4 hours ago
#saudiarabia : በሳውዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ በሚገኘው የንጉሥ ካሊድ ዓለም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በየመን " ሁቲ ታጣቂ ኃይል " በተፈጸመ ከባድ የሚሳይል ጥቃት 12 ሰዎች ሲሞቱ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል።
ሟቾቹ ፦
4 የሳዑዲ አረቢያ
2 የባንግላዴሽ
1 የአሜሪካ
1 የግብፅ
1 የጆርዳን
1 የሶሪያ
✌️ 1 የፍልስጤም
1 የሱዳን ዜጋ ናቸው።
የሳውዲ የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጥቃቱን ተከትሎ በአየር ማረፊያው ላይ የነበረው የበረራ እንቅስቃሴ በጊዜያዊነት መቋረጡን አስታውቋል።
በተመሳሳይ በዳማም በሚገኘው ንጉሥ ፋህድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚሳይል/ተወንጫፊ አካል ወድቋል። የሰው ህይወት አላለፈም፤ ጉዳትም አልደረሰም ተብሏል።
ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ (ረቡዕ እና ሐሙስ) በተመሳሳይ በዚሁ ኤርፖርት እና በሌሎች ኢላማዎች ላይ ተከታታይ ጥቃቶች ተፈጽመው ወደ 6 ሰዎች ተገድለዋል። ከሟቾቹ አንዱ ፓይለት ሲሆን የሳውዲ አየር መንገድ አውሮፕላን ተመቶ ነው ህይወቱ ያለፈው።
ሁቲዎች ለምን ጥቃት ይፈጽማሉ ?
በኢራን የሚደገፉትና የሚታጠቁት የሁቲ ኃይሎች ሳዑዲ አረቢያ እና አጋሮቿ በየመን ውስጥ በቁጥጥራቸው ስር ባሉ አካባቢዎች ላይ አዲስ እና የተጠናከረ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲሁም የአየር ድብደባዎችን መክፈታቸውን በመቃወም አጸፋ እየመለሱ መሆኑን ነው የሚገልጹት። በተለይ ሳዑዲ ለየመን መንግስት በምትሰጠው ድጋፍ ጭምር ነው በሁቲ የድሮንና ሚሳኤል ጥቃት እየተፈጸመባት የሚገኘው።
ሳዑዲ አረቢያ ለምን ሁቲዎችን ታጠቃለች ?
ሳዑዲ አረቢያ በቅርቡ በየመን በኩል የሚገኘውን እና ለዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ወሳኝ የሆነውን የባብ አል-መንደብ የባህር ወሽመጥ ከሁቲዎች ነፃ ለማውጣትና ዓለም አቀፍ እውቅና ያለውን መንግስት ለመደገፍ አብራ ከየመን መንግስት ጋር ዘመቻ ጀምራለች። ይህ ሰፊ የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ የአየር ድብደባን ያከተተ ነው። ከዚህ ባለፈ ሁቲዎች እየፈጸሙባት ላለው ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ነው።
ቪድዮ ፦ ማኅበራዊ ሚዲያ
ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia ቀይ ባህር ላይ ሁለት ግዙፍ የነዳጅ መርከቦች በሁቲ ማስጠንቀቂያ ጉዟቸውን ቀየሩ። ከሳዑዲ አረቢያ ነዳጅ ጭነው በቀይ ባሕር በኩል ሲቀዝፉ የነበሩ ሁለት ግዙፍ መርከቦች ከየመን ሁቲ ኃይሎች በተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ምክንያት አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ መደረጋቸው ተዘገበ። የሳዑዲን የነዳጅ ምርት ጭነው ወደ ቻይና እና ሕንድ ሲጓዙ የነበሩት ሁለቱ መርከቦች ወደ መጡበት የተመለሱት ሁቲዎች በሳዑዲ አረቢያ ላይ…

7 hours ago
"ኢሳያስ" አውሎ ነፋስ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶችን በማውደሙ፣ ከ840ሺ በላይ ደንበኞች በፍሎሪዳ፣ አላባማ እና ጆርጂያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል።
8 hours ago
ሪያል ማድሪድ ድል አድርጓል !
ሪያል ማድሪድ ከቪያሪያል ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐግብር 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ሎስ ብላንኮዎቹን አሸናፊ ያደረገ ብቸኛ ግብ አዲስ ፈራሚው ያን ዲዮማንዴ አስቆጥሯል።
በጨዋታው የሪያል ማድሪዱ ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ቀይ ካርድ ተመልክቷል።
በዚህም ምክንያት ቪንሰስ ጁኒየር ቀጣዩ የኤል ክላሲኮ ጨዋታ በቅጣት ሊያመልጠው ይችላል።
የሊግ ደረጃቸው ?
3ኛ. ሪያል ማድሪድ :- 18 ነጥብ
10ኛ. ቪያሪያል :- 8 ነጥብ
ቀጣይ መርሐግብር ?
ማክሰኞ - ቪያሪያል ከ ናፖሊ ( ucl )
ረቡዕ - ሮማ ከ ሪያል ማድሪድ ( ucl )
@tikvahethsport kidusyoftahe

9 hours ago
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ ከ1ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ
#ethiopia | ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ በ13ኛ ዙር 1,102 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመረቀ። ከተመራቂዎቹ መካከል ከ400 በላይ የሚሆኑት በአቪዬሽን ዘርፍ የሰለጠኑ ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ኮሌጁ በአውሮፕላን ጥገና፣ በበረራ ኦፕሬሽን፣ በበረራ አስተናጋጅነትና በሌሎች የአቪዬሽን ሙያዎች ሥልጠና ለመስጠት ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ፈቃድ ማግኘቱን ገልጿል። ከዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር እና ከእንግሊዙ የኮሜርሻል ማኔጅመንት ተቋም እውቅናዎችን ማግኘቱም ተመልክቷል።
የናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባልና የናሽናል ኤርዌይስ እህት ኩባንያ የሆነው ተቋሙ፣ ከኮሌጅ ወደ ኤሮስፔስ ዩኒቨርሲቲነት ለመሸጋገር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁንም አስታውቋል።
ሽግግሩ የተቋሙን የትምህርትና የሥልጠና አቅም ከማሳደግ ባለፈ፣ በኢትዮጵያና በአፍሪካ የአቪዬሽንና የኤሮስፔስ ዘርፎች ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት፣ ምርምርን ለማስፋፋትና የፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
#nationalaviationcollege #aviation #aerospaceuniversity #ethiopia #aviationtraining #graduationceremony #aerospace #aviationindustry #highereducation

