የማያልቀው የወርቅ ማዕድን ፍለጋ
***************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ "የቀደመው ታሪካችን የዛሬው ትጋታችን" የሚባልበት አዲስና ብሩህ የትንሳኤ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። ትላንት በታሪክ ማማዎቻችንና በተፈጥሮ ዝናችን ብቻ ይነገር የነበረው የሀገራችን ገጽታ ዛሬ በሥራ ጥበብና በፈጠራ በለሙ አዳዲስ መዳረሻዎች ታጅቦ የዓለምን ዓይን በድጋሚ ስቧል።
ይህ ሽግግር "የውኃ መንገድን ውኃ ያውቀዋል" እንደሚባለው ለሀገራዊ ኢኮኖሚው የደም ሥር ከመሆን ባለፈ የኢትዮጵያዊነትን አዲስ ከፍታ ለዓለም የምናሳይበት የገጽታ ግንባታችን አውራ መንገድ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ጉዞ ከነበረበት የቆመ ታሪክ ወጥቶ፣ ዛሬ ወደ ተንቀሳቃሽና ሕያው ልማት ተሸጋግሯል። የዚህ ታላቅ ለውጥ ግንባር ቀደም ማሳያ የሆነው የ"ገበታ ለሸገር" ፕሮጀክት፣ አዲስ አበባን ከነበረችበት የኮንክሪት ጫካነት አውጥቶ ወደ አረንጓዴና ማራኪ የቱሪስት ማዕከልነት ቀይሯታል።
"ሳይቸግሩ ጤፍ አይዘሩ" እንዲሉ ይህ ስኬት በመዲናዋ ብቻ ሳይወሰን በታላቁ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" መርሐ-ግብሮች ወደ ክልሎች በመሻገር እንደ ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ሎጎ ሃይቅ፣ ቤኑና ፣ ኮይሻ ወዘተ ያሉ የተፈጥሮ ጸጋዎችን በአዲስ ዕይታ ለዓለም አብቅቷል።
እነዚህ ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ ሀብትን በዘመናዊ ዕውቀትና በሥነ-ሕንጻ ጥበብ በመደመር፣ የነገውን ትውልድ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የብልጽግና ተምሳሌቶች ሆነዋል።
በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑያሉ የኮሪደር ልማቶች የከተሞቻችንን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ፣ የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን መሰረታዊ ችግር የፈታ ታላቅ ሥራ ነው። ጽዱ መንገዶችና ማራኪ የፓርክ አገልግሎቶች ቱሪስቶች በሀገራችን የሚቆዩበትን ጊዜ እንዲያራዝሙና በቆይታቸውም የልብ እርካታ እንዲያገኙ ያስችሏቸዋል። "ውበት በሥራ ይደምቃል" እንደሚባለው አገልግሎትና ምቾት ሲደመሩ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እያደርጓት ይገኛሉ።
ቱሪዝም ለእኛ "የማያልቅ የወርቅ ማዕድን" ነው። በአንድ በኩል የውጭ ምንዛሬን በማስገኘትና ለሚሊዮን ወጣቶች የሥራ ዕድልን በመክፈት የኢኮኖሚው የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። በሌላ በኩል ደግሞ ሀገራችንን የዓለም የሥራና የዕረፍት መዳረሻ በማድረግ የሀገርን ገጽታ በአዲስ መልክ እየገነባ ነው። ይህ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትንሳኤ "ከመናገር መሥራት፣ ከማለም መድረስ" በሚል ጽኑ እምነት የተገኘ ውጤት ነው።
"ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይደርስም" እንዲሉ እያንዳንዱ ዜጋ ለሀገሩ አምባሳደር በመሆን ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ትርክትና የልማት ፍሰት በዓለም አደባባይ ማስተጋባት ይኖርበታል።
ነባሩን ጥንታዊ ቅርስ ከአዲሱ የፈጠራ ስራ ጋር ደምረን፣ ኢትዮጵያን የዓለም የቱሪዝም ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ የምናደርገው ጉዞ አሁን ካለንበት ከፍታ በላይ እንደሚሻገር ጥርጥር የለዉም።
ኢትዮጵያ በቱሪዝም መስኮት ዓለምን የምታስተናግድበት፣ ልጆቿም በሀገራቸው የሚኮሩበት ብሩህ ጊዜ ዛሬ ነው።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

28 days ago