1 day ago
የኢትዮጵያ ትንሳኤ !
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብስራት አድማስ እና የዓለም ዓይኖች ማረፊያ እየሆነች ትገኛለች።
እሷ የታሪክ እምብርት፣ የሰው ዘር መገኛ እና የነፃነት ማኅተም ናት። ዛሬ ደግሞ በልጆቿ ጽናት እና በማይበገረው ህዝባዊ ወኔያቸው አዲስ የትንሳኤ ምዕራፍ እየተቀኘች ትገኛለች።
ይህ የትንሳኤ ብርሃን ለራሷ ብቻ ሳይሆን፣ ለመላው ጥቁር ህዝብ እና ለአፍሪካ አህጉር አዲስ የብስራት አድማስ እየቀደደ ነው።
የዚህች ታላቅ ሀገር ትንሳኤ ከባዶ የተነሳ ሳይሆን፣ ከጥንታዊው የክብር ሥርዓቷ እና ካልተደፈረው ማንነቷ የተቀዳ ነው። አፍሪካ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሥር በነበረችበት የጨለማ ዘመን፣ ኢትዮጵያ የነፃነት ብቸኛ ፋኖስ ሆና እንዳበራች ሁሉ፣ ዛሬም ያ የወርቃማ ታሪክ በዘመናዊው ትውልድ ልብ ውስጥ እንደገና እየተቀጣጠለ ይገኛል።
በመሆኑም ይህች የአናብስት ምድር የገጠሟትን ዘመናዊ ፈተናዎች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎች እና ማህበራዊ ውጣ ውረዶች በራሷ ልጆች ጥረት እና ጥንካሬ እያሸነፈች ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ህዝብ ታታሪነቱ፣ ለነጻነት ቀናኢነቱ፣ የማይበገረው ፅናቱ እና ለሀገሩ ያለው ጥልቅ ፍቅር አዲሱን የትንሳኤ መንገድ እያቀናው ነው።
በዚህ ጽናት ላይ የተገነባው የኢትዮጵያ ትንሳኤ የመላው አፍሪካም ትንሳኤ ነው። አፍሪካ ለዘመናት የድህነት፣ የጦርነት እና የተስፋ መቁረጥ ምድር ተደርጋ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ስትሳል ብትኖርም፤ ኢትዮጵያ ይህንን የተሳሳተ ትረካ በተግባር እየቀየረችው ትገኛለች።
ከኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እስከ ቢሾፍቱ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶቿ፣ በአረንጓዴ ዐሻራዋ እና በኢኮኖሚ መነቃቃቷ አህጉራዊ ተምሳሌትነቷን በማደስ ላይ ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ አፍሪካውያን በራሳቸው አቅም ማደግ፣ መበልጸግ እና የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ የሚያሳይ ትልቅ የብስራት አድማስ ሆኖ፣ አህጉሪቱ ወደ አዲስ የነፃነት እና የብልጽግና ምዕራፍ እንድትሻገር ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ነው።
በዚህም የምክንያት ዛሬ የዓለም ዓይኖች ወደ እሷ እየተመለከቱ ነው። በዓለም ከሚታወቁት ግዙፍ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው የአሜሪካው ሲኤንኤን የሰሞኑ ዘገባው ይህን ያመለክታል። ይህ ዘገባ የአድናቆት እና የግርምት እይታ ነው።
በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በአቪየሽን እንዲሁም አጠቃላይ በልማት እያስመዘገበቸው ያለውን ዕምርታ በጥልቀት የዳሰሰው ሚዲያው የኢትዮጵያን ትክክለኛ መልክ ያሳዬ ነበር፡፡ በዚህም ሀገራችን የዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን እና ቱሪስቶች ቀልብ ስባለች።
ሰፊው የገበያ እምቅ አቅሟ እና ስትራቴጂካዊ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ የዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል እያደረጋት ሲሆን ፤ ከተፈጥሮ ውበቷ እስከ ጥንታዊ ስልጣኔዎቿ፣ ከላሊበላ እስከ አክሱም ዘመናትን የተሸገሩ ቅርሶቿ ደግሞ ዓለምን ማስደመማቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሩቅ ህልም ሳይሆን የዕለት ተዕለት እውነታ እየሆነ የመጣ ተጨባጭ ክስተት ነው። በራሷ ውስጣዊ ዕምቅ አቅም፣ በህዝቦቿ ላብ እና ጥረት የምታስመዘግበው ስኬት የዓለምን መድረክ እየማረከ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ትናንት የነፃነት ምልክት እንደነበረች ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ የብልጽግና እና የብስራት አድማስ ሆና በዓለም ፊት በኩራት ቆማለች ።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

2 days ago
ፍልሰታ በበአታ
“ትግሁ ወጸልዩ ከመ ኢትባኡ ውስተ መንሱት፤
ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ “ማቴ 26፡40
የበአታ ገዳም መልዕክት
ይህን ታላቅ ጾም በታላቋ ገዳም በዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካነገሥት በአታ ለማርያም በደብረመንክራት
ሥዕልቤት ኪዳነምህረት ገዳም ፡፡
ይህ ጾመ ማርያም (ጾመ ፍልሰታ) ከ7ቱ ታላላቅ አጽዋማት አንዱ እንደሆነ ይታወቃል ይህን ጾም ከሌላው
ለየት የሚያደርገው አባቶቻችን ሐዋርያት ለትምህርተ ወንጌል ከተሰማሩበት ተሰባስበው የእመቤታችንን
ትንሳኤዋንና ዕርገቷን ለማየት ሁለት ሱባኤ ወይም ለ14ቀን ፈጣሪያቸውን በጸሎትና በምህላ ጠይቀው
ትንሳኤዋን እና ዕርገቷን ለማየት በቅተዋል፡፡እኛም የእነሱን መንገድ ተከትለን በቤተ እግዚአብሔር በጸሎት
በቅዳሴ በሰዓታት በምህላ ለሁለት ሱባኤ ወይም ለ14ቀን በየዓመቱ ሱባኤ ይዘን እንጸልያለን፡፡ ይህ ጾመ ሱባኤ
በታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም በስዕል ቤት ኪዳነምህረት ገዳም በልዩ ሁኔታ ይከናወናል፡፡ ሆኖም አሁን
ባለው ሁኔታ በገዳማችን አካባቢ የሚገኙ ምእመናን በመልሶ ማልማት ምክንያት ከስፍራው ርቀው ይገኛሉ ፡፡
ስለሆነም ይህ የጥሪ መልእክት የደረሳችሁ ምእመናን እና ምእመናት በሙሉ በገዳማችን መጥታችሁ ይህን
ታላቅ የሱባኤ ጾም እንድታከናውኑ እናሳስባለን፡
በሱባኤ ጊዜ በገዳማችን የሚከናወኑ መንፈሳዊ የሱባኤ አገልግሎቶች
1ኛ. ከምሽቱ 4ሰዓት እስከ ጠዋት 12፡30 የሰዓታት ቁመት ኪዳንን ጨምሮ ይከናወናል፡፡
2ኛ የውዳሴ ማርያም እና የቅዳሴ ማርያም ትርጉም ከ3፡30 እስከ 6፡00ሰዓት የካሄዳል፡፡
3ኛ ከ6፡00 ሰዓት እስከ 9፡00 ሰዓት የቅዳሴ አገልግሎት በሁለቱም ቤተ ክርስቲያን ይካሄዳል፡፡
4ኛ በገዳማችን ብቻ በተለየ መልኩ የሚጸለይ የሠርክ ጸሎት (የምህላ) አገልግሎት መሐረነአብ ተብሎ
እግዚኦ መሐረነክርስቶስ መቶ ጊዜ በእንተማርያም መሐረነክርስቶስ መቶ ጊዜ እየተባለ ከ9፡30 እስከ 11፡00
ሰዓት ይደረሳል ፡፡
5ኛ ከ11፡00 እስከ 12፡30 የትምህርተ ወንጌል መርሀ ግብር ይፈፀማል፡፡
ይህንን ጾመሱባኤ በእመቤታችን በበአታማርያም ደጅ መጥታችሁ በታላላቅአበው መነኮሳት እጅ
እየተባረካችሁ በመጨረሻም ነሐሴ16 ቀን በዚሁ ገዳም የኪዳነምህረት በአለንግሧን አንግሣችሁ በረከት
እንድታገኙ ጥሪያችንን በእግዚአብሔርስም እያስተላለፍን በበአታ ገዳማችን ተገኝታችሁ እንድትጸልዩ
ተጋብዛችኋል ፡፡
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን አሜን።

17 days ago
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የፈሩት ታሪካዊ ምክክር
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በየዘመናቱ ከቅርብም ከሩቅም የተከፈቱባቸውን ጦርነቶች በመመከት ሀገር የማጽናት የወል ታሪክ ያላቸው ኢትዮጵያውያን፥ ታሪክ ራሱን ይደግም ዘንድ የሰላምና የልማት ደንቃራ ለሆኑ ችግሮች መላ ለማበጀት ተሰባስበዋል።
ኢትዮጵያ ግጭቶችን ተመካክሮ የመፍታት የዳበረ እሴት ያላቸው ሕዝቦች መገኛ ሆና ሳለ፤ አለመግባባት በተፈጠረ ቁጥር የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ አስርገው ለሚያስገቡ ጠላቶች የምንመች ሆነን የመቆየታችን እንቆቅልሽ የሚፈታበት ጊዜ ላይ ነን፡፡
ሀገራችን የሰው ኃይል ሀብቷን፣ የተፈጥሮ ጸጋና ቀደምት የሥልጣኔ መሠረት አጣምራ ወደፊት እንዳትራመድ ሰቅዘው ከያዟት የዘመናት ችግሮች ተላቅቃ አንገቷን ቀና ታደርግ ዘንድ ዜጎቿ ሀሳብ እንዲያዋጡ ትሻለች።
የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያን አላራምድ ብሎ ይዞ የቆየውን ውስብስብ እንቆቅልሽ መፍታት ጊዜ የማይሰጥ የገዘፈ አጀንዳ መሆኑን በወጉ ተገንዝቦ መንገድ ጀምሯል፡፡
ኢትዮጵያ ወደማይቀረው ከፍታዋ የምትወጣው ሕዝቦቿ ተደምረው፣ ቅራኔዎቻቸውን አስረድተው፣ መፍትሔ የሚሏቸውን ሀሳቦች አዋጥተው እንቆቅልሹን በልኩ መፍታት ሲችሉ ነው፡፡
የመደመር መንግሥት የዚህ የዘመናት እንቆቅልሽ መፍቻው ቁልፍ የሚገኝበትን ሀገራዊ ምክክር ከጠነሰሰበት ዕለት አንስቶ የኢትዮጵያን ውድቀት የሚመኙና የልማት ጉዞዋ እረፍት የሚነሳቸው ጠላቶቿን ሲያቃዣቸው ከርሟል፡፡
ከትናንት እስከ ዛሬ ስር እየሰደዱ የሀገራችንን ርምጃ የሚያዘገዩ ችግሮች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሔ ከተበጀላቸው ጠላቶቿ መግቢያ ያጣሉ፡፡
ይህንን ጠንቅቀው የተረዱት እኚሁ ታሪካዊ ጠላቶች ሂደቱን ለማደናቀፍና ኢትዮጵያውያንን ከጀመሩት ታሪካዊ ጉዞ ከመንገድ ለማስቀረት መሸረብን የሙሉ ጊዜ ሥራቸው አድርገውታል፡፡
ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ጉዳይ አንድ ላይ ተሰባስበው ሲመክሩ የሚፈጥሩት የአንድነት አቅም ብሔራዊ ጥቅማችንን ለማስከበር ትልቅ ኃይል መሆኑን ተረድተው ከወዲሁ ብርክ ብርክ ይላቸው ጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያን በጋራ የመልማት መሻት አሻፈረኝ ብለው በጥፋት የተጠመዱት እኚህ ኃይሎች፥ "ምክክሩ አልተጀመረም፤ ችግር ገጥሞታል" እያሉ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ኢትዮጵያውያንን ከሀሳባቸው ለማናጠብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
ዳሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት፥ በእነዚህ አጀንዳዎች ኢትዮጵያውያንን ከጉዟቸው ማስቆም የሚቻል አይደለም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው "በቀላሉ በማይበጠስ ገመድ የተሰናሰለችና ለሺህ ዓመታት ጸንታ የኖረች ኢትዮጵያ አሁን ባለው ፕሮፓጋንዳ ጥቅሟን አሳልፋ ትሰጣለች ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት ነው" ነበር ያሉት፡፡
ኢትዮጵያ በመደመር መንገድ ከግጭት አዙሪትና ከድህነት ቅርቃር ወጥታ የቀደምት ሥልጣኔ ከፍታዋን ዳግም ትንሳኤ የምታበስርበትና የሚፈራ ኃይል ባለቤት የምትሆንበት ምዕራፍ እነሆ ተጀምሯል፡፡ ይኸውም ሀገራዊ ምክክር ነው፡፡