#mekdelaambauniversity
በ2019 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች፣ በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በትግራይ ክልል ከሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
● የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ (ጊምባ ካምፓስ)
● የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በመካነ-ሰላም ካምፓስ
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት መጠኑ 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
● የፋይዳ መታወቂያ (Digital ID)፣
● የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በ2019 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት በቀጣይ ይገለጻል ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity

10 hours ago
#1000 ሰው ለበአታ ለማርያም #250ብር 🙏
በከምባታ ጠምባሮና ሀላባ ሀገረ ስብከት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የምትገኘው #የጎፎሬ_ደብረ_መንክራት_በአታ_ለማርያም ቤተክርስቲያን በእናንተው የሁል ጊዜ ድጋፍና ትብብር እስከአሁን ባለው ጊዜ በረከታ ሥራዎች ተሠርቷል።
ለቀሪዎቹ የበረንዳ ኮሎንና ቢም ሥር የምሆን ሲሚንቶ ለማቅረብ እናንተን ተስፋ በማድረግ እየተንቀሳቀስን እንገኛለን።
ስለሆነም ውድ ኦርቶዶክሳውያን 100 ኩንታል ሲሚንቶ #250 ,000 ብር ነው #1000 ሰው #250ብር ብያዋጣ ሙሉ በሙሉ ይሸፈናል ሥራውም ይከናወናል እናንተም በረከት ተገኛችሁ የገጠሪቷ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሃይማኖታቸው ይጸናሉ።
ድጋፍ ለማድረግ
#የጎፎሬ_ደብረ_መንክራት_በአታ_ለማርያም ቤተክርስቲያን
፩. #ንግድ ባንክ ÷1000624326281
፪. #አቢሲኒያ ባንክ፦ 240587815
፫. #አዋሽ ባንክ፦ 013201006748101
፬. #ዳሽን ባንክ፦ 5640919295011
ስልክ #0933055802 #0911414852
አባቶች በጸሎት እንዲያስቡ የክርስትና ስማችሁን
🙏 t.me/degnet0321
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/nizanudegnite...
🌴🌴🌴🌴

Sponsored by
Surafel
10 hours ago
🏡
+971527866251
🔥 በ24% ቅድመ ክፍያ ብቻ የራስዎ ቤት ይሁንዎ! ቀሪውን ክፍያ በ5 ዓመት ይክፈሉ።
💰 ቅድመ ክፍያ፦ $98,630.10
📈 የተገመተ ዓመታዊ የኪራይ ገቢ፦ $24,657.50
📩 ለበለጠ መረጃ Brook Real Estateን ያነጋግሩ!
#dubairealestate #dubaiproperty #ethiopiandiaspora #realestateinvestment #brookrealestate #ዱባይ #ሪልኢስቴት
10 hours ago
ባርሴሎና በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !
ባርሴሎና ከሄታፌ ጋር ያደረገውን 8ኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የባርሴሎናን የማሸነፊያ ጎሎች ጋብሬል ጄሱስ ፣ አንቶኒ ጎርደን እና ኩንዴ አስቆጥረዋል።
ባርሴሎና በሊጉ ባደረጋቸው የመጀመሪያ ስምንት ጨዋታዎች ለይ 3️⃣4️⃣ ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።
ባርሴሎና በውድድር ዘመኑ ዘጠነኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።
ባርሴሎና በ 2️⃣4️⃣ ነጥቦች ላሊጋውን በበላይነት እየመራ ይገኛል።
@Tikvahethsport kidusyoftahe

#wollouniversity
በ2019 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር ወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 14 እና 15/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
● የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ፣
● ስማችሁ በ A እና K የሚጀምር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች እና አይነ ስውራን ተማሪዎች በደሴ ግቢ፣
● ሌሎች የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት መጠኑ 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
● ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ።

ዩናይትድ ከቶተንሀም ነጥብ ተጋርተዋል !
ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
ለቀያዮቹ ሰይጣኖች ብሪያን ምቤሞ ሲያስቆጥር ዶምኒክ ሶላንኬ ቶተንሀምን አቻ አድርጓል።
በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ የሚመራው ቶተንሀም የአመቱ የመጀመሪያ የሊግ ድሉን ማግኘት አልቻለም።
ማንችስተር ዩናይትድ ያለፉትን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም በሁለቱ ሲሸነፍ በሁለቱ አቻ ወጥቷል።
ቶተንሀም ያለፉትን ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም ሶስቱን በአቻ ውጤት አጠናቋል።
የሊግ ደረጃቸው ?
12ኛ. ማንችስተር ዩናይትድ :- 6 ነጥብ
18ኛ. ቶተንሀም :- 3 ነጥብ
ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?
ማክሰኞ - አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ( UCL )
ሰኞ - ቶተንሀም ከ ኮቬንትሪ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም ሆትስፐር 1 ለ 1 ተለያየ
*********************
በስድስተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ቶተንሃም ሆትስፐርን ያሰተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ የውድድር ዓመቱን 3ኛ የአቻ ውጤት አስመዝግቧል።
የማንቸስተር ዩናይትድን ግብ ማቲያስ ኩኛ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ተጠቅሞ 72ኛው ደቂቃ ላይ ብሪያን እምቡሞ ከመረብ አሳርፏል።
ቤንትናኩርን 78ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ያጣው ቶተንሃም ነጥብ የተጋራበትን ግብ 90+2 ደቂቃ ላይ በዶሚኒክ ሶላንኬ አማካኝነት አስቆጥሯል።
በክረምቱ የዝውውር መስኮት ብራይተንን ለቆ ማንቸስተር ዩናይትድን የተቀላቀለው ካሜሩናዊው ካርሎስ ባሌባ ተቀይሮ ወደ ሜዳ በመግባት ለክለቡ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል።
ውጤቱን ተከትሎ ነጥቡን ስድስት ያደረሰው ማንቸስተር ዩናይትድ 12ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፣ በውደድር ዓመቱ ለሦስተኛ ጊዜ አቻ የተለያየው ቶተንሃም ሆትስፐር በ3 ነጥብ 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
#ebc #epl #premierleague #manchesterunited #tottenham #matchday EBC SPORT ኢቢሲ ስፖርት

