Logo
Getu Temesgen
"በአፍሪካ ትልቁ ዕድል ትብብር እንጂ ውድድር አይደለም”
#ethiopia | በአፍሪካ ትልቁ ዕድል የርስ በርስ ትብብርና አንድነት መሆኑንና አህጉሪቱን በጤናው ዘርፍ የበለጠ ጠንካራ ማድረግ የሚቻለው በጋራ በመቆም እንደሆነ "የሃርት አታክ ኢትዮጵያ መስራቾች ተናገሩ።

ልባሞቹ ዶክተሮች ሰይፉ በኢቢኤስ ፕሮግራም ላይ ባደረገጉት ቃለ መጠይቅ ድርጅቱ ለሰው ልጅ ደህንነት እና ለጤና ዘርፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴና የወደፊት ራዕዩን የተናገሩ ሲሆን ለተደረገለት መገናኛ ብዙኃን ላደረጉላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የጋራ ትኩረታችንን ክህሎታችንን እና ሀብታችንን ለአህጉራችን አጣዳፊ ጉዳዮች ላይ ስናውል ልንደርስበት የማንችለው ግብ የለም ብለዋል።

የተሻለችና በጤና የታነጸች አፍሪካን ለመገንባት የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት እና ትብብር አስፈላጊነት በአፅንዖት አሳስቧል።

በዚህም በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ በጎ ፈቃደኞች፣ ለለጋሾች፣ ለኢንዱስትሪ አጋሮች፣ የቅርንጫፍ አባላትና ለሌሎችም ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #heartattackethiopia #seifufantahun #ebs

6 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.