21 days ago
የአርታኢው ማስታወሻ
#ethiopia | የአርማጌዶን በር የትውልድ ማንቂያ ደውል ነው፤ በግለስብደረጃም ሆነ እንደ ሀገር ከተጠመድንበት የአዙሪት ልክፍት የሚያድን የሀሳብ ፀበል። የዘወትር ትንቅንቃችን ከውጤቱ
ጋር መሆኑ ከመፍትሔ ይልቅ ድካም ብቻ ያተረፈልን ከንቱ
ሩጫ እንደሆነ ገብቶታል፤ ደራሲው።
ይዞንም ወደ ምንጩ ይዘልቃል። የሩቅ ዓለማቱን ልሣን ሳይቀር አንብቦና ተርጉሞ ከሚስጢራቱ ባህር ያጠልቀናል። የተፃፈልንን
እያነበነብን፣ በተነገረን እየፎከርን፤ ያረጀ ያፈጀውን እየመዘዝን ስንራኮት የድራማው ፀሀፊዎች ከዳር ቆመው ሲስቁብን የታዘበውን ሊያሳየን የሞከረበት መንገድም እጅጉን ይደንቃል።
የጦርነት ሜዳውም ሆነ ስልቱ የሚለዋወጥበት ፍጥነት
ለግምት ይከብዳል። በጦርና ጋሻ የጠበቅነው ጠላት
እንዳሞራ በአየር መርዝ ታጥቆ ይመጣል።
ጦርና ጋሻውን ጥለን አዲሱን መሳሪያ ታጥቀን ስንጠብቀው አዲስ መንገድ አበጅቶ በስልካችን በኩል ይመጣና በስውር ጥበቡ ልባችንን ሰውሮ ኃይላችንን በመስለብ ሳንገጥመው በሽንፈት እጅ
ያሰጠናል። ማርኮም በባርነት ይገዛናል።
ሁሌም እንግዶች ነን። አንዱን የቤት ሥራ ሳንጨርስ ሌላ
አዲስ የቤት ሥራ ይጠብቀናል። እረፍት አልባ በሆነ
አዙሪት ውስጥ ተጠምደን ስንኳትን አዲስ የነበረው አርጅቶ
ደሞ ሌላ አዲስ ወይም እራሱ መልኩን አድሶ ይወለዳል።
እኛ ያንኳኳነው የስልጣኔ በር፣ እነሱ የሚከፍቱልን የስይጣኔ
በር፤ ታዲያ ከዚህ በላይ አዙሪት ከወዴት ይገኛል። 10
በጥቅሉ በዚህ መጽሐፍ የአርማጌዶን በር ሲነቀነቅ
የሚያስተጋባውን ስውር ድምፅ በቃላት ተስሎ ታደምጡታላችሁ። ድምፁ ግን ለፍርኃት አሳልፎ የሚሰጥ የጥፋት አዋጅ ሳይሆን የማንቂያ ደውል ነውና ተሸብራችሁ አትበረግጉም። ግን ትደነግጣላችሁ። በመጨረሻም ድንጋጤአችሁ ሰልፋችሁን እንድትለዩ የሚያነቃ የትንሳኤ ዋዜማ ሆኖ ነፃ ያወጣችኋል።
የአርማጌዶን በር፤ በእያንዳንዳችን እጅ ላይ ነው።
መልካም ንባብ!
ተስፋዬ አየለ (ዶ/ር)

Sponsored by
Surafel
21 days ago
የባህር በር፤ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የህልውና አጀንዳ
*************
የባሕር በር ባለቤት መሆን ከኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ባሻገር፣ የሕዝብን አመለካከትና የሀገርን ዕጣ ፈንታ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሻግር የሥልጣኔ ቁልፍ ነው። ለኢትዮጵያም የባህር በር ጥያቄ የንግድ ማሳለጫ ወይንም የዕቃዎች መላኪያና መቀበያ መስመር ፍለጋ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፉ የንግድ መድረክ ላይ የራሷን ዕድል በራሷ የመወሰን የፖለቲካ ነፃነት ዋስትና ነው።
ይህ ጥያቄ የ130 ሚሊዮን ሕዝቧን መጻኢ ዕድል የሚወስን፣ የብልጽግና ጉዞዋን የሚያቀና እና የሀገሪቱን ክብርና ሉዓላዊነት በተግባር የሚያረጋግጥ የህልውና ጉዳይም ነው። ከታሪክ ማህደር እስከ ነገው የትውልድ ተስፋ ድረስ የባህር በር ባለቤትነት ለኢትዮጵያ የነፃነት ሙሉነት መገለጫም ሆኖ ይታያል።
በዓለም ታሪክ ውስጥ የባህር በር ያላቸው ሀገራት የባህር ዳርቻዎቻቸውን ለዘመናዊ ሎጀስቲክስ፣ ለግዙፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ለዓለም አቀፍ የሽርሽር መርከቦች ማረፊያ በማዋል የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን በከፍተኛ ደረጃ አረጋግጠዋል። የባህር ጠረፍን ማልማት የሀገር ውስጥ ገቢን ከማሳደግ ባለፈ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰማያዊ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ የሰማያዊ ኢኮኖሚ ተጠቃሚ በመሆን የአሳ ሀብት ልማትን፣ የባህር ላይ ቱሪዝምን እና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ያላት አማራጭ የባህር በር ባለቤትነትን ዳግም በማረጋገጥ ላይ የተመሰረተ ነው። የራስ ወደብ መኖር በየዓመቱ ለኪራይና ለታሪፍ የሚባክነውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የውጭ ምንዛሬ በማስቀረት፣ ያንን ከፍተኛ ሀብት ለሀገር ውስጥ መሠረተ-ልማት ግንባታ፣ ለትምህርትና ለጤና ዘርፍ ለማዋል ብቸኛው ስልታዊ መንገድ ነው።
የባህር በር ባለቤትነት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን፣ በዓለም አቀፉ የንግድ መድረክ ላይ የራሷን ዕድል በራሷ የመወሰን የፖለቲካ ነፃነት ዋስትና ነው።
በፍጥነት እያደገ የመጣውን ሰፊ የሕዝብ ቁጥር መመገብ፣ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችን በወቅቱ ማስገባት እና የሀገሪቱን ብሔራዊ ደኅንነት በዘላቂነት ማስጠበቅ የሚቻለው የባህር በርን እንደ ቀዳሚ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ አጀንዳ በመያዝ ነው። ይህ ጥያቄ የሌሎችን ሉዓላዊነት የሚጋፋ ሳይሆን፣ በጋራ ተጠቃሚነት እና በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ባለቤትነት ሲረጋገጥ የሚሳካ ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ነው።
ኢትዮጵያ ጠንካራ የባህር ኃይል በመገንባት የአፍሪካ ቀንድን ደኅንነት ለመጠበቅና የዓለም አቀፍ የባህር ላይ ንግድ መስመሮችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ የምታበረክተው አስተዋፅኦ የሚጎላው የራሷ የባህር በር ሲኖራት ብቻ ነው። ወደብ አልባ መሆን የሚፈጥረውን የጂኦ-ፖለቲካ ጫና በመስበር፣ ሀገሪቱን በቀይ ባህርና በአደን ባህረ-ሰላጤ አካባቢ ወሳኝ የፖለቲካና የደኅንነት ውሳኔ ሰጪ እንድትሆን ያደርጋታል።
የኢትዮጵያ የባህር ላይ ታላቅነት የአክሱም ሥልጣኔ ታሪካዊ ቅርስና የአባቶቻችን የነፃነት አሻራ መሆኑ አይዘነጋም። ይህ ትውልድ ያንን የተዘጋ ታሪካዊ በር በሰላማዊ ዲፕሎማሲ፣ በጋራ ልማት ስምምነቶችና በብስለት በመክፈት የኢትዮጵያን ትንሳኤ የሚያረጋግጥበት ጊዜ ላይ ይገኛል።
ይህ ታሪካዊ ጥረት የኢትዮጵያን ዘላለማዊ ክብር የሚያድስ፣ ኢኮኖሚዋን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እና ለመጪው ትውልድ ብሩህና አስተማማኝ ነገን የሚያሰናዳ ትልቅ አሻራ ሆኖ በታሪክ ማህደር ላይ በደማቁ ይመዘገባል።
#ebc #ethiopia #seaaccess #redsea #sovereignty

22 days ago
ተስፋን እና ይቅርታን የምትዘራው ሀገር፡- የኢትዮጵያ ታሪካዊ የጋራ መግባባት ምዕራፍ
***************
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሳተፍ ከሥር ወደ ላይ በዘለቀው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ላይ የተመሰረተው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በቀላሉ የማይደገም እና እጅግ ግዙፍ ዓላማን ያነገበ ታሪካዊ ክስተት ነው።
ይህ ሂደት ሀገራችን ለዘመናት የተሸከመችውን ውስብስብ የፖለቲካ እና የማኅበራዊ ስብራቶች ሸክም ለማራገፍ እና አዲስ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የተዘረጋ መድረክ ነው።
ይህ ዓይነቱ አካሄድ የዜጎችን ድምጽ ከታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ጀምሮ በማዳመጥ እውነተኛ እና አሳታፊ የሆነ ፖለቲካዊ ባህልን ለመገንባት የሚያስችል የነገዋ ኢትዮጵያ ጽኑ መሠረት ነው።
ከጠብመንጃ አፈሙዝ ይልቅ ለጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ቅድሚያ በመስጠት የተጀመረው ይህ ጉዞ፣ ሀገራዊ የፖለቲካ አቅጣጫችን በዘላቂነት የሚቀይር የትውልድ ፕሮጀክት ነው።
ከሁሉም በላይ ይህ ታሪካዊ ሂደት የገጠሙንን አውዳሚ ፈተናዎች ወደ መልካም አጋጣሚዎች ለመቀየር የተፈጠረ ልዩ ዕድል ነው።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሲንጸባረቅ የቆየውን እና ብዙ ዋጋ ያስከፈለውን የኃይል ሽኩቻ ወደ ሠለጠነ የሐሳብ ልውውጥ በማምጣት ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህልን ለማጽናት ትልቅ አቅም አለው።
ይህ ጉባኤ ዛሬ ለሚኖሩ ዜጎች ብቻ ሳይሆን፣ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ መልካም የሰላም እና የአብሮነት ዘርን የሚዘራ ነው። ዛሬ ላይ በምናደርገው ጥልቅ እና አርቆ አሳቢ ምክክር፣ ነገ ለልጆቻችን የሚያፈራውን የሰላም፣ የዕድገት እና የፍትህ ፍሬ በነጻነት እንዲቋደሱ መንገድ እንጠርጋለን።
ያለፈውን ጠባሳ ከማከክ ይልቅ የነገውን ብሩህ ተስፋ ማለም ከቻልን፣ ፈተናዎቻችን የጥንካሬያችን መሠረት መሆናቸው አይቀሬ ነው። ይህ ሀገራዊ ምክክርም እውነተኛ ፍሬ እንዲያፈራ ከተፈለገ እያንዳንዱ ተመካካሪ ከጠባብ የሰፈርተኝነት እና የቡድን አስተሳሰብ ወጥቶ ለታላቋ ኢትዮጵያ መምከር ይጠበቅበታል።
ለልጆቻችን ስንል እና የእነርሱን ብሩህ የነገ ዕጣ ፈንታ እያሰብን ስንወያይ በልባችን ውስጥ የሚሰርጸው ይቅርታ እና ተስፋ የቱን ያህል ጥልቅ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም።
አብረን ተስፋን፣ ይቅርታን እና በጋራ መኖርን በጽኑ መሠረት ላይ መትከል የምንችለው፣ የራስን ጊዜያዊ ፍላጎት ወደ ጎን በመተው የሀገርን ዘላቂ ጥቅም ማስቀደም ስንችል ብቻ ነው።
መነጋገር እና መደማመጥ የችግሮቻችን ሁሉ መፍቻ ቁልፍ መሆኑን በተግባር የምናሳይበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን በመሆኑ፣ ሀገርን በመገንባት ሂደት ውስጥ የእያንዳንዱ ዜጋ አስተዋጽኦ የማይተካ ሚና አለው።
በሀገር ውስጥ በሚደረግ የሠለጠነ ውይይት እና በይቅርታ ችግሮቻችንን በራሳችን አቅም መፍታት መቻላችን፣ ሀገራችንን ከማንኛውም የውጭ ጣልቃ ገብነት የሚታደግ ጋሻ ነው። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ክብር የሚጠበቀው የውስጥ አንድነታችን ሲጠናከር መሆኑን ይህ ሂደት በሚገባ ያሳያል።
የራሳችንን ቁስል በራሳችን ማዳን ስንችል ለውጭ ኃይሎች ክፍተት አንሰጥም። የሀገራዊ የምክክር ጉባኤው የኢትዮጵያን ትንሳኤ የምናበስርበት እንዲሁም መጻኢ ዕድላችንን በራሳችን እጅ የምንጽፍበት ታላቅ አጋጣሚ ነው።
በበረከት ሽመልስ
#ethiopia #ebc #ethiopianationaldialogue #nationalconsensu

