11 hours ago
ኢትዮጵያ ታከብራችኋለች!
የሀገር ህልውና፣ ክብር እና ልዕልና የሚለካው በድንበሮቿ ፅናት እና በህዝቦቿ ሰላም ነው።
ይህንን ሰላም እና ክብር ደግሞ ሌሊት ከቀን፣ በደምና በአጥንታቸው እየገነቡት ያሉት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው። ታሪክ ይለወጣል፣ ትውልድ ያልፋል ነገር ግን ሀገርን ለማፅናት የተከፈለ መስዋዕትነት ሁልጊዜም በክብር መዝገብ ላይ በደማቅ ቀለም ተፅፎ ይኖራል።
ኢትዮጵያ ዛሬም ኩሩ እና ሉዓላዊት ሀገር ሆና እንድትቀጥል ያደረገው የሠራዊቷ የማይበገር ፅናት ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ጠላቶች አከርካሪያቸውን እየሰበረ፣ ዳር ድንበሯን በደሙ እና በአጥንቱ እየጠበቀ ዛሬም በልበ ሙሉነት ቀጥሏል።
የሀገሪቱን አንድነት ለመናድ እና ህልውናዋን አደጋ ላይ ለመጣል የሚነሱ ማናቸውንም የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች ሴራ በማክሸፍ ረገድ የሠራዊቱ ሚና ወደር የለውም።
ይህ ሠራዊት የሰላም ዘብ ብቻ አይደለም፤ የሀገር ሉዓላዊነት የመጨረሻው ምሽግ እና የኩራት ምልክት እንጂ።
የዚህ ሠራዊት ክንዱ ብረት ያቀልጣል! ተራሮችን የሚያናውጥ፣ ጋሬጣዎችን የሚጠርግ እና ማንኛውንም የጠላት ምሽግ የሚያፈራርስ ወታደራዊ የአሸናፊነት ወኔ የተላበሰ ነው።
በጥበብ፣ በብስለት እና በከፍተኛ ሥነ ምግባር የታነፀው መከላከያ ሠራዊታችን የጥፋት ኃይልን ሁሉ ድባቅ በመምታት ሁልጊዜም ድልን ለሀገሩ ያበስራል። ይህ የጀግንነት ሥነ ልቦና እና በላቀ ወታደራዊ ሳይንስ የተገነባው አቅም ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ እንድትቆም አድርጓታል።
ሰሞኑን ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች በጋራ መክፈቻ ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር የሠራዊቱን ድንቅ ተጋድሎ በኩራት አንስተዋል።
ፕሬዝዳንቱ “የመከላከያ ሠራዊት እና የጸጥታ አካላት ኢትዮጵያን የመጠበቅ፣ የመታደግ እና በክብር የማቆየት ትጋታቸው በዘመናት የሚዘከር ነው” በማለት የላቀ እውቅና ሰጥተዋል።
አክለውም ለሠራዊቱ አባላት ያላቸውን ክብር ሲገልጹ÷ “ለቆራጥነታችሁ፣ ለሀገር ፍቅራችሁ፣ ለመፈጸም ብቃታችሁና ለህዝብ ወዳጅነታችሁ መንግስት የላቀ አክብሮት አለው” በማለት የሠራዊቱን የሀገር ፍቅር ጽናት መስክረዋል።
ይህ የሀገሪቱ የበላይ መሪ ምስክርነት ሠራዊቱ የሀገር ጋሻ እና የህዝብ ኩራት መሆኑን በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።
ስለሆነም ህይወታችሁን ለህዝብ ሰላምና ለሀገር አንድነት አሳልፋችሁ የሰጣችሁ፣ በየበረሃውና በየሰንሰለታማ ተራሮች ላይ በብርድና በሙቀት ሀገራችሁን የምትጠብቁ የሠራዊቱ አባላት በሙሉ ታሪክ አይረሳችሁም፣ ትውልድም ያመሰግናችኋል።
ኢትዮጵያ በጀግንነታችሁ ትኮራለች ፤ ኢትዮጵያ ታከብራችኋለች!
በኃይለኢየሱስ መኮንን

12 hours ago
"የራሱን አለም የፈጠረ ባለቅኔ ነበር!"—ፀደንያ ገ/ማርቆስ
#ethiopia | ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ በኢትዮጵያ የሙዚቃና የስነ ጽሁፍ ጉዞ ውስጥ የማይረሱ ደማቅ አሻራዎችን ካሳረፉ ታላላቅ ባለቅኔዎች መካከል አንዱ ነበር።
ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬን አስመልካታ ድምፃዊት ፀደንያ ገማርቆስ የሰጠችው አስተያየት የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።
ፀደንያ ስለ ሙሉጌታ ተስፋዬ ማንነት ጥበባዊ ጥልቅ ስሜቱና የህይወት ፍልስፍናው የተናገረችው አስገራሚ እውነት የባለቅኔውን የተለየ ስብእና አጉልቶ ያሳያል።
ፀደንያ እንደገለጸችው ከሆነ ሙሉጌታ ተስፋዬ ተራ ገጣሚ ሳይሆን "ከዘመኑ ቀድሞ የተፈጠረ ሰው" እንደነበር ገልጻለች።
የምናቡ ጥልቀት የቃላት መረጣውና የነገሮች እይታው የበርካታ ሰዎችን አስተሳሰብ ቀድሞ የተረዳ በሚመስል መልኩ የራሱን እውነተኛና ጥልቅ አለም ፈጥሮ ይኖር የነበረ ታላቅ ባለቅኔ እንደነበር ምስክርነቷን ሰጥታለች።
በዚህ ቁሳቁስና ጊዜያዊ ዝና በተቆጣጠረው አለም ውስጥ ሙሉጌታ የተለየ መንገድ መርጧል።
ፀደንያ እንደምትለው ሙሉጌታ ተስፋዬ "አለም ከማያጓጓቸው ጥቂት ሰዎች መካከል አንዱ" ነበር።
ለውጫዊ ሽልማት፣ ለዝና ወይም ለቁሳዊ ጥቅም ሳይሆን ለጥበቡ እውነተኛ ፍቅርና ለነፍሱ እርካታ ብቻ ይኖር የነበረ ብቸኛ ሰው ነበረ ብላለች።
ሙሌ አለም በጠበቃት ልክ ስላልሆነችለት ወደ ውስጣዊ ማንነቱ ወደ ግጥሙና ወደ አዘጋጀው የራሱ አለም በይበልጥ እንዲያዘነብል አድርጎታል።
የፀደንያ ገማርቆስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ የቀረበችበትና በሙዚቃ አፍቃሪዎች ዘንድ ትልቅ አድናቆትን ያተረፈው "ገዴ" የተሰኘው የመጀመሪያ አልበሟ ሙሉ በሙሉ በባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ ግጥሞች የተሰራ ነው።
ፀደንያ ለስኬቷ መሰረት የሆነውን የሙሉጌታን ብዕርና የጥበብ ጥልቅነት በታላቅ አክብሮትና ፍቅር ታስታውሰዋለች።
በአጠቃላይ የፀደንያ ገማርቆስ ምስክርነት ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ በኪነ ጥበቡ አለም ውስጥ ትልቅ ስም ያለው ብቻ ሳይሆን በህይወት ፍልስፍናውና በመንፈሳዊ ማንነቱ የተለየና ጥልቅ የነፍስ እይታ የነበረው ድንቅ ሰው እንደነበር ዳግም አረጋግጧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen

2 days ago
የአገልግሎትና የቅንነት አርዓያ — ወንድሜ አጋፋሪ ብርሃኑ ስለሺ
የዋሁ፣ ለትንሹም ለትልቁም እኩል ክብርን የምትሰጥ፣ በጎ፣ ቅንና ታማኝ የጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም አገልጋይ... በእውነት ለቃለ እግዚአብሔር አገልግሎትና ምስክርነት የተፈጠርህ በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተህ የምትኖር ሰው ነበርኽ።
በልጅነት አዕምሮዬ የማይጠፋውና ሁልጊዜ በሕሊናዬ የሚመላለሰው ያ ያማረ ገፀ ንባብህ፣ ለቃሉና ለምስጢሩ ያለህ ጥንቃቄ፣ በፍቅርና በተመስጦ የምትሰጠው ምስክርነት ዛሬም ድረስ ትዝ ይለኛል፦
"ሰላም ለአቍያጺከ አዕማድ ያቁም ወበለዝ፤"
"እለ ይጸወራ ቦቶን መልክኣተ ኵሉ ትእዛዝ፤"
"ኢየሱስ ክርስቶስ ምጽላለ ሕይወትየ አርዝ፤"
"ተበአሶ በጽላሎትክ ለአርዌ ዐመፃ ወሕምዝ፤"
"ኢይሳነኒ ለገብርክ ዳግመ እምዝ።"
እያልህ በታላቅ ተመስጦ ምስጢሩን ያቀናኸው የቅድስና ቃል፣ በልባችን ውስጥ የመንፈሳዊነትን ዘር ዘርቶ አልፏል። ለቃሉ ታማኝ ሆነህ ያገለገልከው አምላክ በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖትን ምልጃ ሁላችንንም ይማረን።
መልካሙን ገድል ተጋድለሃል፤ ሃይማኖትህን ጠብቀሃል። አምላከ አቡነ ተክለሃይማኖት ነፍስህን ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጎን በገነት ዕረፍት ያኑርልን። የበረከትህና የቅንነትህ ፍሬ በሁላችንም ዘንድ ይኑር።
ነፍስህ በሰላም ትረፍ፤ ዘላለም በልባችን ትኖራለህ!

9 days ago
እንኳን ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን🙏
በመጽሐፍ ቅዱስ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ያህል ትንቢት የተነገረላት ስለእርሷ የተጻፈላት ሴት የለችም። በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ብዙ ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል፤ የኖኅ መርከብ፣ ሰላማዊት ርግብ፣ የአብርሃም ድንኳን፣ ሙሴ በሲና ያያት ሐመልማል፣ ጽላተ ሙሴ፣ የኢያሱ የምስክርነት ሐውልት፣ የኤልያስ የወርቅ መሶብ፣ የአሮን በትረ፣ የጌዴዎን ፀምር፣ የኖኅ የቃል ኪዳኑ ቀስተ ደመና፣ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት መሰላል፣ የነቢዩ ኤልሳዕ ማሰሮና ሌሎች ምሳሌዎች በሰፊው የተነገሩላት የተጻፉላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ቤተ ክርስቲያን እርስዋን ለመጥራት የምትጠቀምባቸው ቅጽል ስሞቿና ውዳሴዎቿ ምንኛ ድንቅ ቢሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ገላጭነት በቅዱሳን የተነገሩ ምስጋናዎቿስ እጅግ ቢለዩ የክብሯን ያህል የሚገልጿት አይደሉም፡፡
እርሷ የሰው ሁሉ ረዳትና ርኅሩኅ እናት ናት፤ የብርሃን፣ የምሕረት፣ የድኅነትና የአማናዊው ወይን እናት ናት። ከንጉሡ በስተቀኝ የምትቆመው ንግሥት እርስዋ ናት፤ በመስቀል ስር የተቀበልናት የሁላችንም እናት እርሷ ናት፤ እርሷ ዘለዓለማዊ ድንግል ናት፤ እርሷ የእግዚአብሔር ጸጋ የሞላባት ንጽሕት ቅድስት ድንግል ናት፡፡ ከፍጥረት ሁሉ ተለይታ ወላዲተ አምላክ ለመሆን የተመረጠችበት አንዱ ምክንያት እመቤታችን እጅግ ትሑት፣ ፍጽምትና ንጽሕት ስለሆነች ነው። በሉቃስ 1÷48 እንደተጻፈው የአምላክ እናት እንደምትሆን ተነግሯት እንኳን ክብር ይግባትና ከመኩራትና ሌሎችን ከመናቅ ይልቅ ዘመዷ ኤልሳቤጥን ልትጠይቃት ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ወጣች፡፡ ከኤልሳቤጥ ፍጹም ምስጋናና በማሕጸን ያለው ዮሐንስ የሰላምታ ድምጿን ሰምቶ መዝለሉንከሰማች በኋላም “የባሪያይቱን መዋረድ ተመልክቷልና” በማለት በትሕትና ምስጋናዋን አቀረበች እንጂ የትዕቢት ቃል ከአፏ አልወጣም፡፡
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ “እርሷ በእግዚአብሔር ዓይን በታየ የቅድስና ውበት የተሞላች ነበረችና በእርሷ ንጹሕ ማሕፀን ሊያድር ወደደ፤ እንደ ድንግል ማርያም ራሱን ዝቅ ያደረገ ትሑት ማንም የለም” ይላል። ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም “በትሕትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ…” ብሎ ያመሰገናት ይህች ድንግል ከተራሮች አናት ሁሉ ከፍ ያለች ስትሆን ራሷን ዝቅ አድርጋ “እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንደምን ይደረግልኛል” የሚል ምላሽ ለቅዱስ ገብርኤል ሰጠችው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛው አምላክ ልጇ ነውና ማርልኝ ስትለው ምልጃዋ ፍጹም ነው፡፡ በእግዚአብሔር መመረጧ፣ ከሴቶች ሁሉ መለየቷ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆኗ ይህን ክብር አጎናጽፏታልና፡፡ ገዳማውያንም ይህን ልዩ እናትነቷንና ቅድስናዋን አምነው ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሯታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

