Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኤርትራ የተመድ ሰብአዊ መብት ምክር ቤት ‹‹ስሜን እያጠፋ ነው›› አለች፡፡ ወደ31 የሚሆኑ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ትላንት ባወጡት የጋራ መግለጫ የተመድ ሰብአዊ መብት ምክር ቤት የኤርትራ ራፖርተር ስራ ዘመን እንዲራዘም ጠይቀዋል፡፡ ለምክር ቤቱና ለምክር ቤቱ አባል አገራት ባስገቡት በዚህ ደብዳቤ በመጪው ሀምሌ ወር በሚከናወነው ስብሰባ ላይ ራፖርተሩ የኤርትራን ሰብአዊ መብት አያያዝ የተመለከተ ሪፖርት እንዲያቀርቡ አሳስበዋል፡፡ ተቋማቱ እንደገለፁት ባለፈው አመት ለምክር ቤቱ በቀረበው ኤርትራን የተመለከተ ሪፖርት ላይ የሰብአዊ መብት አያያዙ መሰረታዊ ለውጥ እንዳላመጣ መገለፁን አውስተዋል፡፡

ጨምረውም የተመድ የኤርትራ ሰብአዊ መብት መርማሪ ኮሚሽን የመጀመሪያ ሪፖርቱን ካወጣበት ከዛሬ 10 አመት ጀምሮ ምንም አይነት መሻሻል አለመታየቱን አስታውቀው የመንግስት ባለስልጣናት የሚፈፅሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰት አሁንም እንደቀጠሉበት አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም የኤርትራ ራፖርተሩ የስራ ጊዜያቸው እንዲራዘምና ወደኤርትራ በመሄድ ያለውን ሁኔታ ገምግምው በመጪው ሀምሌ ወር ላይ በሚከናወነው የምክር ቤቱ ስብሰባ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለዚህ ጥሪ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ዛሬ መልስ የሰጡ ሲሆን ሲገልፁም ‹‹በኤርትራ ላይ የሚደረገው የስም ማጥፋት ዘመቻ ቀጥሏል›› ብለዋል፡፡ እንዲህ አይነት ዘመቻ ለሁለት አስርት አመት ያህል ሲከናወን መቆየቱን ጠቅሰውም በድርጊቱ ላይ የተወሰኑ አገራት እጃቸው እንዳለበት አስረድተዋል፡፡ ጨምረውም የተመድ ራፖርተር ምስክርነት ‹‹የተለመደ ስም ማጥፋት፣ የጠባብ ቡድኖች ፍላጎትና ተረት ነው›› በማለት በመግለፅ ተቃወሞ አሰምተዋል፡፡

22 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.