የኢትዮጵያ ትንሳኤ !
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብስራት አድማስ እና የዓለም ዓይኖች ማረፊያ እየሆነች ትገኛለች።
እሷ የታሪክ እምብርት፣ የሰው ዘር መገኛ እና የነፃነት ማኅተም ናት። ዛሬ ደግሞ በልጆቿ ጽናት እና በማይበገረው ህዝባዊ ወኔያቸው አዲስ የትንሳኤ ምዕራፍ እየተቀኘች ትገኛለች።
ይህ የትንሳኤ ብርሃን ለራሷ ብቻ ሳይሆን፣ ለመላው ጥቁር ህዝብ እና ለአፍሪካ አህጉር አዲስ የብስራት አድማስ እየቀደደ ነው።
የዚህች ታላቅ ሀገር ትንሳኤ ከባዶ የተነሳ ሳይሆን፣ ከጥንታዊው የክብር ሥርዓቷ እና ካልተደፈረው ማንነቷ የተቀዳ ነው። አፍሪካ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሥር በነበረችበት የጨለማ ዘመን፣ ኢትዮጵያ የነፃነት ብቸኛ ፋኖስ ሆና እንዳበራች ሁሉ፣ ዛሬም ያ የወርቃማ ታሪክ በዘመናዊው ትውልድ ልብ ውስጥ እንደገና እየተቀጣጠለ ይገኛል።
በመሆኑም ይህች የአናብስት ምድር የገጠሟትን ዘመናዊ ፈተናዎች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎች እና ማህበራዊ ውጣ ውረዶች በራሷ ልጆች ጥረት እና ጥንካሬ እያሸነፈች ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ህዝብ ታታሪነቱ፣ ለነጻነት ቀናኢነቱ፣ የማይበገረው ፅናቱ እና ለሀገሩ ያለው ጥልቅ ፍቅር አዲሱን የትንሳኤ መንገድ እያቀናው ነው።
በዚህ ጽናት ላይ የተገነባው የኢትዮጵያ ትንሳኤ የመላው አፍሪካም ትንሳኤ ነው። አፍሪካ ለዘመናት የድህነት፣ የጦርነት እና የተስፋ መቁረጥ ምድር ተደርጋ በምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ስትሳል ብትኖርም፤ ኢትዮጵያ ይህንን የተሳሳተ ትረካ በተግባር እየቀየረችው ትገኛለች።
ከኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ እስከ ቢሾፍቱ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ በታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶቿ፣ በአረንጓዴ ዐሻራዋ እና በኢኮኖሚ መነቃቃቷ አህጉራዊ ተምሳሌትነቷን በማደስ ላይ ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ አፍሪካውያን በራሳቸው አቅም ማደግ፣ መበልጸግ እና የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው መወሰን እንደሚችሉ የሚያሳይ ትልቅ የብስራት አድማስ ሆኖ፣ አህጉሪቱ ወደ አዲስ የነፃነት እና የብልጽግና ምዕራፍ እንድትሻገር ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ነው።
በዚህም የምክንያት ዛሬ የዓለም ዓይኖች ወደ እሷ እየተመለከቱ ነው። በዓለም ከሚታወቁት ግዙፍ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው የአሜሪካው ሲኤንኤን የሰሞኑ ዘገባው ይህን ያመለክታል። ይህ ዘገባ የአድናቆት እና የግርምት እይታ ነው።
በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በአቪየሽን እንዲሁም አጠቃላይ በልማት እያስመዘገበቸው ያለውን ዕምርታ በጥልቀት የዳሰሰው ሚዲያው የኢትዮጵያን ትክክለኛ መልክ ያሳዬ ነበር፡፡ በዚህም ሀገራችን የዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን እና ቱሪስቶች ቀልብ ስባለች።
ሰፊው የገበያ እምቅ አቅሟ እና ስትራቴጂካዊ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ የዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል እያደረጋት ሲሆን ፤ ከተፈጥሮ ውበቷ እስከ ጥንታዊ ስልጣኔዎቿ፣ ከላሊበላ እስከ አክሱም ዘመናትን የተሸገሩ ቅርሶቿ ደግሞ ዓለምን ማስደመማቸውን ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሩቅ ህልም ሳይሆን የዕለት ተዕለት እውነታ እየሆነ የመጣ ተጨባጭ ክስተት ነው። በራሷ ውስጣዊ ዕምቅ አቅም፣ በህዝቦቿ ላብ እና ጥረት የምታስመዘግበው ስኬት የዓለምን መድረክ እየማረከ ይገኛል።
ኢትዮጵያ ትናንት የነፃነት ምልክት እንደነበረች ሁሉ፤ ዛሬ ደግሞ የብልጽግና እና የብስራት አድማስ ሆና በዓለም ፊት በኩራት ቆማለች ።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

2 days ago