Logo
SeledaPost
የኤሌክትሪክ ኃይል አዲስ ኃይል ማስገቢያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ በሙሉ ተነሳ‼️

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስገቢያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች ይጠየቅ የነበረውን ከ3 እስከ 9 በመቶ የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ።

ቀደም ሲል የዱቤ ክፍያ ጊዜው እስከ 24 ወራት ሲሆን፣ ከ6 ወራት በላይ ለሚቆይ ክፍያ ወለድ ይጣል ነበር።

አሁን ወለዱ መነሳቱ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መፈጸም ለማይችሉ ዜጎች የምስራች መሆኑንና አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከሰኔ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተጀመረው የአዲስ ቆጣሪ የዱቤ አሰራር በሁለት ሳምንታት ብቻ 19,231 አዳዲስ ደንበኞች ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል።

ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 664,505 አዳዲስ ደንበኞችን ያገናኘ ሲሆን፣ በ2019 ዓ.ም. ደግሞ 1.1 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን ለማገናኘት አቅዷል።

ኢንጅነር ጌቱ እንደገለጹት፣ አገልግሎቱ በ70 ዓመታት ታሪኩ 5.88 ሚሊዮን ደንበኞችን ማገናኘት ችሏል፤ አሁን ግን በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ደንበኞችን የማገናኘት አቅም ላይ ደርሷል።

Seledadotio
Seledadotio
1 day ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.