የምግብ ምርቶች ማስታወቂያ ቁጥጥር ይደረጋል!
- የሚዲያ ተቋማትና አስተዋዋቂዎች ተጠያቂዎች ናቸው
#ethiopia | አዳማ — የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና ጤና አገልግሎት ቁጥጥር ባለሥልጣን የምግብ ምርቶች ማስታወቂያ ለሕዝብ ከመሰራጨቱ በፊት በሕግና በሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ፣ እውነተኛና አሳሳች ያልሆነ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል የማስታወቂያ ቁጥጥር መመሪያ መኖሩን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ በአዳማ ክሎቨርዴል ሆቴል ዛሬ ባዘጋጀው የሚዲያ ግንዛቤ መድረክ፣ የምግብ ምርቶች ማስታወቂያ ቁጥጥርን በተመለከተ ለሚዲያ አካላት ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የምግብ ምዝገባና ፈቃድ ባለሙያዋ ዳግማዊት ንጋቱ እንዳብራሩት፣ የማስታወቂያ አሰራጮች ከአስተዋዋቂዎች የሚቀበሉት መረጃ ትክክለኛነትና ማስታወቂያው የቁጥጥር መመሪያውን ማሟላቱን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው።
በመመሪያው መሠረት የማስታወቂያ አሰራጭ ድርጅቶች በባለሥልጣኑ የተሰጠ ሕጋዊ የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸው እንደሚገባና ባለሥልጣኑ በሚጠይቅበት ጊዜ ያስተላለፏቸውን ማስታወቂያዎች ቅጂና አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ያልተረጋገጡና የተጋነኑ የጤና ጥቅም ጥያቄዎች አይፈቀዱም
የምግብ ማስታወቂያዎች በተገቢ ሳይንሳዊ ማስረጃ ያልተደገፉ የጤና ጥቅም ወይም የፈውስ ተግባር እንዳላቸው አድርገው ማቅረብ እንደማይችሉ ተመላክቷል።
እንዲሁም “ብቸኛ”፣ “ለመጀመሪያ ጊዜ”፣ “ከዚህ ቀደም ያልነበረ”፣ “የሁሉም ምርጫ”፣ “ልዩ” እና “አንደኛ” የመሳሰሉ የተጋነኑ መግለጫዎች በተገቢው ማስረጃ ሳይደገፉ መጠቀም እንደማይፈቀድ ተገልጿል።
የአልኮል መጠጦች ማስታወቂያ ላይ ገደቦች
መመሪያው የአልኮል መጠጦች ለጤና ተስማሚ፣ ለማህበራዊ ስኬት ወይም ለአካላዊ ብቃት ጠቃሚ እንደሆኑ አድርጎ ማስታወቅን ይከለክላል።
በተጨማሪም ከ12 በመቶ በላይ የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦችን ከቤት ውጭ ማስታወቂያ በስተቀር በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮና በሌሎች የሚዲያ አውታሮች ማስታወቅ ላይ ገደቦች መኖራቸው ተጠቁሟል።
ከዚህ ባለፈ አካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናትን በአልኮል ማስታወቂያ ላይ መጠቀም፣ በሕፃናት ፕሮግራሞች ላይ የአልኮል ማስታወቂያ ማስተላለፍና ከ12 በመቶ በላይ የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦች አምራቾች ወይም ነጋዴዎች ፕሮግራሞችን ስፖንሰር ማድረግ እንደማይችሉ ተገልጿል።
የጨቅላ ሕፃናት ምግብ ማስታወቂያ
የጨቅላ ሕፃናት ምግብን በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በጋዜጣና በኢንተርኔት ጨምሮ በማንኛውም የሚዲያ መድረክ ማስታወቅ እንደተከለከለ ተብራርቷል።
በምርቶቹ ማሸጊያ ላይም ከእናት ጡት ወተት ጋር ማወዳደር ወይም “የማይተካ” የሚሉ መግለጫዎችን መጠቀም እንደማይፈቀድ ተጠቁሟል። በሽያጭ ቦታዎች ናሙና መስጠትና የዋጋ ቅናሽ ማስታወቂያ መለጠፍም ከተገደቡት ተግባራት መካከል ናቸው።
ሕፃናትን ያማከሉ ማስታወቂያዎች
ሕፃናትን ያማከሉ ማስታወቂያዎች የልጆችን ዕድሜና የማስተዋል ደረጃ ያገናዘቡ መሆን እንዳለባቸው ተገልጿል።
አንድ ምግብ የተጠቀመ ልጅ ካልተጠቀመ ልጅ በላይ የማህበራዊ ወይም የአእምሮ ብልጫ እንዳለው ማሳየትና ሕፃናት ፈጣን ምግቦችን ከመጠን በላይ እንዲወስዱ ማበረታታት እንደማይፈቀድ ተመላክቷል።
በተጨማሪም የግለሰቦችን ምስክርነት ወይም የግል ልምድ በመጠቀም ስለ አንድ ምግብ ጣዕም፣ ይዘት ወይም ጥቅም ማስታወቅ በመመሪያው የተገደበ መሆኑ ተብራርቷል።
ለሚዲያ ተቋማት የተሰጠው መልዕክት
የምግብ ምርት ማስታወቂያን ከማስተላለፍ በፊት ይዘቱ ከተደነገጉት የሕግና የቁጥጥር መስፈርቶች ጋር መጣጣሙን ማረጋገጥ የሚዲያና የማስታወቂያ አሰራጭ ተቋማት ኃላፊነት መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
መመሪያው ከነሐሴ 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ የፀና መሆኑን የገለጸው ማብራሪያው፣ መመሪያውን በመጣስ የሚተላለፍ ማስታወቂያ ለሚያስተላልፉ አካላት ሕጋዊ ተጠያቂነት ሊያስከትል እንደሚችል አመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#adama #media #foodregulation #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

15 days ago
ተስፋዬ ገሠሠ
ጎምቱ የጥበብ ባለሟል
የሕይወት ታሪክ
ደራሲ፦ ደረጀ ትዕዛዙ
የአዘጋጁ መልዕክት
#ethiopia | የሰው ልጅ ሲፈጠር በምክንያት ነው። እግዚአብሔር አዶልፍ ሂትለርን እና ሞሶሎኒን በአንድ በኩል፤ ማሃትመ ጋንዲ እና አልበርት አንስታይን በሌላ ቋት ሲፈጥር፤ ሕይወትን ፅንሰ ሀሳብ ለመስጠት፤ ለሰዎች ወጥ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ እንዳይኖር ፈልጎ ሊሆን ይችላል ብሎ ማሰብ ይቻላል።
እነዚህ በአንድ ወቅት በተግባራቸው ዓለም ያገናኛቸው ሰዎች፤ ማንነታቸው ቢፈተሽ ማህበራዊ እርከናቸው፤ ስብዕናቸው የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን። ባሕሪያቸው ከተወለዱበት፤ ከያዙትና አብረው ከኖሩት ማህበረሰብ ሊቀዳ እንደሚችል ሁሉ፤ ከየራሳቸውም የዚያ ሥራቸው ነፀብራቅ እንደሆነ ይታመናል። መልካምነትና መጥፎነት ዘወር ብሎ ምንጩ ከዚያው ነው። የሆነው ሆኖ፤ ቅንና አስተዋይ ልቦና መታደል ግን መልካም መታደል ነው። ሁሉም በሚፈፅሙት ተግባር ምድራዊም ሆነ በሰማይ የሚጠየቁበት ወይም የሚመሰገኑበት ነገር እንዳለ ሁሉ፤ እነሱም በየራሳቸው የተደሰቱበት ወይም ተፀፅተው ያለፉባቸው ጊዜያት ስለመኖራቸው አይጠረጠርም።
የሰው ልጅ በማንነቱ፤ በቀለሙ እና በተግባሩ ዥንጉርጉር ነው። እያንዳንዱ ግለሰብ በኖረበት ዘመናት ሁሉ በተግባሩ ለዚች ዓለም ይነስም ይበዛም ስለማንነቱ የሚያስቀምጠው አሻራ አለው። መታወቂያው እንደየ ተግባሩ ቢለያይም ሁሉም ታሪክ አለው። የግለሰቦች ታሪክ የሀገር ታሪክ አካል የሚሆንበትም አገባብ አለ። ይህ የሚሆነው ደግሞ ታሪክ ከቃል ትሬት ወደ ጽሑፍ ተለውጦ ሲመዘገብ፤ በአግባቡ ሲሰነድ፤ ሲያያዝ፤ ከዚያም አልፎ ለቀጣዩ ትውልድ ሲተላለፍ ነው። "የግለሰቦች ታሪክ ስብስብ የሀገር ታሪክ ይሆናል" የሚለውም ከዚሁ ጋር ነው።
ከዚህ ሀሳብ በመነሳት ይህ መጽሐፍ ምን ይዟል? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም።፤ ዋናው ነገር ገልጦ ማነበብ ነው። መጽሐፉ የዕድላቸው እና የሥራቸው ስለ አጋጣሚያቸው ጎምቱ የጥበብ ባለሟል ተባለው ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ የሕይወት ታሪክና ሥራዎችን ይተርካል:: ተስፋዬ ማን ነው? በኖሩባቸው ዓመታት ምን ሠሩ፤ አሻራቸው በሀገር ታሪክ ውስጥ ምን ፋይዳ አለው? የሚሉና ሌሎችንም ተያያዥ ጉዳዮችን ይጠይቃል፤ ይመልሳል፤ ይተነትናል።
ተስፋዬ በአንድ ሙያና ሥራ ብቻ የተወሰነ አይደለም:: የሕይወቱን ከሥራው ጋር እያነፃፀርኩ ማቅረቤም ለዚሁ ነው። ይህ ደግሞ ታሪኩ ሲነበብ ሰልችቶት እንዳይፈጠር ይረዳል የሚል እምነት አለኝ።
አብዛኛው የመጽሐፉ ክፍል ሲዘጋጅ ባለ ታሪኩ በሕይወት ስለነበረ ለመረጃ መብዛትና ተአማኒነት በአጅጉ ጠቅሞኛል። ከዚህ ቀደም ስለ ባለ ታሪኩ የተጻፉና የተነገሩ አጠራጣሪ ታሪኮችንና መረጃዎችን በቃለ መጠይቅ ለማጣራት ዕድሉን ፈጥሮልኛል።
ተስፋዬ በባህሪው "እንዲህ አደረግሁ፤ እንዲህ ፈጠርሁ..." እያለ ማንነቱን የመጎረድም ሆነ የመጎዳት ሰው አይደለም። ድንቅ ድንቅ ተግባሮቹ፤ መናገር የማይፈልጋቸው በጎ ሥራዎቹ ብዙ ናቸው። ስለዚህም በአመዛኙ በደራሲያን ደረጃ የተቀመጡ፤ በማስረጃዎችና በእውነቶች ተረጋግጠው እንዲወጡ ለማድረግ ጥሬአለሁ።
የጥበብ ሰው "አንቱ" አይባልም ከሚል ሀሳብ በመነሳት በአብዛኛው የመጽሐፉ ክፍል "አንተ"ን ብጠቀምም፤ አልፎ አልፎ እንደጽሑፉ አገባብና እንደየሁኔታው አጠራር "ጋሽ ተስፋዬ"፤ "ተጋባዥ ፕሮፌሰር ተስፋዬ" እና "አንቱ"ን ተጠቅሜበታለሁ። በዚህም የባለታሪኩን የመጫወቻም ሆነ የማህበራዊ ክብር የጎደልሁ ሁኚ እንደማይታሰብኝ አተማመናለሁ። እሱም ይህ እንዲሆን ፍቃዱን ሰጥቶኛል። አልፎ አልፎ ሌሎች የጥበብ ሰዎችንም በዚህ መልኩ መጥራቴ አልቀረም።
አልፎ አልፎ በታሪክ አፅንኦት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችን እና በቃለ መጠይቅ ያገኛኋቸውን ሀሳቦች እንዳሉ አስቀምጣቸዋለሁ። በዚህም ወዳጆቹን፤ የሥነ ጥበብ ተማሪዎቹን፤ ቅርበት ያላቸው ቤተሰቦቹን እና ዘመዶቹን ጭምር አነጋግሬ የእውነተኝነት ቃላቸውን እንደ አግባቡ አሰፍሬአለሁ። አንዳንድ በሕይወት የሌሉና እኔ በአካል ያላገኘኋቸው ጥቂት ወዳጆቹ፤ በተለያዩ ወቅቶችና መድረኮች ስለ ተስፋዬ የሰጡትን የምስክርነት ቃል ስብስቤ አድርጌ አቅርቤአለሁ። ሥራዎቹን፤ በተለያዩ ጊዜያት ስለ እሱ የተጻፉና የተነገሩ ጉዳዮችን ፈትሻለሁ። የግል ማስታወሻና የተወሰኑ የዕለት ማስታወሻዎቹን /Daily diary/ ጭምር በርብሬአለሁ። ለዚህ ይጠቅማል፤ ይበጃል ያልኩትን ቁም-ነገር፤ ፍሬ-ነገር፤ ይሆናል ልክነቱን ነቅሼ በማውጣት በአስፈላጊው ቦታ አስፍሬአለሁ። ይህ ነው የዚህ መጽሐፍ ሂደት።
ይህ መጽሐፍ፤ የሕይወት ታሪክ (Biography) አጻጻፍ መርሁን የተከተለ እንዲሆን አድርጌአለሁ። ጋሽ ተስፋዬ የዚችኛውን ዓለም የጥበብ አውራ ኖሮ በ84 ዓመት ዕድሜው ወደማይቀረው ሄዷል። ከዚችኛዋ ዓለም በአካል ሞት ቢለይም ሥራውና ማንነቱ ግን እንዲህ ሲወሳ እና ሲዘከር ይኖራል።
መልካም ንባብ
***
የመጽሐፉ የጀርባ
“ግልጽነትን የሚያደፋፍርህ እውነት ነው። ሐሰት ውስጥህ ካለ ለመናገር ትሸማቀቃለህ። እርግጥ የፖለቲካ ሰዎች ይህንን ሊያደርጉት ይችላሉ፤ የፖለቲካ ሰው ግን ዲፕሎማት ነው። የሚናገረው የት፤ መቼ፤ እንዴት፤ ለማን፤ የሚሉትን አጢኖ፤ መትሮ ነው።
እኔ የፖለቲካ ሰው አይደለሁም፤ ተፈጥሮዬ አልፈቀደም። ስለዚህ ፊት ለፊት እናገራለሁ። መስዋዕትነት መክፈል አለብኝ፤ ይሁኑ! ይክፈል፤ እውነትን የያዘ ሁሉ ግን አሸናፊ ነው። በነጻ ህሊና ይኖራል።”
“ከፖለቲካዊ ሹመቱ በሕዝብ የታመነበት ሽልማት ይበልጥብኛል። ያስተማርኳቸው የጥበብ ልጆቼ በመድረክ፤ በፊልም፤ በሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ተሰማርተው ማየት ደስታ ይሰማኛል። ፍሬ አለኝ፤፤ ትልቁ ሽልማቴ እነሱ ናቸው።”
***
የአዘጋጁ ቀደሙት ሥራዎች፦
ደራሲ ደረጀ ትዕዛዙ
ጳውሎስ ኞኞ ከ1926-1984 (የሕይወት ታሪክ)
ሳተናው (የአጫጭር ልብወለዶችና የግጥሞች ስብስብ)
#የሕይወትታሪክ #ተስፋዬገሠሠ #መጽሐፍ #ኪነጥበብ #ደራሲደረጀትዕዛዙ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

