2 hours ago
የእሥራኤል 78ኛ ዓመት የነፃነት ቀን፤
የሰባ ዓመታት የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት
#ethiopia | በአዲስ አበባ የሚገኘው የእሥራኤል ኤምባሲ የሀገሪቱን 78ኛ ዓመት የነፃነት ቀን ዮም ሃአትዝማውትን ደማቅ በሆነ ስነ ስርዓት አክብሯል።
በዓሉ በእሥራኤል የቀን አቆጣጠር መሰረት በሚያዝያ ወር መከበር የነበረበት ቢሆንም በወቅቱ በነበሩ አካባቢያዊ ክስተቶች ሳቢያ ወደ ሌላ ጊዜ መሸጋገሩ ተገልጾ በተለይ የዕለቱ የክብር እንግዶች ላሳዩት ትዕግስትና ላበረከቱት ወዳጅነት ምስጋና ቀርቧል።
በክብረ በዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የእሥራኤል አምባሳደር ዶ/ር አብርሃም ንጉሤ ሀገራቸው እ.ኤ.አ. በ1948 ነፃነቷን ካወጀችበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የህልውና ፈተናዎችን በጽናት መወጣቷን አስታውሰዋል።
እሥራኤል በዘመናዊ መዋቅር የ78 ዓመት ወጣት ሀገር ብትሆንም ታሪኳ ከአብርሃምና ከሙሴ ዘመን የሚቀዳ የ4 ሺህ ዓመታት ጥንታዊ ቅርስና የነፃነት ታሪክ መሠረት እንዳለው አብራርተዋል።
ይህ የዘንድሮ በዓል በኢትዮጵያና በእሥራኤል መካከል የተጀመረውን ዘመናዊ የሁለትዮሽ መደበኛ ግንኙነት 70ኛ ዓመት ወርቃማ ኢዮቤልዩ የሚዘክር በመሆኑ ልዩ ትርጉም አለው።
አምባሳደር ዶ/ር አብርሃም ሰፊ ገለጻ አኳያ እ.ኤ.አ. በ1956 በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የእሥራኤል ቆንስላ መከፈቱ ለዘመናዊው ትስስር መነሻ ቢሆንም የሁለቱ ሕዝቦች ወዳጅነት ግን በንግሥተ ሳባና በንጉሥ ሰሎሞን ታሪክ ላይ የተገነባ የ3 ሺህ ዓመታት ጥልቅ ታሪካዊ መሠረት ያለው መሆኑ ተገልጿል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከ1973 እስከ 1989 ላለፉት 16 ዓመታት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በሕዝቦች ልብ ውስጥ ባለው ጠንካራ ትስስር ምክንያት ይበልጥ በጠነከረ መሠረት ላይ ሊመለስ ችሏል።
በአሁኑ ወቅት የሁለትዮሽ ግንኙነቱ እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የተጠቀሰ ሲሆን ባለፉት ወራት የእስራኤሉ ፕሬዚዳንት ይስሐቅ ሄርዞግ በአዲስ አበባ ያደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት እንዲሁም የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሐደራ አበራ በእስራኤል ያደረጉት የፖለቲካ ምክክር የዚህ ማረጋገጫዎች ናቸው ብለዋል።
አምባሳደር ዶ/ር አብርሃም አያይዘውም ሀገራቱ በማሻቭ በኩል በግብርና ቴክኖሎጂ፣ በውሃ አጠቃቀም፣ በጤና እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች በጋራ እያከናወኗቸው ያሉ የልማት ሥራዎች ስኬታማ መሆናቸው ተነስቷል። የባህል ትስስሩን ይበልጥ ለማሳደግም በቅርቡ የሁለቱ ሀገራት የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የእሥራኤል-ኢትዮጵያ የባህል ምሽት ተካሂዷል።
ከ35 ዓመታት በፊት በሰሎሞን ዘመቻ በ36 ሰዓታት ውስጥ ከ14 ሺህ በላይ የቤተ እሥራኤል ማህበረሰብ አባላት ወደ እስራኤል መጓዛቸውና በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው ከ180 ሺህ በላይ የደረሱት ቤተእስራኤላውያን ለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዋነኛ የሕዝብ ድልድይ መሆናቸው አውስተዋል።
በመጨረሻም ጥቅምት 2023 የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እሥራኤል አሁንም የደኅንነት ስጋቶች ቢገጥሟትም የታገቱ ዜጎቿን በሙሉ ባለፈው ጥቅምት ወር ማስመለስ መቻሏ ትልቅ እፎይታን የፈጠረ ሲሆን የሀገሪቱ ኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ አሁንም በጠንካራ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ለሦስት ዓመታት በምክትል አምባሳደርነት ያገለገሉትን ቶመር ባር-ላቪን የሥራ ዘመን መጠናቀቅን አስመልክቶ በኤምባሲው ስም ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና የቀረበላቸው ሲሆን የበዓሉ ታዳሚዎች በባህላዊ የሙዚቃና የምግብ ዝግጅቶች እጅግ ደስ የሚል ጊዜን አሳልፈዋል።
በዚህ ልዩ የክብር ሥነ ሥርዓት ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰሎሞን ሶካ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ እስያና ፓስፊክ ሀገራት ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር አምሃ ኃይለጊዮርጊስ፣ የፓርላማ አባላት፣ አምባሳደሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
#israel #yomhaatzmaut #ethioisrael #diplomacy #history #culture #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments