21 days ago
“ኢንቲማ ሄልዝ ኬር ሲቲ ” ቢሾፍቱ ከተማ ሊገነባ ነው
#ethiopia | ለዓመታት በልብ ህክምና በጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማራው “ኸርት አታክ ኢትዮጵያ”፣ የበጎ አድራጎት አገልግሎቱን ይበልጥ ዘላቂና ተደራሽ ለማድረግ “ኢንቲማ ሄልዝ ኬር ሲቲ” የተሰኘ የህክምና ማዕከል ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ።
ቢሾፍቱ እየተገነባ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርፖርት አቅራቢያ በ10 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፈው ፕሮጀክት፣ ትርፍንና በጎ አድራጎትን ባጣመረ ማህበራዊ የንግድ ስራ መርህ የሚመራ ነው።
የፕሮጀክቱ መጀመር ይፋ የሆነው ድርጅቱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ታሪካዊ ስምምነት በተፈራረመበት ወቅት ሲሆን፣ በፊርማ ስነ-ስርዓቱም ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ድጉማ፣ እና የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋን ጨምሮ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የድርጅቱ ተባባሪ መስራችና የልብ ሀኪም የሆኑት ዶክተር ተስፋዬ ተሊላ እንደገለጹት፣ ሃርት አታክ ኢትዮጵያ እስካሁን የ660 ታካሚዎችን ህይወት መታደግ ቢችልም፣ ካለው ሰፊ የልብ ህመም ችግር አንጻር የበጎ አድራጎት ስራ ብቻ በቂ ባለመሆኑ ወደዚህ አዲስ አሠራር መሸጋገር አስፈልጓልብለዋል።
ይህ አዲስ መዋቅር አቅም ያላቸው ታካሚዎች እየከፈሉ እንዲታከሙ፣ አቅም የሌላቸው ደግሞ በነጻ የህክምና እድል እንዲያገኙ በማድረግ ዘላቂነት ያለው ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የተደረገው ስምምነት የኢትዮጵያውያንን የውጭ ሀገር የህክምና ፍሰት ከመቀነስ ባለፈ፣ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ታካሚዎችን ወደ ሀገሪቱ ለመሳብ የሚያስችል “ፍላይት ቱ ሂል” (Flight to Heal) የተሰኘ ፕሮግራም ለማስጀመር ትልቅ በር ይከፍታል። የልብ ህክምናን ጨምሮ የእናቶችና ህጻናት ጤናን፣ ካንሰርን፣ የነርቭ እና የድንገተኛ አደጋ ህክምናዎችን ያካተቱ ዘመናዊ የህክምና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገባው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ በሀገር ውስጥ የመድኃኒት ማምረቻን ለማስፋፋትና ባለሙያዎችን በህንድ ሀገር በልዩ ሁኔታ ለማሰልጠን አቅዷል።
በተጨማሪም በህክምና ከተማው ውስጥ የሚመሰረተው የህክምና ትምህርት ቤት ቀጣዩን የኢትዮጵያ የህክምና ባለሙያዎች ትውልድ በራሱ አቅም ለማስተማርና ለማብቃት ታላቅ ራዕይ ሰንቆ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ethiopia #intimahealthcity #heartattackethiopia #ethiopianairlines #medicaltourism #healthcareafrica #flighttoheal #africahealthcare

2 months ago
ከ50 በላይ የልብ ሕክምና ባለሞያዎችን የያዘ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ነው
#ethiopia | ከ50 በላይ የልብ ሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎችን የያዘ የሕክምና ቡድን ከአንድ ወር በኋላ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ተነግሯል። ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት አራት መሰል ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጡ ያደረገው 'ኸርት አታክ ኢትዮጵያ' የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት፤ በቀጣዩ ሰኔ ወር መጨረሻ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣው ቡድን የልብ ሕክምና ለማግኘት ወረፋ እየተጠባበቁ ለሚገኙ ሕጻናት እና አዋቂዎችን ሕክምና እንደሚሰጥ ገልጿል።
የሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎች ቡድኑ የልብ ስፔሻሊስት ሃኪሞች እና ነርሶች፣ እንዲሁም ሌሎች ባለሞያዎችን ያካተተ መሆኑ ተነግሯል። የሕክምና በጎ ፈቃደኛ ባለሞያዎቹ ከህንድ፣ ካናዳ፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ሩዋንዳ እና ቦትስዋና የተወጣጡ መሆናቸውንም የኸርት አታክ ኢትዮጵያ መሥራች ዶክተር ተስፋዬ ተሊላ ገልጸዋል።
ኸርት አታክ ኢትዮጵያ በየጊዜው ተመሳሳይ ሥራዎችን በማከናወን የልብ ሕመም ህክምና ለማግኘት ወረፋ እየተጠባበቁ ለሚገኙ ሕጻናት ሕክምና መስጠቱን እንደሚቀጥልም ዶክተር ተስፋዬ አረጋግጠዋል ሲል ሀገሬ ቴሌቪዥን ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #digitalhagerie #dr .Tesfaye #heartattackethiopia

Comments