30 days ago
የቱሪዝም ዘርፍ ትንሳኤ እና አዳዲስ መዳረሻዎች
የዛሬ አምስት ዓመት መንግሥት ሲመሠርት፣ ሀገር ለመምራት በምርጫ የህዝብ ድምጽ ያገኘው ፓርቲ በቱሪዝም ዘርፍ ለማሳካት ቃል የገባቸው በርካታ ጉዳዮች ነበሩ፡፡
እነዚህም በሀገሪቱ የነበሩ የቱሪስት መዳረሻዎችን ማዘመን፣ አዳዲስ ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦችን መገንባት፣ የሀገር ገፅታን ማሻሻል እና ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ የሚሉ ታላላቅ ቃሎች ነበሩ፡፡
በዝርዝር ስናይ፡-
1. የገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ሜጋ ፕሮጀክቶች፡-
የተገባ ቃል፦ ከባህላዊ እና ታሪካዊ ቅርሶች በተጨማሪ አዳዲስና ዘመናዊ የተፈጥሮ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በመላ ሀገሪቱ በከፍተኛ ጥራት መገንባት።
አፈጻጸም፦
የገበታዎች ስኬት፦ ይህ ዘርፍ መንግሥት ባለፉት አምስት ዓመታት እጅግ አስደናቂ እና ፈጣን አፈጻጸም ካሳየባቸው መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ ነው። መንግሥት በአዲስ አበባ በገበታ ለሸገር ፕሮጀክቶች አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡ ቀጥሎ በገበታ ለሀገር መዳረሻ ፕሮጀክቶች ሀገር ተጨማሪ ሀብቶችን በዘርፉ አፍርታለች፡፡
የገበታ ለሸገርና የገበታ ለሀገር ስኬትን ተከትሎ የተጀመረው የገበታ ለትውልድ መርሃ ግብር በርካታ ታሪካዊ ስፍራዎችን ወደ ዘመናዊ ሪዞርት እና መዝናኛነት በመቀየር አዲስ የሀገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ፍሰት መፍጠር ችሏል።
2. የአዲስ አበባ ከተማ ገፅታ ግንባታ :-
የተገባ ቃል፦ ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ለአፍሪካ እና ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ምቹ፣ ውብ እና ማራኪ የቱሪዝም ማዕከል ማድረግ።
አፈጻጸም፦
የኮሪደር ልማት እና አዳዲስ መስህቦች፦ ባለፉት አምስት ዓመታት በአዲስ አበባ የተከናወኑት ታላላቅ የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ የአብርሆት ቤተ መጻሕፍት፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የእንጦጦ ፓርክ፣ የወዳጅነት እና የአንድነት ፓርኮች ግንባታ የከተማዋን ገፅታ ሙሉ በሙሉ ቀይረውታል።
የኮንፈረንስ ቱሪዝም ማደግ፦ እነዚህ አዳዲስ መሠረተ ልማቶች ከተማዋ የዓለም አቀፍ ስብሰባዎችን፣ ኤክስፖዎችን እና የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤዎችን በከፍተኛ የደኅንነትና የውበት ደረጃ እንድታስተናግድ በማድረግ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል።
3. የቪዛ ሥርዓትን ማዘመን እና የሀገር ውስጥ ቱሪዝም፡-
የተገባ ቃል፦ የውጭ ቱሪስቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡበትን የቪዛ አሰጣጥ ሥርዓት ማቅለል እና የሀገር ውስጥ የቱሪዝም ባህልን ማሳደግ።
አፈጻጸም ፦
የኢ-ቪዛ መስፋፋት፦ የኢሚግሬሽን ሥርዓቱን በማዘመን የውጭ ዜጎች በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በኦንላይን ቪዛ የሚያገኙበት ሥርዓት ይበልጥ ተጠናክሯል።
የሀገር ውስጥ ቱሪዝም መነቃቃት፦ ቀደም ሲል ቱሪዝም በውጭ ዜጎች ላይ ብቻ ተደግፎ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፉት አምስት ዓመታት በተሰሩት ሰፊ ሥራዎች የሀገር ውስጥ ተወላጆች፣ ተማሪዎች እና ድርጅቶች አዳዲስ ፓርኮችንና መዳረሻዎችን የመጎብኘት ባህላቸው በከፍተኛ ደረጃ አድጓል።
በአጠቃላይ ባለፉት አምስት የመደመር መንግሥት ዓመታት መንግሥት በቱሪዝም ዘርፍ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ እና ስኬታማ አፈጻጸም አስመዝግቧል።

1 month ago
የቀይ ባሕር ጥሪ እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ትንሳኤ
*****************
(የዕለቱ መልዕክት)
ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቶችና የኃያላን የሽኩቻ መድረክ በሆነው በአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ህልውና እና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከቀይ ባህርና ከባህር በር ጥያቄ ጋር በቀጥታ የተሳሰረ ነው።
ተፈጥሮና መልክዓ-ምድራዊ እውነታዎች በግልጽ እንደሚያሳዩት ቀይ ባህርና አባይ የዚች ታላቅ ሀገር የደም ስሮች ናቸው።
ከዚህ ተፈጥሯዊ ትስስር ባሻገር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የባህር ህግ አንቀጽ 69 እና 125 የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት በአካባቢያቸው ካለው ባሕር የተፈጥሮ ሀብት እኩል የመጠቀም እና የመሸጋገሪያ አለም አቀፍ መብት እንዳላቸው በግልጽ ይደነግጋል።
ኢትዮጵያ ይህንን ህጋዊና ተፈጥሯዊ መብቷን ለማስከበር ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያከናወናቻቸው ስራዎች የሀገራችን መጻኢ ዕድል አዲስ አቅጣጫ ላይ ያስቀመጣት ሆነዋል።
በሀገራችን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በባህርና ቀጠናዊ ተወዳዳሪነት ዙሪያ ከተከናወኑት ተግባራት መካከል ዋነኛውና ደማቅ ስኬት ሆኖ የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ ባህር ኃይል እንደገና መመስረቱና መዋቀሩ ነው።
ለሶስት አስርት ዓመታት ተዘንግቶ የነበረውን ይህንን ወሳኝ ዘርፍ በቁርጠኝነት ዳግም በማንሳት የባህር ኃይል አድሚራል በመሾም ተቋማዊ ኃይሏን በተግባር አጠናክራለች።
ይህ ስኬት በምኞት የተገነባ ሳይሆን አለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ አጋርነቶችን በመጠቀም፣ ለባህር ኃይሉ ዘመናዊ ስልጠናና ሁለንተናዊ የቴክኒክ ድጋፍ በማሰባሰብ የተመዘገበ ታላቅ ውጤት ነው።
ይህ ተቋማዊ ትንሳኤ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ኮሪደር ላይ ሊኖራት የሚገባውን ስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ እና የተጠቃሚነት ፍላጎት በፅኑ መሠረት ላይ ያቆመ ኩነት ነው።
የተከናወኑት እነዚህ ስራዎች የባህር በር ጉዳይን ከስሜታዊነት በራቀ፣ በጥንቃቄና በመርህ ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ኢኮኖሚ እሳቤ መሆኑን ለአለም ማህበረሰብ ያሳዩ ናቸው።
10 በመቶ የሚሆነው የአለም ንግድ በሚያልፍበት፣ በዘይትና በከበሩ ማዕድናት በበለፀገው እና በቢሊዮኖች የሚቆጠር የንግድ እንቅስቃሴ በሚስተናገድበት በቀይ ባህር ቀጠና ውስጥ፣ ኢትዮጵያ የነበራትን የጥገኝነት መገለጫ በመቀየር የራሷን የባህር ኃይል መገንባቷ ወደፊት ለሚደረጉ የዲፕሎማሲ ድርድሮች ትልቅ አቅም ፈጥሯል።
ይህ ስኬት የቀድሞ መሪዎች ስለ አባይ መብት ሲናገሩ "እኔ አቅም የለኝም ልጆቼ ይሰራሉ" እንዳሉት ሁሉ ዛሬ የተጣለው መሠረትም ትውልዱ የቀይ ባህርን መብት በሰላማዊ መንገድና በአለም አቀፍ ህግጋት መሠረት አስከብሮ እንዲረከብ የሚያስችል አርቆ አሳቢ እርምጃ ነው።
ባለፉት ዓመታት በዘርፉ የተመዘገቡት ስኬቶች ኢትዮጵያ ጦር ሳትሰብቅ፣ የወንድማማች ሀገራትን ሉዓላዊነት ሳትደፍር፣ የራሷን ስትራቴጂካዊ ቦታ የምታስከብርበትን መዋቅር የፈጠሩ ናቸው። የባህር ኃይሉ መደራጀት ሀገራችን በአለም አቀፍ የባህር ህግ የተሰጧትን መብቶች በተግባር ለመተርጎም ያላትን ዝግጁነት ያረጋገጠ ሲሆን ለቀጣዩ ትውልድም ከስሜት ነጻ በሆነ መንገድ የተሰላ፣ የታመቀ አቅም እና ብሩህ የባህር በር ተስፋን የጫረ ታሪካዊ ስራ ነው።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

‹‹TDF እየሸሸ ነው፤ አልዋጋም ብሏል›› ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ‼️
‹‹ቲዲኤፍ የሚባለው ጦር እየሸሸ ቤቱ ተቀምጧል፤ አልዋጋም ብሏል፤ ትግራይ ያሉ መሪዎች ከሻብያ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ተቀብለው የጦርነት ፍላጎታቸውን አልተዉም፤ ነገር ግን አቅማቸው ስለተመናመነ እየወላወሉ ነው፡፡ በፊት ማስተዳደር በቻሉበት አቅም ማስተዳደር ስላልቻሉ አፋኝ ሕግ አውጥተው ማስተዳደር ነው የሚፈልጉት፤ ቀደም ሲል የሰሩት ወንጀል ለመሸፈን ሌላ ወንጀል እየሰሩ እንዳለ ይሰማኛል፡፡
ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ በዛሬው ዕለት የተናገሩት
Seledadotio

2 months ago
በወዙና በደሙ ኢትዮጵያን ያፀና:- የጀግንነት አምባ
*****************
"የኩሩ ህዝቦች መኖሪያ የህብረ ብሄር ቡቃያ፣ የሰላም ተምሳሌት ዓርማ የቀለሞች ህብር ኢትዮጵያ!"
ይህ የክብርና የሉዓላዊነት ብሔራዊ መዝሙር ስንኝ፣ ተራ የቃላት ድርደራ ሳይሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የታሪክ፣ የፅናትና የማንነት መልክ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የህሊና ብሩህ መስታወት ነው።
የመከላከያ ሰራዊቱ የማይበገር ጥንካሬ የሚመነጨው በልቡ ውስጥ ከነደደው የማያልቅ የሀገር ፍቅር እሳትና በውስጡ ከሰረጸው ጠንካራ ወታደራዊ ዲሲፕሊን ነው።
ሰራዊቱ ሀገርን በመጠበቅና ዳር ድንበርን በማስከበር ረገድ በዓለም መድረክ ላይ ተወዳዳሪ የሌለው፣ የታሪክን ታላላቅ ፈተናዎች በትከሻው የተሸከመ የሰላም ጽኑ ዐለት ነው።
የጦር ሜዳ ውሎው ስልታዊና አስፈሪ፣ የሰላም ጊዜው ደግሞ ለህዝብ አጋዥና መከታ ነው።
ይህ ሰራዊት የሀገር ውስጥ ጋሻ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም በአህጉሪቱና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተሰማራባቸው የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ሁሉ ሰብአዊነትንና የህግ የበላይነትን ያስቀደመ፣ የሌሎችን ህዝቦች ነፃነትና ክብር እንደ ራሱ አድርጎ የጠበቀ እጅግ ተወዳጅና የተከበረ ኃይል ነው። በሊቤሪያ፣ በሩዋንዳ፣ በዳርፉርና በሶማሊያ በረሃዎች ውስጥ የፈሰሰው ላቡና ደሙ፣ የኢትዮጵያን ስም በዓለም የክብር መዝገብ ላይ በደመቀ ቀለም አስፍሮታል።
የሰራዊቱ አባላት ሌሎችን ማክበርና ለተቸገሩት መድረስ ከአባቶቻቸው የወረሱት የደም እሴት በመሆኑ, በተሰማራበት አህጉርና ቀጠና ሁሉ በህዝቦች ልብ ውስጥ የማይጠፋ የፍቅርና የታማኝነት አሻራ ጥሏል። በዚህም የተነሳ በአፍሪካ ምድር ህዝቦች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ ነው።
ከዚህም በላይ፣ ይህ የጀግኖች ስብስብ ጠመንጃ ብቻ ሳይሆን አካፋና ዶማም መያዝ የሚችል የልማት ግንባር ቀደም ኃይል ነው። በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ፣ በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብና በህዝባዊ አገልግሎቶች ላይ ቀዳሚ በመሆን ድህነትን የሚዋጋ፣ ህዝቡን ከረሃብና ከችግር የሚታደግ የላብ አርበኛ ነው።
ሰላምን በደሙ፣ ልማትንና ብልጽግናን ደግሞ በላቡ እያረጋገጠ የኢትዮጵያን ትንሳኤ እውን ያደርጋል። ይህ ሰራዊት በጦር ግንባር ጀግና፣ በልማት ግንባር ደግሞ መሀንዲስ ሆኖ ሀገርን ወደ ታላቅ ከፍታ ይመራታል።
ባጠቃላይ፣ የኩሩ ህዝቦች መኖሪያ የሆነችውን ኢትዮጵያን እንደ አክሊል ደፍቶ፣ ቀለማቷን ጠብቆ፣ ታሪኳን አድሶ፣ ፈተናዎችን በብቃት ተሻግሮና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አግዞ የሚጓዘው የመከላከያ ሰራዊታችን፣ የኢትዮጵያ ህያው ህልውና፣ የነፃነቷ ዐለት፣ የብዝሃነቷ ውበት እና የነገው ታላቅነቷ እውነተኛ ዋስትና ነው።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
Ethiopian Broadcasting Corporation #ጀግንነት #ኢትዮጵያ #ሰላም

