2 hours ago
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) የወልቂጤ መሶብ የአንድ ማዕከልን አገልግሎት ሥራ አስጀመሩ
**********************
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ ወልቂጤ ከተማ በክልሉ 3ኛውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ በይፋ መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በ7 ተቋማት 22 አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ያለባቸው፣ ተገልጋይ የሚበዛባቸው፣ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጡ እንዲሁም ቅሬታ የሚበዛባቸው ተቋማት ተለይተው ወደ ማዕከሉ እንዲገቡ መደረጋቸው በወቅቱ ተጠቁሟል፡፡
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች በአንድ ቦታ ብዙ አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ፣ ጊዜና ወጪ እንዲቆጥቡ እና የአገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል የሚያስችል ዘመናዊ የአገልግሎት ሥርዓት መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎን ጨምሮ የተለያዩ የክልልና ዞን መንግሥት ስራ ኃላፊዎች መገኘታውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #mesob #onestopservice

Comments