አገልግሎቱ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ ለመሉ አነሳ
********************
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች የሚጣለውን የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ።
ኢንጅነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፣ የወለድ ክፍያው መነሳቱ የአዲስ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስገባት ፍላጎት ያላቸው ሆነው የማስቀጠያ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ ዜጎች አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ የሚያደርግ ነው።
በቅርቡ ሥራ ላይ በዋለው የአዲስ ቆጣሪ የዱቤ አሰራር ከሰኔ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 19 ሺህ 231 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል።
አሰራሩ በተለይ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ ደንበኞች ክፍያውን በተወሰነ ጊዜ ተከፋፍለው እንዲከፍሉ ዕድል የሚሰጥ ነው።
እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፣ ቀደም ሲል የክፍያ ጊዜው እስከ 24 ወራት የሚደርስ ሲሆን፣ ከ6 ወራት በላይ ለሚቆይ ክፍያ ከ3 እስከ 9 በመቶ የሚደርስ ወለድ ይታሰብ ነበር። አሁን ይህ የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል።
የወለድ ክፍያው መነሳቱ በተለይ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያን በአንድ ጊዜ መፈጸም ለማይችሉ ደንበኞች ትልቅ የምስራች መሆኑን ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ገልጸዋል።
በዚህ ውሳኔ ደንበኞች ያለባቸውን የአንድ ጊዜ የክፍያ ጫና በማቃለል፣ በዱቤ ክፍያ ሥርዓት አማካኝነት አዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስገባት ይችላሉ።
ይህም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃይልን ለበለጠ የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ፣ ዜጎች ከኤሌክትሪክ ኃይል የሚገኘውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻልና የደንበኛ ተኮር አገልግሎቱን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።
ይህ አሰራር የዜጎችን የአንድ ጊዜ የክፍያ ጫና በማቃለል የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋትና የአዲስ ደንበኞችን ቁጥር ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት 1.1 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ ይዟል። ይህም ተቋሙ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋትና በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ካለው ሥራ አንዱ አካል ነው።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጅነር ጌቱ ገረመው እንዳብራሩት፣ ተቋሙ በ70 ዓመታት ታሪኩ ማገናኘት የቻለው የደንበኞች ቁጥር 5.88 ሚሊዮን ያህል ሲሆን፣ አሁን ላይ ግን በየዓመቱ ወደ 1 ሚሊዮን ደንበኞችን የማገናኘት አቅም ላይ ደርሷል።
በተያያዘም ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 664 ሺህ 505 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል። ይህ አፈጻጸም ተቋሙ አዳዲስ ደንበኞችን በማገናኘት ያለውን አቅም ያሳያል።

10 hours ago