስገንዝበዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚያመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም ረገድ መጀመሪያ ተጠቃሚ መሆን ያለባቸው የቅርብ ጎረቤት ሀገራት መሆናቸውን የገለጹት ፓውሎ አንቶኒዮ፤ በተመሳሳይ የኤርትራ ወደቦች ክፍት ሆነው ለኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ከሩቅ ሀገር ከሚመጡት ግብፆች ይልቅ ለቀጣናው ሕዝቦች ቀጥተኛ ጠቃሜታ እንዳለው አመልክተዋል።
በአሁኑ ወቅት በቀይ ባሕር ዙሪያ የሚታዩት የጸጥታ ሥጋቶች ለኤርትራም ሆነ ለኢትዮጵያ እኩል ሥጋቶች በመሆናቸው፥ ሁለቱ ሀገራት አካባቢያዊ ሰላምን ለማረጋጋት በጋራና በትብብር መሥራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
የሥጋት መነሻዎችን ለይቶ ወደ ሰላማዊና ቀጣናዊ ትብብር ማምራት ከተቻለ የውጭ ኃይሎች በመካከላቸው እየገቡ የሚፈጥሩት ሥጋት እየቀነሰ የሚመጣ በመሆኑ፥ ሀገራቱ የቤት ሥራቸውን በአግባቡ መሥራት እንዳለባቸውም አመልክተዋል።
የግብፅና የኤርትራ መሪዎች በተደጋጋሚ የሚያወጧቸው «የቀይ ባሕር ደኅንነትን የመጠበቅ መብት የባሕሩ ተጎራባች ሀገራት ብቻ ነው» የሚሉት መግለጫዎች፤ ኢትዮጵያ ያነሳችውን የባሕር በር ፍላጎት ጥያቄ ለማደናቀፍና የኢትዮጵያን ስም ሳይጠቅሱ ለመቃወም የታለመ እንደሆነ ፕሬዝደንቱ አጋልጠዋል።
በአሁኑ ወቅት ከኤደን ሰርጥ እስከ ባቢል መንደብ ባለው ወሳኝ የዓለም መተላለፊያ መስመር ላይ የሚታየው አለመረጋጋት ከፍተኛ ሥጋትን መፍጠሩን የጠቀሱት የማህበሩ ፕሬዝደንት፤ ሀገራቱ ያላቸውን የተፈጥሮ ጸጋና የጂኦ-ፖለቲካ አቀማመጥ በአግባቡ ባለመጠቀማቸው ምክንያት ዕቃዎች ቀይ ባሕርን አልፈው ዱባይ ከሄዱና ከተጫኑ በኋላ ተጨማሪ የትራንስፖርት ወጪ ተከፍሎባቸው ወደ ቀጣናው እንዲመለሱ ማድረጉ በዜጎች ላይ ድህነትን የሚያውጅ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህንን ተጨባጭ ሁኔታ ለመቀየርም የቀጣናው መንግሥታት የተሻለ ዕድላቸውን በጋራና በትብብር ሊወስኑ እንደሚገባም ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።
በመሐመድ ፊጣሞ
#ethiopianbroadcastingcorporation #redseasecurity #regionalcooperation #geopolitics

Comments