በ110 ሺህ ብር በተገዛ ሰንጋ በሬ ውስጥ ከ10 ግራም በላይ የወርቅ ክምችት ተገኘ
የትንሳኤ በዓል በቃሊቲ የመኖሪያ ካምፕ ለሚገኙ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ፖሊስ አባላት ያልተጠበቀ ነገር አጋጥሟቸዋል።
አባላቱ ለበዓል ቅርጫ ካረዱት ሰንጋ በሬ ሀሞት ውስጥ ከ10 ግራም በላይ የሚመዝን ወርቅ ማግኘታቸውን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አስታውቋል።
የፖሊስ አባላቱ እንደሚናገሩት፣ በዘንድሮው በዓል የከብት ዋጋ በመወደዱ ምክንያት ይህንን ሰንጋ በሬ ለመግዛት ብዙ ድካምና እንግልት አሳልፈዋል።በመጨረሻም በ110 ሺህ ብር የገዙት ሰንጋ፣ ለበዓሉ ድግስ ብቻ ሳይሆን ያልተጠበቀ ወርቅ ይዞላቸው እንደሚመጣ አልገመቱም ነበር።
በአሁኑ ሰዓት የፖሊስ አባላቱ የተገኘውን ወርቅ ለመሸጥ ከወርቅ ተረካቢዎች ጋር የዋጋ ድርድር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።
Via የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
seledadotio

2 months ago