11 hours ago
ለኢትዮጵያ ጠላቶች ያለኝ መልዕክት
#ethiopiafirst #ethiopianunity #sovereignty #standwithethiopia #nationalpride #medemer #ethiopianews
12 hours ago
አምባሳደር ፍጹም አረጋ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተቋማት ውስጥ ለሚያገለግሉ 11 አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል
1. ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን — የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ
2. ጃፋር በድሩ — የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ
3. ሃና ተኸልቁ — የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
4.መልዕክት ሳህሉ — የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
5.ዶ/ር ባይሳ በዳዳ — የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
6. ዳግማዊት ሽፈራው — የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
7.ዶ/ር ይርጋዓለም አሰፋ — የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር
8.አምባሳደር ፍፁም አረጋ — የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
9.ይታገሱ ደሳለኝ — የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር
10.አምባሳደር ሌንጮ ባቲ — የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
11.መሐመድ ራፊ — የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ (አፍሊኤክስ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ
#ዳጉ_ጆርናል

በግብር አመቱ ከተፈቀደላቸው ዘርፎች ውጪ የሂሳብ መዝገብ ሳያቀርቡ በሚቀሩ ግብር ከፋዮች ላይ በግብር ህጉ መሰረት ቅጣት በማድረግ ህጉ ተፈጻሚ እንዲሆን መመሪያ ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በህጉ የተቀመጠውን የሂሳብ መዝገብና መግለጫ የማቅረብ ግዴታ ወደ ጎን በመተው ገቢያቸውን ለመደበቅ በሚሞክሩ አካላት ላይ አስተማሪ እርምጃ እንዲወሰድ መመሪያ ሰጥቷል።
ቢሮው የ2018 የግብር ዘመን የማሳወቂያ ጊዜ የሂሳብ መዝገብ የማይዙ ግብር ከፋዮች የሚስተናገዱበትን የአሰራር ስርዓትን የሚዘረጋ መመሪያ አውጥቷል።
ቢሮው ባወጣው መመሪያ እንዳስታወቀው፣ የሂሳብ መዝገብ አለመያዝ እንደ አማራጭ ሊወሰድ እንደማይችልና አሰራሩን ጥሰው በሚገኙ ከፋዮች ላይ አስተማሪ የህግና የአስተዳደር ቅጣቶች ይጣላሉ።
እንደ ገቢዎች ቢሮ ማብራሪያ፣ በተሻሻለው የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀጽ 3/ሀ፣ 6 እና አንቀጽ 50/ለ እንዲሁም በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 21፣ 33 እና 82 ድንጋጌዎች መሰረት ማንኛውም የደረጃ «ሀ» እና ደረጃ «ለ» ግብር ከፋይ አመታዊ ጠቅላላ ገቢውን በሰነድና በሂሳብ መዝገብ አስደግፎ የማሳወቅ፣ ሰነዶችን የመያዝ እና ግብር የመክፈል ሙሉ ግዴታ አለበት።
ሆኖም መመሪያው በልዩ ሁኔታ ካካተታቸው የተወሰኑ ዘርፎች ውጪ ሆነው ሰነድ ሳያቀርቡ የሚቀሩ አካላት ድርጊት በቀጥታ «ግብርን ለመሰወር የሚደረግ ድርጊት» ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብሏል።
በመሆኑም ይህንን የህግ ጥሰት በፈጸሙ ግብር ከፋዮች ላይ በግብር ህጉ መሰረት የሚከተሉት ቅጣቶች ተፈፃሚ የሚደረጉ መሆኑም ገልጿል፦
- በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 80 መሰረት፣ በደንብ ቁጥር 410/2009 ለደረጃ «ሐ» ግብር ከፋዮች የተቀመጠው የትርፋማነት ህዳግ ለእነዚህ አካላት በእጥፍ አድጎ እንዲሰላ ይደረጋል።
- በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 109 እና 110 ድንጋጌዎች መሰረት፣ ታክሱን ባለማሳወቃቸው ምክንያት በሚፈጠረው የታክስ ጉድለት ላይ 40 በመቶ እንዲሁም በዋናው የታክስ መጠን ላይ 200 በመቶ ተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት እንዲጣል ይደረጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ አክሎ እንዳሳሰበው፣ በዚህ መልኩ በቅጣትና በእጥፍ የትርፍ ህዳግ የሚስተናገዱ ማናቸውም ግብር ከፋዮች ዝርዝር ፋይልና መረጃ ተደራጅቶ ለህግ ተገዥነት ዘርፍ እንዲተላለፍ ይደረጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia Photo

ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እና አልባሳት ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
አረጋዊ ገ/ህይወት እና ካሳ ተክሌ የተባሉት ተጠርጣሪዎ ች የስርቆት ወንጀሉን የፈጸሙት መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ/ም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ውሀ ልማት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ ነው።
ካሳ ተክሌ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይን ልጅ ት/ቤት የሚያደርስ ሲሆን ት/ቤት ካደረሳት በኋላ የስጋ ዘመዷ ከሆነው አረጋዊ ገብረህይወት ከተባለው አባሪው ጋር በመደዋወል ወንጀሉን ለመፈጸም ውሳኔ ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።
የግል ተበዳይ ስራ ቦታ መሆኗን ደውለው ካረጋገጡ በኋላ የመኖሪያ ቤቷን መኝታ ቤት መስኮት ገንጥለው ወደ ውስጥ በመግባት 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት 3 ኪሎ ግራም ወርቅ፣ 2 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ 4 ኪሎ ግራም ወርቅ፣ የዋጋ ግምታቸው 1ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ብር የሚገመቱ ከውጪ የመጡ የተለያዩ የወንድ ጃኬቶች በአጠቃላይ 33 ሚሊዮን 5 መቶ ሺ ብር የዋጋ ግምት ያላቸውን ንብረቶች ሰርቀው መሰወራቸውን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአድዋ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ጠቁሟል።
የግል ተበዳይ ጉዳዩን ለፖሊስ ካሳወቁ በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌ/ጀኔራል አስራት ደኔሮ፣ የወንጀል መከላከል ም/ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ቶፊክ መደድ፣ የወንጀል ምርመራ ም/ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር እርዚቅ ኢሳ አማካኝነት አስቸኳይ ክትትል እና ምርመራ እንዲደረግ ስምሪት ሰጥተዋል።
በመሆኑም የዋና ጠቅላይ መምሪያው የየካ ክ/ከተማ ዋና ፖሊስ መምሪያ እና የአድዋ ፖሊስ መምሪያ የክትትል እና የምርመራ ቡድን፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት/INSA የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአፋር ክልል የሚሌ ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እና የተሰረቀውን ንብረት ለማስ መለስ እልህ አስጨራሽ ርብርብ አድርገዋል።
በተደረገው እልህ አስጨራሽ ማፈላለግ ተጠርጣሪዎች ከላም በረት መናኸሪያ በመሳፈር በአፋር ክልል አድርገው ከሀገር ሊወጡ ሲሉ በአፋር ክልል ሚሌ ከሚባለው ኬላ ላይ በክልሉ ፖሊስ እና በተቀናጀው የጸጥታ ግብረ ኃይል ፍተሻ ከነ ኤግዚቢቱ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