የኢትዮጵያ ቱሪዝም፦ ከአቧራ የተነሱ ጸጋዎች፣ ለዕለት ጉርስ የሆኑ ዐሻራዎች!
**************
የዕለቱ መልዕክት
ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ የታየው አዲስ ተነሳሽነትና ስር ነቀል መዋቅራዊ ሽግግር፣ ሀገራችን ለዘመናት በአቧራ ተሸፍነው የቆዩ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ጸጋዎቿን ለሕዝብ ጥቅምና ለሀገር ግንባታ የምታውልበትን አዲስ ምዕራፍ ፈጥሯል።
ይህ ለውጥ ቱሪዝምን ከተራ የኢኮኖሚ ዘርፍነት ባሻገር የብሔራዊ አንድነት፣ የሰላም፣ የብዝኃነት መገናኛና የሀገር ገጽታ ግንባታ ታላቅ መሣሪያ አድርጎታል።
ለ16 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየውን የቱርዝም ፖሊሲ በአዲስ በመተካት ዘርፉን በሚኒስቴር ደረጃ ማደራጀት፣ የዲጂታል አሰራርንና የኢ-ቪዛ ቴክኖሎጂን መተግበር እንዲሁም የስብሰባና ኤግዚቢሽን ስትራቴጂን መቅረጽ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ አድርጓታል።
እንደ “ገበታ ለሸገር”፣ “ገበታ ለሀገር” እና “ገበታ ለትውልድ” ያሉ ታላላቅ ፅንሰ-ሀሳቦች በተግባር ተተርጉመው በአጭር ጊዜ ውስጥ አዳዲስ የመስህብ ስፍራዎችን መፍጠር ችለዋል።
በአዲስ አበባ የተከናወነው ሰፊ የኮሪደር ልማትም የሀገራችን ዋና መግቢያ በር ውበትና ምቾት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ፈታኝ በሆኑ ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን እነዚህ ስልታዊ የልማት ፕሮጀክቶች የኢኮኖሚውን ትንሳኤ የሚያፋጥኑ ትልልቅ በረከቶችን ይዘውልን መጥተዋል።
የዚህ ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤትም ተጨባጭ ስኬት አስገኝቷል። ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የውጭ ቱሪስቶች ቁጥር ከ781 ሺህ ወደ 1.3 ሚሊዮን ማደጉ፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ከማሳደጉም በላይ ለሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
እንጦጦ ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚየም፣ ታላቁ ብሔራዊ ቤተመንግስት፣ ደንቢና ጎሪጎራ ኢኮ ሪዞርቶች፣ የሃላላ ኬላ እና የኮይሻ ፓርክ "ከቅርሱ ወደ ቁርሱ" የሚለውን መርህ በተግባር ያሳዩ ናቸው። ኢትዮጵያ በዓለም ቱሪዝም ድርጅት ልዩ ዕውቅና ማግኘቷና በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት አዳዲስ ቅርሶችን በዩኔስኮ ማስመዝገቧም የዚሁ ታሪካዊ ስኬት አካል ነው።
ይሁን እንጂ የተመዘገቡት ስኬቶች የዛሬ ጥንካሬዎቻችን ማሳያ እንጂ የነገው ስልታዊ ጉዟችን ማዘናጊያ አይደሉም። ሀገራችን በቀጣይ ዓመታት የውጭ ቱሪስት ፍሰቱን እስከ 7.3 ሚሊዮን ለማድረስ የሰነቀችው ግዙፍ ብሔራዊ ራዕይ ትልቅና የተቀናጀ ሥራን ይጠይቃል።
ይህንን ታላቅ ግብ ለማሳካት የመንግሥት፣ የግል ዘርፍና የኅብረተሰቡ የተቀናጀ አጋርነት ወሳኝ ነው። የመሠረተ ልማት አውታሮችን በተለይም መንገዶችን፣ አስተማማኝ ኤሌክትሪክን፣ ንጹህ ውሃንና የቴሌኮም ኔትወርኮችን በመዳረሻዎች አካባቢ ማሻሻልና ደህንነቱ የተጠበቀ ምቹ ሁኔታን መፍጠር የቀዳሚነት ደረጃ ሊሰጠው ይገባል።
በተጨማሪም የዲጂታል ቴክኖሎጂን፣ ዘመናዊ የዳታ አያያዝንና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በመጠቀም አገልግሎቶችን ማዘመን፤የጎብኚዎችን ልምድ መጠቀምና የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን መደገፍና ማበረታታት ይኖርብናል።
ቱሪዝም ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዜጎች ኑሮ መሻሻል ያለውን የማይተካ ሚና በመገንዘብ፣ የተጀመረው አገራዊ የልማት ዐሻራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሀገራችን ራዕይ እውን እንዲሆን ሁላችንም በጋራ ልንረባረብ ይገባል።
በብሔራዊ ዕድገታችንና በትውልድ ገጽታ ግንባታችን ላይ የሚጋረጡ ማናቸውንም ተግዳሮቶች የምንሻገረው በጀመርነው የልማት መስመር ላይ በጽናትና በአንድነት ስንቆም ብቻ ነው።

የማዕድን ዘርፍ እና አዲስ የኢኮኖሚ ምዕራፍ
******************
(የዕለቱ መልዕክት)
በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ትንሳኤ ውስጥ ለዓመታት ተኝቶ የነበረው የማዕድን ሀብታችን አሁን ለሀገር ኢኮኖሚ ትከሻውን እየሰጠ ይገኛል። ከባህላዊ የግብርና አጥር ወጥተን አገራችንን ወደ አፍሪካ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያ ያሏትን የሀብት ክምችት በዕውቀትና በቴክኖሎጂ አቀነባብራ መጠቀም ጀምራለች። በዚህም የከርሰ ምድርና ገጸ ምድር ሀብቷን ወደ ብሔራዊ ምርታማነት የመቀየር አዲስ ምዕራፍ ከፍታለች።
የማምረቻው ዘርፍ እንደ ወንዝ ውሃ የኢኮኖሚውን አቅጣጫ የሚቀይር ከሆነ ማዕድን ደግሞ የዚያ ወንዝ ምንጭ ነው። አገራችንን የኢንዱስትሪ ፋና ለማድረግ የጀመርነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፣ የማዕድን ዘርፉን ከምድር ውስጥ አውጥቶ ወደ ፋብሪካዎች ግብዓትነት የመቀየር ግዴታ አለበት።
የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን እያሳዩት ባለው አቅም የማዕድን ዘርፉን በቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ጥገኝነታችንን መቀነስ የምንችለው አሁን ነው። በገዛ መሬታችን ያለውን ሀብት በጥራትና በክህሎት ተጠቅመን የውጭ ገበያን በዋጋና በጥራት መፎካከር የሚችል አቅም መገንባትም አለብን።
ከውጥን ወደ እውነታ እየተሸጋገርን ባለበት በዚህ ወቅት የማዕድን ልማታችን ከጥሬ ዕቃ ሽያጭ አልፎ እሴት በተጨመረባቸው ምርቶች መደገፍ አለበት። የወርቅ፣ የኦፓል፣ የታንታለም እና የሌሎች ማዕድናት ፍሰት ለሀገር ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆን የሚችለው፣ የማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች በፓርኮቻችን ውስጥ ሲጠናከሩ ብቻ ነው።
የኢኮኖሚ ነፃነት ማለት በውጭ ምንዛሪ መግዛት ሳይሆን በእጅ ያለን ሀብት በአገር አቅም አምርቶ ለዓለም ማቅረብ ነው። ይህ ጉዞ በሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የሉዓላዊነትና የብልጽግና መለኪያ ነው።
የማዕድን ዘርፉን ወደ ኢንዱስትሪ ማቀናጀት ማለት የአገርን የቴክኖሎጂ አቅም መፈተን ማለት ነው። ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው ማዕድናት ማቀነባበሪያ ማዕከላት ሲሆኑ ኢትዮጵያ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ምርት አምራችነት ትሸጋገራለች።
ይህ ሽግግር በተለይም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን፣ የፀሐይ ኃይል መሣሪያዎችን እና የሕክምና መሣሪያዎችን ለማምረት ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን በአገር ውስጥ መጠቀምን ይጠይቃል።
"ውኃ ካልጠራ አይጠጣም፣ ሰው ካልተማረ አይጠቅም" እንደተባለው የምንፈልገውን የኢንዱስትሪ ለውጥ የምናመጣው በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በዘርፉ በሰለጠነ የሰው ኃይል ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ በወረቀት ላይ የተጻፈ ራዕይ ሳይሆን በየፋብሪካው መጋዘን የሚከማች ምርት፣ በየኢንዱስትሪ ፓርኩ የሚሰማ የቴክኖሎጂ ምት እና በምድር የተገኙ ማዕድናት በኢትዮጵያዊ ክህሎት ሲቀረጹ የሚታይ እውነት ነው።
በአሁኑ ወቅት የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን እየሳቡት ያለው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት፣ የማዕድን ዘርፉን እንደ ታላቅ የኢኮኖሚ ምንጭ ለመጠቀም ያለንን አቅም ያሳያል። የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጁም ለዚህ ዘርፍ የሚሰጠው የግብርና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች፣ ባለሀብቶች ወደ ማዕድን ልማት እንዲገቡ ትልቅ ማበረታቻ ሆኗል።
የማዕድን ሀብታችንን በዘመናዊ አሠራር ፈትሸን፣ የኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲያንሰራራ ማድረጉ የጊዜው ትልቁ አገራዊ ጥሪ ነው።
ኢትዮጵያ በምርቷ ትከበራለች፤ በምድሯ የተከማቸው ሀብትም ለቀጣዩ ትውልድ የብልጽግና ፋና ሆኖ ይደምቃል። ይህ የኢንዱስትሪ አብዮት የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ ከፍ የሚያደርግ፣ የኢኮኖሚ መዋቅራችንን ለዘመናት የሚያጸና የትንሳኤ ብሥራት ነው።
በየደረጃው ያለው የማዕድን ምርታችን ሲጎለብት ኢትዮጵያ የራሷን የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነት ታውጃለች። ነገ የምናያት ኢትዮጵያ በምርቷ የምትኩራራ፣ በሀብቷ የምትበለጽግ እና ለአፍሪካ የብልጽግና ፋና የምትሆን አገር ናት።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebcdotstream #ethiopia #ebc #ማዕድን #ኢኮኖሚ

