Logo
SeledaPost
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በስብሰባዎች ላይ ማንቀላፋታቸውን ተከትሎ አዳዲስ ቅጽል ስሞች እየተሰጧቸው መሆኑ ተገለጸ::

ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሃውስ የስብሰባ አዳራሾች እና በተለያዩ ይፋዊ መድረኮች ላይ አይናቸውን ጨፍነው ሲያንቀላፉ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችና ፎቶግራፎች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ከፍተኛ የፖለቲካ ውይይትና ክርክር አስነስቷል።

በተለይም ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና የፖለቲካ ታዛቢዎች በጉዳዩ ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጡ ይገኛሉ።

በቅርቡ በዋይት ሃውስ በተካሄደ የካቢኔ ስብሰባ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ስለ ቀጠናዊ የውጭ ፖሊሲ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ፕሬዚዳንቱ ለተወሰኑ ደቂቃዎች አይናቸውን ጨፍነው በመቀመጣቸው፣ ተቺዎቻቸው ቀደም ሲል ለጆ ባይደን ይሰጡት የነበረውን “ Sleepy Joe" (አንቀላፋው ጆ) የሚለውን ስም ወደ *Sleepy Donald" (አንቀላፋው ዶናልድ) እና *Slump Trump"በመቀየር አዳዲስ የፌዝ ቅጽል ስሞችን እየሰጧቸው ይገኛሉ።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ምላሽ በስብሰባዎች ላይ አልተኛሁም፤ ይልቁንም "አይኖቼን እያሳረፍኩ ነበር" በማለት የቀረበውን ክስ አስተባብለዋል።

ጤንነታቸውም ፍጹም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና ብርቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በእጃቸው ላይ ስለሚስተዋለው የመቁሰል ወይም የደም መቋጠር ምልክት ሲጠየቁ፣ ደም ለማቅጠኛ የሚወስዱት አስፕሪን ከፍተኛ በመሆኑ ምክንያት በቀላሉ የሚፈጠር ምልክት እንደሆነና ምንም አይነት ከባድ የጤና እክል እንደሌለባቸው አስረድተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ በምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ምስክርነት "ትራምፕ በስብሰባ ላይ ሲተኙ አይቼ አላውቅም፤ እንዲያውም እኩለ ሌሊትና ማለዳ 11 ሰዓት ላይ ስልክ እየደወሉ ስለሚቀሰቅሱኝ እሱ የማይተኛ መሆኑ ነው ትልቁ ችግር" በማለት በምክር ቤቱ አባላት የቀረበውን ወቀሳ ተከላክለዋል።

ይህ የፕሬዚዳንቱ ሁኔታ በዋይት ሃውስ ውስጥ ባሉ የውስጥ አዋቂዎችና በፖለቲካ ተቀናቃኞቻቸው ዘንድ የእድሜና የጤና ሁኔታ ክትትል ጥያቄዎችን በድጋሚ እንዲነሱ ምክንያት ሆኗል😁

Seledadotio
Seledadotio
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.