Logo
Getu Temesgen
አገልግሎቱ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ ለመሉ አነሳ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች የሚጣለውን የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ።

ኢንጅነር ጌቱ ገረመው እንደገለጹት፣ የወለድ ክፍያው መነሳቱ የአዲስ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስገባት ፍላጎት ያላቸው ሆነው የማስቀጠያ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ ዜጎች አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ የሚያደርግ ነው።

በቅርቡ ሥራ ላይ በዋለው የአዲስ ቆጣሪ የዱቤ አሰራር ከሰኔ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 19 ሺህ 231 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል።

አሰራሩ በተለይ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መክፈል ለማይችሉ ደንበኞች ክፍያውን በተወሰነ ጊዜ ተከፋፍለው እንዲከፍሉ ዕድል የሚሰጥ ነው።

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ፣ ቀደም ሲል የክፍያ ጊዜው እስከ 24 ወራት የሚደርስ ሲሆን፣ ከ6 ወራት በላይ ለሚቆይ ክፍያ ከ3 እስከ 9 በመቶ የሚደርስ ወለድ ይታሰብ ነበር። አሁን ይህ የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል።

የወለድ ክፍያው መነሳቱ በተለይ የአዲስ ኃይል ማስቀጠያ ክፍያን በአንድ ጊዜ መፈጸም ለማይችሉ ደንበኞች ትልቅ የምስራች መሆኑን ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ገልጸዋል።

በዚህ ውሳኔ ደንበኞች ያለባቸውን የአንድ ጊዜ የክፍያ ጫና በማቃለል፣ በዱቤ ክፍያ ሥርዓት አማካኝነት አዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስገባት ይችላሉ።

ይህም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኃይልን ለበለጠ የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ፣ ዜጎች ከኤሌክትሪክ ኃይል የሚገኘውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻልና የደንበኛ ተኮር አገልግሎቱን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

ይህ አሰራር የዜጎችን የአንድ ጊዜ የክፍያ ጫና በማቃለል የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋትና የአዲስ ደንበኞችን ቁጥር ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

8 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.