3 months ago
ኢትዮጵያ፡ የዓለም ቀጣዩ የቱሪዝም መናገሻ
**************************
የቀደሙ አባቶቻችን ክብር የትውልድ ኩራት ነው፡፡ የዛሬው ትጋት ደግሞ የነገው መተኪያ የሌለው ቅርስ ነው፡፡ ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ማዕዘን፣ የሰው ዘር በኩር መገኛና የታሪክ ማኅደር መሆኗን ዓለም አውቆት፣ እኛም ደግመን ደጋግመን ተርከነው የኖርነው እውነት ነው።
ሆኖም ግን "ያለፈው ታሪክ ለዛሬ ስንቅ እንጂ መኖሪያ አይሆንም" እንደሚባለው በትናንት ታሪክ ማማ ላይ ብቻ ተቀምጦ መኖር የጉዞ መዳረሻን አያሰፋም።
ዛሬ ሀገራችን ኢትዮጵያ የታሪኳን አቧራ አራግፋ፣ የተፈጥሮ ዝናዋን በሥራ ጥበብና በፈጠራ አድሳ የቱሪዝም ተስፋዋ እንደ አዲስ ፋክቶ የሚታይበት የትንሳኤ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።
ትናንት በሙዚየሞችና በጥንታውያን ገዳማት ብቻ ዓይኑን ጥሎብን የነበረው ዓለም ዛሬ በጉልበትና በእውቀት በለሙት አዳዲስ መዳረሻዎቻችን ሳቢያ ቀልቡን ወደ እኛ መልሷል።
ይህ የቱሪዝም ሽግግር ለሀገራችን የኢኮኖሚ ሞተር ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነትን አዲስ ከፍታ ለዓለም የምናሳይበት የገጽታ ግንባታችን አውራ መንገድ ሆኗል። "ጉልበት ካለ ድንጋይም ይፈጫል፤ እውቀት ካለ ምድርም ይለማል" ነውና የኢትዮጵያ የቱሪዝም ጉዞ ከነበረበት የቆመና ታሪክን ብቻ ከመተረክ ወጥቶ ወደ ተንቀሳቃሽ ልማት ተሸጋግሯል። በዚሁ እውነት መሠረት፣ የገበታ ለሸገር ፕሮጀክቶች አዲስ አበባን ከኮንክሪት ጫካነትና ከትካዜ ድባብ አውጥተው ወደ አረንጓዴ፣ ሕያውና ሳቢ የቱሪስት ማዕከልነት ቀይሯታል።
ይህ ስኬት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ሳይወሰን ወደ ክልሎች ተሻጋግሮ የተፈጥሮ ጸጋዎችን በዕውቀትና በሥነ-ሕንጻ ጥበብ በመደመር እሳቤ በማልማት ለዓለም ዕይታ ማብቃት ተችሏል። እነዚህ ልማቶች መሬት ላይ ያለውን እምቅ ሀብት ከዘመኑ የፈጠራ ጥበብ ጋር በማቀናጀት የነገውን ትውልድ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የብልጽግና ተምሳሌቶች ናቸው።
ከዚህም ባሻገር አሁን ላይ በአዲስ ጉልበት እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የከተሞቻችንን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ዋነኛ ማነቆ የነበረውን የመሰረተ ልማት ምቾት እጥረት በዘላቂነት የፈታ ታላቅ ሀገራዊ ሥራ ነው።
"መንገድ ካለ አገር አለ" እንዲሉ ጽዱና ሰፋፊ መንገዶች፣ ማራኪ የእግር ጉዞ ትራኮችና ማራኪ የፓርክ አገልግሎቶች ቱሪስቶች በሀገራችን የሚቆዩበትን ጊዜ እንዲያራዝሙና በቆይታቸውም የልብ እርካታን እንዲያገኙ የሚያስችሉ የለውጥ አውታሮች ሆነዋል። ውበትና ጥራት፣ ምቾትና ደህንነት ሲደመሩ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ እያደረጓት ነው። ለዚህም በቅርቡ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ በመገኘት መደነቃቸውን በተለያዩ መንገዶች ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም የቱሪዝም ልማት ለእኛ ቁሳዊ ገቢ ብቻ ሳይሆን ዘርፈ-ብዙ ፋይዳ ያለው የስትራቴጂ ዘርፍ ነው። በአንድ በኩል፣ የውጭ ምንዛሬን በማስገኘትና ለሚሊዮን ወጣቶች የሥራ ዕድልን በሰፊው በመክፈት የኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ካላት የዲጂታል አቅምና ቴክኖሎጂ ጋር ተዳምሮ፣ ሀገራችንን የዓለም የሥራ፣ የጉባኤና የዕረፍት መዳረሻ በማድረግ የሀገርን ገጽታ በአዲስ መልክ እየገነባ ይገኛል።
ሲጠቃላል የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትንሳኤ የመንግሥት የፖሊሲ ውጤት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ዜጋና የዘርፉ ባለሙያ የጋራ ጥረትና የቅንጅት ፍሬ ነው። "ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲሉ ነባሩን ጥንታዊ ቅርስ ከአዲሱ የፈጠራ ስራ ጋር ደምረን፣ ኢትዮጵያን የዓለም የቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ የምናደርገው ጉዞ አሁን ካለንበት ከፍታ በላይ እንደሚሻገር ቅንጣት ታህል ጥርጥር የለንም። እናም እያንዳንዱ ዜጋ ሀገሩን በመወከል ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ትርክትና የልማት ፍሰት በዓለም አደባባይ ማስተጋባትና ማሳወቅ ይጠበቅበታል።
የሀገራችንን አዲስ ትንሳኤ በጋራ እናብስር።

በዘመናት መካከል የጸኑ ደጋፊዎች የደስታ ምሽት...
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) "አርሰናል ዋንጫ ይበላል?" አዎ ሆኗል መልሱ። የለንደን ሰማይ ወደ ቀይነት ተቀይሯል። የመድፈኞቹ ትንሳኤ ከ22 አመት በኋላ በቬታሊቲ ስታዲየም ተበስሯል ።
ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ (ከፈረንጆቹ 2004 ጀምሮ) የዘለቀው የአርሰናል ደጋፊዎች የዋንጫ ጥማት ሊሽር የአንዲት ነፍስ ወደ ምድር መጥታ ወጣት እስክትባል ተስፋ አስቆራጭ ነበር ።
ደጋፊዎቹ ግን በፅናት ስንት ጉድ መጥቶ በሄደበት ትንፋሻቸውን ውጠው ጠብቀዋል።
ዓለም ቅርጿን ብትቀያይር የአለም ዋንጫ ወደ አፍሪካ ምድር ቢመጣ፣ እነ ቤጂንግ የሉሏ ዘዋሪ ቢሆኑ፣ ኢትዮጵያ ዓባይን ገድባ ድግሷን ብትመርቅም አርሰናል ግን ዋንጫ አልበላም።
ዛሬ ግን ኤሚሬትስ ስታዲየም የናፈቀውን የፕሪሚየር ሊግ ክብር ዳግም አጊንቶ የደጋፊዎቹ ምድር ርዳለች ። ምድር አርግዳለች ።
ዋንጫው አርሰናል ዛሬ ላይ በቆመበት ደረጃ በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ ባለፉት አራት ዓመታት ሚኬል አርቴታ በትዕግስት የገነባው ሂደትን የማመን ፍሬ ነው።
ታዋቂው የእግር ኳስ ተንታኝ ጂሚ ካራገር በቅርቡ በሰጠው ትንታኔ፣ "የዘንድሮው አርሰናል ካለፉት ሁለት ዓመታት የሚለየው በአእምሮ ጥንካሬው ነው" ብሎ ነበር።
መድፈኞቹ ቀደም ሲል ወሳኝ ጨዋታዎች ላይ የመንሸራተት ባህሪ ነበራቸው፤ ዘንድሮ ግን በሜዳቸውም ሆነ ከሜዳቸው ውጪ እንደ ሻምፒዮን መጫወትን ተላምደዋል።
በመከላከሉ ረገድ የገነቡት የብረት ግንብ ለሊጉ ጥቂት ጎል ተቆጣሪ ቡድን እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።
በመካከለኛው ክፍል ደግሞ እንግሊዛዊው ዴክላን ራይስ የቡድኑ ሞተር በመሆን መከላከሉንና ማጥቃቱን በሚገርም ሁኔታ አስተሳስሮታል።
"እግር ኳስ በሜዳ ላይ ቢጫወትም አሸናፊው ግን በቁጥሮች ውስጥ ቀድሞ ይታያል" እንደሚባለው ሁሉ፣ የመረጃ ትንታኔዎች ለአርሰናል ትልቅ ተስፋ ነበራቸው።
አርሰናል ዘንድሮ በንፁህ ግብ መውጣት የሊጉን ክብረ ወሰን አድሷል ፤ ግብ ጠባቂው የወርቅ ዋንጫን ወስዷል።
እንግሊዛዊው ተንታኝ ጋሪ ኔቭል "አርሰናል ዘንድሮ ያንን የድል ተራራ መውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ተራራው ላይ ባንዲራቸውን ለመትከል የሚያስችል ትጥቅ እንዳላቸው አሳይተዋል።"
ተንታኞች እንደሚስማሙት አርሰናል ካለፈው ዓመት ስህተቱ ተምሮ ስብስቡን በማስፋቱ፣ ተጫዋቾች ቢደክሙም የሚተኩት አቅም ተመሳሳይ ሆኗል።
የሊጉ ዋንጫ እጣ ፈንታ በሁለት ስፔናውያን አሰልጣኞች ፍልሚያ ሆኖ ፔፕ ጋርዲዮላን ለስንብት አርቴታን ለአሸናፊነት አብቅቷል።
ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ እንደሚባለው አርቴታ በጭንቅም ቢሆን የናፈቀውን ዋንጫ ለመሳም ታድሏል።
የ "ኖርዝ ለንደን ፎርኤቨር" መዝሙር በኤምሬትስ ሰማይ ስር በድል አድራጊነት እየተዘመረ ነው ።
የሉዊስ ደንፎርድ ግጥሞች "ይህ የደሜ ቀለም ነው፤ ለዘላለም የኔ ነው" እያሉ ሲያስተጋቡ፣ በደጋፊዎች አይን ላይ የሚታየው እንባ የክለቡን ጥልቅ ትስስር ያሳያል።
ይህ መዝሙር ደጋፊውን ከመጫወቻ ሜዳው ጋር በማስተሳሰር፣ ተጫዋቾቹ እስከ መጨረሻው ሰከንድ እንዲዋጉ የሚያደርግ የሞራል ስንቅ ነበር ።
ደጋፊዎቹ ቀይ ጭስ በማዘጋጀት ለንደንን ወደ ቀይ ቀለም ለመቀየር ቆርጠዋል። ይህ ድል ለደጋፊዎቹ ከእግር ኳስ ዋንጫ በላይ ነው፤ የለንደን የበላይነትን ዳግም የሚያረጋግጡበት ታላቅ ክስተት ነው።
አርሰናል ዋንጫ ይበላል? አዎ! የተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተመልካች ዓለም ነዋሪዎች የሚቀበሉት እውነት ሆኗል።
የመድፈኞቹ የቀረረው እንባ በደስታ ፈንጠዝያ ባሉበት የምድር ጫፍ ተተክቷል።

የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት ተመሠረተ
«የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» የተባለ ስብስብ አዲስ አበባ ዉስጥ ተቋቋመ። የተለያዩ የሃገር ዉስጥ መገናኛዎች እንደዘገቡት፤ ከስምንት ወራት በፊት የትግራይ ለውጥ ፈላጊ ኃይሎች ንቅናቄ በሚል የተቋቋመው ማህበር ማኒፌስቶውን በማሻሻል «የትግራይ የሰላም ለውጥ ምክር ቤት» በሚል አዲስ አበባ ላይ የመጀመሪያ የምስረታ ጉባዔውን ትናንት ሰኞ አደርጓል።
በምክር ቤቱ ምስረታ ጉባዔ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተደራዳሪዎች መካከል የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ጀነራል ጎዕሽ ገብረ ፣ ሰባት ማህበራዊ መሠረታቸውን ትግራይ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የቀድሞ የክልሉ አመራሮች፣ የቀድሞ ወታደራዊ አዛዦችና ታጋዮች እንዲሁም ማህበራት መገኘታቸዉን የአገር ዉስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። አቶ ጌታቸዉ ረዳ እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ በቅርቡ መቀሌ እንደሚገባ ተናግረዋል። የምክር ቤቱ ምስረታ ዋና አላማ በክልሉ የሚስተዋለውን ሕገ-መንግስታዊ ስርዓት እና የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ በጉልበት ስልጣን የተቆጣጠረውን የህወሓትን ቡድን በማስወገድ በክልሉ ምርጫ ተደርጎ ህጋዊ መንግስት እንዲመሠረት በተደራጀ መንገድ በመጓዝ ሰላማዊ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር ነው መባሉም ተመልክቷል።
ከዚህ ሌላ ትግራይ ክልልን ከጦርነቱ ወደነበረችበት ሕገ መንግሥታዊ የግዛት ቅርጿ በመመለስ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ በተደራጀ ሁኔታ መስራት ነዉ። ምክር ቤቱ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ስምረት፣ ባይቶና፣ ዓረና ትግራይ፣ ትንሳኤ 70 እንደርታ እና ቃንቺ ሀቂ እንዲሁም በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱትን የሀራ_መሬት ታጋዮችን ወታደራዊ ክንፍ ማሰባሰቡ ተገልጿል።
DW Amharic

