(ዘ-ሐበሻ ዜና) ለወራት ያህል በውዝግብ ውስጥ የቆየው አንበሳ ባንክ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ፡፡ በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በተከናወነው በዚህ ጉባኤ አዳዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ተመርጠዋል፡፡ ባንኩ የዛሬ 9 ወር ገደማ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጡ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁንና የምርጫውን ውጤት ተከትሎ የተወሰኑ ባንኩ ባለአክስዮኖች ለብሄራዊ ባንክ ቅሬታ ማስገባታቸውን ተከትሎ ብሄራዊ ባንክ ምርመራ አድርጎ ነበር፡፡ በምርመራውም በቦርዱ አባላት መካከል አለመግባባት መኖሩን መረዳቱን ጠቅሶ ይህም ‹‹የባንኩን ህልውና አደጋ ውስጥ የሚከትና የባለአክስዮኖችን ፍላጎት የሚጎዳ ነው›› በሚል ድጋሚ ምርጫ እንዲከናወን መመሪያ መስጠቱን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡
የትላንቱ ጠቅላላ ጉባኤ የተከናወነው ከዚህ በመነሳት ሲሆን በጉባኤው በተደረገው ምርጫ ከ9 ወር በፊት ተመርጠው የነበሩት 11ዱም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ከሀላፊነት ተነስተው በምትካቸው አዳዲስ ተመርጠዋል፡፡ ከአዲሶቹ የቦርድ አባላት መካከል 8ቱ ከባለአክስዮኖች መካከል የተመረጡ ሲሆን እነሱም መኮንን ገብረዋህድ፣ ፀበል ሀዱሽ፣ ካህሳይ ገብረሚካኤል፣ ግዛው አማረ፣ ካህሳይ ሀይሌ፣ ቴዎድሮስ አማረ፣ መኩሪያ አለማየሁና የባንኩ የብድር ክፍል ሀላፊ ፌቨን ቢኒያም ናቸው፡፡ ገለልተኛ የቦርድ አባል በመሆን ሀይለማሪያም ግደይ፣ ኪሮስ ሀብቱና አወት ብርሀኔ መመረጣቸውም ተገልጿል፡፡ አዲሱ ቦርድ ስራ ከመጀመሩ በፊት ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር እንዲሁም የኮሚቴ አባላትን እንደሚመርጥ ይጠበቃል፡፡
ከ9 ወር በፊት ተመርጠው የነበሩት የቦርድ አባላት በዚህኛው ምርጫ ላይ ያልተካተቱት ብሄራዊ ባንክ እገዳ የጣለባቸው በመሆኑ ነው፡፡ የባንኩ ማኔጅመንት የአዲሱን ቦርድ ምርጫ ደግፎታል፡፡ ላለፉት 4 አመታት ባንኩን በፕሬዝደንትነት እየመሩ ያሉት አቶ ዳንኤል ተከስተ አዲሶቹ የቦርድ አባላት የካበተ ሙያዊ ልምድና የትምህርት ዝግጅት ያላቸው መሆኑን ጠቅሰው ‹‹ይህ ለባንኩ መልካም እድል ነው›› ብለዋል፡፡ ከምርጫው በኋላ ለፎርቹን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ ሲናገሩ ‹‹ከአዲሱ ቦርድ ጋር በመሆን የባንኩን እድገት ዘላቂና ስትራቴጂውን የተከተለ እንዲሆን እናስችላለን የሚል ተስፋ አለን›› በማለት አስረድተዋል፡፡
የባንኩ ባለአክስዮኖች ግን የተለያየ ሀሳብ አላቸው፡፡ በባንኩ ውስጥ ከፍተኛ አክስዮን ያላቸው አቶ ገብረፃዲቅ ገብረኪዳን ሲናገሩ ‹‹አዲሱ ቦርድ ስለባንክና እንዴት ማስተዳደር እንደሚቻል እውቀት በሌላቸው ሰዎች የተሞላ ነው›› ካሉ በኋላ ከበፊቱ ቦርድ የተወሰኑ ሰዎች መካተት እንደነበረባቸው ገልፀዋል፡፡ ያልተካተቱት በተከፈተባቸው ‹‹ዘመቻ›› መሆኑን ጠቅሰው ‹‹የብሄራዊ ባንክ አካሄድ አንበሳ ባንክን የሚያጠፋ ነው፡፡ አዲሶቹ የቦርድ አባላትም በባንኩ ላይ ችግር የሚፈጥሩ ይሆናሉ›› ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡
ሌላኛው ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ከፍተኛ ባለአክስዮን ደግሞ ምርጫውን ደግፈዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹እኔ ከፍተኛ ረብሻ እንደይፈጠር ሰግቼ ነበር፡፡ ግን ያ አልሆነም›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹አዲሶቹ የቦርድ አባላት ጠንካራ ተቃውሞ እንደሚገጥማቸው አስቤ የነበረ ቢሆንም የተፈጠረው ግን ተቃራኒ ነው፡፡ ይህ ጥሩ ነገር ነው›› ሲሉ ገልፀዋል፡፡

6 hours ago