18 days ago
«ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር» - ሮዛ
በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የተለቀቀውንና ውዝግብ ያስነሳውን የሃይማኖት አባት ፀያፍ ቪዲዮ እውነተኛነት አስመልክቶ «ተበዳይ ነኝ» ያለችው ግለሰብ ምስክርነት ሰጠች።
የግንኙነቱ መጀመር፦ አክሱም ከተማ ውስጥ ሆቴል በአስተናጋጅነት የምታገለግለው ሮዛ የተባለችው ግለሰብ፤ ከዓመት በፊት የትግራይ መንበረ ሰላም ጳጳስና ዋና ጸሐፊ ከሆኑት አቡነ አረጋዊ ጋር መተዋወቋን እና ቆይቶም ግንኙነታቸው ወደ ጾታዊ ግንኙነት ማደጉን ተናግራለች።
የቪዲዮው መቅረጽ እና የቀረበው ጉቦ፦ ጳጳሱ ጾታዊ ጥቃት እንዳደረሱባት በመግለጽ፣ መግቻ ይሆን ዘንድ በድብቅ ቪዲዮ መቅረጿን የገለጸች ሲሆን፤ ቪዲዮውን እንድታጠፋ ከጳጳሱ እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ እንደቀረበላት ገልጻለች።
የዛቻና የደህንነት ስጋት፦ ብር ከመቀበል ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ጸያፍ ተግባር እንድትላቀቅ ባላት አቋም እስከ የመግደል ሙከራ ዛቻ እንደተደረሰባትና ቪዲዮው ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ መለቀቁን አብራርታለች።
ተጨማሪ ጥቆማዎች፦ ሮዛ እሷን ጨምሮ በአክሱምና ከአክሱም ውጪ የጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው 4 ሴቶችን እንደምታውቅና እንደምታጋልጥ አረጋግጣለች።
የአሁኑ ሁኔታ፦ ጳጳሱም ሆኑ በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ እስካሁን የሌለ ሲሆን፤ ሮዛ በቂ የሕግ አገልግሎት እየተሰጣት በአክሱም ከተማ ትገኛለች።
Seledadotio

21 days ago
የተፈጥሮ ሕግ ለምን አይሻሻልም?
* ከተፈጥሮአዊ ህጋዊ እይታ አንጻር የህግ አወጣጣችንን ለመዳሰስ የቀረበ ጹሑፍ
መግቢያ #ethiopia | የተፈጥሮ ህግ (Natural Law) ከሰው ልጅ ታሪክ፣ ስልጣኔና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ቀድሞ የነበረ፣ አጽናፈ-ዓለምና የሰው ልጅ ህልውና የሚመሩበት ዘላለማዊ ሰንሰለት ነው። የሰው ልጅ ማህበራዊ ኑሮውን ለመምራት ህጎችን ያወጣል፣ ይሽራል፣ ያሻሽላል። ነገር ግን የተፈጥሮ ህግ ጊዜ የማይሽረው፣ ቦታ የማይወስነውና በፍጹም የማይሻሻል ፍጹም እውነት ነው። ይህ ጽሑፍ የተፈጥሮ ህግ ለምን ሊሻሻል እንደማይችል፣ በሳይንስ፣ በሃይማኖትና በጥንታውያን ፈላስፋዎች እይታ መርምሮ፣ እኛ ሰዎች በህግ አወጣጥ ሂደታችን ውስጥ ምን መማር እንዳለብን በጥልቀት ያብራራል።
ዋና ዋና አንኳር ይዘቶች
1. ፍጹም ንጽህና፣ ፍጹም እውቀትና የህግ ምንጭ
በፍልስፍና እይታ ህግን ለመደንገግ ፍጹም ንጽህና (ከራስ ወዳድነትና ከጥቅም ግጭት የጸዳ እውነት) እና ፍጹም የበሰለ እውቀት ያስፈልጋል። ይህ ፍጹም ንጽህናና እውቀት ደግሞ የሁሉም ነገር ፈጣሪ የሆነው የአምላክ መገለጫ ነው። የተፈጥሮ ህግ ምንጩ ፍጹም የሆነው መለኮታዊ ጥበብ በመሆኑ መሻሻል አያስፈልገውም። እኛ ሰዎች ግን ማህበራዊ ህጎችን ስናወጣ ፍጹም ንጽህና (ከቡድንና ከግል ጥቅም የጸዳ) እና የበሰለ እውቀት (የማህበረሰቡን ስነ-ልቦና፣ ታሪክና የወደፊት እጣ ፈንታ ያገናዘበ) ሊኖረን እንደሚገባ የተፈጥሮ ህግ ያስተምረናል። ፍጹም እውቀት ሳይኖር የሚወጣ ህግ ሁልጊዜም ጎደሎና ተሻሻይ ነው።
2. የኮስሞስ ምስክርነት እና የተፈጥሮ ህግጋት መገለጫዎች
የተፈጥሮ ህግጋት የማይለወጡና የማይደክሙ መሆናቸውን በዙሪያችን ባለው ዓለም በተግባር እንረዳለን፡
• የፀሐይ ብርሃንና ኃይል፦ ፀሐይ በየቀኑ የምትሰጠው የብርሃንና የሙቀት ኃይል መቼም ቢሆን አያልቅም። ይህ ጽኑ ህግ ማሻሻያ አያስፈልገውም።
• ብርሃን፣ ጨለማና የፀሐይ ዙረት፦ መሬትና ፕላኔቶች በፀሐይ ዙሪያ የሚያደርጉት ስልታዊ ዙረት የቀንና የሌሊት (የብርሃንና የጨለማ) ኡደትን ይፈጥራል። ይህ የስነ ፈለክ ህግ ሳይዛነፍ ለዘመናት የጸና ነው።
• የህይወት ኡደት (መወለድ፣ መኖር፣ መሞት)፦ ማንኛውም እንስሳም ሆነ እጽዋት ይወለዳል፣ ይኖራል፣ ይሞታል። የእነሱ የእንትንፋስና የህልውና ህግ ማንም ሰው ሊሽረው የማይችል የተፈጥሮ ዑደት ነው።
3. የሳይንስ ህግጋት ጽኑነት (ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪና ባዮሎጂ)
በሳይንስ ዓለም ውስጥ የምናገኛቸው ህጎች የሰው ልጅ የደረሰባቸው የተፈጥሮ እውነታዎች እንጂ ሰዎች የፈጠሯቸው አይደሉም። ለዚህም ነው የማይሻሻሉት፡
• የፊዚክስ ህግ (የኃይል ጥረት ህግ)፦ በፊዚክስ ትልቅ ስፍራ ያለው ህግ "ኃይል (ኢነርጂ) አይፈጠርም፣ አይጠፋምም፤ ከአንድ ቅርጽ ወደ ሌላ ቅርጽ ይለወጣል እንጂ" (Energy is neither created nor destroyed, it can only be transformed from one form to another) ይላል። ይህ ህግ ከዘላለም እስከ ዘላለም የማይሻሻል የተፈጥሮ እውነት ነው።
• የኬሚስትሪና ባዮሎጂ ህግጋት፦ ውሃ ሁልጊዜ ከሁለት ሀይድሮጅንና ከአንድ ኦክስጅን (H₂O) ይፈጠራል። የሰው ልጅ ስነ-ህይወታዊ (Biological) መዋቅር፣ የደም ዝውውርና የሴሎች ኡደት በተመሳሳይ ጽኑ ህግ የሚመሩ ናቸው። እነዚህ የሳይንስ ህጎች የሰው ልጅ ህግጋት ምን ያህል ደካማና ተለዋዋጭ እንደሆኑ ትልቅ ማስረጃዎች ናቸው።
4. "አዳም አትብላ"፦ የመጀመሪያው ህግ፣ ሞት፣ ካሳ እና ህይወት
በትዕዛዝ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠው ህግ ለአዳም የተቀመጠው "ይህን ዕፅ አትብላ፣ ሌላውን ግን ብላ" የሚለው መለኮታዊ ህግ ነበር። ይህ ክስተት የህግን መዋቅር ፍልስፍናዊ በሆነ መንገድ ያሳያል፡
• ህግ (Law)፦ ድንበርንና ክልከላን ያስቀምጣል። "አትብላ" መባሉ የህግ የበላይነትን ያሳያል።
• ሞት (Death)፦ ህግ ሲጣስ የሚመጣውን ፍጹም ቅጣትና ውጤት ያመለክታል። አዳም ህጉን በመጣሱ ምክንያት ሞት ወደ ዓለም ገባ።
• የሞት ካሳ (Compensation for Death)፦ ፍትህ መዛባትን አትፈቅድም። ለተፈጠረው ጥፋትና ሞት ተመጣጣኝ የሆነ የካሳ ወይም የቤዛነት ህግ አስገዳጅ ሆነ።
• ህይወት (Life)፦ ከካሳውና ከፍትህ መረጋገጥ በኋላ የሚመጣውን አዲስ ተስፋና ህይወትን ያሳያል። ይህ ዑደት ህግ የራሱ የሆነ የውጤትና የፍትህ ሚዛን ማስጠበቂያ ሰንሰለት እንዳለው ያስገነዝበናል።
5. የሰው ልጅ ህግጋት ተለዋዋጭነት (የምዕራባውያን አገራት ማሳያ)
ከተፈጥሮ ህግ በተቃራኒ፣ በሰዎች የሚወጣ ህግ ሁልጊዜም ተለዋዋጭ ነው። የሰዎች ህግ የመንግስታት ስልጣን በየጊዜው ሲቀያየር፣ የመሪዎች ወንበር ሲናወጥና እንደየአስፈላጊነቱ አብሮ ይለወጣል። ለአብነት ያህል የታላላቅ ምዕራባውያን አገራትን ህግ መመልከት ይቻላል፡
• የአሜሪካ ህግ (United States)፦ የአሜሪካ ህገ-መንግስት ከተረቀቀ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከ27 ጊዜ በላይ ማሻሻያ (Amendments) ተደርጎበታል። ይህም የሰዎች ህግ ፍጹም ባለመሆኑ በየጊዜው መታረም እንዳለበት ያሳያል።
• የካናዳ ህግ (Canada)፦ የካናዳ የህግ ስርዓትም እንደ ማህበረሰቡ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ፍላጎት በየጊዜው ማሻሻያዎችንና አዳዲስ አዋጆችን ያወጣል።
• የእንግሊዝ ህግ (United Kingdom)፦ እንግሊዝ ያልተጻፈ ህገ-መንግስት ያላት አገር ስትሆን፣ ህጎቿ እንደ ፓርላማውና እንደ ገዢው ፓርቲ ፍላጎት በየቀኑ ሊለወጡና ሊሻሻሉ ይችላሉ።
እኛ ሰዎች በህግ አወጣጥ ምን እንማር?
የሰው ልጅ ህግ አውጪዎች ከተፈጥሮ ህግ መማር ያለባቸው ዋናው ቁምነገር፡ ህግ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ጥቅም ወይም ለስልጣን ማራዘሚያ የሚሆን ሳይሆን፣ እንደ ተፈጥሮ ህግጋት ሁሉ ትውልድ ተሻጋሪ፣ ፍትሃዊ፣ ተገማችና ሚዛናዊ መሆን እንዳለበት ነው። ህግ ሲወጣ በጥልቅ እውቀትና ከግል ጥቅም በጸዳ ንጽህና መሆን አለበት። ከተፈጥሮ ህግ (ከሞራልና ከፍትሃዊነት) የራቀ ሰው ሰራሽ ህግ ህግ ሳይሆን የጭቆና መሳሪያ ነው።
ማጠቃለያ
የተፈጥሮ ህግ የማይሻሻለው አስቀድሞ ፍጹም፣ ፍትሃዊና ሚዛናዊ በሆነው መለኮታዊ እውቀትና ንጽህና ስለተሰራ ነው። የሰው ልጅ ህግ ግን የመንግስታት መቀመጥና መነሳት፣ የሰዎች ፍላጎት መቀያየር የሚወስነው ተለዋዋጭ ሂደት ነው። የህግ ባለሙያዎችም ሆኑ ማህበረሰቡ ህግን ሲያወጡና ሲተገብሩ፣ ከተፈጥሮ ህግጋት በስተጀርባ ያለውን ፍጹም ንጽህና፣ የበሰለ እውቀት፣ ተገማችነትና ፍትሃዊነት እንደ መርህ በመውሰድ፣ የሰዎች ህግም ለዘላቂ ትውልድና ለፍትህ መከበር የሚቆም እንዲሆን ማድረግ ይኖርባቸዋል።
ማጣቀሻዎች
• ቅዱስ መጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስ)፦
o "ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም" (ማቴዎስ 24:35) — መለኮታዊና የተፈጥሮ ህግጋት የማይለወጡ መሆናቸውን ያሳያል።
o "በገነት ካለው ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ..." (ዘፍጥረት 2:16-17) — የመጀመሪያው ህግ፣ ክልከላ እና የሞት ውጤት ምሳሌ።
• ቅዱስ ቁርዓን፦
o "በአላህ የፍጥረት ህግ ላይ ምንም ለውጥ አታገኝም፤ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው" (ሱረቱ አል-ሩም 30:30) — ፍጥረት የተገነባበት የተፈጥሮና የመለኮት ህግ ጽኑና የማይቀየር መሆኑን ያስረዳል።
• የትላልቅ ሰዎች ፍልስፍና፦
o ሶክራትስ (Socrates)፦ ህግ ከጽንሰ-ሃሳባዊ ፍትህና ከሞራል እሴት መነጨት እንዳለበትና ፍጹም እውቀትን መፈለግ የህግ መሠረት መሆኑን አስተምሯል።
o ፕላቶ (Plato)፦ "ሪፐብሊክ" (The Republic) በተሰኘው መጽሐፉ ላይ አገሪቱን የሚመሩና ህግ የሚያወጡ ሰዎች ጥበብና የበሰለ እውቀት ያላቸው "ፈላስፋ ነገሥታት" (Philosopher Kings) መሆን እንዳለባቸውና ይህም የህግን ንጽህና እንደሚያስጠብቅ ገልጿል።
o አሪስጣጣሊስ (Aristotle)፦ የተፈጥሮ ፍትህ (Natural Justice) በሁሉም ቦታ እኩል ኃይል አለው፣ ሰዎች ስላጸደቁት ወይም ስላልተቀበሉት አይለወጥም በማለት የሰው ልጅ ህግ ከተፈጥሮ ህግ ጋር መጣጣም እንዳለበት ተከራክሯል።
https://www.facebook.com/s...
በፋንታሁን ደለለው (Fantahun Delelew)
ህግ አዋቂ (Lawyer)
ስልክ፦ 0929101037