#ads
Ⓜ️ 📱 ቀደም ብለው የከፈቱት LinkedIn Acccount ካለዎት ጥሩ ገንዘብ መስራት ይችላል (5000⭐በሳምንት )።
📱አካውንት ያላችሁ ብቻ በጥሩ ገንዘብ እየተከራየን ነው አውሩኝ ።
(LinkedIn rental service available)
😄accountes above 1 year
✅Rate 👇
🧡100+=1800birr0 p.week
🧡200+=2000 birr p.week
🧡300+=2500 birr p.week
🧡500+=2800 birr p.week
✅1000+=3000 birr p.week
✅1500+=3500 birr p.week
✅2000+=4500 birr p.werk
😄Payment systems all💰
🧡cryptosystem (binance)
🧡CBE
🧡BOA
🧡TELL BIRR
🤑fast payment system available
በቴሌግራም 🔥 coalmon
https://t.me/p2pethiopia12
0982009298

13 hours ago
በሊዝበን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንድ እስከ አምስት ተከታትለው በመግባት አሸነፉ
**********
በፖርቹጋል በተካሄደው የሊዝበን ማራቶን የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ያሉትን ደረጃዎች ይዘው በመግባት አሸንፈዋል።
አትሌት መስከረም ማሞ ርቀቱን 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ04 በመጨረስ ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅ፤ ጠጅቱ ስዩም ደግሞ በ7 ማይክሮ ሰከንድ ዘግይታ ሁለተኛ ሆናለች።
በሻንኬ ኢሙሼ፣ ስንታየሁ ጥላሁን እና አበበች አፈወርቅ ከሦስት እስከ አምስት ያሉትን ደረጃዎች በመያዝ በሊዝበን ጎዳናዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ አድርገውል።
በወንዶች ዘርፍ ዳሳለኝ ይሌ አራተኛ ሲወጣ ፣ አብዲ አሊ እና ደምሱ ገመዳ ሰባተኛ እና ስምንተኛ ደረጃን አግኝተዋል።
በአዲስ የሺዋስ
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

ኦሮሚያ ባንክ ጠቅላላ ሀብቱን ከ105.7 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረሱን አስታወቀ
#fastmereja I ኦሮሚያ ባንክ በ2025/2026 የበጀት ዓመት በሁሉም ዋና ዋና ቁልፍ የአፈፃፀም መለኪያዎች አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን አስታወቀ። የባንኩ 17ኛው መደበኛ እና 6ኛው አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የተካሄደ ሲሆን፤ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አስፋ ስሜ ለጉባዔው ዓመታዊ የስራ ሪፖርት አቅርበዋል። እንደ ባንኩ መግለጫ፣ የፋይናንስ ዘርፉ በአለም አቀፍ እና ሀገራዊ ተግዳሮቶች እየተፈተነ ቢገኝም፣ ባንኩ ለፈተናዎቹ ሳይበገር ጠቅላላ ሀብቱን ከ105.7 ቢሊዮን ብር በላይ ማድረስ ችሏል። ይህ አፈፃፀም ካለፈው የበጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ24 በመቶ እድገት አሳይቷል።
በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን 88.1 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ የተከፈለ ካፒታል በ14 በመቶ በማደግ 7.8 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ ካፒታል ደግሞ 14 ቢሊዮን ብር ደርሷል። እንዲሁም በሂሳብ ዓመቱ 15.24 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ የተገኘ ሲሆን፣ ከዲሲፕሊን ጋር ከተመራ የወጪ አስተዳደር ጋር ተዳምሮ ከታክስ በፊት 3.82 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ተገኝቷል። ይህ የትርፍ አፈፃፀም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ49 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም የባንኩ የተበላሸ ብድር (NPLs) ምጣኔ 2.43 በመቶ በመሆን በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የተሻለ የብድር ጥራት ካላቸው ቀዳሚ ባንኮች ተርታ አሰልፎታል። የዲጂታል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር 5.7 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ባንኩ ከአለም አቀፍ የዲጂታል ክፍያ መሪ ከሆኑት ቪዛ (Visa) እና ፕሪሚየር ስዊች ሶሉሽንስ (PSS) ጋር በመተባበር “ኦሮ ቪዛ ክላሲክ”፣ “ጎልድ” እና “ፕላቲንየም” የተሰኙ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን ለአገልግሎት አብቅቷል። በጉባዔው ማጠናቀቂያ ላይም ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የኮርፖሬት ገቨርነንስ መመሪያ መሰረት ለቀጣይ 3 ዓመታት ባንኩን የሚመሩ የዳይሬክቶሬት ቦርድ አባላት ምርጫ ተካሂዷል።

አትሌት መስከረም ማሞ በሊዝበን ማራቶን አሸነፈች
39ኛው የሊዝበን ማራቶን ዛሬ ተካሄዷል
በሴቶች አትሌት መስከረም ማሞ 2 ሰዓት ከ28 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ አሸንፋለች።
ጠጂቱ ስዩም እና በሻንኬ ኢሙሼ ሁለተኛና ሶስተኛ በመውጣት የኢትዮጵያን የበላይነት አረጋግጠዋል።
በወንዶች ዩጋንዳዊው ማርቲን ናይቤይ ሙሳ አሸንፏል።
ኢትዮጵያዊው አትሌት ደሳለኝ ይሌ አራተኛ ወጥቷል።
አብዲ ዓሊ ሰባተኛ እና ደምሱ ገመዳ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
የሊዝበን ማራቶን ከእ.አ.አ 1986 አንስቶ እየተካሄደ የሚገኘው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ነው።
የማራቶን ውድድሩ እውቅ አትሌቶች ከሚሳተፉባቸው ውድድሮች መካከል ይጠቀሳል።