ሰውዬው "አትርሱኝ" የሚለውን ቃል እንደ እናቱ ምርቃት ሳይሆን እንደ ታክስ መክፈያ ደረሰኝ ነው የሚያየው። አንዳንዱ "አትርሱኝ" ባይ ደግሞ "አትርሱኝ" የሚለውን ቃል ሲጠቀም፣ ቃልኪዳን እየገባ ሳይሆን "ሪከርድ" እያደረገ ነው የሚመስለው።
ለካስ ሳናውቀው "አትርሱኝ" ማለት ያለ እረፍት እኔን በማሰብ ተሰቃዩ ማለት ሆኗል!
ይህ ሰውዬ አገር ሰላም ሆኖ፣ ፀሐይ ወጥቶ ሲገባም ጭምር "አትርሱኝ" ይላል። ቆይ ምን ያህል ቢረሳ ነው? ወይስ ረሺው ብዙ ነው? እኔ የምለው... ሰውዬው "የረሳኝ" ብሎ የሚጠረጥራቸው ሰዎች ብዛት፣ በምርጫ ወቅት "ያልመረጠኝ" ብሎ ከሚቆጥር ፖለቲከኛ ይበልጣል።
ለሠርግ ተጠርቶ "እንኳን ደስ አላችሁ" ከማለት ይልቅ "አትርሱኝ" ይላል። ሙሽሮቹ በጫጉላ ሰዓት እንኳ የእርሱን ፊት እያሰቡ "እንዴት ይረሳል?" እያሉ እንዲጨነቁ ይፈልጋል። ደግሞ እኮ የሚረሳ ነገር ቢኖረው አይቆጭም። ሰውዬው እንደ ድሮ ስልክ "ኮንታክት" በቃሉ የያዘው ቁጥር የለም፤ ግን "አትርሱኝ" ማለቱን አይረሳም።
አንድ ቀን እንዲያውም እንዲህ ሆነ... ሞት መጥቶ በሩን ሲያንኳኳ፣ ሰውዬው መርዶውን ከመቀበሉ በፊት "እሺ መሞቴንስ እሞታለሁ፤ ግን በኋላ ስትመለስ እንዳትረሳኝ" ብሎታል ይባላል። መቃብሩ ላይ "አትርሱኝ" የሚል ፅሁፍ ካልተፃፈማ፣ ትንሳኤ ቀን መጥቶ "አልተፃፈም" ብሎ "ሪፖርት" እንደሚያደርግ አልጠራጠርም።
እሱ "አትርሱኝ" የሚለው ቃል ለእርሱ የህይወት "ሴፍቲ ቤልት" ናት። አየር በነፃ እንደምናገኘው ሁሉ እርሱም ትዝታን በነፃ ማግኘት ይፈልጋል። ግን የሚገርመው ነገር፣ እርሱን ለማስታወስ ስትሞክር የምታስታውሰው ብቸኛ ነገር እርሱ "አትርሱኝ" ማለቱን ብቻ ነው።
ወዳጄ... የዚህን ሰውዬ ስም ከረሳኸው አይከፋም፤ "አትርሱኝ" ማለቱን ከረሳህ ግን እራሱ መጥቶ "ለምን ረሳኸኝ?" ብሎ ትዝታህን "አፕዴት" ያደርገዋል። እንዲያውም እኮ "አትርሱኝ" ማለት የአማርኛ ቋንቋ "ቫይረስ" ሆኗል። አንድን ነገር ለመናገር መግቢያህ "አትርሱኝ" ከሆነ፣ ንግግሩ ሳይጀምር ሰልችቶሃል ማለት ነው።
በእውነት ለመናገር... ሰውዬው ከሞተ በኋላ እንኳ በመንፈስ መጥቶ የቁም ጓደኞቹን "ቅምጥል ትዝታ" እያሳከከ "እንዴ... የዛሬ አምስት ዓመት እንዲህ ብዬህ አልነበር? እንዴት ረሳኸኝ?" ሳይላቸው አይቀርም።
እኔ የምለው... ሐኪም ቤት ሄዶ "ዶክተር... መታመሜን እንዳትረሳው" ቢል ሐኪሙ መድኃኒት ይፅፍለታል ወይስ "የመርሳት በሽታ" ያለበት እራሱ ሐኪሙ እንደሆነ ይቆጥራል?
ለማንኛውም... ይህንን ወግ አንብባችሁ ስትጨርሱ "አትርሱኝ" እንዳትሉኝ። ምክንያቱም እኔ "ረሱኝ" ብዬ ኮርጃለሁ!
አበጀ በለው የላኩልን

የማያልቀው የወርቅ ማዕድን ፍለጋ
***************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ "የቀደመው ታሪካችን የዛሬው ትጋታችን" የሚባልበት አዲስና ብሩህ የትንሳኤ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። ትላንት በታሪክ ማማዎቻችንና በተፈጥሮ ዝናችን ብቻ ይነገር የነበረው የሀገራችን ገጽታ ዛሬ በሥራ ጥበብና በፈጠራ በለሙ አዳዲስ መዳረሻዎች ታጅቦ የዓለምን ዓይን በድጋሚ ስቧል።
ይህ ሽግግር "የውኃ መንገድን ውኃ ያውቀዋል" እንደሚባለው ለሀገራዊ ኢኮኖሚው የደም ሥር ከመሆን ባለፈ የኢትዮጵያዊነትን አዲስ ከፍታ ለዓለም የምናሳይበት የገጽታ ግንባታችን አውራ መንገድ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ጉዞ ከነበረበት የቆመ ታሪክ ወጥቶ፣ ዛሬ ወደ ተንቀሳቃሽና ሕያው ልማት ተሸጋግሯል። የዚህ ታላቅ ለውጥ ግንባር ቀደም ማሳያ የሆነው የ"ገበታ ለሸገር" ፕሮጀክት፣ አዲስ አበባን ከነበረችበት የኮንክሪት ጫካነት አውጥቶ ወደ አረንጓዴና ማራኪ የቱሪስት ማዕከልነት ቀይሯታል።
"ሳይቸግሩ ጤፍ አይዘሩ" እንዲሉ ይህ ስኬት በመዲናዋ ብቻ ሳይወሰን በታላቁ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" መርሐ-ግብሮች ወደ ክልሎች በመሻገር እንደ ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ሎጎ ሃይቅ፣ ቤኑና ፣ ኮይሻ ወዘተ ያሉ የተፈጥሮ ጸጋዎችን በአዲስ ዕይታ ለዓለም አብቅቷል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ ሀብትን በዘመናዊ ዕውቀትና በሥነ-ሕንጻ ጥበብ በመደመር፣ የነገውን ትውልድ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የብልጽግና ተምሳሌቶች ሆነዋል።
በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑያሉ የኮሪደር ልማቶች የከተሞቻችንን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን መሰረታዊ ችግር የፈታ ታላቅ ሥራ ነው። ጽዱ መንገዶችና ማራኪ የፓርክ አገልግሎቶች ቱሪስቶች በሀገራችን የሚቆዩበትን ጊዜ እንዲያራዝሙና በቆይታቸውም የልብ እርካታ እንዲያገኙ ያስችሏቸዋል። "ውበት በሥራ ይደምቃል" እንደሚባለው አገልግሎትና ምቾት ሲደመሩ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እያደርጓት ይገኛሉ።
ቱሪዝም ለእኛ "የማያልቅ የወርቅ ማዕድን" ነው። በአንድ በኩል የውጭ ምንዛሬን በማስገኘትና ለሚሊዮን ወጣቶች የሥራ ዕድልን በመክፈት የኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራችንን የዓለም የሥራና የዕረፍት መዳረሻ በማድረግ የሀገርን ገጽታ በአዲስ መልክ እየገነባ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትንሳኤ "ከመናገር መሥራት፣ ከማለም መድረስ" በሚል ጽኑ እምነት የተገኘ ውጤት ነው።
"ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይደርስም" እንዲሉ እያንዳንዱ ዜጋ ለሀገሩ አምባሳደር በመሆን ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ትርክትና የልማት ፍሰት በዓለም አደባባይ ማስተጋባት ይኖርበታል።
ነባሩን ጥንታዊ ቅርስ ከአዲሱ የፈጠራ ስራ ጋር ደምረን፣ ኢትዮጵያን የዓለም የቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ የምናደርገው ጉዞ አሁን ካለንበት ከፍታ በላይ እንደሚሻገር ጥርጥር የለዉም።
ኢትዮጵያ በቱሪዝም መስኮት ዓለምን የምታስተናግድበት፣ ልጆቿም በሀገራቸው የሚኮሩበት ብሩህ ጊዜ ዛሬ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በመጋቢት እና ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ወራት ያከናወኗቸው ተግባራት
በመጋቢት እና ሚያዚያ 2018 ዓ.ም ወራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳይንሳዊ የምርምር ልህቀት፣ በከተማ ልማት፣ በኢኮኖሚ ሪፎርም እና በቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ዙሪያ ያተኮሩ የተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ክንውኖችን አድርገዋል።
• የፕሮጀክቶች ምረቃ እና የሥራ ጅማሮ
የመጋቢት ወር በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች የተመረቁበት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት (AHRI) ውስጥ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል መርቀዋል። ይህ ማዕከል 40 የላብራቶሪ ክፍሎችን እና በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራት የሚያረጋግጥ የባዮ-ኢኩቫለንስ (bioequivalence) ማዕከልን ያካተተ ነው።
በከተማ ልማት ዘርፍ፣ የሚያዝያ ወር በአገልግሎት እና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ግንባታ ረገድ ጉልህ እመርታ የታየበት ወር ነበር። የአራዳ ፓርክ ፕሮጀክት ከፍተኛ የሆነ የከተማ ገጽታ ለውጥ የታየበት ሲሆን፤ ቀደም ሲል ችላ ተብለውና ለአደጋ ተጋልጠው የነበሩ ቤቶች የሚገኙበትን 40 ሄክታር መሬት ወደ ዘመናዊ ሁለገብ መዳረሻነት ቀይሮታል። ይህ የተቀናጀ የመሠረተ-ልማት እና የመሬት አጠቃቀም ውጤታማነት የታየበት ፕሮጀክት፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ከ700 በላይ ነባር ቤቶችን የማደስ ስራን አካቷል።
ከዚህም በተጨማሪ በ5.7 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈውና የኦሊምፒክ ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት መሠረተ-ልማቶችን፣ የ15 የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊዎችን ሃውልት እና ለተነሺ ነዋሪዎች ተብለው የተገነቡ 105 የንግድ ሱቆችን የያዘው የአዲስ ስፖርት ፓርክ በዚሁ ወር ተመርቋል።
የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት አቅም ለማሳደግ የ100 ሜጋ ዋት የአሰላ የነፋስ ኃይል ማመንጫ ተመርቋል። በተጨማሪም በሀዋሳ የቶዮ ምዕራፍ 2፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎች ሥራ ጀምረዋል። እነዚህ ፋብሪካዎች ከአዲሱ የኤች.ዜድ (HZ) ጋዝ ፋብሪካ ጋር በመሆን በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹህ ኃይል ያመነጫሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በቱሪዝም ዘርፍ፦ በገበታ ለትውልድ መርሃ-ግብር የተገነባው የሀሮ ደንዲ ሎጅ በይፋ ተመርቋል። በመጨረሻም፣ እንደ መታወቂያ ምዝገባ እና የሥራ ፈቃድ ያሉ መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀጥታ ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የታለመው የመሶብ ተንቀሳቃሽ የአውቶቡስ አገልግሎት ስራ ጀምሯል።
• ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ ኅብረት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና የዲጂታል ጤና መሪ ሆነው የተሾሙት በያዝነው የሚያዝያ ነው።
ይህ ኃላፊነት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሉዓላዊነት፣ ለውጤታማነት እና ለአካታች ዕድገት ቁልፍ መሣሪያ የሆኑትን የፈጠራ ሥራዎችን እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን በማሳደግ ረገድ እያሳዩት ያለውን የአመራር ጥበብ እውቅና የሰጠ ሲሆን ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንቁ አመራር ሰጪነት በዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ያስመዘገበችውን ጉልህ ስራ የሚያሳይ ነው።
• የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የአፈጻጸም ግምገማ፦
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሦስተኛውን የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም እና የዘጠኝ ወራት ሪፖርት ግምገማ መርተዋል። በዚህም የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት 9.2 በመቶ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ ወደ 10.2 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል። ሪፖርቱ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ላይ የተመዘገበውን ስኬታማ ሽግግር በዝርዝር ያሳየ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ኪሳራ ያስመዘግቡ የነበሩ ተቋማት በአሁኑ ወቅት 2.1 ትሪሊዮን ብር ገቢ ወደ ማስገባት ተሸጋግረዋል። ለዚህ ውጤት መገኘት ቁልፍ የሆነው የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ እድገቱ ዋና መሪ እንዲሆን ቅድሚያ የሚሰጠው የሪፎርም አጀንዳ ነው።
ይህም እንደ ካፒታል ገበያ ባሉ አዳዲስ የፋይናንስ ሥርዓቶች እና እያደገ በመጣው የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነት እየተደገፈ ይገኛል።
• የኢንዱስትሪ ስትራቴጂ ፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቅርቡ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማጠናከር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) እና ሮቦቲክስን በመጠቀም ወደ ቺፕስ እና ዳታ (ኢንዱስትሪ 4.0) መሸጋገር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ የውጭ ምርቶችን መተካት የቻለው “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን የይዞታ መጠን ወደ 88 በመቶ ማድረሱን በስኬትነቱ ጠቅሰዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ሰላማዊ የባሕር በር ማግኘት የሀገር የህልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት የሰጡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መሆኗ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዳትሆን ከፍተኛ የሎጂስቲክስ ወጪ እንደሚጨምርባት አስገንዝበዋል።
• ማህበራዊ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ አመራር፦
“ማኅበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ” በተሰኘው እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት የምክክር መድረክ ላይ፣ መንግሥት ባለፉት ስምንት ዓመታት ከ19.8 ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን እና ይበልጥ ተዓማኒነት ያለው ሥርዓተ-ትምህርት ተግባራዊ መደረጉ ተገልጿል።
በጤናው ዘርፍም በቅደመ መከላከል እና አክሞ ማዳን፤ መካከል የተሻለ ሚዛን ለመፍጠር ለ30 ዓመታት ያገለገለው ፖሊሲ እንዲሻሻል ተደርጓል። በአካባቢ ጥበቃ ረገድም ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን የኮፕ32 (COP32) ጉባኤን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅት የጀመረች ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ዝግጅቱ ከሀገራዊው የአረንጓዴ ልማት ግቦች ጋር የተጣጣመ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴውን ሰብስበው አቅጣጫ ተሰጥተዋል።
• ዲፕሎማሲ እና ቀጣናዊ ትስስር፦
ኢትዮጵያ የብሩንዲ፣ የላይቤሪያ፣ የደቡብ ሱዳን እና የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንቶችን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያስተናገደች ሲሆን፤ ይህም በመከላከያ፣ በጤና፣ በትምህርት እና በዲጂታል መሠረተ-ልማት ዘርፎች ላይ ያተኮሩ በርካታ የመግባቢያ ስምምነቶች እንዲፈረሙ አስችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ህብረት ዓለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር፣ ከአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት (Afrexim) ባንክ ፕሬዝዳንት፣ እንዲሁም ከፖርቹጋል የውጭ ጉዳይ እና የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጅቡቲ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትርን በመቀበል በሁለትዮሽ ትብብሮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፤ ከአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) ዋና ዳይሬክተር ጋር ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል ጤና ረገድ የተሰጣቸውን ሚና ጨምሮ ሰፋ ባሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በሀገር ውስጥ ጉዳይ፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ከሆኑት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ ጋር በመገናኘት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን የገመገሙ ሲሆን፣ የፕሬዝዳንቱን የሥራ ዘመን ለተጨማሪ አንድ ዓመት በይፋ አራዝመዋል።
የሚያዝ ወር የትንሳኤ በዓል የተከበረበት በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም በማዘጋጀትና አነስተኛ ገቢ ላላቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሠራተኞች የቁሳቁስ ድጋፍ በማጋራት ተጠናቋል።
#ethiopiadelivers #pmoethiopia

