(ዘ-ሐበሻ ዜና) በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር የሆኑት ኤቭጀኒ ተሬክሂን "ከዲፕሎማሲ ባሻገር፡ ገደብ የለሹ የአውሮፓውያን ግብዝነት" በሚል ርዕስ ባሳተሙት ጽሑፍ፣ አውሮፓውያን በተለይም ጀርመን በዩክሬን ቀውስ ዙሪያ እያሳዩት ያለውን አቋም በከፍተኛ ሁኔታ አውግዘዋል። አምባሳደሩ ምዕራባውያን ዲፕሎማቶች እውነታውን በመካድ እና ጥቁሩን ነጭ በማለት እያቀረቡ ነው ሲሉ ከሰዋል። በተለይም በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር በቅርቡ ያወጡትን መግለጫ በእጅጉ በመተቸት፣ ይህ አካሄድ የተናጠል እውነታዎችን ከዐውዳቸው ውጪ በመነጠል የሚቀርብ ሆን ተብሎ እውነታን የመካድ እና የ"ግማሽ እውነት" ስልት መሆኑን አብራርተዋል።
አምባሳደር ኤቭጀኒ ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ያለውን "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ሲከላከሉ፣ ዓላማው በኪየቭ ሥርዓት ለዓመታት ጭቆና እና የዘር ማጥፋት ሲፈጸምባቸው የነበሩ ሰዎችን ለመጠበቅ እንዲሁም ዩክሬንን ከናዚ አስተሳሰብ እና ከጦር መሣሪያ ለማጽዳት መሆኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል። የክሪሚያን ወደ ሩሲያ መቀላቀልን በተመለከተ የጀርመን አምባሳደር ያነሱትን "በኃይል የመጠቅለል" ክስ ያጣጣሉት የሩሲያ አምባሳደር፣ ድርጊቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር የሚያዘውን የህዝቦችን የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የተከተለና 96 በመቶው የክሪሚያ ነዋሪዎች በህዝበ ውሳኔ ያረጋገጡት መሆኑን አስገንዝበዋል። ይልቁንም እውነተኛ በኃይል የመጠቅለል ምሳሌ የሚሆነው፣ በ1989 ዓ.ም ምዕራብ ጀርመን አብዛኛውን የምስራቅ ጀርመን ህዝብ ፍላጎት ሳታዳምጥ ያካሄደችው ውህደት ነው በማለት ሞግተዋል።
የሩሲያ አምባሳደር ትችት ጀርመን ላይ ይበልጥ ጠንክሮ የታየ ሲሆን፣ የዓለም ጦርነትን በማስነሳትና የዘር ማጥፋት በመፈጸም አሳዛኝ የታሪክ ጠባሳ ያላት ጀርመን ዛሬ ላይ ለሩሲያ ስለ ዓለም አቀፍ የሞራል እሴቶች ልትሰብክ አይገባትም ብለዋል። ጀርመን ዛሬ ላይ የናዚዝም አስተሳሰብን የሚያራምደውን እና ሕገ-መንግሥታዊ ቅቡልነት የሌለውን የኪየቭ ሥርዓት በግልጽ እየደገፈች መሆኗን ገልጸው፣ ሰላምን ከማምጣት ይልቅ ጦር መሣሪያ በማምረት እና በማቅረብ የተወካይ ጦርነትን እያራዘመች ትገኛለች ሲሉ ወቅሰዋል። ይህ የጀርመን አካሄድም የሂትለሩን ፕሮፓጋንዲስት ዶክተር ጎብልስን የሚያኮራ ተግባር ነው በማለት ጠንካራ ቃላትን ተጠቅመዋል።
አምባሳደር ኤቭጀኒ የኢትዮጵያ ህዝብ ስለ ሉዓላዊነት፣ ነጻነት እና ስለ ምዕራባውያን የድርብ ስታንዳርድ አካሄድ ጥልቅ ታሪካዊ ግንዛቤ እንዳለው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያውያን የአውሮፓውያንን ግብዝነት በቀላሉ መረዳት እንደሚችሉ ጠቁመው፣ በምዕራባውያን የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እና መርዛማ የሀሰት ትርክቶች መሃል በናዚዎች የተገደለው ፀረ-ፋሺስቱ ጸሐፊ ጁሊየስ ፉቺክ ያስተላለፈው "ህዝብ ሆይ፣ ንቁ ሁን!" የሚለው ታሪካዊ ማስጠንቀቂያ ዛሬም ጊዜው የሚጠይቀው እውነት መሆኑን በማሳሰብ ጽሑፋቸውን አጠናቅቀዋል።

3 hours ago