15 hours ago
የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ የሽግግር ምዕራፍ
**************
የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ታሪክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ነጻነቷንና ሉዓላዊነቷን ከማስከበር ባለፈ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ውስጥ ቀደምትና ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቅ ቢሆንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች የሀገራችን የውጭ ፖሊሲ ከውስጣዊ ደኅንነትና ሉዓላዊነትን ከማስከበር ባሻገር ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን በሙሉ አቅም ለመጠቀም ውስንነቶች ነበሩበት።
በንጉሠ ነገሥቱ ዘመን የውጭ ፖሊሲው በዋናነት የምዕራባውያንን ድጋፍ በማጠናከርና ሉዓላዊነትን በማስከበር ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ በደርግ ዘመን ደግሞ የሶቭየት ኅብረትን የርዕዮተ-ዓለም ካምፕ በመከተል በደኅንነትና የወታደራዊ ትስስር ላይ ያተኮረ አካሄድን ይከተል ነበር።
ከ1983 ዓ.ም በኋላ የወጣው ፖሊሲ ደግሞ ድህነትን መዋጋትን ዋና መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲንና የጎረቤቶች ሰላምን ማዕከል ያደረገ ቢሆንም፣ የዓለም አቀፍ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች መለወጥ፣ የጂኦ-ፖለቲካ ፉክክር መጨመር እና የሀገር ውስጥና የአካባቢው ለውጦች ፖሊሲውን ማሻሻልና ማሳደግ አስፈላጊ አድርገውታል።
በቅርብ ዓመታት ደግሞ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በቀጥታ ከዓለም አቀፍ ተቀባይነት ፍለጋ በመውጣት፣ በክልላዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ንቁ አጀንዳ ሰጭነት እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ዲፕሎማሲያዊ ሚና ወደ መጫወት ተሸጋግሯል።
ዓለም ከአንድ ወገን የበላይነት ወደ ባለብዙ ወገን መሸጋገሯ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አቅጣጫዎቿን እንድታሰፋና የፖሊሲ አማራጮቿን እንድታበዛ ያስገደዳት ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ፍላጎትን ለማሟላት፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግና የኃይል ሽያጭን ጨምሮ ክልላዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ለማጠናከር አዲስ አቀራረብ ተከትላለች።
በዚህም መሠረት ቀደም ሲል ከነበራት በተወሰኑ ምዕራባውያን ወይም ታላላቅ ኃይሎች ላይ የተመሠረተ ግንኙነት በመውጣት፣ ከሁሉም ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ተግባራዊ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ መከተል ጀምራለች።
የዚህ የውጭ ፖሊሲ ትልቁ የስኬት ማሳያ ሀገራችን የብሪክስ አባል መሆኗ ሲሆን፣ ይህም በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የንግድ ሥርዓት ውስጥ ድምጿ እንዲሰማ፣ ከአስደናቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለቤቶች እንደ ቻይና፣ ህንድ፣ ብራዚልና ሩሲያ ጋር ያላትን ትስስር እንድታጠናክርና አማራጭ የልማት ፋይናንስ ምንጮችን እንድታገኝ በር ከፍቷል።
በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅና ኃይል ማመንጨት መጀመሩ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀንድ የንጹሕ ኃይል አቅርቦት ማዕከል ያደረጋት ሲሆን፣ ለሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ እየቀረበ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል የቀጣናውን የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከሩ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሀገራት ዘንድ ያላትን ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት አሳድጎታል።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የተመጣጠነና የብዙ ወገን ዲፕሎማሲ በመከተል በታላላቅ ኃይሎች ፉክክር ውስጥ ገለልተኝነቷንና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እየሠራች ትገኛለች።
የብሪክስ አባልነት፣ የኢኮኖሚና የኃይል ዲፕሎማሲ እንዲሁም በቀጣናው የሚደረጉ የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴዎችም ብሔራዊ ጥቅሟን ከቀጣናዊ ትስስር እና ከዓለም አቀፍ ትብብር ጋር አጣጥማ በመጓዝ የጀመረችውን የአጀንዳ ሰጭነት ሚና አጠናክራ እንድትቀጥል የሚያስችሏት ናቸው።
በአድማሱ አራጋው
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopianforeignpolicy #brics #gerd #የመደመርመንግሥት

#adigrat 📍
የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ኃይል ወደ ዓዲግራት ከተማ መግባታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ወደ ከተማዋ ሲገቡ ህዝቡ አደባባይ ወጥቶ እንደተቀበላቸው ተናግረዋል።
ከኤርትራ ድንበር 35 ኪ/ሜ የምትርቀው ከተማዋ ላለፉት ቀናት ያለአንዳች የጥበቃ ኃይል ነው የቆየችው።
በተመሳሳይ ሁኔታ እንዳስላሰ ሽረ ከተማ በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ሰራዊት ቁጥጥር ስር እንደገባቸው ታውቋል።
ቪድዮ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ (ዓዲግራት)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #adigrat 📍 ዓዲግራት ከተማ ዛሬም የሚጠብቃት ኃይል ሳይኖር ውላለች። ነዋሪዎች በየሰፈሩ ተደራጅተው አካባቢያቸውን ከዘራፊዎች እየጠበቁ ይገኛሉ። የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ዛሬ ቀን እንዲሁም አሁን በዚህ ሰዓት (በለሊት) " ተቋማችንን አናስደፍርም " በማለት ከዝርፊያ እየጠበቁ ይገኛሉ። ከሀገር መከላከያ ጋር የሚንቀሳቀሰው የትግራይ ሰለም ኃይል ወደ ዓዲግራት መቃረቡንና ከተማዋ በከበባ ውስጥ…

