ብርብር ማርያም
📌 እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ
#ethiopia | በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን በጨንቻ ወረዳ ከከተማው 30 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኘው ብርብር ማርያም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ ታሪኳን የምታስታውስበት ታላቅ ገዳም ናት።
በዚህ ገዳም ከክርስቶስ ልደት በፊት ጀምሮ የመሥዋዕተ ኦሪት ማዕከል እንደነበረች የሚነገርላት ሲሆን፣ መሥዋዕቱ ይቀርብበት የነበረው "ዳታን" የተባለው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ ለታሪክ ምስክር ሆኖ ይገኛል።
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአብርሃ ወአጽብሐ ዘመነ መንግሥት የክርስትና እምነት በኢትዮጵያ ሲስፋፋ፣ በብርብር ማርያም ይከናወን የነበረው የኦሪት ሥርዓት በሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት እንዲተካ ተደርጓል።
ከጌታችን ልደት በፊት 400 ዓመት አካባቢ ጀምሮ የብሉይ ኪዳን ትምህርት ሲሰጥባትና መሥዋዕት ሲሰዋባት የኖረችው ይህች ስፍራ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የሃይማኖት ማዕከል በመሆን አገልግላለች።
በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ዐፄ ገብረ መስቀል፣ ቅዱስ ያሬድንና አቡነ አረጋዊን በማስከተል ወደ ደቡብ ሲጓዙ የታቦተ ማርያምን ጽላት ይዘው ወደዚሁ ስፍራ አቅንተዋል።
ግንቦት 20 ቀን ገዳሟ ደርሰው ሌሊቱን በጸሎትና በማኅሌት ካደሩ በኋላ፣ በማግሥቱ ግንቦት 21 ቀን አቡነ አረጋዊ ቤተ መቅደሱን በሜሮን ባርከው ታቦተ ማርያምን በክብር አግብተዋል። በዚሁ ዕለት ዐፄ ገብረ መስቀል ለገዳሟ መተዳደሪያ የሚሆን ሰፊ ርስት መስጠታቸው በታሪክ ድርሳናት ተመዝግቦ ይገኛል።
በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቡዳ ኬንና የተባለ ፀረ-ሃይማኖት ኃይል ገዳሟን ለማጥፋትና ለማቃጠል ቢሞክርም፣ በተአምር ሳይሳካለት መቅረቱ የገዳሟን ቅዱስነት የሚያሳይ ሌላኛው ታሪክ ነው። ከብዙ ዘመናት መረሳት በኋላ በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዐፄ እስክንድር ዘመን በድጋሚ የተተከለች ሲሆን፣ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብና በዐፄ ልብነ ድንግል ዘመነ መንግሥታትም የታደሰችና የተገደመች መሆኗ ይነገራል።
የገዳሟ የመጀመሪያው መምህር አባ ሠርጸ ድንግል ሲሆኑ፣ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩት ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ምሁርና ደራሲ አባ ባሕርይም በዚህች ደብር ለረጅም ጊዜ ኖረዋል።
በዐፄ ምኒልክ ዘመን የኢትዮጵያ ግዛት ሲቀናጅ ገዳሟ በወርቅና በብር የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳት፣ የነገሥታት ዘውዶችና ልዩ ልዩ ቅርሶች መገኛ ነበረች። ምንም እንኳ አሁን ላይ አብዛኞቹ ቅርሶች ባይገኙም፣ ገዳሟ አሁንም ድረስ ጥንታዊ አሻራዋን ጠብቃ ትገኛለች።
በ1928 ዓ.ም. ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ይህችን ታሪካዊ ቤተክርስቲያን በአውሮፕላን ቦምብ ለማጋየት ቢሞክርም፣ ተወርውሮ የወረደው ቦምብ ሳይፈነዳ እንደ ድንጋይ ተንከባሎ መውረዱ የእግዚአብሔር ጥበቃ ያልተለያት መሆኑን ያረጋግጣል።
ይህ ዛሬም ድረስ በግቢው ውስጥ የሚገኘው ቦምብና ሌሎች ታሪካዊ ምልክቶች፣ ብርብር ማርያም ለኢትዮጵያ ካላት መንፈሳዊና ታሪካዊ ፋይዳ በተጨማሪ ለጎብኚዎችና ለተመራማሪዎች ትልቅ መስህብ መሆኗን ያሳያሉ።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

2 months ago