ለ5 ሺህ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ለማቅረብ ያለመ ሀገር አቀፍ የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ ሊጀመር ነው
#fastmereja I በ2012 ዓ.ም የተመሰረተው አቢዘር ማህበረሰብ አቀፍ የልማት ድርጅት በመጪው የትምህርት ዘመን ለ5,000 ወላጅ አልባና ለችግር ተጋላጭ ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ ለማቅረብ ያለመ ሀገር አቀፍ የሀብት ማሰባሰብ ዘመቻ ከነሐሴ 9 እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚያካሂድ አስታወቀ።
ይህ በስድስት ዙሮች ተከፋፍሎ በ60 ከተሞች ላይ የሚካሄደው ግዙፍ ዘመቻ ዋና ዓላማው እስከ 30 ሚሊዮን ብር በማሰባሰብ የትምህርት ቁሳቁሶችን ማቅረብ፣ የማህበረሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ፣ አዳዲስ ደጋፊዎችን መመዝገብ፣ የዲጂታል ሚዲያ ተጠቃሚዎችን መሳብ እና ዘላቂ ስትራቴጂካዊ ስምምነቶችን መፈፀም እንደሆነ ተገልጿል።
የዚሁ ዘመቻ አካል የሆነው የመጀመሪያው ዙር ጉዞ ከአዳማ ተነስቶ እስከ ጅግጅጋ ባሉ 10 ከተሞች ላይ የሚካሄድ ሲሆን፣ ድርጅቱ በዋናነት በአማራና በአፋር ክልሎች በሚንቀሳቀሱ ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትና ባሎቻቸውን ያጡ እናቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል፤ እንቅስቃሴውን በ15 ህፃናት የጀመረው አቢዘር የ234 ወላጅ አልባ ህፃናት ደጋፊ መሆን መቻሉን የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አብዱ ገልጸዋል።

5 hours ago