ዛሬ ማዕዶት ነው!
#ethiopia | የትንሳኤ በዓልን በደስታ አክብረን፣ ዛሬ የበዓሉ ማግስት ሰኞ ላይ እንገኛለን። ይህች ቀን በቤተክርስቲያን ስነ-ስርዓት "ማዕዶት" ትባላለች።
ማዕዶት ማለት ምን ማለት ነው?
"ማዕዶት" የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "መሻገር" ማለት ነው። ይህም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ባርነት ወደ ከነዓን መሻገራቸውን፣ እንዲሁም እኛ የሰው ልጆች ከሞት ወደ ህይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሲኦል ወደ ገነት የተሻገርንበትን ታላቅ ምስጢር የምናስብበት ነው።
ትናንት የጀመርነው ታላቅ የደስታ በዓል ዛሬም በቤተሰባዊ ጨዋታና በምስጋና ይቀጥላል።
ትናንት በስራ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ያልተገናኙ ዘመድ አዝማድ የሚጠያየቁበት፣ ማዕድ የሚጋሩበትና ፍቅር የሚታደስበት ቀን ነው።
ከረዥሙ የሁዳዴ ጾም በኋላ ሰውነታችንና መንፈሳችን አዲስ ብርታትን የሚያገኝበት፣ ወደ መደበኛ ስራችን ከመመለሳችን በፊት የምናርፍበት ዕለት ነው።
ፈጣሪ ሀገራችንንና ህዝባችንን ከክፉ ነገር ሁሉ አሻግሮ ለሰላምና ለፍቅር ብርሃን ያብቃን!
መልካም የትንሳኤ ማግስት ይሁንላችሁ! 🕊️
Getu Temesgen - (ጌጡ
#getutemesgen #getu

4 months ago