የኢትዮጵያ ቱሪዝም፦ ከአቧራ የተነሱ ጸጋዎች፣ ለዕለት ጉርስ የሆኑ ዐሻራዎች!
**************
የዕለቱ መልዕክት
ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ የታየው አዲስ ተነሳሽነትና ስር ነቀል መዋቅራዊ ሽግግር፣ ሀገራችን ለዘመናት በአቧራ ተሸፍነው የቆዩ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ጸጋዎቿን ለሕዝብ ጥቅምና ለሀገር ግንባታ የምታውልበትን አዲስ ምዕራፍ ፈጥሯል።
ይህ ለውጥ ቱሪዝምን ከተራ የኢኮኖሚ ዘርፍነት ባሻገር የብሔራዊ አንድነት፣ የሰላም፣ የብዝኃነት መገናኛና የሀገር ገጽታ ግንባታ ታላቅ መሣሪያ አድርጎታል።
ለ16 ዓመታት ሳይሻሻል የቆየውን የቱርዝም ፖሊሲ በአዲስ በመተካት ዘርፉን በሚኒስቴር ደረጃ ማደራጀት፣ የዲጂታል አሰራርንና የኢ-ቪዛ ቴክኖሎጂን መተግበር እንዲሁም የስብሰባና ኤግዚቢሽን ስትራቴጂን መቅረጽ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ አድርጓታል።
እንደ “ገበታ ለሸገር”፣ “ገበታ ለሀገር” እና “ገበታ ለትውልድ” ያሉ ታላላቅ ፅንሰ-ሀሳቦች በተግባር ተተርጉመው በአጭር ጊዜ ውስጥ አዳዲስ የመስህብ ስፍራዎችን መፍጠር ችለዋል።
በአዲስ አበባ የተከናወነው ሰፊ የኮሪደር ልማትም የሀገራችን ዋና መግቢያ በር ውበትና ምቾት በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። ፈታኝ በሆኑ ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ሁኔታዎች ውስጥም ቢሆን እነዚህ ስልታዊ የልማት ፕሮጀክቶች የኢኮኖሚውን ትንሳኤ የሚያፋጥኑ ትልልቅ በረከቶችን ይዘውልን መጥተዋል።
የዚህ ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤትም ተጨባጭ ስኬት አስገኝቷል። ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የውጭ ቱሪስቶች ቁጥር ከ781 ሺህ ወደ 1.3 ሚሊዮን ማደጉ፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢን ከማሳደጉም በላይ ለሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
እንጦጦ ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚየም፣ ታላቁ ብሔራዊ ቤተመንግስት፣ ደንቢና ጎሪጎራ ኢኮ ሪዞርቶች፣ የሃላላ ኬላ እና የኮይሻ ፓርክ "ከቅርሱ ወደ ቁርሱ" የሚለውን መርህ በተግባር ያሳዩ ናቸው። ኢትዮጵያ በዓለም ቱሪዝም ድርጅት ልዩ ዕውቅና ማግኘቷና በአንድ ዓመት ውስጥ ሦስት አዳዲስ ቅርሶችን በዩኔስኮ ማስመዝገቧም የዚሁ ታሪካዊ ስኬት አካል ነው።
ይሁን እንጂ የተመዘገቡት ስኬቶች የዛሬ ጥንካሬዎቻችን ማሳያ እንጂ የነገው ስልታዊ ጉዟችን ማዘናጊያ አይደሉም። ሀገራችን በቀጣይ ዓመታት የውጭ ቱሪስት ፍሰቱን እስከ 7.3 ሚሊዮን ለማድረስ የሰነቀችው ግዙፍ ብሔራዊ ራዕይ ትልቅና የተቀናጀ ሥራን ይጠይቃል።
ይህንን ታላቅ ግብ ለማሳካት የመንግሥት፣ የግል ዘርፍና የኅብረተሰቡ የተቀናጀ አጋርነት ወሳኝ ነው። የመሠረተ ልማት አውታሮችን በተለይም መንገዶችን፣ አስተማማኝ ኤሌክትሪክን፣ ንጹህ ውሃንና የቴሌኮም ኔትወርኮችን በመዳረሻዎች አካባቢ ማሻሻልና ደህንነቱ የተጠበቀ ምቹ ሁኔታን መፍጠር የቀዳሚነት ደረጃ ሊሰጠው ይገባል።
በተጨማሪም የዲጂታል ቴክኖሎጂን፣ ዘመናዊ የዳታ አያያዝንና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን (AI) በመጠቀም አገልግሎቶችን ማዘመን፤የጎብኚዎችን ልምድ መጠቀምና የሀገር ውስጥ ቱሪዝምን መደገፍና ማበረታታት ይኖርብናል።
ቱሪዝም ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዜጎች ኑሮ መሻሻል ያለውን የማይተካ ሚና በመገንዘብ፣ የተጀመረው አገራዊ የልማት ዐሻራ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሀገራችን ራዕይ እውን እንዲሆን ሁላችንም በጋራ ልንረባረብ ይገባል።
በብሔራዊ ዕድገታችንና በትውልድ ገጽታ ግንባታችን ላይ የሚጋረጡ ማናቸውንም ተግዳሮቶች የምንሻገረው በጀመርነው የልማት መስመር ላይ በጽናትና በአንድነት ስንቆም ብቻ ነው።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

4 days ago