ማህበራዊ ትንሳኤ ከምኞት ወደ እውነታ
*****************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ የነበሩባትን ሥር የሰደዱ ማህበራዊ ስብራቶች ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት በብልሃትና በጥልቀት ስትጠግን ቆይታለች። ዛሬ ላይ ቆመን ስንመለከት ሀገራዊ ግንባታችን በወረቀት ላይ ከሰፈረው ወጥቶ፣ በዜጎች ጤና፣ በእውቀት ብርሃንና በምግብ ዋስትና ዐውድማ ላይ በተግባር እየተተረጎመ ይገኛል። ይህ ጉዞ ተራ የፖሊሲ ማሻሻያ ሳይሆን የኢትዮጵያን የነገ ማንነት የሚወስን ታላቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
ለሰላሳ ዓመታት በፖሊሲ ማነቆ ታስሮ የቆየው የጤናው ዘርፍ፣ ዛሬ አዲስ እስትንፋስ ዘርቶበታል። “ቀድሞ መከላከል ለነገው ተስፋ፣ አክሞ ማዳን ለዛሬው ዋስትና” በሚል ፖሊሲያችን መከላከልን ብቻ ሳይሆን ሕይወትን ታድጎ ማቆየትንም ትልቅ ግቡ አድርጓል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተከናወኑት ተግባራት ዘርፉን ከመሠረቱ የለወጡ ናቸው።
ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓቶችን የማምረት አቅሟን ማሳደጓ፣ የውጭ ጥገኝነትን ቀንሶ የሉዓላዊነታችን አንዱ አካል ሆኗል። ይህ ስኬት በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይወሰን፣ በዓለም አቀፍ የጤና ዲፕሎማሲ መድረክ ኢትዮጵያን የአፍሪካ ድምፅ እንድትሆን አስችሏታል።
ወረርሽኞችን የመለየትና የመቆጣጠር አቅም ማደግ፣ የዲጂታል ጤና ሥርዓት ትግበራ እና የባለሙያዎች ብቃት መጨመር የሀገራችንን የጤና ዋስትና አስተማማኝ አድርገውታል።
“ሳይደግስ አይጣላም” እንዲሉ በትምህርት ዘርፍ የነበረውን የጥራት ውድቀት ለመቀልበስ የተከፈለው መስዋዕትነት ለነገው ትውልድ ትልቅ መሠረት ጥሏል። የሥርዓተ-ትምህርት ክለሳውና የፈተናዎች አስተዳደር መሻሻል የዕውቀት ሌብነትን አክስሞ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋን የመቅረጽ ጉዟችንን አፋጥኖታል።
በተለይም ለጥራት መውደቅ ዋነኛ ምክንያት የነበረውን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ክፍተት ለመሙላት የተጀመረው ንቅናቄ የሚደነቅ ነው። “እንጨት በለጋነቱ፣ ልጅ በጨቅላነቱ” እንደሚባለው የነገውን ምሁር ዛሬውኑ በጥራት ለመቅረጽ የተያዘው ስትራቴጂ በተግባር እየታየ ነው።
በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚገነቡት 1 ሺህ 452 አዳዲስ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ87 ሺህ በላይ ሕጻናትን ወደ ዕውቀት ማዕድ የሚጋብዝ ድንቅ የሀገር ግንባታ ምሰሶ ነው። ይህ ኢንቨስትመንት ለነገው ትውልድ የሚቆረስ የዕውቀት እንጀራ ነው።
ሀገር የምትገነባውና ማህበራዊ ልማት ትርጉም የሚኖረው በምግብ ዋስትና ነውና “የዘሩትን ያጭዳሉ” የሚለው ብሂል በበጋ መስኖ ስንዴ ልማታችን ላይ እውን ሆኗል። በላባችንና በውኃ ሀብታችን የፈጠርነው ተዓምር፣ ኢትዮጵያ ከልመና እጅ ወደ ሰጪነት የምታደርገውን ሽግግር እያፋጠነው ይገኛል።
የውኃ ሀብታችንን በአግባቡ በመጠቀም፣ ባልተቋረጠ ጥረት እና ቁርጠኝነት፣ የመልማት ጉዟችን አስተማማኝና ዘላቂ የሆነ የምግብ ዋስትና ወደምናረጋግጥበት ብሩህ ተስፋ እያሸጋገረን ነው። ይህ የታታሪነት ውጤት ለሀገር ግንባታ ሂደት የጸና መሠረት ጥሏል።
ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩት የማህበራዊ ዘርፍ እንቅስቃሴዎች የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን የኑሮ ጥራት የሚቀይሩ ተጨባጭ ተግባራትን ያቀፉ ናቸው። “ድር ቢያብር አንበሳ ያስር” እንዲሉ፣ እነዚህ የፖሊሲና የተግባር ውጤቶች ተደምረው ነገ የምንረከባት ኢትዮጵያ በጤና የተሻለች፣ በእውቀቷ የዳበረችና በልመና የማታፍር እንድትሆን አድርገዋታል።
ይህ የለውጥ ጉዞ የፖሊሲ ማሻሻያ ብቻ ሳይሆን፣ የዜጎችን ኑሮ በተግባር የመቀየር ታላቅ የትውልድ አደራ መፈጸሚያ ሆኗል። ባለፉት ዓመታት በትምህርት፣ በጤና፣ በክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በባህልና ስፖርት የተመዘገቡ ውጤቶች የነገውን ጉዞ ብሩህ የሚያደርግ ነው። ኢትዮጵያ በማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ የምታደርገው ጥረት ለሌሎችም አርአያ የሚሆንና የዜጎችን ተስፋ የሚያለመልም ታላቅ ስኬት ነው።
የኢቢሲዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

1 month ago