ማህበራዊ ትንሳኤ ከምኞት ወደ እውነታ
*****************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ የነበሩባትን ሥር የሰደዱ ማህበራዊ ስብራቶች ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በብልሃትና በጥልቀት ስትጠግን ቆይታለች። ዛሬ ላይ ቆመን ስንመለከት ሀገራዊ ግንባታችን በወረቀት ላይ ከሰፈረው ወጥቶ፣ በዜጎች ጤና፣ በእውቀት ብርሃንና በምግብ ዋስትና ዐውድማ ላይ በተግባር እየተተረጎመ ይገኛል። ይህ ጉዞ ተራ የፖሊሲ ማሻሻያ ሳይሆን የኢትዮጵያን የነገ ማንነት የሚወስን ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
ለሰላሳ ዓመታት በፖሊሲ ማነቆ ታስሮ የቆየው የጤናው ዘርፍ፣ ዛሬ አዲስ እስትንፋስ ዘርቶበታል። “ቀድሞ መከላከል ለነገው ተስፋ፣ አክሞ ማዳን ለዛሬው ዋስትና” በሚል ፖሊሲያችን መከላከልን ብቻ ሳይሆን ሕይወትን ታድጎ ማቆየትንም ትልቅ ግቡ አድርጓል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑት ተግባራት ዘርፉን ከመሠረቱ የለወጡ ናቸው።
ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶችን የማምረት አቅሟን ማሳደጓ፣ የውጭ ጥገኝነትን ቀንሶ የሉዓላዊነታችን አንዱ አካል ሆኗል። ይህ ስኬት በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይወሰን፣ በዓለም አቀፍ የጤና ዲፕሎማሲ መድረክ ኢትዮጵያን የአፍሪካ ድምፅ እንድትሆን አስችሏታል።
ወረርሽኞችን የመለየትና የመቆጣጠር አቅም ማደግ፣ የዲጂታል ጤና ሥርዓት ትግበራ እና የባለሙያዎች ብቃት መጨመር የሀገራችንን የጤና ዋስትና አስተማማኝ አድርገውታል።
“ሳይደግስ አይጣላም” እንዲሉ በትምህርት ዘርፍ የነበረውን የጥራት ውድቀት ለመቀልበስ የተከፈለው መስዋዕትነት ለነገው ትውልድ ትልቅ መሠረት ጥሏል። የሥርዓተ-ትምህርት ክለሳውና የፈተናዎች አስተዳደር መሻሻል የዕውቀት ሌብነትን አክስሞ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን የመቅረጽ ጉዟችንን አፋጥኖታል።
በተለይም ለጥራት መውደቅ ዋነኛ ምክንያት የነበረውን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ክፍተት ለመሙላት የተጀመረው ንቅናቄ የሚደነቅ ነው። “እንጨት በለጋነቱ፣ ልጅ በጨቅላነቱ” እንደሚባለው የነገውን ምሁር ዛሬውኑ በጥራት ለመቅረጽ የተያዘው ስትራቴጂ በተግባር እየታየ ነው።
በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚገነቡት 1 ሺህ 452 አዳዲስ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ87 ሺህ በላይ ሕጻናትን ወደ ዕውቀት ማዕድ የሚጋብዝ ድንቅ የሀገር ግንባታ ምሰሶ ነው። ይህ ኢንቨስትመንት ለነገው ትውልድ የሚቆረስ የዕውቀት እንጀራ ነው።
ሀገር የምትገነባውና ማህበራዊ ልማት ትርጉም የሚኖረው በምግብ ዋስትና ነውና “የዘሩትን ያጭዳሉ” የሚለው ብሂል በበጋ መስኖ ስንዴ ልማታችን ላይ እውን ሆኗል። በላባችንና በውኃ ሀብታችን የፈጠርነው ተዓምር፣ ኢትዮጵያ ከልመና እጅ ወደ ሰጪነት የምታደርገውን ሽግግር እያፋጠነው ይገኛል።
የውኃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እያሸጋገረን ነው። ይህ የታታሪነት ውጤት ለሀገር ግንባታ ሂደት የጸና መሠረት ጥሏል።
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩት የማህበራዊ ዘርፍ እንቅስቃሴዎች የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን የኑሮ ጥራት የሚቀይሩ ተጨባጭ ተግባራትን ያቀፉ ናቸው። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ፣ እነዚህ የፖሊሲና የተግባር ውጤቶች ተደምረው ነገ የምንረከባት ኢትዮጵያ በጤና የተሻለች፣ በእውቀቷ የዳበረችና በልመና የማታፍር እንድትሆን አድርገዋታል።
ይህ የለውጥ ጉዞ የፖሊሲ ማሻሻያ ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን ኑሮ በተግባር የመቀየር ታላቅ የትውልድ አደራ መፈጸሚያ ሆኗል። ባለፉት ዓመታት በትምህርት፣ በጤና፣ በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በባህልና ስፖርት የተመዘገቡ ውጤቶች የነገውን ጉዞ ብሩህ የሚያደርግ ነው። ኢትዮጵያ በማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ የምታደርገው ጥረት ለሌሎችም አርአያ የሚሆንና የዜጎችን ተስፋ የሚያለመልም ታላቅ ስኬት ነው።
የኢቢሲዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

በሞቱ ህይወትን የሰጠን በትንሳኤው ትንሳኤያችንን ያወጀልንን የአባታችንን የመድኃኔዓለምን ቤት ከመፍረስ እንታደግ! 🙏✨
የወደቀውን ለማቅናት፣ የፈረሰውን ለመጠገን ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን እንረባረብ!
ከ60 አመት በላይ ያስቆጠረው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ የሚገኘው መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዛሬ በከባድ ችግር ላይ ይገኛል። ከእድሜ ብዛት የተነሳ የቤተ መቅደሱ ቋሚ ምሰሶዎች በምስጥ ተበልተው፣ ጣሪያውም በማፍሰሱ ምክንያት የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ፣ ምንጣፍ እንዲሁም ንዋየቅድሳቱ በመሉ ከጥቅም ውጪ ሆኗል የአባታችን የመድኃኔዓለም ማደሪያ መቅደሱም ሊወድቅ ጥቂት ቀርቶታል።
አባቶችም በተማፅኖ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውን እርዱን እያሉ ከፊታችን ቆመዋል!
ስለ እኛ በቀራንዮ አደባባይ ስጋውን የቆረሰው ፣ደሙን ያፈሰሰውና የእሾህ አክሊል የደፋው በትንሳኤው ትንሳኤያችንን ያወጀልን መድኃኔዓለም፣ ዛሬ የእኛን እጅ ይፈልጋል። ከ 200 ብር ጀምረን የአቅማችንን በመለገስ ይህንን ታሪካዊ መቅደስ ከመፍረስ እንታደግ።
የባንክ አካውንት (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - CBE)፦
🏦 1000756255626
(መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤ/ክ)
📞 ለበለጠ መረጃ
+251-920-950007
(እባክዎን የክርስትና ስምዎን በቴሌግራም ወይም በዋትሳፕ በዚሁ ስልክ ይላኩላቸው በፀሎት ያስቧችኋል)
እባካችሁ ሼር (Share) በማድረግ ድምፅ ሁኑልኝ! 🙏⛪
#getu #medhanealem #savethechurch #northshewa #ethiopianorthodox #humanitariancall #heritageconservation #ethiopia #የመድኃኔዓለምቤት #ሰሜንሸዋ #ቤተክርስቲያን #ጥሪ #ጌጡተመስገን #getutemesgen
4 months ago

ከ60 አመት በላይ ያስቆጠረው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ የሚገኘው መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዛሬ በከባድ ችግር ላይ ይገኛል። ከእድሜ ብዛት የተነሳ የቤተ መቅደሱ ቋሚ ምሰሶዎች በምስጥ ተበልተው፣ ጣሪያውም በማፍሰሱ ምክንያት የአባታችን የመድኃኔዓለም ማደሪያ ሊወድቅ ጥቂት ቀርቶታል።
አባቶችም በተማፅኖ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውን እርዱን እያሉ ከፊታችን ቆመዋል!
ስለ እኛ በቀራንዮ አደባባይ ስጋውን የቆረሰው ፣ደሙን ያፈሰሰውና የእሾህ አክሊል የደፋው በትንሳኤው ትንሳኤያችንን ያወጀልን መድኃኔዓለም፣ ዛሬ የእኛን እጅ ይፈልጋል። ከ 200 ብር ጀምረን የአቅማችንን በመለገስ ይህንን ታሪካዊ መቅደስ ከመፍረስ እንታደግ።
የባንክ አካውንት (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - CBE)፦
🏦 1000756255626
(መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤ/ክ)
📞 ለበለጠ መረጃ
+251-920-950007
(እባክዎን የክርስትና ስምዎን በቴሌግራም ወይም በዋትሳፕ በዚሁ ስልክ ይላኩላቸው በፀሎት ያስቧችኋል)
እባካችሁ ሼር (Share) በማድረግ ድምፅ ሁኑልኝ! 🙏⛪
#getu #medhanealem #savethechurch #northshewa #ethiopianorthodox #humanitariancall #heritageconservation #ethiopia #የመድኃኔዓለምቤት #ሰሜንሸዋ #ቤተክርስቲያን #ጥሪ #ጌጡተመስገን #getutemesgen
Sponsored by
Surafel
4 months ago
ከፍተኛ የፖሊስ አመራር የነበሩት ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ በታጠቁ ኃይሎች ተገደሉ
#fastmereja I በከምባታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ፣ የትንሳኤ በዓል ከቤተሰቦቻቸው ጋር አሳልፈው ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱ በታጠቁ ኃይሎች በተከፈተባቸው ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ። ኮማንደሯ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በኩል ተመርጠው በሀገር መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዋር ኮሌጅ የስትራቴጂክ አመራር ስልጠና በመከታተል ላይ ነበሩ።
ግድያው የተፈጸመው ሚያዝያ 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡35 ላይ ኮማንደሯ ከቤተሰብ ጥየቃ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ሳሉ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ባወጣው የሀዘን መግለጫ አረጋግጧል።
ኮማንደር አልማዝ የሁለት ሴትና የአንድ ወንድ ልጅ እናት ነበሩ። የከምባታ ዞን ፖሊስ መምሪያ በከፍተኛ አመራሩ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።

ዛሬ ማዕዶት ነው!
#ethiopia | የትንሳኤ በዓልን በደስታ አክብረን፣ ዛሬ የበዓሉ ማግስት ሰኞ ላይ እንገኛለን። ይህች ቀን በቤተክርስቲያን ስነ-ስርዓት "ማዕዶት" ትባላለች።
ማዕዶት ማለት ምን ማለት ነው?
"ማዕዶት" የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "መሻገር" ማለት ነው። ይህም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ባርነት ወደ ከነዓን መሻገራቸውን፣ እንዲሁም እኛ የሰው ልጆች ከሞት ወደ ህይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሲኦል ወደ ገነት የተሻገርንበትን ታላቅ ምስጢር የምናስብበት ነው።
ትናንት የጀመርነው ታላቅ የደስታ በዓል ዛሬም በቤተሰባዊ ጨዋታና በምስጋና ይቀጥላል።
ትናንት በስራ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ያልተገናኙ ዘመድ አዝማድ የሚጠያየቁበት፣ ማዕድ የሚጋሩበትና ፍቅር የሚታደስበት ቀን ነው።
ከረዥሙ የሁዳዴ ጾም በኋላ ሰውነታችንና መንፈሳችን አዲስ ብርታትን የሚያገኝበት፣ ወደ መደበኛ ስራችን ከመመለሳችን በፊት የምናርፍበት ዕለት ነው።
ፈጣሪ ሀገራችንንና ህዝባችንን ከክፉ ነገር ሁሉ አሻግሮ ለሰላምና ለፍቅር ብርሃን ያብቃን!
መልካም የትንሳኤ ማግስት ይሁንላችሁ! 🕊️
Getu Temesgen - (ጌጡ
#getutemesgen #getu

