1 month ago
የባሕር በር ባለቤትነት፤ የትውልዱ ታሪካዊ ኃላፊነት
***************
ኢትዮጵያ በንግድና በሸቀጥ ልውውጥ የብዙ ሺህ ዓመታት የንግድ ታሪክ ባለቤት ናት። ከጥንት ጀምሮ ንግድ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኖ የዘለቀ ሲሆን፤ ከጎረቤት አገራት፣ ከቀጣናው አልፎም ከሩቅ ዓለም ጋር የነበራት የንግድ ትስስር እጅግ የጠነከረ ነበር።
የታሪክ ድርሳናት እንደሚመሰክሩትም፣ ኢትዮጵያ ለዚህ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነት ዋነኛው መተንፈሻና መገናኛ ደግሞ በቀይ ባህር በመጠቀም የምታደርገው የንግድ እንቅስቃሴ ነበር።
ዛሬ ላይ የንግድ መንገዶቹ ዘምነው በየብስ፣ በባቡር፣ በአየርና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ቢተኩም፤ መሠረታዊው ፍላጎት ግን አሁንም አልተቀየረም። ይህም ምርትን ለሰፊው የዓለም ገበያ ማቅረብና ብሔራዊ ኢኮኖሚውን ከዓለም አቀፉ የንግድ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር ነው።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ካላቸው አገራት አንዷ መሆኗ፣ የንግድና የሎጂስቲክስ ፍላጎቷን እጥፍ ድርብ አድርጎታል።
ምርቶችን ለዓለም ገበያ ለማቅረብ፣ ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ ግብዓቶችን ለማስገባትና በዓለም አቀፍ የንግድ ውድድር ውስጥ ውጤታማ ተዋናይ ለመሆን የባህር በር አማራጭ መኖር ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው።
የዛሬው ትውልድ ኢትዮጵያ ገና ከጥንት ጀምሮ የነበራትን የታሪክ እውነታ መሠረት በማድረግ፣ የባህር በር ጥያቄን በሰለጠነና በሰላማዊ የዲፕሎማሲ መንገድ የመመለስ የታሪክ ኃላፊነት አለበት።
ይህ ጥያቄ የመልክዓ ምድር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ ከኢኮኖሚ ዕድገት፣ ከሎጂስቲክስ ቅልጥፍና፣ ከሀገራዊ ደኅንነትና ከቀጣናዊ ትስስር ጋር የተያያዘ የዘመናችን ወሳኝ አጀንዳ ነው።
የአሞሌ ጨው በግመልና በበቅሎ ተጭኖ የሚጓዝበት ዘመን ቢያልፍም፣ ንግድ ሁልጊዜም መንገድ እንደሚፈልግና መንገድ ደግሞ ሰዎችንና አገራትን እንደሚያገናኝ የሚያሳየው መሠረታዊ እውነት ዛሬም እንደቀጠለ ነው።
በመሆኑም ከጥንቱ የአሞሌ ጨው ንግድ የጀመረውን ጉዞ ዳር ለማድረስ፣ ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ለመሆን የጀመረችውን ዲፕሎማሲያዊ ትግል አጠናክራ ልትገፋበት ይገባል።
በልዩ እሸቱ
#ebc #ethiopiatrade #maritimeaccess #redsea #economicdiplomacy #ethiopiarising #regionalintegration

4 months ago
ከተፈጥሮ ጥበቃ እስከ ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት
***************
ባለፉት ዓመታት የብዝሃ ሕይወት መመናመን፣ የመሬት መራቆት፣ የምርታማነት መቀነስ እንዲሁም የውኃ አካላት በደለል መሞላትና መጥፋት ማኅበረሰባችንን ለድርቅ፣ ለጎርፍ እና ለምግብ ዋስትና ችግሮች ተጋላጭ አድርጎት መቆየቱ ይታወሳል።
ይህን ታሳቢ በማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሀገር በቀል ዕፅዋትንና የተፈጥሮ ሀብትን ከመጠበቅ ባለፈ፣ የአየር ንብረት ለውጥን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመከላከልና የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ግንባር ቀደም የለውጥ መሠረት መሆን ችሏል።
ባለፉት ሰባት ዓመታት በተሰሩ ብርቱ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን፣ በመርሐ ግብሩ እስካሁን 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የሀገራችን አረንጓዴ ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ተችሏል።
ይህ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ባለፈ፣ የአየር ንብረት ተፅዕኖን በመቀነስ ለሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና ዲፕሎማሲያዊ መስኮች ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እያስገኘ ይገኛል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተፈጥሮን የመንከባከብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገርን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ታላቅ ተግባርም ጭምር ነው።
በተለይም ለምግብነት የሚውሉ ዛፎችና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ባላቸው ዕፅዋት ላይ ትኩረት መደረጉ ለምግብ ዋስትና እና ለሥርዓተ ምግብ መሻሻል ለሚደረገው ጉዞ ትልቅ አቅም ፈጥሯል።
መርሐ ግብሩ የውኃ እጥረትን በከፍተኛ ደረጃ ከመቅረፉና የውኃ አካላት በደለል እንዳይሞሉ ከመከላከሉ ጋር ተያይዞ፣ አርሶ አደሮች ከክረምት ወቅት ጥገኝነት ወጥተው በበጋ ወቅትም በመስኖ በዓመት ሁለቴና ከዚያም በላይ እንዲያመርቱ ሰፊ ዕድል ከፍቷል።
ስለሆነም ዘንድሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ዝግጅት እየተደረገበት የሚገኘው 7ኛው ዙር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የነገዋን ኢትዮጵያ ገጽታ የሚወስን ታላቅ ብሔራዊ ንቅናቄ ነው።
ይህንን መርሐ-ግብር በታቀደለት መንገድ ማሳካት የደን ሽፋንን ከማሳደግ ባለፈ፣ አረንጓዴና የተደላደለች ሀገርን በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት ዋነኛው መሣሪያ በመሆኑ "ነገን ዛሬ እንትከል፣ የነገው አረንጓዴ አሻራ የዛሬው እጃችን ሥራ ነው"።
በብሌን ደምበሎ
#greenlegacy #climateaction #foodsecurity #economicdiplomacy #ethiopianbroadcastingcorporation

Comments