ለአስታጥቃቸው ይሁን ስጦታ ሊበረከት ነው
ጥቅምት 7 2019 ዓ.ም የምስጋና መርሀ- ግብር የሚደረግለት የቴአትር ባለሙያ አስታጥቃቸው ይሁን ታሪኩ በዶክመንተሪ ሊሠራ ነው።
ቦሌ ፍላሚንጎ በሚገኘው የህፃናትና ወጣቶች የቴአትርና የሲኒማ ኮምፕሌክስ ከ10 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው በዚህ የምስጋና መርሀ ግብር ስለ ከያኒው ምስክርነት የሚሰጡ ባለሙያዎች የሚታደሙ ሲሆን ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶችም ይኖራሉ ተብሏል።
ተመስጋኙ የኪነ ጥበብ ባለሙያ አስታጥቃቸው ይሁን እና ቤተሰቡ የምስጋና መርሀ ግብሩን እንዲያዘጋጅ ይሁንታቸውን በህጋዊ መንገድ ለተወዳጅ ሚድያ የሰጡ ሲሆን በምስጋና መርሀ ግብሩ እለት ለሚታየው ዶክመንተሪም ቃለ ምልልስና መረጃ ሰጥተዋል።
የአስታጥቃቸው ልጆች ወይዘሮ መልካም አስታጥቃቸው እና የኤሌክትሪክ መሀንዲስ ዮርዳኖስ አስታጥቃቸው እንዳሉት አባታቸው እዩኝ እዩኝ የማይል ሥራውን ግን አድምቶ የሚሠራ ለብዙዎች ተምሳሌት የሆነ ሰው መሆኑን ተናግረዋል።
በቀረፃ ሥራው ወቅት ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን 10 የሚጠጉ የአስታጥቃቸው ኦሪጅናል ስክሪፕቶችን የተመለከተ ሲሆን ወደፊትም ሥራዎቹ መታተም እንዳለባቸው ምክረ- ሀሣብ ቀርቧል።
በአስታጥቃቸው እጅ ከሚገኙ የቲያትር ስክሪፕቶች መካከል ተናጋሪው ዲዳ የተሰኘው የሬድዮ ድራማ የሚገኝበት ሲሆን የፃፈበት ጊዜም 1975 እንደሆነ ታውቋል።ሌላው በሚያዝያ 30 1989 የዛሬ 30 አመት የተፃፈው ባለ 11 ገፅ የሬድዮ ድራማ ባለሱሪው የሚል ርዕስ የሰጠው ነው።ሳልሣዊው ባልንጀራ ባለ 3 ገቢር ተውኔት ሲሆን በ1975 ለእይታ የበቃ ነው።ሌሎች ስክሪፕቶቹም ፍፁም ቅጣት፣ ቅሌት በድንኳን፣ፈታኙ አስክሬን 1985(የሬድዮ ድራማ)፣ቀባሪ ያጣ በድን 1974ባለአንድ ገቢር ድራማ፣ በ1983 የተፃፈው ድርሳነ ፀጋ፣ አንቺን አሉ እናትነሽ በእጁ ከሚገኙ ድርሰቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።
በኢትዮጵያ የቴአትርና የጥበብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፈው ሁለገብ ከያኒ አስታጥቃቸው ይሁንን ለማመስገንና የ69ኛ ዓመት ልደቱን በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ከተወዳጅ ሚድያ ጋር በባህር ማዶና በአገር ቤት የሚኖሩ ወዳጆቹ ከፍተኛ ትብብር ያሳዩ ሲሆን በአሁኑሰዓትም መርሀ ግብሩን እውን ለማድረግ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ ታውቋል።
ከያኒ አስታጥቃቸው ይሁን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ1974 ዓ.ም በቴአትር ጥበብ የተመረቀ ሲሆን፣ ይህም ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ ማስተማር ከጀመረበት ሁለተኛው ባች (ምሩቃን) ያደርገዋል።
ከተመረቀበት ዓመት ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በሥነ-ፅሁፍና ቋንቋ ኤክስፐርትነት የተቀጠረው ከያኒው፣ ላለፉት 37 ዓመታት በጥበቡ ዓለም ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች ሀገሩን ህዝቡን በታማኝነት አገልግሏል።
አስታጥቃቸው አጠቃላይ ከ60 በላይ የተውኔት ፅሁፎችን ያበረከተ ሲሆን፣ በርካታ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ድራማዎችን፣ መጣጥፎችን፣ አጫጭር ልቦለዶችንና ግጥሞችን ፅፏል።
አስታጥቃቸው ይሁን ፋንታ ከ1990-1995 ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤትን በዋናሥራ አስኪያጅነት ያገለገለ ሲሆን በሥነ ምግባሩ እና በትህትናው በብዙዎች የሚወደድ የጥበብ ሰው እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህ መርሀ ግብር ላይ ታላላቆች የቴአትር ፈርጦች አያልነህ ሙላት፣ ጌትነት እንየው፣ ተስፋዬ ሲማ ፣ ተፈሪ አለሙ እና ሌሎችም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንደሚገኙ ተነግሯል ።
በምስጋና መርሀ ግብሩ ላይ ለከያኒው ለየት ያለ ስጦታ እንደሚበረከትለት ታውቋል።

