Logo
YenetaTube
የተናገሩትን መኖር
***
ለሰው ልጅ በተለይ ደግሞ ለህዝብ መሪ ከባዱ ፈተና ቃል የገቡትን መፈፀም አለመቻል ነው። ቃል ተስፋን ይፈጥራል፣ ተስፋ ደግሞ መጠበቅን። የተገባው ቃል ወደ ተግባር ካልተቀየረ የማይፈፀም ተስፋ ይሆንና ልብን ያሳዝናል። ስለዚህ ቃል እዳ ነው፤ ያውም የእምነት እዳ። በመሆኑም መፈፀም አለበት። ካልተፈፀመ ቅሬታን ያመጣል፣ መተማመንን ይሸረሽራል፣ በመጨረሻም ተቀባይነትን ያሳጣል። የተገባ ቃል ሲፈፀም ደግሞ ደስ ያሰኛል፣ መተማመንን ያመጣል፣ በውጤቱም ቃሉን ለጠበቀው አካል ተቀባይነትና ክብርን ያስገኛል።

የህዝብ አመራር የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት በእቅድ ወይም ከማህበረሰቡ በሚቀርብለት ጥያቄ መነሻ በተለያዩ ጊዜያት ቃል ይገባል። ማህበረሰቡም ቃል ተገብቶለታልና ተግባር ይጠብቃል።
በታሪካችንም ሆነ በእድሜያችን እንዳየነው ቃሉን ከሚጠብቅ ይልቅ ቃሉን ላለመጠበቁ ምክንያት የሚቆጥር መሪ ይበዛል። ቃላቸውን ለመጠበቅ የሚተጉና በእለት ተእለት የሥራ ትጋታቸው ውጤት የሚያሳዩ ጥቂት መሪዎች ደግሞ አሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአመራር ሚናቸው የተናገሩትን በመኖር የሚታወቁ መሪ ናቸው። ለህዝብ ቃል ከገቡ ይተገብሩታል። ለዚህ ደግሞ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ እየተቀየረች ያለችው የአዲስ አበባ ከተማ ለጠየቃት ሁሉ መናገር ትችላለች።
የሀገሪቱ ጠ/ሚ/ር አንድ መድረክ ላይ "የሴት ምሳሌ፣ ብርቱ፣ ማርሽ ቀያሪ" በማለት ስለ ወ/ሮ አዳነች መስክረዋል። ከእረፍት አልባ የለውጥ መሪ አንደበት እንደዚህ ዓይነት ምስክርነት መስማት መቻል የከንቲባዋን ብርቱ ጥረትና ውጤታማነት ያሳያል።
እኔም እላለሁ ከንቲባዋ ለመናገር ብለው የሚናገሩ ሳይሆን የተናገሩትን የሚኖሩ ናቸው። ይህም ለብዙ አመራሮች አርዓያና ትምህርት የሚሆን ነው እላለሁ።

ይመጣል ባህሩ

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.