Sponsored by
Surafel
22 days ago
ተናግሮ ማድረግ ፣ ቃል ገብቶ መፈጸም:- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ
***********************
የዘንድሮው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ተራ የቀን መቁጠሪያ ለውጥ ብቻ አይደለም። ሀገራችን አዲስ ገጽ ገልጣ አዲስ ታሪክ ጽፋለች፤ መርጣለች፣ መክራለች፣ አሸንፋለች፣ አንሰራርታለችም። ፈተናዎች ወደ ታላቅ ዕድል ተቀይረዋል።
በጸኑ እና ዝቅ ብለው በሠሩ ልጆቿ ጥረት የዘመናት የአዙሪት ጥላ ላይመለስ ተገፏል፤ ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት ብቻ ለበርካታ አስርት ዓመታት ያላሳካናቸውን ድሎች ማሳካት ችለናል። ሩቅ የማለም፣ አቅዶ የመጀመር እና በፍጥነት የማጠናቀቅ አዲስ የሥራ ባህልም ገንብተናል። ይህ የሀገራችንና የመንግሥቷ ልዩ መገለጫ ሆኗል።
ዛሬ በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር የሚጨበጥ ብርሃን ፈንጥቋል። ከአፈሙዝ የሥልጣን ውርስ ተላቆ «ሀገረ መንግሥት በሕዝብ ካርድ ብቻ ይጽና» የሚል ድምፅ ከአጽናፍ አጽናፍ አስተጋብቷል። ሕዝባችን ቀን በፀሐይ፣ ሌት በውርጭ፣ ከሕመሙ ታግሎ፣ አትምረጥ ካለው ጋር ገጥሞ፣ የሚፈልገውን ነግሮናል። ሀገር አጽንቷል፣ ዴሞክራሲን መርጧል።
በሀገራዊ የምክክር ማዕቀፍ የኅብረ-ብሔራዊቷ ሀገራችን ልጆች ተሰባስበው ስለ እናት ሀገራቸው በአንድ አዳራሽ መክረዋል፤ ዘክረዋል። ይበጃል ያሉትን በጎ ሐሳቦች በነፃነት አቅርበዋል። በአጭሩ በኢትዮጵያ ምድር በዘመኑ አርበኞች አዲስ ገድል ተፈጽሟል። ይህ እውነት የልጆቻችንን ተስፋ ያለመለመ፣ በዘመናት መካከል በኩራት የምንተርከው ወርቃማ ታሪካችን ነው።
አንቆምም! ገና ብዙ ሥራ አለብን፤ እንፈጥናለን፣ መሰናክሎቻችንን ሁሉ በብሕላት እየዘለልን ወደ ሀገራችን መሻቶችና ሕልሞች በጽናት እንዘልቃለን። ታላቅ ሀገር አለችን፤ እየተማከርን እንገነባታለን፣ እየገነባንም እንማክራለን። ሁሉንም አሸናፊ ያደረገው አዲሱ መንገዳችን ይኸው ነው። መመካከር ።መመካከር ። መመካከር።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሕግ የበላይነት በጥብቅ ዲሲፕሊን ከተመራበት መንገድ ጎን ለጎን፣ መንግሥታችን ያጠፉ ልጆቹን በምሕረት አቅፏል፤ በርካታ የፖለቲካ እስረኞችን በይቅርታ ፈትቷል። ይህ ውሳኔ ብዙ ሀገራት የተመኙት፣ ኢትዮጵያ ግን ያሳካችው የበቀል አዙሪትን የሰበረ ታላቅ እርምጃ ነው።
ውሳኔው ለሀገራችን ዘላቂ ጥቅም ሲባል የተከፈለ ውድ ዋጋ መሆኑን የመደመር መንግሥት ይገነዘባል። ይቅርታ የጽኑ ሀገረ-መንግሥት ዋነኛ ምሰሶ ነው፤ ውሳኔው ከሀገራዊ ምክክሩ ጋር ተጣጥሞ ብሔራዊ መግባባትን ያጠናክራል። የተፈቱት ወገኖቻችን ዕውቀታቸውን እና አቅማቸውን ለሀገር ግንባታ እንደሚያውሉ እናምናለን፤ ይህም ለነገዋ ኢትዮጵያ የማይናወጥ መሠረት ይጥላል።
ከፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ መግባባት ጎን ለጎን፣ በአንድ ሀገር ፖለቲካዊ መረጋጋት እየተሻሻለ የሚመጣው በሀገር ደረጃ ጠንካራ የኢኮኖሚ ስኬቶች ሲመዘገቡ እና ሕዝባዊ አመኔታ ሲገነባ ነው። ኢትዮጵያ ይህን አድርጋዋለች።
ዛሬ ላይ በሀገራችን እየተመዘገበ ያለው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት በአፍሪካ ፈጣኑ እና መሠረቱ የሰፋ አስደናቂው እድገት ነው። ይህን እውነት ባንዳውም ባዳውም ሳይወድ በግዱ ይቀበለዋል።
የመደመር መንግሥት ጉርሷን የማትለምን እና ክብሯን የጠበቀች ሉዓላዊት ሀገር ለመፍጠር
በሁሉም መስክ ጥረት አድርጓል ።አበራታች ስኬቶች ተመዝግበዋል። ከለጋሽ እጅ ስንዴ የመጠበቅ ታሪካችን አብቅቶ በበጋ ስንዴ ራስን ከመቻል ያለፈ አዲስ ታሪክ ጽፈናል።
በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል የራሳችንን ክብረ ወሰን ደጋግመን አሻሽለናል፤ በአካባቢ ጥበቃም ለዓለም አቀፍ ትብብር አርአያ ሆነናል። ይህ ስኬት በሌላ ሀገር የተፈጸመ ቢሆን ምንኛ በተነገረ ነበር፤ ዳሩ ግን እኛ ድልን ደጋግመን ያጣጣምን የጀግኖች አባቶቻችን ልጆች ነን። ፈጽመነዋል።
ርዕያችን ሩቅ ነው ፣ መንገዳችን መደመር ነው፣ ስንደመር አትርፈናል ፤ ስንሰባሰብ ጠንክረናል። በሌሎች ሀገራት የጸብ መንስኤ፣ የሀገር ዕዳ የሆኑትን ማዕድናት እኛ የሀገር ምንዳ ፣ የሀገር ተስፋ አድርገናል፤ በታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶቻችን ቀጣናውን አስተሳስረናል፤ የከተሞቻችን ገጽታ በዘመናዊ የኮሪደር ልማት ተለውጧል። የኮንፈረንስ ቱሪዝም ተስፋፍቷል ፤ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ገንበተናል።
ነባር ቅርሶቻችንንም አቧራቸውን አራግፈን ወደ ነገ አሻግርናል።
ትውልድን አስበን የዲጂታል 2030 ስትራቴጂን ተግባራዊ እያደረግን ነው። የመንግሥት አሠራርንም ግልጽና ቀልጣፋ ለማድረግ መሠረት ተጥሏል ። ከሁሉም በላይ ሀገራችንን ከሚሽኮረመም የውጭ ፖሊሲ አላቀን ለብሔራዊ ጥቅማችን በጽናት ቆመናል ፤ በአለም መድረክ የሚገባንን ጠይቀናል።
የምንገነባው ሀገረ-መንግሥት የመደመር እሳቤ ላይ የተመሠረተ ነው ፣ ትኩረቱም በጽኑ ተቋማት ግንባታ ላይ ነው። የፍትሕ፣ የፀጥታ እና የዴሞክራሲ ተቋሞቻችን ጠንካራ መሠረት ይዘዋል። ወገባችንን አጥብቀን ዝቅ ብለን በሠራነው ሥራ ቀና ብለን መሄድ ጀምረናል፣ ዛሬ ላይ ሀገር የሚሸከሙ፣ መጪውን ጊዜ የተለሙ እና ከሥርዓት መቀያየር የተሻገሩ ተቋማዊ አቅሞች ተፈጥረዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት፣ የለውጡ መንግሥት ልዩ የሚያርገውን መገለጫን አስተዋውቋል፤ ፕሮጀክቶችን ይጀምራል፣ አጠናቆም ይመርቃል። ይህ በሕዝባችን አንደበት ተደጋግሞ የሚነገር እውነትኛ ምስክርነት ነው። የተዘጉ ኢንዱስትሪዎች ተከፍተዋል፤ ለዘመናት የኪሳራ ምሳሌ የሆኑ ተቋማት ወደ ትርፋማነት ተሸጋግረዋል ፤ በኢንቨስትመንት ፣በኤክስፖርት እና በተኪ ምርት እመርታዊ ለውጥ አሳክተናል።
ከዚህም በላይ ታላቁን የህዳሴ ግድባችንን ባጠናቀቅንበት ማግስት በጉባ ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ እና የኢትዮጵያን መጻኢ ዕድል የሚወስኑ አዳዲስ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ለሕዝባችን አብሰረነዋል።
የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ የኒውክሌር ማዕከል ለመገንባት አዲስ ውል ታስሮ ሥራ ተጀምሯል ፤ በሶማሌ ክልል የኢትዮጵያ ጸጋዎችን ገልጠናል። የተፈጥሮ ጋዝ ማጣሪያ ፕሮጀክቶች ቀን ከሌት እየተሰራ ይገኛል ። በዓመት 100 ሚሊዮን መንገደኞችን የሚያስተናግደው የቢሾፍቱ ኤርፖርት የአፍሪካ አቪዬሽን ዘውድ ደፍቶልን በሰማዩ ያነግሰናል።
በዓመት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያድነው የማዳበሪያ ፋብሪካም የግብርና ምርታማነትን በማረጋገጥ ለገበሬዎቻችን እፎይታ ይሆናል ፤ ተስፋችን ብዙ ነው። የብዙዎችን ህይወት የሚቀይረው የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ልማት ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ሥራው ተጀምሯል። እናሳካዋለን ! ተናግሮ ማድረግ ፣ ቃል ገብቶ መፈጸም በመደመር መንግሥት ለትውልድ የተጣሉ ጠንካራ መሠረቶች ናቸው።

24 days ago
በአበሽጌ 13 ሰዎች ተገደሉ‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው እና ልዩ ስሙ "ዋልጋ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ፣ ትላንት መስከረም 4/2019 ዓ.ም ምሽት 3 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች በከፈቱት አሰቃቂ ጥቃት ቢያንስ 13 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ተሰማ። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ምስክርነት፣ ታጣቂዎቹ ንጹሃኑን ከመግደል ባለፈ 16 ያህል ሴቶችን በአስገዳጅ ሁኔታ አፍነው ወስደዋል።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ታፍነው የተወሰዱት ሴቶች የት እንዳሉ እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅ አልተቻለም።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው እና ልዩ ስሙ "ዋልጋ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ፣ ትላንት ምሽት 3 ሰዓት ገደማ ታጣቂዎች በከፈቱት አሰቃቂ ጥቃት ቢያንስ 13 ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ተሰማ። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ምስክርነት፣ ታጣቂዎቹ ንጹሃኑን ከመግደል ባለፈ 16 ያህል ሴቶችን በአስገዳጅ ሁኔታ አፍነው ወስደዋል።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ታፍነው የተወሰዱት ሴቶች የት እንዳሉ እና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ማወቅ አልተቻለም። ጥቃቱን የፈጸሙት አካላት እነማን ናቸው በሚለው ዙሪያ ነዋሪዎቹ ሲያስረዱ፣ አጥቂዎቹ ራሳቸውን "ፋ .. ኖ" ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ናቸው ብለው እንደሚያምኑ መግለጻቸው ተሰምቷል። ይህ ክስተት በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን እና የጸጥታ ስጋትን የፈጠረ ሲሆን፣ የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል የጸጥታ አካላት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጡት ይፋዊ መግለጫ የለም።
ይህ በጉራጌ ዞን የተፈጸመው አሳዛኝ ጥቃት፣ የሀገሪቱ የጸጥታ መደፍረስ ከዋና ዋና የጦርነት ቀጠናዎች አልፎ አንጻራዊ ሰላም ወደነበረባቸው አካባቢዎችም እየተስፋፋ መምጣቱን የሚያሳይ አደገኛ ምልክት ነው ተብሏል። በተለይም ንጹሃንን ከመግደል ባለፈ ሴቶችን አፍኖ መውሰድ፣ ግጭቶች ምን ያህል ወደ አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና የሽብር ተግባር እያመሩ መሆናቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ጥቃቱን ፈጽመዋል የተባሉት አካላት ማንነት በነዋሪዎች የተጠቆመ ቢሆንም፣ የጸጥታ አካላት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብተው እውነታውን በማጣራት ታጋቾቹን ማስለቀቅ እና በአካባቢው ላይ የተደቀነውን የደህንነት ስጋት መፍታት ካልቻሉ፣ የዜጎች በመንግስት ጥበቃ ላይ ያላቸው እምነት ይበልጥ ሊሸረሸር ይችላል።

26 days ago
ኢትዮጵያ - የአፍሪካ ጠንካራ ተሟጋች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪኳ የአፍሪካን የጋራ ድምጽ ከማስተጋባትና ለአህጉሪቱ ጥቅም መከበር ጥብቅና ከመቆም ተነጥሎ የሚታይ አይደለም፡፡
ትናንት አፍሪካውያን ከቅኝ ግዛት ለመላቀቅ ባደረጓቸው ተጋድሎዎች ለነጻነታቸው አጋር ነበረች፤ የአፍሪካ ሀገራት አንድነታቸውን አጠንክረው ተሰሚነታቸውን እንዲያሳድጉ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጥላ ሥር በማሰባሰብ ደማቅ ታሪክ ጽፋለች፡፡
የመደመር መንግሥት ይህንን ታሪካዊ አሻራ በሚያጎላ የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ መንገድ፤ ኢትዮጵያ ዛሬም ስለ አፍሪካና አፍሪካውያን መብትና ጥቅም በተገኘችባቸው የዓለም መድረኮች ሁሉ ድምጽ ሆና ቀጥላለች፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ስለ አፍሪካ ፍትሃዊ ውክልናና ተጠቃሚነት በጽኑ ሞግተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ከጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና፤ አፍሪካን ያማከለ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓትን እስከማንበር ያነሷቸው ጠንካራ ጉዳዮች ኢትዮጵያ ታሪካዊ ሚናዋን አጠናክራ መቀጠሏን ያረጋገጡ ናቸው፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ አፍሪካ ቋሚ ውክልና እንዲኖራት በአፍሪካ ኅብረት በኩል የተያዘውን የጋራ አቋም እንደምትጋራ ገልጸው፤ ብሪክስ ለአፍሪካ የፍትሃዊ ውክልና ጥያቄ ድጋፍ እንዲያደርግ አበክረው ጠይቀዋል፡፡
አፍሪካ በኃይል ልማት፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና ቀጣናዊ ንግድ ወሳኝ እድሎች እንዳሏት ጠቁመው፤ አህጉራችን ከፍተኛ መሰረተ ልማት ያስፈልጋታል ሲሉ በመድረኩ ላይ የአፍሪካን መሻት አስተጋብተዋል፡፡
የብሪክስ ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ በአፍሪካ ሰፊ ተሳትፎ ሊያደርግ እንደሚገባ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ የአፍሪካን ልማት የመደገፍ ተነሳሽነት እውን እንዲሆን የአህጉሪቱ መዲና አዲስ አበባ ለባንኩ ሁነኛ ማዕከል እንደምትሆን አረጋግጠዋል፡፡
ከትናንት እስከ ዛሬ በዓለም አደባባይ ለአፍሪካ ድምጽ መሆን መገለጫዋ የሆነችው ሀገራችን በመደመር መንግሥት የዲፕሎማሲ ፍኖት ቀጣናውን ለማስተሳሰር እየተጋች ትገኛለች፡፡
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዚሁ የብሪክስ ጉባኤ ላይ፤ ከአፍሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ናት ሲሉ የሰጡት ምስክርነትም ለአህጉራዊ ሚናዋ እውቅና የሰጠ ነው፡፡
በኃይለማርያም ተገኝ

27 days ago
ከመቅደስ ጀርባ ያለው የጨለማ ገበያ፡
የኔልሰን ሳምቦኮ እና የፓስተሮቹ የመንፈሳዊ ማጭበርበር ሚስጥር
በናይሮቢ ኬንያ የሚኖረውና ቀደም ሲል በሉሲፈሪያን የጨለማ አስማትና መተት ውስጥ ለዓመታት ሲሰራ የነበረው ኔልሰን ሳምቦኮ፣ በቅርቡ ይፋ ያደረጋቸው ምስጢሮች በአለም አቀፍ ደረጃ አፍ የሚያስከፍቱ እና "ወይ ጉድ!" የሚያስብሉ ናቸው።
ኔልሰን እንደሚናገረው ከሆነ፣ ስማቸው በትልልቅ መድረኮች በሚጠሩ እና በሺዎች በሚቆጠሩ ተከታዮቻቸው በሚመለኩ ታዋቂ ነቢያት እና ፓስተሮች ጀርባ የነበረው ዋና የሃይል ምንጭ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጸሎት ሳይሆን፣ እሱ ከጨለማው ዓለም እያዘጋጀ የሚሸጥላቸው እቃ እና የተደገመባቸው አስማቶች ነበሩ።
አንድ ፓስተር ወደ እሱ ሲመጣ የመጀመሪያው ነገር "የሰው አእምሮ የመቆጣጠር እና የመሳብ" (Mind Control) ሀይል መጠየቅ ነው። ኔልሰን እነዚህን አገልጋዮች ነን ባዮች እንዴት ህዝቡን እንደሚያታልሉ ሲያጋልጥ፣ በየቤተክርስቲያኑ "የተፀለየበት" ተብለው በውድ ዋጋ የሚሸጡ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ በእኩይ ድግምት የታሸጉ እንደነበሩ ይናገራል።
እያንዳንዱ እቃ እንዴት ለደብቅ አላማ እና ሰዎችን በስሜት ባሪያ ለማድረግ እንደዋለ ኔልሰን ሚስጥሩን እንደሚከተለው ይተረክበታል፡
የተፀለየበት ዘይት እና ውሃ (Hypnotic Anointing Oil & Water)
ምእመናን በሽታ ይፈውሳል ወይም በረከት ያመጣል ብለው በየቀኑ የሚቀቡትና የሚጠጡት ዘይትና ውሃ፣ በእውነቱ አእምሮን የሚያደነዝዝ እና የመታዘዝ ስሜት የሚፈጥርበት ድግምት ይደረግበታል።
ኔልሰን እንደሚለው፣ ዘይቱ የተወሰነ የመተት ድብልቅ ከተቀላቀለበት በኋላ ፓስተሩ በሰውነት ወይም በግንባር ላይ ሲቀባው፣ ግለሰቡ ለአገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ እጅ እንዲሰጥ፣ ያየውን ተአምር ሁሉ ሳያወጣ አምኖ እንዲቀበል እና ገንዘቡን ያለ ምንም ጥያቄ እንዲያፈስ ያደርገዋል።
የተፀለየበት ጨው (The Binding Salt)
በብዙ ጉባኤዎች ላይ "የእርግማን መስበሪያ" ተብሎ የሚበተነው ወይም የሚሰጠው ጨው ሌላው ትልቅ የማታለያ መሳሪያ ነበር። ኔልሰን እንደሚያስረዳው፣ ይህ ጨው በቤተክርስቲያኑ መግቢያ ላይ ወይም በምእመናን ቤት እንዲበተን ይደረጋል።
ዋና አላማውም የሰዎችን የጸሎት እና የመንፈስ ንቃት ማደንዘዝ፣ ከዛም አልፎ አእምሯቸው ስለ ፓስተሩ ብቻ እንዲያስብ እና ከቤተክርስቲያኑ ፈጽመው እንዳይወጡ አድርጎ በካቴና ማሰር ነው።
የተፀለየበት ማር (The Sweet Deception / Honey)
በአገልግሎት መድረክ ላይ ማር ተባርኮ ለሰዎች ሲታደል፣ ተከታዮቹ "የህይወት ጣፋጭነት" ይመጣል ብለው ያስባሉ። ኔልሰን ግን እውነቱን ሲያጋልጥ "ወይ ጉድ" ያሰኛል።
ማሩ የሚዘጋጀው የፓስተሩን ቃል እና ንግግር በሰዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እና ጣፋጭ ለማድረግ ነው። ማሩን የቀመሰ ወይም የወሰደ ሰው የፓስተሩን ውሸት እና አስመሳይነት በፍጹም ማየት አይችልም፤ ይልቁንም ንግግሩ ሁሉ እንደ ማር ይጣፍጠዋል፣ ስህተቱንም እንደ ጽድቅ ይቆጥራል።
የተፀለየበት ፎጣ እና ጨርቆች (The Touch of Possession)
ፓስተሮች ከመድረክ ላይ ሆነው ሰዎችን የሚጥሉበት ወይም ላባቸውን አብሰው የሚጥሉት ፎጣ ሌላው የተደገመበት እቃ ነው። ኔልሰን እንደሚናገረው፣ እነዚህ ፎጣዎች የሰዎችን ስሜት በቅጽበት የሚያደነዝዝ የርኩስ መንፈስ አሰራር ይጫንባቸዋል። ፎጣው ሰዎችን ሲነካ በድንገት የመውደቅ፣ የመጮህ እና የመደንገጥ ስሜት ይፈጥራል።
ህዝቡ ይህን እንደ "መንፈስ ቅዱስ ሀይል" ሲቆጥረው፣ ከበስተጀርባው ግን በፎጣው አማካኝነት የተላለፈ የሳይኮሎጂ እና የጨለማ አሰራር ግፊት ነበር። ኔልሰን በቃለ መጠይቁ ላይ እንደገለጸው፣ እነዚህን የጨለማ ዘዴዎች የሚጠቀሙ በርካታ ታዋቂ አገልጋዮች አሉ።
ምንም እንኳን በህግ እና በደህንነት ስጋት ምክንያት የሁሉንም ስም ዝርዝር ባይዘረዝርም፣ በተለይም በምዕራብ እና በምስራቅ አፍሪካ (እንደ ናይጄሪያ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ባሉ ሀገራት) የሚንቀሳቀሱ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ተከታዮች እና ግዙፍ ሜጋ-ቸርች (Mega-churches) ያላቸው ታዋቂ "ነቢያት" እና "ሐዋርያት" ወደ እሱ ይመጡ እንደነበር አረጋግጧል።
እነዚህ መሪዎች ፈጣን ዝና፣ የሰዎችን አእምሮ የመቆጣጠር አቅም እና ከፍተኛ ሀብት ለማከማቸት ሲሉ የቅርብ ዘመዶቻቸውን እና የተከታዮቻቸውን ህይወት እንደ መስዋዕትነት አሳልፈው ለመስጠት እንኳን ወደኋላ እንደማይሉ አጋልጧል።
ይህ የኔልሰን ሳምቦኮ አስደናቂ ምስክርነት፣ ሰዎች በመድረክ ላይ የሚዩትን ተአምር፣ ዘይት፣ ጨው እና ፎጣ በጭፍን ከመከተል ይልቅ እያንዳንዱን ነገር በንቃትና በምክንያት መመርመር እንዳለባቸው ትልቅ ማቂያ ደወል ሆኖ አልፏል።

