Logo
FastMereja
እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏

ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትሻላችሁ? እነሆ እደተናገረ ተነስቷል

“እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ወረደ፣ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፣ እናንተስ አትፍሩ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንድትሹ አውቃለሁና። እንደ ተናገረው ተነስቷልና በዚህ የለም ኑና እዩ አላቸው።” ይለናል ማቴዎስ 28÷5። ስለ አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አስቀድመው ነቢያት ተናግረዋል። ስለ ጌታችን ትንሣኤ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ ጌታችን ራሱ በትምህርቱ ግልጽ አድርጎ ቢናገርም ሰዱቃውያንና ሌሎች ብዙ ሰዎች ለማመን ያዳግታቸው ነበር። አራቱ ወንጌላውያን፣ በማቴ 28፣ በማር 16፣ በሉቃ 24 እና በዮሐ 20 እንዲሁም ቅዱሳን ሐዋርያት በስብከታቸውና በመጽሐፋቸው ስለ ትንሣኤው ምስክርነት በመስጠት አረጋግጠው አስፍተውና አምልተው አስተምረዋል፤ ጽፈዋል።

ከሐዋርያትም መካከል የሆነው ቅዱስ ቶማስ እንኳ ጌታችን በዝግ ቤት ሰላም ለእናንተ ይሁን ብሎ የተወጋውን ጎኑን አሳይቶ በክብር መነሣቱን እስከሚያረጋግጥለት ድረስ የጌታችንን ትንሣኤ ለማመን እንደተቸገረ ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል። በተጨማሪም የጌታን ትንሣኤና ትንሣኤ ሙታንን በአጠቃላይ ለመቀበል የተቸገሩ ብዙዎች እንደነበሩ ከቅዱሳት መጻሕፍት እንረዳለን። ክርስቶስ ስለትንሣኤው በዮሐንስ 2÷19 በምሳሌ ሲናገር “ይህንንን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን አስነሣዋለሁ” ብሎ የተናገረውን ሐዋርያቱ የተረዱትና ያመኑት ከትንሣኤው በኋላ ነበር። በ2ኛ ጢሞ 3÷14 ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ልጁ ለጢሞቴዎስ “አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፣ ከማን እንደ ተማርከው ታውቃለህና።” ሲል እንደጻፈለት እኛም ከማን እንደተማርነው እናውቃለንና የጌታን ትንሣኤ በፍጹም ልብ አምነን ለራሳችን ትንሣኤ እንዘጋጃለን።

ጌታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ለሰው ልጅ ድህነት ሲል ጽኑ መከራና ስቃይን ተቀብሏል። አይሁድ ከያዙት በኋላም ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ ስቃይ፣ መከራ፣ እንግልትና ግርፋትን ተቀብሎ፤ በቀራንዮ አደባባይ በዕለተ አርብ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ፤ ነፍሱን በፈቃዱ ሰጠ፡፡ አዳምንና ዘሩንም ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መለሳቸው፡፡ በ3ኛው ቀን መቃብር ክፈቱልኝ፣ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብርሃንን ተጎናጽፎ በታላቅ ኃይልና ስልጣን በክብር ተነስቷል። መላዕክቱም ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትሻላችሁ እነሆ እደተናገረ ተነስቷል ብለው መስክረዋል፡፡ ገዳማውያን በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ለተነሳው ጌታ ፍቅር ዓለምን ትተዋታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.