በ110 ሺህ ብር በተገዛ ሰንጋ በሬ ውስጥ ከ10 ግራም በላይ የወርቅ ክምችት ተገኘ
የትንሳኤ በዓል በቃሊቲ የመኖሪያ ካምፕ ለሚገኙ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት ያልተጠበቀ ነገር አጋጥሟቸዋል።
አባላቱ ለበዓል ቅርጫ ካረዱት ሰንጋ በሬ ሀሞት ውስጥ ከ10 ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ማግኘታቸውን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አስታውቋል።
የፖሊስ አባላቱ እንደሚናገሩት፣ በዘንድሮው በዓል የከብት ዋጋ በመወደዱ ምክንያት ይህንን ሰንጋ በሬ ለመግዛት ብዙ ድካምና እንግልት አሳልፈዋል።በመጨረሻም በ110 ሺህ ብር የገዙት ሰንጋ፣ ለበዓሉ ድግስ ብቻ ሳይሆን ያልተጠበቀ ወርቅ ይዞላቸው እንደሚመጣ አልገመቱም ነበር።
በአሁኑ ሰዓት የፖሊስ አባላቱ የተገኘውን ወርቅ ለመሸጥ ከወርቅ ተረካቢዎች ጋር የዋጋ ድርድር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
Via የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
seledadotio

አስቸኳይ የእርዳታ ተማጽኖ
ለጀግናው ብስክሌተኛ ሀይላይ አርአያ ደራሽ እንሁን! 🚴♂️🙏
#ethiopia | ሀገሩን በብስክሌት ስፖርት ለብዙ ዓመታት በክብር ያስጠራው፣ በፅናቱ ለብዙዎች አርአያ የነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባል ሀይላይ አርአያ፣ በአሁኑ ሰዓት በከባድ የጤና ችግር ምክንያት በሆስፒታል አልጋ ላይ ይገኛል።
ከዚህ በፊት ታክሞ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ህመሙ በአጣዳፊ ሁኔታ በማገርሸቱ ጀግናው የእያንዳንዳችንን ድጋፍ ይፈልጋል።
ድጋፍ ለማድረግ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
(CBE)፦ 1000365329854
ሀይላይ አርአያ ገ/ማርያም
(HAILAY ARAYA G/MARIAM)
ለተጨማሪ መረጃ
+251-915-815264
"ጀግና ሲወድቅ አይታይም" የሚለውን አባባል በተግባር ቀይረን፣ ይህን ጀግና በጋራ እናንሳው።
ዛሬ የምናደርገው ትንሽ ድጋፍ ለሀይላይ የነገ ህይወቱ ትንሳኤ ነው።
እባካችሁ ይህ መረጃ ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ ተባበሩን።
#getu #helphailayaraya #ethiopianhero #cyclingethiopia #humanitarianaid #sportscommunity #addisababa #ethiopia #supportourheroes #ርዳታ #ለሀይላይአርአያ #ጀግናሲወድቅአይታይም #ጌጡተመስገን #getutemesgen

በትንሳኤ ሳምንት የጊፍት ኤክስፖን ሳያዩ ቤት እንዳይገዙ!
****
ለአጭር ጊዜ በተዘጋጀው የጊፍት የትንሳኤ ኤክስፖ በአፓርትመንቶችና በንግድ ሱቆች እስከ 15% ቅናሽ ተደርጓል፡፡
በ5% ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ዕድሉ ተመቻችቷል!
ኤክስፖው ሚያዝያ 10/2018 ዓ.ም. ይጠናቀቃል!
ጊፍት ሪል ስቴት
ማህበረሰብን እንገነባለን!
ለበለጠ መረጃ
+251 984 6565 65
Visit 🌐 https://www.giftrealestate...

ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያን ለሩሲያ ምስጋና አቀረቡ
#ethiopia | የኢራኑ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ከሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
መሪዎቹ በውይይታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን መልካም ጉርብትና እና ስልታዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ፕሬዝዳንት ፔዜሽኪያን ሩሲያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ግጭቶችን ለማርገብ ለምትከተለው መርህ-ተኮር አቋም ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ ሞስኮ ለኢራን ሕዝብ ላደረገችው ሰብአዊ እርዳታም አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የኢራኑ ፕሬዝዳንት ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና ለመላው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ይህ የመሪዎቹ የሁለትዮሽ ውይይት በምዕራባውያን ማዕቀብ ውስጥ የሚገኙት ሁለቱ አገራት በኢኮኖሚ፣ በጸጥታና በዲፕሎማሲ መስኮች ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚጥሩበት ወቅት የተደረገ ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #iran #russia #diplomacy #putin #pezeshkian #geopolitics #tehran #moscow #ኢራን #ሩሲያ #ዲፕሎማሲ #ዜና

ብርብር ማርያም
📌 እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ
#ethiopia | በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በጨንቻ ወረዳ ከከተማው 30 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኘው ብርብር ማርያም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ ታሪኳን የምታስታውስበት ታላቅ ገዳም ናት።
በዚህ ገዳም ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የመሥዋዕተ ኦሪት ማዕከል እንደነበረች የሚነገርላት ሲሆን፣ መሥዋዕቱ ይቀርብበት የነበረው "ዳታን" የተባለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ለታሪክ ምስክር ሆኖ ይገኛል።
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአብርሃ ወአጽብሐ ዘመነ መንግሥት የክርስትና እምነት በኢትዮጵያ ሲስፋፋ፣ በብርብር ማርያም ይከናወን የነበረው የኦሪት ሥርዓት በሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት እንዲተካ ተደርጓል።
ከጌታችን ልደት በፊት 400 ዓመት አካባቢ ጀምሮ የብሉይ ኪዳን ትምህርት ሲሰጥባትና መሥዋዕት ሲሰዋባት የኖረችው ይህች ስፍራ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የሃይማኖት ማዕከል በመሆን አገልግላለች።
በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ዐፄ ገብረ መስቀል፣ ቅዱስ ያሬድንና አቡነ አረጋዊን በማስከተል ወደ ደቡብ ሲጓዙ የታቦተ ማርያምን ጽላት ይዘው ወደዚሁ ስፍራ አቅንተዋል።
ግንቦት 20 ቀን ገዳሟ ደርሰው ሌሊቱን በጸሎትና በማኅሌት ካደሩ በኋላ፣ በማግሥቱ ግንቦት 21 ቀን አቡነ አረጋዊ ቤተ መቅደሱን በሜሮን ባርከው ታቦተ ማርያምን በክብር አግብተዋል። በዚሁ ዕለት ዐፄ ገብረ መስቀል ለገዳሟ መተዳደሪያ የሚሆን ሰፊ ርስት መስጠታቸው በታሪክ ድርሳናት ተመዝግቦ ይገኛል።
በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቡዳ ኬንና የተባለ ፀረ-ሃይማኖት ኃይል ገዳሟን ለማጥፋትና ለማቃጠል ቢሞክርም፣ በተአምር ሳይሳካለት መቅረቱ የገዳሟን ቅዱስነት የሚያሳይ ሌላኛው ታሪክ ነው። ከብዙ ዘመናት መረሳት በኋላ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዐፄ እስክንድር ዘመን በድጋሚ የተተከለች ሲሆን፣ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብና በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥታትም የታደሰችና የተገደመች መሆኗ ይነገራል።
የገዳሟ የመጀመሪያው መምህር አባ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ፣ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ምሁርና ደራሲ አባ ባሕርይም በዚህች ደብር ለረጅም ጊዜ ኖረዋል።
በዐፄ ምኒልክ ዘመን የኢትዮጵያ ግዛት ሲቀናጅ ገዳሟ በወርቅና በብር የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳት፣ የነገሥታት ዘውዶችና ልዩ ልዩ ቅርሶች መገኛ ነበረች። ምንም እንኳ አሁን ላይ አብዛኞቹ ቅርሶች ባይገኙም፣ ገዳሟ አሁንም ድረስ ጥንታዊ አሻራዋን ጠብቃ ትገኛለች።
በ1928 ዓ.ም. ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ይህችን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን በአውሮፕላን ቦምብ ለማጋየት ቢሞክርም፣ ተወርውሮ የወረደው ቦምብ ሳይፈነዳ እንደ ድንጋይ ተንከባሎ መውረዱ የእግዚአብሔር ጥበቃ ያልተለያት መሆኑን ያረጋግጣል።
ይህ ዛሬም ድረስ በግቢው ውስጥ የሚገኘው ቦምብና ሌሎች ታሪካዊ ምልክቶች፣ ብርብር ማርያም ለኢትዮጵያ ካላት መንፈሳዊና ታሪካዊ ፋይዳ በተጨማሪ ለጎብኚዎችና ለተመራማሪዎች ትልቅ መስህብ መሆኗን ያሳያሉ።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

📜 18-8-8-8፡ የታሪክና የጥበብ ዘላለማዊነት ቀመር
የኢትዮጵያ ሰው "ንብን የነካ ማር አይቀምስም"ይላል።
እኛም ሳናውቅ በቀናነት እና በፍቅር የሰጠነው ሃሳብ የንቦቹን ንጉሥ ነክተን የአድናቂዎቹ ሲገስፁን ነው ነገሩ የገባን!
አልበሙን ለማጀብ በየቀለሙና በየመስመሩ ላይ የተደረገው የግራፊክስ ጥንቃቄም ሆነ የዜማው ብስለት፣ስራው "ጊዜ የማይሽረው" እንዲሆን ታስቦ መሆኑን ከቅርብ ሰው ተደውሎ ተረድተናል።
ታላቁ ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ አዲሱን አልበም "ኢዮሪካ" (ETORIKA) ለማቅረብ ጊዜ የወሰደው እንዲሁ በቸልታ ሳይሆን፣ በየዘመኑ የማይጠወልግ እና በትውልድ ዘንድ የሚኖር ጥበብን ለመቅረጽ ነው።
ይህ በልዩ ጥንቃቄ የተቀመረ ምስላዊ ጥበብ (Graphics) በውስጡ የያዛቸው ምልክቶች ራሳቸው ትልቅ የታሪክ ምስጢር አላቸው
የ"ቶ" ፊደልና የአክሱም ሐውልት (ጽዮን)
ጥንታዊ ስልጣኔያችንን እና የሕይወት ትንሳኤን የሚወክሉ ሆነው አልበሙ እንደ ሐውልቱ ጸንቶ የሚኖር መሆኑን ያበስራሉ።
የአፍሪካ ሰዓት ⏱️
የአፍሪካ ምስል ያለበት የእጅ ሰዓት ማሰሪያው የአክሱም ሐውልት ሆኖ መሰራቱ ጊዜና ታሪክ ተሳስረው "የአፍሪካ ሰዓት" መድረሱን ያሳያል።
ባንዲራና ጥለቱ 🟢🟡🔴
አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ጥለቱ የማንነታችንና የነጻነታችን ዘላለማዊ አርማ ሆኖ ሎጎውን አሽቆጥቁጦታል።
ይህ በልዩ ጥንቃቄ የተሰራ ጥበብ ደግሞ ከ1888 ዓ.ም የዓድዋ ድል ታሪክ ጋር በሚገርም የቁጥሮች ቀመር ተሳስሯል፦
* 18 ዘፈኖች (Tracks)
* ሚያዝያ 8 ቀን
* 2018 ዓመተ ምህረት
* ከቀኑ 8 ሰዓት
ይህ በስምንት ቁጥር የታጀበ የቁጥሮች ሰልፍ ዝም ብሎ አጋጣሚ አይደለም። ስምንት ቁጥርን በጋድም ስናስቀምጠው የዘላለማዊነት (♾️)ምልክት ነው።
ይህም ቴዲ ስለ ዓድዋ ጀግኖች "ጥቁር ሰው" ብሎ ሲዘፍን ታሪክን ዘላለማዊ እንዳደረገው ሁሉ ይህ አዲስ አልበምም ከታየው ረቂቅ ግራፊክስ ጀምሮ እስከ 18ቱ ዜማዎች ጊዜ የማይሽረውና እንደ ምልክቱ ለዘላለም በልባችን የሚኖር ጥበብ መሆኑን ያበስራል።
ሚያዝያ 8 ጥበብ ከታሪክ ጋር ተጋብታ ዘላለማዊነቷን ለዓለም የምታውጅበት ዕለት ይሆናል!
ላስቀየምናችሁ አፉ በሉን🙏
Case closed

Comments