1 month ago
✨ “በቅድስት ኪዳነ ምሕረት ታሪኬ ተቀየረ!” 🙏
ይህን ቃል በምስክርነት የምትናገሩበትን ቀን እግዚአብሔር ያድርሳችሁ! ❤️ አሜን!
🎁 “የአዲስ ዓመት ስጦታዬን ለእናቴ ለቅድስት ኪዳነ ምሕረት!” ⛪️
በሀድያ ሶሮ ወረዳ የሚገኘውን የቅድስት ኪዳነ ምሕረት እና የቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የቤተ መቅደሱን አገልግሎት በፍቅር እንደግፍ።
🙏 ከ200 ብር ጀምሮ የምታደርጉት ድጋፍ ለዚህ ቅዱስ አገልግሎት ትልቅ አስተዋጽኦ አለው።
🏦 የንግድ ባንክ
1000644937128
የቤተክርስቲያኑ አካውንት
📞 ለበለጠ መረጃ:
0954 441 078
📩 በቴሌግራም የክርስትና ስምዎን በመላክ፣ በቅዳሴና በጸሎት እንዲጠራ ያድርጉ። 🙏
📖 “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል።”
— 2ኛ ቆሮንቶስ 9፥7
❤️ የአዲስ ዓመት ስጦታችን ፍቅር ይሁን፤ ፍቅራችንም በመልካም ተግባር ይገለጥ!
#ቅድስት_ኪዳነ_ምሕረት #ቅዱስ_ሩፋኤል #አዲስ_ዓመት #የፍቅር_ስጦታ #እምነት #ድጋፍ #ሀድያ

የታሪክ ስብራትን ማቃናት እና የአዲሱ አርበኛ ትውልድ ጥሪ፦ የቀይ ባሕር ደሴቶቻችን ምስክርነት
*************************
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ቀጣና ውስጥ የነበራት ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ሚና የረጅም ዘመናት ታሪክ ያለው ነው። በተለይም በባሕር ላይ ኢንዱስትሪ፣ በባሕር ኃይል እና በንግድ እንቅስቃሴዎች ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት የቀጣናው የኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ በርካታ ስኬታማ ሥራዎችን አከናውናለች።
ከእነዚህ ታሪካዊ አሻራዎች መካከል በአፍሪካ ቀዳሚ የነበረው እና ከአሰብ ወደብ በስተደቡብ በምትገኘው ሃሌብ ደሴት ላይ ተገንብቶ የነበረው ግዙፍ የባሕር ላይ ኢንዱስትሪ፣ የመርከብ ጥገና ማዕከል እና የባሕር አካዳሚ ዋነኛ ማረጋገጫዎች ናቸው።
ሆኖም በ1983 ዓ.ም. በነበረው የፖለቲካ ለውጥ እና ጂኦፖለቲካዊ ሁነቶች ምክንያት ሀገራችን ይህንን ታሪካዊ ሀብቷን እና የባሕር በሯን በማጣት በዓለማችን ትልቋ በየብስ የተከበበች ሀገር ለመሆን ተገደደች።
ይህ ታሪካዊ እና ጂኦግራፊያዊ ስብራት ሀገራችንን በየዓመቱ ለወደብ ኪራይ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንድታወጣ አስገድዷታል።
ዛሬ ላይ የባሕር በር ጉዳይ የዘመናት የታሪክ እና የጂኦግራፊ ስብራታችን የሚጠገንበት ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራዊ ህልውናችንን የሚያረጋግጥ አዲስ “አርበኛ ትውልድ” የምናሰባስብበት ትልቁ ሀገራዊ አጀንዳችን ነው።
የመደመር መንግሥት ይህንን ስብራት ለመቀልበስ የያዘው እሳቤ በጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win) መርህ ላይ የተመሠረተ እንጂ የኃይል አማራጭ አይደለም።
ቀይ ባሕር በዓለማችን ከሚካሄደው የባሕር ንግድ 12 በመቶ የሚሆነው የሚያልፍበት ስትራቴጂካዊ መስመር በመሆኑ፣ በዚሁ ቀጣና ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲኖር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እና ጸጥታዊ መረጋጋት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
በመሆኑም አዲሱ ትውልድ የሃሌብ ደሴትን የመሰሉ ታሪካዊ እምቅ አቅሞችን በመገንዘብ፣ የሀገራችንን ፍትሐዊ ጥያቄ በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በመግፋት ለቀጣናው ዘላቂ ሰላምና ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ታሪካዊ አሻራውን ማሳረፍ አለበት።
በሀይማኖት ከበደ
#ethiopia #ebc #redseaaccess #ethiopianhistory #hornofafrica #economicsovereignty #geopolitics

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ሴናተር በርኒ ሳንደርስ የእስራኤልን ወታደራዊ ፖሊሲዎች እና በዌስት ባንክ (ምዕራብ ዳርቻ) የሚገኙ ሰፋሪዎች በፍልስጤማውያን ላይ እያደረሱ ያለውን ጥቃት በጽኑ አውግዘዋል። ሴናተሩ ይህንን ቁጣቸውን የገለጹት፣ ጡረታ የወጡ የእስራኤል የጦር ጀነራሎች የሰጡትን አስደንጋጭ ምስክርነት የሚያትተውን የ'ኒውዮርክ ታይምስ' ዘገባ በ'ኤክስ' ገጻቸው ላይ በማጋራት ነው።
ሳንደርስ በመልዕክታቸው "በዌስት ባንክ ፍልስጤማውያንን እያሸበሩ ያሉትን የእስራኤል ሰፋሪዎች ድርጊት የሚቃወሙትን ጡረተኛ የእስራኤል ጀነራሎች ንግግር አድምጡ" ሲሉ አሳስበዋል። በዘገባው ላይ ከተጠቀሱት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች መካከል፣ የቀድሞው የጤና ጥበቃ ሚኒስትር እና ጡረተኛው ብርጋዴር ጀነራል ኤፍሬም ስኔህ፣ ሰፋሪዎቹ እያደረሱ ያሉትን ጥቃት "ይህ የዘር ማጽዳት ወንጀል ነው" ሲሉ በግልጽ ኮንነውታል።
በተጨማሪም ሌላኛው ጡረተኛ የአየር ሀይል ጀነራል አሳፍ አግሞን "አንድ ማህበረሰብ በዚህ መልኩ አሰቃቂ ድርጊት መፈጸም ከጀመረ፣ ያ ማህበረሰብ በእርግጠኝነት የጠፋ ነው" ሲሉ የሁኔታውን አሳሳቢነት አስጠንቅቀዋል።
ሴናተር በርኒ ሳንደርስ አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን የገንዘብ እና የጦር መሳሪያ ድጋፍ አጥብቀው እንደሚቃወሙ በድጋሚ በማረጋገጥ፣ "ለአክራሪው የኔታንያሁ መንግስት ከዚህ በኋላ አንዲት ሳንቲም አንሰጥም!" ሲሉ ጽኑ አቋማቸውን አሳውቀዋል።

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በማንችስተር አስገድዶ በመድፈር የተከሰሰው ኤርትራዊ የ8 አመት እስር ተፈረደበት፡፡ አንዲት ሴትን አስገድዶ በመድፈር ክስ የቀረበበት ኤርትራዊ ላይ በትላንትናው እለት የእስራት ቅጣት እንደተላለፈበት ተዘገበ፡፡ ተከሳሹ እድሜው 29 የሆነና ፍቃዱ የማነ የሚባል ሲሆን የቼስተር ክራውን ፍርድ ቤት ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው ለ10 ተከታታይ ቀናት ጉዳዩን ሲመለከት ከቆየ በኋላ ነው፡፡ በቀረበው ክስ እንደተገለፀው ፍቃዱ ከ19 አመቷ እንግሊዛዊት ወጣት ጋር የተዋወቀው በማህበራዊ ሚዲያ ነበር፡፡
ትውውቃቸውን ተከትሎ ከአንድ ጓደኛው ጋር ወደሴቷ ቤት መሄዳቸውን የጠቀሰው ክሱ ልክ ጓደኛው ሲወጣ ጠብቆ ወደመኝታ ቤት በግዳጅ ወስዶ ልብሷን በማውለቅ እንደደፈራት አስረድቷል፡፡ ይህንን ድርጊት በሚፈፅምበት ወቅት እንዳትጮህ አፏን አፍኖ ስለነበር ወጣቷ ልትሞት ደርሳ እንደነበርም ክሱ ይገልፃል፡፡ ልክ ጓደኛው ሲመለስ ፍቃዱ ከዚያ ቤት ሮጦ የወጣ ሲሆን በስፍራው ኮንዶምና የተጎጂዋ የውስጥ ልብስ ወድቆ መገኘቱንም አስረድቷል፡፡
ከዚያ በኋላ ለ6 ቀናት ያህል ተደብቆ ከቆየ በኋላ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡ ግለሰቡ በፖሊስ ከተያዘ በኋላ የተፈፀመው ድርጊት በሁለቱ ስምምነት የተፈፀመ መሆኑን ቢናገርም ተጠቂዋ በሰጠችው ምስክርነትና በቀረበለት መስቀለኛ ጥያቄ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን ፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ፍቃዱ እስሩን ጨርሶ ከወጣ በኋላ ላልተወሰነ ጊዜ በፆታዊ ጥቃት ፈፃሚዎች መዝገብ ላይ እንዲሰፍርም ተወስኖበታል፡፡

6 አመታትን ቁርሱን ሳይበላ ቆጥቦ ያሳተመው "እነሆ የምለው" የተሰኘ የግጥም ሊመረቅ።
በገጣሚ መለሰ ኪዳኔ የተደረሰው እነሆ የምለው የተሰኜ የግጥም መድብል ታትሞ ለንባብ ይፋ ሆኗል። እነሆ የምለው የግጥም መድብል ታሪክን፣ ባህልን፣ ፍቅርን እንዲሁም ማንነትን በማንጸባረቅ የትውልድን ድምጽ የሚያስተጋቡ ግጥሞች ስብስብ ነው።
እነሆ የምለው የግጥም መድብልን ለ 6 አመታት ቁርሱን ሳይበላ ቆጥቦ ለህትመት እንዳበቃው ሲናገር ገጣሚው በመንግስት ደሞዝ መጽሀፍ ማሣተም ከባድ ቢሆንም ከታሰበበት ግን የማይቻል የለም ብሏል።
ስለ መድብሉ ጸሀፊ ተውኔትና ባለቅኔ አያልነህ ሙላቱ ቆንጆ ምስክርነት የሰጡት ሲሆን እውናዊ ታሪኮች በመወድስ የአጻጻፍ ስልት ተሰንደውበታል። ከግጥሞቹ መሀል ፍቅር በገጠር፣ አድዋ፣ ሴተኛ አዳሪ ናት፣ የምስራቋ ፀሐይ፣ ሸዋን ተዋወቁት፣ ብራምባሯን ባገኝ እንዲሁም በወጣቶች የሱስ ህይወት ላይ የሚያጠነጥን ቁራኛ የተሰኘ ግጥሞች ተጠቃሽ ናቸው።
እነሆነ የምለው የግጥም መድብል ቅዳሜ ነሀሴ 23 አ አ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ቫምዳስ ሲኒማ አንጋፋና ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል። ውድ የጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ ተጋብዛችኋል።

"አዲስ አበቤ አረጋ ከበደን ሊያመሰግነው ይገባል! ጣሂር ሙሀመድ"
አዲስ አበባን ወክለው የመጡ አመራሮች አዲስ አበባ የኦሮሚያ ናት ሲሉ፤ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ግን አዲስ አበባ የነዋሪዎቿ ናት ብለው የተሟገቱት እሳቸው ብቻ ናቸው ሲሉ ጣሂር ሙሀመድ ምስክርነት ሰቷል::
''እናም አዲስ አበቤ አረጋ ከበደን ሊያመሰግናቸው እና ይሄ ቁርጠኝነታቸው በታሪክ ሲወሱ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል ሲል ተናግሯል።

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏
በመጽሐፍ ቅዱስ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ያህል ትንቢት የተነገረላት ስለእርሷ የተጻፈላት ሴት የለችም። በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ብዙ ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል፤ የኖኅ መርከብ፣ ሰላማዊት ርግብ፣ የአብርሃም ድንኳን፣ ሙሴ በሲና ያያት ሐመልማል፣ ጽላተ ሙሴ፣ የኢያሱ የምስክርነት ሐውልት፣ የኤልያስ የወርቅ መሶብ፣ የአሮን በትረ፣ የጌዴዎን ፀምር፣ የኖኅ የቃል ኪዳኑ ቀስተ ደመና፣ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት መሰላል፣ የነቢዩ ኤልሳዕ ማሰሮና ሌሎች ምሳሌዎች በሰፊው የተነገሩላት የተጻፉላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ቤተ ክርስቲያን እርስዋን ለመጥራት የምትጠቀምባቸው ቅጽል ስሞቿና ውዳሴዎቿ ምንኛ ድንቅ ቢሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ገላጭነት በቅዱሳን የተነገሩ ምስጋናዎቿስ እጅግ ቢለዩ የክብሯን ያህል የሚገልጿት አይደሉም፡፡
እርሷ የሰው ሁሉ ረዳትና ርኅሩኅ እናት ናት፤ የብርሃን፣ የምሕረት፣ የድኅነትና የአማናዊው ወይን እናት ናት። ከንጉሡ በስተቀኝ የምትቆመው ንግሥት እርስዋ ናት፤ በመስቀል ስር የተቀበልናት የሁላችንም እናት እርሷ ናት፤ እርሷ ዘለዓለማዊ ድንግል ናት፤ እርሷ የእግዚአብሔር ጸጋ የሞላባት ንጽሕት ቅድስት ድንግል ናት፡፡ ከፍጥረት ሁሉ ተለይታ ወላዲተ አምላክ ለመሆን የተመረጠችበት አንዱ ምክንያት እመቤታችን እጅግ ትሑት፣ ፍጽምትና ንጽሕት ስለሆነች ነው። በሉቃስ 1÷48 እንደተጻፈው የአምላክ እናት እንደምትሆን ተነግሯት እንኳን ክብር ይግባትና ከመኩራትና ሌሎችን ከመናቅ ይልቅ ዘመዷ ኤልሳቤጥን ልትጠይቃት ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ወጣች፡፡ ከኤልሳቤጥ ፍጹም ምስጋናና በማሕጸን ያለው ዮሐንስ የሰላምታ ድምጿን ሰምቶ መዝለሉንከሰማች በኋላም “የባሪያይቱን መዋረድ ተመልክቷልና” በማለት በትሕትና ምስጋናዋን አቀረበች እንጂ የትዕቢት ቃል ከአፏ አልወጣም፡፡
ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ “እርሷ በእግዚአብሔር ዓይን በታየ የቅድስና ውበት የተሞላች ነበረችና በእርሷ ንጹሕ ማሕፀን ሊያድር ወደደ፤ እንደ ድንግል ማርያም ራሱን ዝቅ ያደረገ ትሑት ማንም የለም” ይላል። ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም “በትሕትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ…” ብሎ ያመሰገናት ይህች ድንግል ከተራሮች አናት ሁሉ ከፍ ያለች ስትሆን ራሷን ዝቅ አድርጋ “እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንደምን ይደረግልኛል” የሚል ምላሽ ለቅዱስ ገብርኤል ሰጠችው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛው አምላክ ልጇ ነውና ማርልኝ ስትለው ምልጃዋ ፍጹም ነው፡፡ በእግዚአብሔር መመረጧ፣ ከሴቶች ሁሉ መለየቷ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆኗ ይህን ክብር አጎናጽፏታልና፡፡ ገዳማውያንም ይህን ልዩ እናትነቷንና ቅድስናዋን አምነው ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሯታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000766349227
ወይም
አቢሲንያ ባንክ
262281132
የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

