ከፍተኛ የፖሊስ አመራር የነበሩት ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ በታጠቁ ኃይሎች ተገደሉ
#fastmereja I በከምባታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከፍተኛ አመራር የነበሩት ኮማንደር አልማዝ ዮሐንስ፣ የትንሳኤ በዓል ከቤተሰቦቻቸው ጋር አሳልፈው ወደ ትምህርት ገበታቸው ሲመለሱ በታጠቁ ኃይሎች በተከፈተባቸው ጥቃት ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ። ኮማንደሯ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በኩል ተመርጠው በሀገር መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዋር ኮሌጅ የስትራቴጂክ አመራር ስልጠና በመከታተል ላይ ነበሩ።
ግድያው የተፈጸመው ሚያዝያ 05 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡35 ላይ ኮማንደሯ ከቤተሰብ ጥየቃ ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ ሳሉ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ባወጣው የሀዘን መግለጫ አረጋግጧል።
ኮማንደር አልማዝ የሁለት ሴትና የአንድ ወንድ ልጅ እናት ነበሩ። የከምባታ ዞን ፖሊስ መምሪያ በከፍተኛ አመራሩ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ተመኝቷል።

2 months ago