16 hours ago
16 hours ago
8 ፍሬያማ ዓመታት፤ ትሩፋት ላለው ሕይወት!
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ በደንበኞቻችን እና በኩባንያችን ቤተሰብ አጠራር "ፍርዬ" ባለፉት ስምንት ዓመታት ባሳዩት ወደር የለሽ ጽናት፣ ብስለትና ቁርጠኛ አመራር ተቋማችን ዘመን ተሻጋሪና አመርቂ ታሪካዊ ስኬቶችን እንዲያስመዘግብ አስችለዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ከስምንት ዓመታት በፊት አንጋፋውን ኩባንያችንን ሲረከቡ፣ ተቋሙ ሰፊ መሠረተ ልማትና እምቅ አቅም ቢኖረውም ወደ ተጨባጭ ውጤት ያልተቀየረ፣ “ያንቀላፋ ግዙፍ” (The Sleeping Giant) ተብሎ የሚታወቅ፣ በከፍተኛ የዕዳ ጫና የተተበተበ፣ የታሪፍ ውድነት ቅሬታ የነበረበት እንዲሁም የአገልግሎት አማራጮቹ በ3ጂ እና በጥቂት አካባቢዎች ብቻ በ4ጂ የሞባይል ዳታ የተገደቡበት እንደነበር ይታወሳል።
ሆኖም ‘ኢትዮ ቴሌኮምን በመቀየር የሀገራችንን ዕድገት ማፋጠን እንችላለን’ የሚል የጋራ ራዕይ በማስረጽ፣ ሰውን ያማከለ (Human Centric) እሴትን በማስፈንና ልህቀትን (Excellence) መርህ በማድረግ መላውን ሠራተኛ በአንድ ዓላማ አሰልፈዋል። የተቀመጡትን ስትራቴጂያዊ ግቦች መላው የተቋማችን ቤተሰብ በከፍተኛ ዲሲፕሊንና ትጋት ወደ ተግባር በመቀየሩም፣ ዛሬ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ለሀገር ኩራት የሆነ ተቋም እንደገና መገንባት ተችሏል።
በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን የላቀ አመራር መሠረታዊውን የቴሌኮም ግንኙነት (Connectivity) አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ በተከናወኑ መጠነ-ሰፊ የመሠረተ ልማት ማስፋፊያና ማሻሻያ ሥራዎች፣ የደንበኞቻችን ቁጥር ከ37.9 ሚሊዮን ወደ 90.1 ሚሊዮን አድጓል፤ 99.8 በመቶ ሕዝባችን የአውታረ መረብ (Network) ሽፋን ሲያገኝ ደንበኛ የመሸከም አቅማችን 115.1 ሚሊዮን ደርሷል። የ4ጂ የሕዝብ ሽፋናችን ከ82.2 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ሀገራችን ዘመናዊውን የ5ጂ ቴክኖሎጂ ቀድመው ተግባራዊ ካደረጉ ጥቂት የአፍሪካ ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ በማድረግ ዛሬ አገልግሎቱ በ33 ከተሞች ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓል።
በፋይናንስ አስተዳደር ረገድ በተወሰዱ ቁልፍ እርምጃዎች የኩባንያችን ዓመታዊ ገቢ ከ37.16 ቢሊዮን ብር ወደ 215.8 ቢሊዮን ብር፣ ከወለድና ከታክስ በፊት ያለው ትርፍ (EBITDA) ከ14.9 ቢሊዮን ብር ወደ 92.99 ቢሊዮን ብር አድጓል። በተጨማሪም በአቅራቢዎች የፋይናንስ ድጋፍ (Vendor Financing) ለተገነቡ መሠረተ ልማቶች የተወሰደው 1.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብድር ሙሉ በሙሉ ተከፍሎ ተጠናቋል።
በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ሃሳብ አመንጪነት የሀገራችን ፈር ቀዳጅ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት የሆነውን “ቴሌብር”ን እውን በማድረግ፣ የክፍያ ሥርዓቱን ከማዘመን ባለፈ ሁሉን አቀፍ የፋይናንስ ተደራሽነትን ከማረጋገጥ ባሻገር አጠቃላይ የዲጂታል ሥነምህዳሩን ለማነቃቃት ተችሏል። ያለማስያዣ የሚሰጡ የብድር አገልግሎቶችን፣ የቁጠባ ባህልንና አጠቃላይ የዲጂታል ግብይትን ወደ ማኅበረሰቡ በማስረጽ፣ ቴሌብር ዛሬ ከ60 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ምርጫ በመሆን ከ9.13 ትሪሊዮን ብር በላይ ግብይት ማስተናገድ ችሏል።
ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ የተደረጉት ዘመኑን የዋጁ ሦስት ስትራቴጂዎች ኩባንያችንን ከመሠረታዊ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢነት ወደ የተቀናጀ የዲጂታል መፍትሔዎች መሪነት አሸጋግረውታል። የዳታ ማዕከልና የቴሌክላውድ አገልግሎቶች፣ ዘኔክሰስ፣ ቴሌስትሪም፣ ዘመን ገበያ እንዲሁም የፋይበር መስመር ዝርጋታና የሆራይዘን ፋይበር ኢኒሼቲቮች በማከናወን የማኅበረሰቡን አኗኗር በማቅለል፣ የመንግሥት ተቋማትን አሠራር በማዘመንና የንግድ እንቅስቃሴን በማቀላጠፍ የሀገራችንን ዲጂታል ራዕይ ዕውን የማድረግ ሂደትን በግንባር ቀደምትነት መርተዋል።
በክብርት ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ አመራር ተነድፎ በመተግበር ላይ የሚገኘው “ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028” (Next Horizon: Digital and Beyond 2028) ስትራቴጂ የሀገራችንን የልማት አቅጣጫና የዘርፉን የወደፊት ዕድሎች ያገናዘበ ነው።
ለተቋማችን ታላቅ ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን መሳካት ጉልህ አሻራ ያሳረፉት፣ በኢትዮ ቴሌኮም ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ዋና ሥራ አስፈጻሚና ለመላው የሀገራችን ሴቶች የጥንካሬ ተምሳሌት የሆኑት ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የተሰማንን ልባዊ ደስታ እየገለጽን፣ በቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የላቀ ውጤትና ስኬት እንዲጎናጸፉ ከልብ እንመኛለን።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ በተቋማችን ውስጥ ባሳዩን ፍቅር፣ የማይናወጥ ጥንካሬና የቁርጠኝነት ተምሳሌትነት ምንጊዜም በልባችን በከፍተኛ አክብሮትና ፍቅር የሚኖሩ ሲሆን፤ መላው የተቋማችን ቤተሰብ እርሳቸው የጣሉብንን አደራ በጽናት ይዞ ይቀጥላል።
በዚህም የ'ቀጣዩ አድማስ' ስትራቴጂን ከዳር በማድረስ፣ የሚገነቡ መሠረተ ልማቶችና የሚቀርቡ ዲጂታል መፍትሔዎች ለሕዝባችን ተጨባጭ ፋይዳ እንዲሰጡ በማድረግ የሀገራችንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ በማፋጠን ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ ሁሌም የሚኮሩብን ታታሪ ቤተሰብ ሆነን እንዘልቃለን።