2 months ago
ከ«እንታዘዝ» ወደ «እንምራ» የማያድግ የቀነጨረው የአማራ ፖለቲካ
የአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የዛሬው የህይወት አጋጣሚ ግለሰባዊ የታማኝነት ምስክርነት ብቻ ሳይሆን፣ የአማራ የፖለቲካ ሊሂቃን (Elites) እና የክልሉን ባለሥልጣናት ስትራቴጂካዊ ውድቀትና የራእይ አልባነት ገጽታ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ አሳዛኝ ክስተት ነው።
በሀገሪቱ የፖለቲካ መዋቅር ውስጥ ከፍተኛ ቦታ ላይ ደርሰው የነበሩ መሪዎች ከስልጣን ሲወርዱ የሚጠብቃቸው ተቋማዊና ማህበራዊ ዋስትና አለመኖሩ፣ የክልሉ ባለሥልጣናት እርስ በእርስ የመደጋገፍ፣ የጋራ ህልውናን የማስከበር እና የራሳቸውን ሰዎች በክብር የመጠበቅ ባህል ምን ያህል እንደወደቀ ማረጋገጫ ነው።
በየወቅቱ የስልጣን መንበር ላይ የሚወጡ የአማራ ባለሥልጣናት የራሳቸውን እና የህዝባቸውን የረጅም ጊዜ ጥቅም የሚቀርፅ ራእይ ከመሰነቅ ይልቅ፣ የማዕከላዊው አገዛዝ ታዛዥ እና የፖለቲካ መሳሪያ ሆነው ሲያገለግሉ መኖራቸው አዲስ ክስተት አይደለም።
ይህም ባለሥልጣናቱ «እንታዘዝ» እንጂ «እንምራ» የማይሉ፣ «በተቀደደልን ቦይ እንፍሰስ» እንጂ «ራሳችን ቦይ እንቅደድ» ብለው ለማስሰብ የማይደፍሩ፣ ለህዝባቸው ተሻጋሪ መንገድ ማሳየት የማይችሉ ራዕይ አልባዎች መሆናቸውን በግልጽ ያሳያል።
የኦሮሚያ ክልል በአንድ ፕሬዝዳንት ይህን ያህል ጊዜ ዘላቂ አመራርና ፖለቲካዊ መረጋጋት ውስጥ ሆኖ ለቀድሞ መሪዎቹ ተገቢውን ክብርና ቤት ሰጥቶ በመንከባከብ የነባር መሪዎቹን ህይወት ዋስትና ሲያስጠብቅ፣ በአንፃሩ በዚሁ ጊዜ ውስጥ የአማራ ክልል የመሩ በርካታ ፕሬዝዳንቶችን (አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና አቶ አረጋ ከበደን) እየቀያየረ የፖለቲካ አለመረጋጋትና የመዋቅር መበታተን ሰለባ ሆኗል።
የአማራ ባለሥልጣናት የራሳቸውን እና ነባር መሪዎችን በክብር የመያዝ፣ ከስልጣን በኋላም ቢሆን እውቀታቸውንና ልምዳቸውን በመጠቀም ለህዝብ አገልግሎት እንዲያውሉ የማድረግ አቅም ማጣታቸው፣ የፖለቲካ መዋቅሩ ምን ያህል መበታተን እና መጠፋፋት እንደነገሰበት ያሳያል።
የሌሎች ክልሎችና ድርጅቶች ፖለቲከኞች ነባር አመራሮቻቸውን እንደ ትልቅ አሴት አቅፈውና ጠብቀው በሚያቆዩበት ምህዳር ውስጥ፣ የአማራ ባለሥልጣናት ግን አንዳቸው ሌላውን ከመገፋፋት፣ ከማሳደድ እና ለጊዜያዊ ጥቅም ሲሉ እርስ በእርስ ከመበላላት አልፈው ለህዝባቸው ተሻጋሪ ራእይ ማዘጋጀት አልቻሉም።
ይህ የአቶ ገዱ የሰሞኑ ሁኔታ ለክልሉ ባለሥልጣናት ከጥልቅ እንቅልፍ የሚያባንንና «ንቁ!» የሚል ትልቅ የደወል ጥሪ ነው።
ባለሥልጣናቱ አሁንም ከዚህ የታዛዥነትና የይስሙላ ስልጣን መንፈስ ካልወጡ፣ የሚመሩትን ታላቅ ህዝብ ታሪክና የታገገለውን ዋጋ ዝቅ ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ። ህዝቡን የሚመጥን መሪ ማለት በተቀደደለት ቦይ የሚፈስ ሳይሆን የራሱን ህዝብ መብትና ጥቅም የሚያስከብር መንገድ የሚቀድ፣ አርቆ አስተዋይ እና የራሱ ራእይ ያለው አመራር ነው።
ያለ ተቋማዊ አንድነት፣ ያለ እርስ በእርስ መደጋገፍ እና የራስን መሪዎች በክብር የመጠበቅ ባህልን ሳይገነቡ የሚደረግ የፖለቲካ ጉዞ መጨረሻው ውድቀትና በሌሎች መጠቀሚያ መሆን ብቻ ነው።
በመሆኑም ከነባር ስህተቶች በመማር፣ ከጊዜያዊ የታዛዥነት እና የመላላክ መንፈስ ወጥቶ የጋራ ራእይን በመቅረፅ፣ የታመኑና ሀገራቸውን ያገለገሉ መሪዎችን በክብር ማቆየት፣ የራስን ፈለግ እና ራዕይ የሚከተል ጠንካራ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መዋቅር መገንባት የቀጣይ ህልውና ወሳኝ ጉዳይ ነው።

የኢትዮጵያ ሠራዊት፤ የጀግንነት እና የሰብዓዊነት ሕያው ተምሳሌት
******************
የኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ የሀገር ሉዓላዊነትን ከማስከበር እና ከጦር ሜዳ ጀግንነት ጋር ተያይዞ በስፋት ይነሳል።
ከዚህም ባሻገር የሠራዊቱ መሠረታዊ የሥነ ልቦና ግንባታ ከሰብዓዊነት እና ከሕዝብ ደጀንነት እሴቶች ጋር የተሳሰረ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
የኢትዮጵያ ወታደር በውጊያ ሜዳ የሚያሳየው ጥንካሬ እንደተጠበቀ ሆኖ በሰላምም ሆነ በግጭት ወቅት ለሰው ልጅ የሚያሳየው ርኅራኄ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘ መገለጫው ነው። ይህ ሰውነትን የማስቀደም ፍልስፍና ከማኅበረሰባችን የዳበረ ባህላዊ እና መንፈሳዊ እሴት የሚቀዳ እውነት ነው።
በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ስምሪቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ከተሰጠው ወታደራዊ ግዳጅ ባሻገር ማኅበራዊ አወቃቀራቸው በወደመባቸው ስፍራዎች ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊነት አለኝታነቱን በተግባር አሳይቷል።
ይህንንም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በዓለም አቀፍ መድረክ የሚያሳየውን ተነሳሽነት እና ርኅራኄ በማድነቅ በተደጋጋሚ ገልጸዋል።
እንዲሁም የቀድሞው የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን የኢትዮጵያ ሠራዊት በሰላም ማስከበር ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለ እና የብዙ ዜጎችን ሕይወት የታደገ መሆኑን መስክረዋል።
ይህ ዓለም አቀፍ ምስክርነት መሬት ላይ ከሚታየው የሠራዊቱ ተግባር የመነጨ ነው። እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት ማግሥት፣ በላይቤሪያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ፣ እንዲሁም በአብዬ ስምሪት የኢትዮጵያ ሠራዊት ያከናወናቸው ተግባራት ለዚህ አስረጂ ናቸው።
በነዚህ ስፍራዎች ሠራዊቱ የተራራቁ ማኅበረሰቦችን ከማስታረቅ ባሻገር፣ የፈረሱ መንገዶችን፣ ድልድዮችን እና የትምህርት ቤት ሕንፃዎችን በራሱ ጉልበት ጠግኗል።
በተለይም ሰላማዊ ሰዎች በተጠለሉባቸው ካምፖች ውስጥ የምግብ እጥረት በነበረበት ጊዜ የኢትዮጵያ ወታደሮች የራሳቸውን የዕለት ስንቅ (ሬሽን) በመቀነስ ለተራቡ ህጻናትና እናቶች ሲያካፍሉ ቆይተዋል።
በወታደራዊ ሳይንስ የዕለት ስንቅ በከባድ ግዳጅ ወቅት የሚፈስስን ላብ እና የሚቃጠልን ኃይል ለመተካት በካሎሪ መጠን ተሰልቶ የሚሰጥ ነው።
የኢትዮጵያ ወታደር ይህን ጉልበት ማደሻ ስንቁን ቀንሶ ለተቸገሩ ማካፈሉ፣ የራሱን አካላዊ አቅም አሳልፎ በመስጠት እውነተኛ ሰብዓዊነትን በተግባር ያረጋገጠበት የሞራል ልዕልና ማሳያ ነው።
በሀገር ውስጥም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገሩን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ እና ከሕግ ማስከበር ሚናው ባለፈ ከማኅበረሰቡ የዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር የተቆራኘ ነው። ሠራዊቱ ዜጎችን ከውስጥ እና ከውጭ ትንኮሳዎች ከመጠበቅ ባሻገር፣ በምርት ዘመን የአርሶ አደሩ ቀኝ እጅ ነው።
በአቅም ማነስ፣ በበሽታ ወይም በእርጅና ምክንያት ማሳቸውን ማረስ ላልቻሉ አቅመ ደካሞች መሬት ያርሳል፣ ዘር ይዘራል፣ ምርት ይሰበስባል። ይህም የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ አርሶ አደሩን ከኪሳራ ይታደጋል።
በተጨማሪም የሠራዊቱ አባላት ከደመወዛቸው እና ከስንቃቸው በማካፈል የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን እና ማኅበራዊ ተቋማትን ይገነባሉ።
አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና የደንብ ልብስ በነፃ ከማደል አልፈው፣ በቋሚነት በማስተማር የዕውቀት ብርሃን ያካፍላሉ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚያከናውናቸው እነዚህ ተግባራት የእውነተኛ የሕዝብ ልጅነቱ ማረጋገጫዎች ናቸው።
ሠራዊቱ ጠላትን በጀግንነት ከመመከት ባለፈ ለሰው ልጅ ሁሉ የሚያሳየው ርኅራኄ፣ የሚያካፍለው ጉልበት እና የሚለግሰው ዕውቀት የኢትዮጵያዊነት ሕያው መገለጫ ሆኖ ይቀጥላል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #ethiopianarmy #humanityfirst #peacekeepers #beyondheroism #militaryforpeace

