4 months ago
🌍 "ፍትሃዊ ያልሆነው የዓለም የፋይናንስ ሥርዓት አፍሪካን አንቆ ይዟል!" — አንቶኒዮ ጉተሬዝ 📢🇪🇹
#ethiopia | በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተገኙት የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፤ አህጉሪቱ በዓለም አቀፍ መድረኮች እየደረሰባት ያለውን ኢ-ፍትሃዊነት በጽኑ ተቃውመዋል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
💰 የፋይናንስ ኢ-ፍትሃዊነት፦
አፍሪካውያን ከበለጸጉት ሀገራት ጋር ሲነጻጸር እስከ ስምንት እጥፍ የሚበልጥ ከፍተኛ የብድር ወለድ እንዲከፍሉ መገደዳቸው "ፍትሃዊ አይደለም" ብለዋል። ይህ አስቸጋሪ ሁኔታ ኢንቨስትመንትንና የሥራ ዕድልን አንቆ ይዟል።
📉 የገንዘብ ጉድለት፦
በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በየዓመቱ የ 4 ትሪሊዮን ዶላር የፋይናንስ ጉድለት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
🏛️ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር፦
"አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር አለማግኘቷ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና የታሪክ ስህተት ነው" ሲሉ በንግግራቸው አፅንኦት ሰጥተዋል። አፍሪካ ውሳኔ በሚተላለፍበት ጠረጴዛ ዙሪያ የግድ መገኘት አለባት ብለዋል።
🤝 መፍትሔው፦
ተመጣጣኝ የረጅም ጊዜ ፋይናንስ፣ ጠንካራ የልማት ባንኮች እና የዕዳ መፍትሔዎች በአስቸኳይ እንደሚያስፈልጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዋና ጸሐፊው አክለውም "የአፍሪካ ጥንካሬ የሚመነጨው በራሱ በሚተማመን እና በተባበረ ሕብረት ነው" ብለዋል።
የአንቶኒዮ ጉተሬዝ ንግግር ለአፍሪካ አዲስ የዲፕሎማሲ ንቅናቄ ይፈጥር ይሆን?
#antonioguterres #un #africanunion #ausummit #financialjustice #unsc #addisababa #ethiopia #africarising #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments