የትግራይ የሰላም እና ለውጥ ምክር ቤት ተመሠረተ
«የትግራይ ሰላምና ለውጥ ምክር ቤት» የተባለ ስብስብ አዲስ አበባ ዉስጥ ተቋቋመ። የተለያዩ የሃገር ዉስጥ መገናኛዎች እንደዘገቡት፤ ከስምንት ወራት በፊት የትግራይ ለውጥ ፈላጊ ኃይሎች ንቅናቄ በሚል የተቋቋመው ማህበር ማኒፌስቶውን በማሻሻል «የትግራይ የሰላም ለውጥ ምክር ቤት» በሚል አዲስ አበባ ላይ የመጀመሪያ የምስረታ ጉባዔውን ትናንት ሰኞ አደርጓል።
በምክር ቤቱ ምስረታ ጉባዔ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተደራዳሪዎች መካከል የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ እና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ጀነራል ጎዕሽ ገብረ ፣ ሰባት ማህበራዊ መሠረታቸውን ትግራይ ያደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣የቀድሞ የክልሉ አመራሮች፣ የቀድሞ ወታደራዊ አዛዦችና ታጋዮች እንዲሁም ማህበራት መገኘታቸዉን የአገር ዉስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። አቶ ጌታቸዉ ረዳ እንደተናገሩት፤ ምክር ቤቱ በቅርቡ መቀሌ እንደሚገባ ተናግረዋል። የምክር ቤቱ ምስረታ ዋና አላማ በክልሉ የሚስተዋለውን ሕገ-መንግስታዊ ስርዓት እና የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት በመጣስ በጉልበት ስልጣን የተቆጣጠረውን የህወሓትን ቡድን በማስወገድ በክልሉ ምርጫ ተደርጎ ህጋዊ መንግስት እንዲመሠረት በተደራጀ መንገድ በመጓዝ ሰላማዊ አስቻይ ሁኔታን መፍጠር ነው መባሉም ተመልክቷል።
ከዚህ ሌላ ትግራይ ክልልን ከጦርነቱ ወደነበረችበት ሕገ መንግሥታዊ የግዛት ቅርጿ በመመለስ ተፈናቃዮች እንዲመለሱ በተደራጀ ሁኔታ መስራት ነዉ። ምክር ቤቱ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ስምረት፣ ባይቶና፣ ዓረና ትግራይ፣ ትንሳኤ 70 እንደርታ እና ቃንቺ ሀቂ እንዲሁም በአፋር ክልል የሚንቀሳቀሱትን የሀራ_መሬት ታጋዮችን ወታደራዊ ክንፍ ማሰባሰቡ ተገልጿል።
DW Amharic

16 days ago