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕርገት ነሐሴ 16፤ እንኳን አደረሳችሁ፣ አደረሰን🙏
ቶማስ ትንሣኤሽን አይቷልና እኛም በረከት አይቅርብን
ፍልሰታ የሚለው ቃል የተገኘው ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ መለየት፣ ማረግ፣ ወደላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ይይዛል። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ “ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች” በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ ከሞትና መቃብር መለየትና ማረግን ያመለክታል። ይህ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከተወሰኑት ሰባቱ አጸዋማት ለዓመቱ የመጨረሻው ጾም ነው። እመቤታችን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ከኖረች በኋላ ጥር 21 ቀን 49 ዓመተ ምሕረት ዐርፈለች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና፣ ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል፤ እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው ብለው ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡ መላእክት የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ በስምንተኛው ወር በነሐሴ ሐዋርያት ቅዱስ ይህን በረከት አይቶ እኛ ሳናይ ቀረን ብለው ከነሐሴ 1 እስከ 14 ሁለት ሱባዔ ይዘው ከጌታችን ተቀብለው በጸሎትና በምህላ ቀበሯት።
ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወጥቶ ነበርና ሲቀብሯት አልተገኘም። እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ከሙታን ተነሥታ ስታርግ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ አገኛት። በዚህን ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው እርሱ የቀረበት መስሎት “ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንችን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ” ብሎ ራሱን ከደመና ላይ ሊወረውር ቃጣው። እመቤታችን ከእርሱ በስተቀር ትንሣኤዋን ያየ አለመኖሩን ነግራ ግን ቶማስን አፅናናችው፡፡ ለምስክርነት እንዲሆንም በቀብሯ ጊዜ የነበረውን ሰበኗን ሰጥታው አረገች። ቅዱስ ቶማስም ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ አላቸው፡፡ እነርሱም አግኝተን ቀበርናት አሉት፡፡
እርሱም “ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ ይህ እንዴት ይሆናል?” ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ “ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ” ብሎት ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ” ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸውና ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡ በዓመቱም ቶማስ ትንሣኤሽን አይቷልና እኛም በረከት አይቅርብን ብለው ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባዔ ገቡ። ነሐሴ 16 ጌታችን እመቤታችንን አምጥቶ ሐዋርያትን ቀድሶ አቁርቧቸዋል።
ቅዱሳን ሐዋርያት ከአንዴም ሁለቴ የጾሙትን ጾም አብነት አድርገን በረከታቸው እንዲያድርብን የእመቤታችንን ጾመ ፍልሰታ እንጾማለን። በተለይ ገዳማውያን አባቶች የስጋቸውን ጉዳይ ትተው ዓለምን ንቀው መንነዋልና ሁሌም ቢሆን በጾም ይኖራሉ። እኛ በቅበላውም በጾም ፍቺውም ከመብሉም ከመጠጡም ከልክ በላይ እንደፈለግን ስንሆን እነርሱ ግን እጅግ በሚያስቸግር ሁኔታ ውስጥ ሆነው፣ የገዳሙ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል። ካለን ከፍለን ልንደግፋቸው ይገባል።
የንግስተ ሰማይ ወምድር ልመናዋ፣ ክብራ፣ የልጇ የወዳጇ ቸርነት በኛ ላይ አድሮ ይኑር አሜን!!!
ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444

“ደምፀ ቃል” - ቃላት ድምፅ ሲሆኑ
ቃላት ይነበባሉ ፣ ይሰማሉ
ቃል ስሜት ነው
ቃል ትዝታ ነው
ቃል ተስፋ ነው
ቃል ምስክርነት ነው
ቃል ማንነት ነው
ቃል ህይወት ነው
ቃል ድምፅ ነው።
"ደምፀ ቃል" የምልዕቲ ኪሮስ የግጥም መፅሀፍ፣ ቃልን ወደ ድምፅ፣ ስሜትን ወደ ግጥም፣ ግጥምን ወደ ትዝታ የሚያስጉዝ አዲስ የግጥም መድብል።
ምልዕቲ ኪሮስ በግጥም፣ በስክሪፕት ጽሑፍ፣ በዘፈን ግጥም እና በሬዲዮ ፕሮዳክሽን አቅራቢነት የተለያዩ ስራዎችን የሰራች ዘርፈ ብዙ የኪነ ጥበብ ባለሟል ።
ምልዕቲ የተለያዩ የዘፈን ግጥም ስራዎችን ለተለያዩ ታዋቂ ድምፃውያን ሰጥታለች ከነዚህም መካከል ለፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ለብስራት ሱራፌል፣ ለሄዋን ገ/ወልድ(ጃኖ) ፣ አህመድ ተሾመ ዲንቢ፣ ያሬድ ነጉ፣ ሜላት ቀለመወርቅ እና ለሌሎችም ድምፃውያን የሰጠች ሲሆን በሀገራችን የሙዚቃ ዘርፍም ላይ አሻራዋን እያኖረች ያለች ሁለገብ የኪነ ጥበብ ሰው ነች።
የግጥም ቃሏን በመጽሐፍ አትማ ከአንባቢያን ጋር ለመገናኘት ቀን ቆርጣለች።
“ደምፀ ቃል” የግጥም መፅሀፍ
ቃሉን ያንብቡ ድምፁን ያዳምጡ
ቀን- ነሀሴ 20
ሰአት- 11:30 ጀምሮ
ቦታ- በቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት አሸናፊ ከበደ አዳራሽ
#ድምፀቃል #ምልዕቲኪሮስ #የግጥምመድብል #የመጽሐፍምረቃ #ኢትዮጵያዊሥነጽሑፍ #ግጥም #ሥነጽሑፍ #ethiopianliterature

ድምፀ ቃል” - ቃላት ድምፅ ሲሆኑ
ቃላት ይነበባሉ ፣ ይሰማሉ
ቃል ስሜት ነው
ቃል ትዝታ ነው
ቃል ተስፋ ነው
ቃል ምስክርነት ነው
ቃል ማንነት ነው
ቃል ህይወት ነው
ቃል ድምፅ ነው።
"ድምፀ ቃል" የምልዕቲ ኪሮስ የግጥም መድብል፣ ቃልን ወደ ድምፅ፣ ስሜትን ወደ ግጥም፣ ግጥምን ወደ ትዝታ የሚያስጉዝ አዲስ የግጥም መድብል።
ምልዕቲ ኪሮስ በግጥም፣ በስክሪፕት ጽሑፍ፣ በዘፈን ግጥም እና በሬዲዮ ፕሮዳክሽን አቅራቢነት የተለያዩ ስራዎችን የሰራች ዘርፈ ብዙ የኪነ ጥበብ ባለሟል ።
የግጥም ቃሏን በመጽሐፍ አትማ ከአንባቢያን ጋር ለመገናኘት ቀን ቆርጣለች።
“ድምፀ ቃል” የግጥም መድብል
ቃሉን ያንብቡ ድምፁን ያዳምጡ
ቀን- ነሀሴ 20
ሰአት- 11:30 ጀምሮ
ቦታ- ቅዱስ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት አሸናፊ ከበደ አዳራሽ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ታዋቂው የሂፕ-ሆፕ አርቲስት ቱፓክ ሻኩር በ1996 (እ.ኤ.አ.) በላስ ቬጋስ በተተኮሰበት ጥይት ከተገደለ ከሦስት አሥርት ዓመታት በኋላ፣ ጉዳዩ አዲስ መልክ እየያዘ ነው። አሁን ላይ እየተካሄደ ያለው የዱዌን "ኬፌ ዲ" ዴቪስ የፍርድ ሂደት፣ በሾን "ዲዲ" ኮምብስ ላይ አዲስ ክስ ለማስከፈት በር ሊከፍት እንደሚችል የህግ ምንጮች ገልጸዋል።
የኬፌ ዲ የፍርድ ሂደት እና የ1 ሚሊዮን ዶላር የነፍስ ማጥፋት ውንጀላ
በሁለት የሎስ አንጀለስ ወንበዴዎች መካከል በነበረው ግጭት ምክንያት የቱፓክን ግድያ አቅዷል በሚል ኬፌ ዲ ፍርድ ቤት ቀርቧል። የአቃቤ ህግ ክስ በአብዛኛው የተመሰረተው ኬፌ ዲ ራሱ በዶክመንተሪዎች፣ በማስታወሻ መጽሐፉ፣ እንዲሁም ፖሊስ በ2008 በድብቅ በቀረጸው የድምጽ ማስረጃ ላይ በሰጠው የእምነት ቃል ላይ ነው። በድብቅ በተቀረጸው ማስረጃ ላይ ኬፌ ዲ እንደተናገረው፣ ሾን "ዲዲ" ኮምብስ ቱፓክን እንዲገድልለት 1 ሚሊዮን ዶላር አቅርቦለት ነበር። የኬፌ ዲ ጠበቃ ማይክል ሳንፍት በበኩላቸው፣ ደንበኛቸው በግድያው ዙሪያ የሰጠው ቃል ዝናን ለማትረፍ የተናገረው ፍጹም ውሸት መሆኑን በመክፈቻ ንግግራቸው ተከራክረዋል።
ዲዲ በአሁኑ ወቅት በዝሙት አዳሪነት ወንጀል ጋር በተያያዙ ክሶች የ50 ወራት (4 ዓመት ከ2 ወር) የእስር ቅጣት እያጠናቀቀ ይገኛል (እ.ኤ.አ. በ2025 ከቀረቡበት ከባድ የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ክሶች ነጻ መባሉ ይታወሳል)። ለክላርክ ካውንቲ ዲስትሪክት አቃቤ ህግ ቢሮ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለቴሌግራፍ እንደገለጹት፣ አቃቤ ህግ ኬፌ ዲን ጥፋተኛ ማስባል ከቻለ በዲዲ ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ አረንጓዴ መብራት ያገኛል። ሆኖም አቃቤ ህግ የዳኞችን ትኩረት ላለመሳብ ሲል በአሁኑ ወቅት የዲዲን ስም ከዋናው ክስ አግልሎታል። ዲዲ በበኩሉ ከግድያው ጋር በተያያዘ የሚነሳበትን ውንጀላ ፈጽሞ ውሸት እና አስቂኝ ሲል ከዚህ ቀደም አስተባብሏል።
በዘጠናዎቹ የነበረው የምስራቅ እና የምዕራብ ጠረፍ የሂፕ-ሆፕ ፉክክር ለዚህ ግጭት መነሻ ነው። በወቅቱ ዲዲ የኒውዮርኩን ‘Bad Boy Records’ ሲመራ፣ ሹግ ናይት ደግሞ የቱፓክ አሳታሚ የሆነውን የሎስ አንጀለሱን ‘Death Row Records’ ያስተዳድር ነበር። የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ኬፌ ዲ ጥፋተኛ ከተባለ፣ አቃብያነ ህጎች ዲዲን በድጋሚ ኢላማ ሊያደርጉት ይችላሉ። የህግ ባለሙያው ሳም ሚሬጆቭስኪ፣ በቅርቡ በተደረገው የዲዲ የፍርድ ሂደት የተሰጠው ቅጣት አነስተኛ ነው ብለው የሚያምኑ አቃብያነ ህጎች፣ ይህንን ታዋቂነትን የሚያስገኝ ክስ ሊገፉበት እንደሚችሉና በአሁኑ ሰዓት የዲዲ ቦታ መሆን እንደማይመኙ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የቀድሞ የኤፍቢአይ ወኪል ፊል ካርሰን፣ ከቅርብ ጊዜ የፍርድ ሂደቱ በኋላ የዲዲ የቀድሞ የቅርብ ሰዎች መረጃዎችን አሳልፈው ሊሰጡ የሚችሉበት ዕድል ሰፊ መሆኑን ጠቁመዋል። በኬፌ ዲ የፍርድ ሂደት ላይ የዲዲ የቀድሞ የንግድ አጋር፣ የቀድሞ ጠባቂው እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የ28 ዓመት እስር ላይ የሚገኘው ሹግ ናይት በምስክርነት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሙዚቃውን ዓለም ለሦስት አሥርት ዓመታት ሲያነጋግር የኖረው የቱፓክ ሻኩር ግድያ አሁን ላይ አዲስ አቅጣጫ መያዙን እንዴት ያዩታል?

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሪፐብሊካን ፓርቲ የቅድመ ምርጫ የደገፏቸው እጩዎች ማሸነፋቸውን በ'ትሩዝ ሶሻል' ገጻቸው እያከበሩ ሲሆን፣ በተጓዳኝም አሌክስ ቪንድማን በዲሞክራቲክ ፓርቲ የቅድመ ምርጫ በአሜሪካ ዲሞክራቲክ ሶሻሊስቶች አባል መሸነፉን በደስታ ገልጸዋል።
ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ "አጭበርባሪው ቪንድማን ዛሬ ምሽት በአክራሪ የግራ ክንፍ እብድ ተሸንፏል። ይሄ እንዴት ደስ ይላል???" በማለት ጽፈዋል።
በኪየቭ ተወልዶ ከቀድሞው ሶቭየት ህብረት የተሰደደው አይሁዳዊው ቪንድማን፣ ቀድሞ የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት አባል የነበረ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2019 ትራምፕ ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ያደረጉትን አወዛጋቢ የስልክ ልውውጥ ተከትሎ በትራምፕ የመጀመሪያ የክስ (Impeachment) ሂደት ላይ ለኮንግረስ ምስክርነት መስጠቱን ተከትሎ ነበር ስሙ በስፋት የታወቀው።
መንታ ወንድሙ በቨርጂኒያ የኮንግረስ አባል የሆነው ቪንድማን፣ ከዋና ተቀናቃኙ 16 እጥፍ የሚበልጥ የምርጫ በጀት ቢያሰባስብም፣ ፍልስጤምን የሚደግፉ ህጎችን በግዛት (ስቴት) ደረጃ እንዲጸድቁ በመግፋት በፓርቲዋ ውስጥ ስም ባወጣችው አንጂ ኒክሰን በቀላሉ ሊሸነፍ ችሏል።
ትራምፕ በሪፐብሊካን የቅድመ ምርጫዎች ያላቸውን ተጽዕኖ እና የድጋፍ ኃይል ለማሳየት የሚያደርጉት ጥረት አካል የሆኑት እነዚህ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቶች፣ በየምርጫው ምሽት በተከታታይ ሲወጡ ይስተዋላል። ፕሬዝዳንቱ "በዛሬው ምሽት ብዙ ታላላቅ ድሎች ተመዝግበዋል!!!" በማለትም አክለው ጽፈዋል።

Comments