17 hours ago
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቺካጎ ማራቶን ለድል ይጠበቃሉ!
#ethiopia | ከዓለማችን ስድስቱ የማራቶን ሜጀር ውድድሮች አንዱ የሆነው የባንክ ኦፍ አሜሪካ ቺካጎ ማራቶን በመጪው እሑድ ይካሄዳል። በውድድሩ በሁለቱም ጾታዎች የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለድል ከሚጠበቁ ተወዳዳሪዎች መካከል ይገኛሉ።
ከ160 በላይ ሀገራት የተውጣጡ ሯጮች በሚሳተፉበት በዚህ ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር፣ ኢትዮጵያውያኑ በሴቶችም ሆነ በወንዶች ምድብ የአገራቸውን ስም ለማስጠራት ይሮጣሉ።
በሴቶች ምድብ የኢትዮጵያ ጠንካራ ተወካዮች
በሴቶች ምድብ አምስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለድል ይፎካከራሉ። ከእነዚህም አራቱ በማራቶን ከ2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ በታች የሆነ የግል ምርጥ ሰዓት እንዳላቸው ተገልጿል።
ባለፈው ዓመት የቺካጎ ማራቶንን በ2:14:57 በማጠናቀቅ ድል የተቀዳጀችው ሃዊ ፈይሳ፣ በዚህ ዓመትም ድሏን ደግማ ለማሸነፍ ትሮጣለች። አትሌቷ የውድድሩ ዋነኛ ተጠባቂ ተወዳዳሪዎች መካከል ትጠቀሳለች።
ሁለት ጊዜ የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊ የሆነችውና 2:15:55 የግል ምርጥ ሰዓት ያላት ሱቱሜ አሰፋ፣ ደጊቱ አዝመራው፣ መገርቱ ዓለሙ እና በዱባይ ማራቶን ጠንካራ ብቃቷን ያሳየችው ፋንቱ ወርቁ ሌሎች የኢትዮጵያ ተስፋዎች ናቸው።
ሆኖም የኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች የድል ጉዞ ቀላል አይሆንም። ኬንያውያኑ ብሪጊድ ኮስጌይ እና ሻሮን ሎኬዲ በውድድሩ ጠንካራ ተፎካካሪዎች በመሆናቸው የሴቶቹ ምድብ ከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቅበት ሆኗል።
በወንዶች ምድብ ከባድ ፉክክር ይጠበቃል
በወንዶች ምድብ የበርሊን ማራቶን አሸናፊው ሚልኬሳ መንገሻ እና የቶኪዮ ማራቶን አሸናፊው ታደሰ ታከለ የኢትዮጵያን የድል ተስፋ ይዘው ይቀርባሉ። በ48ኛው የቺካጎ ማራቶን ከሚጠበቁት ከፍተኛ ተፎካካሪዎች መካከልም ይገኛሉ።
ከእነሱ በተጨማሪ፣ በሴቪያ ማራቶን አስደናቂ ብቃቱን ያሳየው አስራር ኸይረዲን እና ቦኪ ድሪባ በውድድሩ ይሳተፋሉ። አትሌቶቹ ከዓለም አቀፍ ተፎካካሪዎቻቸው ጋር በመፋለም የኢትዮጵያን የማራቶን ብቃት ለማሳየት ይጥራሉ።
በወንዶች ምድብ የሚኖረው ፉክክር ግን እጅግ ከባድ እንደሚሆን ይጠበቃል። በማራቶን 2:00:28 የግል ምርጥ ሰዓት ያለው ዩጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞ እና ኬንያዊው አሞስ ኪፕሩቶ ለድል ከሚፎካከሩት አትሌቶች መካከል ይጠበቃሉ።
የኢትዮጵያ የማራቶን ብቃት የሚፈተንበት መድረክ
የቺካጎ ማራቶን በዓለም አቀፍ የረጅም ርቀት ሩጫ ውድድሮች ውስጥ ከፍተኛ ዝና ያለው ሲሆን፣ ብዙ ጊዜ ፈጣን የማራቶን ሰዓቶች የሚመዘገቡበት መድረክ ነው። የዘንድሮው ውድድርም ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች አዲስ ድል ለመጨመርና በዓለም አቀፍ የማራቶን መድረክ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማሳየት ትልቅ ዕድል ይሰጣል።
የሁለቱም ጾታዎች ፉክክር በምን መልኩ እንደሚጠናቀቅና ኢትዮጵያውያኑ ወደ ድል መድረክ መመለስ እንደሚችሉ የስፖርት ቤተሰቡ በጉጉት ይጠብቃል።
#ethiopia #chicagomarathon #athletics #getutemesgen

መቐለ 📍
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን የጫነች አውሮፕላን ዛሬ መቐለ አሉላ አባነጋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መግባቷን የጀርመን ድምጽ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
ዛሬ መቐለ የገባችው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የአየር መንገዱ የቴክኒክና ሌሎች ሰራተኞችን የጫነች ናት ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ መቐለ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል።
መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia ወደ መቐለ እሁድ ጥቅምት 1 በረራ ይጀመራል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረው ወደ መቐለ ከተማ የሚያደርገው መደበኛ በረራ ከጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል። ደንበኞች በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ በመሄድ ወይም ወደ ጥሪ ማዕከሉ 6787 በመደወል የጉዞ ምዝገባ ማስያዝ እንደሚችሉ ገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ መስከረም…

18 hours ago
#maddawalabuuniversity
በ2019 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው ዋና ካምፓስ
ትምህርት ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ፋይዳ መታወቂያ (National ID)፣
● ከ8-12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
● ጉርድ ፎቶግራፍ፣
● ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በ2019 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

ንስር ማይክሮፋይናንስ በበጀት ዓመቱ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ
ንስር ማይክሮፋይናንስ ኢንስቲትዩሽን አክሲዮን ማኅበር በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት 522 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ይፋ አደረገ። ተቋሙ ከታክስ በኋላ ያስመዘገበው የተጣራ ትርፍም 384 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ደርሷል።
ተቋሙ 13ኛውን መደበኛ እና 5ኛውን አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት እንዳስታወቀው፤ የተጣራ ትርፉ ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ207 ነጥብ 6 በመቶ ከፍተኛ ዕድገት አሳይቷል። በዚህም ለአንድ ሺህ ብር የአክሲዮን ድርሻ 625 ብር የትርፍ ድርሻ ተመድቧል።
በበጀት ዓመቱ በርካታ የኢኮኖሚና የፋይናንስ ዘርፍ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፤ የተቋሙ አጠቃላይ ሀብት ከ5 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወደ 9 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል።
በተመሳሳይ የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ 6 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር፣ የብድር መጠኑ ደግሞ 6 ነጥብ 69 ቢሊዮን ብር ደርሷል። የተቋሙ የተበላሹ ብድሮች ምጣኔ 2 ነጥብ 87 በመቶ ብቻ ሆኖ በብሔራዊ ባንክ ከተቀመጠው ገደብ በታች መገኘቱ ተጠቁሟል።
ንስር ማይክሮፋይናንስ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ሀብቱን ወደ 34 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ማውጣቱን ገልጿል።
በዚህም በ2019 ዓ.ም ብቻ 10 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት አጠቃላይ ቅርንጫፎቹን 30 ለማድረስ፣ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ የጀመረውን የዘመናዊ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታ ለማጠናከር እንዲሁም የዲጂታል አገልግሎቱን ይበልጥ ለማስፋፋት አቅዶ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።
በሰብል አበበ

#kue
በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 05 እና 06/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ውጤት ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ሦስት ፓስፖርት መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
ፋይዳ መታወቂያ እና TIN No.
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
የትምህርት ማስረጃዎቹ ስካን ተደርገው በአንድ PDF ሶፍት ኮፒ መዘጋጀት አለባቸው። ስካን የተደረገ ጉርድ ፎቶ ሶፍት ኮፒ መያዝ አይዘንጉ።

Comments